ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 28–ነሐሴ 3፦ “የአምላክ አይነት ሃይል”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84


“ሐምሌ 28–ነሐሴ 3፦ ‘የአምላክ አይነት ሃይል’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ጆሰፍ ስሚዝ የመልከ ጼዴቅ ክህነትን እየተቀበለ

ዝርዝሩ ከThe Restoration of the Melchizedek Priesthood [የመልከ ፄዴቅ ክህነት ዳግም መመለስ]፣ በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

ሐምሌ 28–ነሐሴ 3፦ “የአምላክ አይነት ሀይል”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84

በ1829 (እ.አ.አ) የክህነት ስልጣን ከተመለሰ ጊዜ ጀምሮ፣ ቀደምት ቅዱሳን በጌታ ቅዱስ ሃይል እየተባረኩ ነበር። ልክ እንደዛሬው እንደ እኛ፣ እነርሱም በክህነት ስልጣን ይጠመቁ፣ ማረጋገጫ ይቀበሉ እና እንዲያገለግሉ ይጠሩ ነበር። ነገር ግን የክህነት ሀይልን ማግኘት ማለት እሱን ሙሉ በሙሉ መረዳት ማለት አይደለም፣ እንዲሁም እግዚአብሔር፣ ቅዱሳኑ እንዲገነዘቡ ይፈልግ የነበረው ብዙ ነገር ነበር—በተለይም እየመጡ የነበሩትን የቤተመቅደስ ሥርዓቶች ዳግም መመለስን የሚመለከቱ። አሁን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84 የሆነው በ1832 (እ.አ.አ) ስለክህነት የተሰጠው ራዕይ፣ ስለክህነት እውነተኛ ምንነት በተመለከተ የቅዱሳንን እይታ አስፍቷል። እንዲሁም ዛሬ ለእኛ ተመሳሳይ ነገር ሊያደርግልን ይችላል። ከሁሉም በላይ፣ “የእግዚአብሔርን የእውቀት ቁልፎች“ ስለሚይዘው “የአምላክ አይነት ሃይል“ እንዲገለጥ ስለሚያደርገው እና “የእግዚአብሔርን ፊት፣ እንዲሁም አብን፣ ለመመልከት እና ለመኖር“ ስለሚያዘጋጀን ስለ መለኮታዊው ኃይል ብዙ የምንማራቸው ነገሮች አሉ (ቁጥር 19–22)።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥17–32

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
የእግዚአብሔርን የክህነት ሀይል እና በረከቶች ማግኘት እችላለሁ።

ክህነት የሚለውን ቃል ስታስቡ ወደ አዕምሮአችሁ የሚመጣው ምንድን ነው? የእግዚአብሔር የክህነት ሃይል በህይወታችሁ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?

በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ ካሰላሰላችሁ በኋላ፣ ጌታ ስለእርሱ የክህነት ስልጣን ምን እንድታውቁ እንደሚፈልግ እየፈለጋችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥17–32ን ልታጠኑ ትችላላችሁ። እነዚህን ጥቅሶች ለአንድ ሰው ስለክህነት እና ስለዓላማዎቹ ለማብራራት እንዴት ልትጠቀሙባቸው እንደምትችሉ አስቡ።

ከምታገኙት ነገር አንዱ በክህነት ሥርዓቶች ውስጥ፣ “የአምላክ አይነት ሀይል እንደሚታይ” ነው። (ቁጥር 19–21 ተመልከቱ)። ምናልባት የተሳተፋችሁባቸውን የክህነት ሥርዓቶች መዘርዘር ትችላላችሁ (በአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ ውስጥ ያለው ዝርዝር፣ 18.118.2፣ ሊረዳ ይችላል)። እነዚህ ሥርዓቶች—እና ከእነርሱ ጋር የተያያዙት ቃል ኪዳኖች—የእግዚአብሔርን ኃይል ወደ ህይወታችሁ ያመጡት እንዴት ነው? ያለ እነርሱ ህይወታችሁ እንዴት ይሆን ነበር?

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፣ “ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖችን የገቡ እያንዳንዳቸው ሴቶች እና ወንዶች እንዲሁም እነዚያን ቃል ኪዳኖች የሚጠብቁ እና በክህነት ሥርዓቶች ውስጥ በብቁነት የሚሳተፉ ሁሉ የእግዚአብሔርን ኃይል በቀጥታ የመጠቀም ስልጣን አላቸው” (“መንፈሳዊ ሀብቶች፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 77)። “የአዳኙን ኃይል ወደ ህይወ[ታችሁ] ማምጣት” የምትችሉባቸውን መንገዶች እየፈለጋችሁ የፕሬዚዳንት ኔልሰንን መልዕክት ማጥናትን አስቡ።

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥10፣ 13፣ 15121፥34–37፣ 41–46፤ Topics and Questions፣ “Priesthood፣” “Joseph Smith’s Teachings about Priesthood፣ Temples፣ and Women፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ3.6፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥31–44

ክህነት የሚገኘው በመሐላ እና በቃል ኪዳን ነው።

የክህነት መሃላ እና ቃል ኪዳን (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፡31–44ን ተመልከቱ) ለክህነት አገልግሎት በተሾሙት የሰማይ አባት ወንዶች ልጆች በተለየ ሁኔታ ተፈፃሚ ይሆናል፣ ነገር ግን በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ ቃል የተገቡ በረከቶች የሚገኙት ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ነው። እነዚህ ተስፋዎች ምንድን ናቸው፣ እንዲሁም እነርሱን እንቀበል ዘንድ እግዚአብሔር ምን እንድናደርግ ጠይቆናል?

ሽማግሌ ፖል ቢ. ፓይፐር እንዳስተማሩት፦ “በክህነት መሐላ እና ቃል ኪዳን ውስጥ [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥31–44]፣ ጌታ ማግኘት እና መቀበል የሚሉትን ግሶች መጠቀሙ ትኩረትን የሚስብ ነው። መሾም የሚለውን ግሥ አልተጠቀመም። ወንዶች እና ሴቶች የሁለቱንም የአሮናዊ እና የመልከ ጸዴቅ የክህነት በረከቶች እና ሀይል—አብረው—የሚያገኙት እና የሚቀበሉት በቤተመቅደስ ውስጥ ነው (“Revealed Realities of Mortality [የተገለጹት የሚአችነት እውነታዎች]፣” ኤንዛይን፣ ጥር 2016 (እ.አ.አ)፣ 21)።

ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 84፥31–44ን ስታጠኑ፣ ክህነትን “ማግኘት“ እና “መቀበል“ ማለት ምን ማለት ሊሆን እንደሚችል አሰላስሉ። ይህ በክህነት ክፍል ከመሾም የሚለየው እንዴት ነው? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጌታ ሌላ ምን እንድትቀበሉ ይጋብዛችኋል? ያንን እያደረጋችሁ ያላችሁት እንዴት ነው?

አዳኙን፣ የእርሱን አባት፣ አገልጋዮቹን እና የክህነት ኃይሉን ለመቀበል ይበልጥ ታማኝ ለመሆን የሚያነሳሳችሁ ምን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥36–46ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥43–61

በእግዚአብሔር ቃል መኖር ብርሃንን እና እውነትን ወደ ህይወቴ ያመጣል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥43–61 ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ያለማቋረጥ ማጥናት ለምን እንደሚያስፈልጋችሁ እንድትገነዘቡ የሚረዷችሁ ምን እውነቶችን ታገኛላችሁ? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በብርሃን እና በጨለማ መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ፤ “[የ]ዘለዓለም ህይወት ቃላት[ን] በትጋት ማዳመጥ” ብርሃንን፣ እውነትን እና “የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስን” ወደ ህይወታችሁ ያመጣው እንዴት ነው? (ቁጥር 43፣ 45)።

በተጨማሪም 2 ኔፊ 32፥3ን ተመልከቱ።

የወንጌል መርሆዎችን ከታወቁ ነገሮች ጋር አወዳድሩ።ቁጥር 43–44 ውስጥ ያሉትን እውነቶች የሚያስረዳን ንፅፅር ማሰብ ትችላላችሁ? ለምሳሌ፣ በምግብ አሰራር ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ቅደም ተከተሎች መከተል “[በ]እግዚአብሔር … በእያንዳንዱ ቃል” እንደመኖር የሚሆነው እንዴት ነው?

ምስል
አንዲት ሴት ቅዱሳት መጻህፍትን እያነበበች

“[የ]ዘለዓለም ህይወት ቃላት[ን] በትጋት ታደምጡ ዘንድ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥62–91

እርሱን በማገለግልበት ጊዜ ጌታ ከእኔ ጋር ይሆናል።

እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ፣ ጌታ አገልጋዮቹን እንደሚደግፋቸው የተናገረባቸውን መንገዶች መለየት ትችላላችሁ። እነዚህ ቃል ኪዳኖች እርሱ እንድትሰሩ ከጠየቃችሁ ሥራ ጋር እንዴት ሊገናኙ ይችላሉ? ለምሳሌ በቁጥር 88 ውስጥ ያሉት ቃል ኪዳኖች በህይወታችሁ ውስጥ የተፈፀሙት እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥106–110

ሁሉም ሠው በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ አስተዋፅዖ ሊያደርግ ይችላል።

ከእነዚህ ጥቅሶች ጌታ ሥራውን ስለሚፈጽምበት መንገድ ምን ትማራላችሁ? ምን ምክር እና በረከቶች ታገኛላችሁ? በቤተሰባችሁ ውስጥ ያሉትን ጨምሮ “በመንፈስ ጠንካራ” ከሆነ ሰው ጋር ስላገለገላችሁ፣ “በየዋህነት ሁሉ [እንዴት] እንደታነፃችሁ” ልታስቡም ትችላላችሁ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥4–5

የቤተ መቅደሥ ሥርዓቶች እንደገና ከሰማይ አባት ጋር ለመኖር እንድችል ይረዱኛል።

  • ልጆቻችሁ ወደ ቤተመቅደስ ለመሄድ በጉጉት እንዲጠብቁ ለመርዳት፣ የቤተመቅደስ ምስልን በመጠቀም የመገጣጠም ጨዋታን መፍጠር ትችላላችሁ። በእያንዳንዱ ቁራጭ ተገጣጣሚ ጀርባ ላይ፣ በቤተመቅደስ ውስጥ የምናደርገውን የተወሰነ ነገር፣ ለምሳሌ ለቅድመ አያቶች እንደ መጠመቅ፣ ከቤተሰቦቻችን ጋር እንደ መታተም እና ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንደመግባት የመሳሰሉ የተወሰኑ ነገሮችን መፃፍ ትችላላችሁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥4–5ን ከልጆቻችሁ ጋር አንብቡ፣ ከዚያም ጌታ፣ ቅዱሳኑ ምን እንዲገነቡ እንዳዘዛቸው እንዲሰሙ ጠይቋቸው። እናንተ እና ልጆቻችሁ የመገጣጠም ጨዋታውን በምትገጣጥሙበት ጊዜ፣ ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት ለመዘጋጀት ልናደርጋቸው ስለምንችላቸው ነገሮች አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–22

በክህነት ሥርዓቶች በኩል የሰማይ አባትን ሃይል መቀበል እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ ሥርዓት ምን እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለመርዳት፣ከእነርሱ ጋር የወንጌል የአርት መፅሐፍቁጥር. 103–8ን ወይም የዚህን ሣምንት የአክቲቪቲ ገፅ.የመሣሠሉ በርካታ የክህነት ሥርዓቶች ምስሎችን ማየትን አስቡ። በእያንዳንዱ ሥዕል ላይ ምን እየተከናወነ እንደሆነ እንዲገልፁ ጠይቋቸው። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–22ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። የሰማይ አባት እነዚህን ሥርዓቶች እንድንቀበል የሚፈልገው ለምንድን ነው? በተቀበላችኋቸው ሥርዓቶች እና በገባችኋቸው ቃል ኪዳኖች ምክንያት የእግዚአብሔር ኃይል እንዴት እንደተሰማችሁ ለልጆቻችሁ ንገሯቸው። (በተጨማሪም በ”አባሪ ሀ ወይም አባሪ ለ.ውስጥ “የክህነት ኃይል፣ ሥልጣን፣ እና ቁልፎችን” ተመልከቱ)።

ምስል
Young Couple Going to the Temple; GAK 609; GAB 120; Primary manual 2-32; Doctrine and Covenants 131:1-3; 132:4-7, 19-20
ምስል
ልጆች ቅዱስ ቁርባንን እየወሰዱ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥77

እርሱን ስከተለው የኢየሱስ ጓደኛ ነኝ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥77ን አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ፣ ጓደኛ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ልጆቻችሁን ጠይቋቸው። ስለነበሯችሁ መልካም ጓደኞች ልትናገሩም ትችላላችሁ። ኢየሱስ ጓደኞቹ እንድንሆን እንደሚፈልግ ያሳየን እንዴት ነው? እኛም ያንን እንደምንፈልገው ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? እንደ “I’m Trying to Be like Jesus፣” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 78–79) ያለ መዝሙር ለዚህ ውይይት ሊረዳ ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥88

የሰማይ አባት አገልጋዮቹን ይረዳል።

  • ልጆቻችሁ፣ ሚስዮናውያን እናንተን፣ ቤተሰባችሁን፣ ወይም ቅድመ አያቶቻችሁን ወንጌልን እንድትቀበሉ እንዴት እንደረዷችሁ በመስማት ይደሰቱ ይሆናል። ከዚያም በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥88.ውስጥ ጌታ ለሚስዮናውያን ስለገባው የተለየ ቃል ኪዳን ማንበብ ትችላላችሁ። ምናልባት ልጆቻችሁ ከዚህ ጥቅስ ጋር የሚሄዱ ተግባራትን ሊያስቡ ይችላሉ። ጌታን እያገለገላችሁ ስለነበራችሁበት እና በቁጥር 88 ውስጥ እንደተገለፀው እርሱ ከእናንተ ጋር እንዳለ የተሰማችሁን ጊዜ ማካፈልን አስቡ። ልጆቻችሁ አሁን ሚስዮናውያን ሊሆኑ የሚችሉባቸውን መንገዶች እንዲያስቡ ልትረዷቸውም ትችላላችሁ። ከሌሎች ጋር ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በምንነጋገርበት ጊዜ የሰማይ አባት ምን እንደምንናገር እናውቅ ዘንድ እንደሚረዳን ምስክርነታችሁን ሥጡ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም