ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 4–10፦ “በተቀደሱ ስፍራዎች ቁሙ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85–87


“ነሐሴ 4–10፦ ‘በተቀደሱ ስፍራዎች ቁሙ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85–87፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85–87፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ቤተሰብ ወደ ቤተመቅደስ እየቀረቡ

ነሐሴ 4–10፦ “በተቀደሱ ስፍራዎች ቁሙ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85–87

አብዛኛውን ጊዜ የገና ቀን እንደ “ሰላም በምድር” (ሉቃስ 2፥14 ተመልከቱ) ያሉ መልዕክቶችን የማሰላሰያ ጊዜ ነው። ታህሳስ 25 ቀን 1832 (እ.አ.አ.) ግን የጆሴፍ ስሚዝ አዕምሮ በጦርነት ስጋት ተወጥሮ ነበር። በዩናይትድ ስቴትስ የምትገኘው የሳውዝ ካሮላይና ግዛት ለመንግስት አልታዘዝም አለች እንዲሁም ለጦርነት እየተዘጋጀች ነበር። ጌታም ይህ ነገር ገና ጅማሬው ብቻ እንደሆነ ገለጠ፦ “ጦርነት በሁሉም ህዝብ ላይ [ይፈሳል]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥2) ሲል ተናገረ። ይህ ትንቢት በጣም በቅርቡ የሚፈጸም መሰለ።

ነገር ግን በዚያን ጊዜ አልተፈፀመም። በጥቂት ሳምንታት ውስጥ፣ ሳውዝ ካሮላይና እና የአሜሪካ መንግስት ሥምምነት ላይ ደረሱ፣ እናም ጦርነቱ ቀረ። ነገር ግን ራዕይ ሁልጊዜ በተጠበቀው ጊዜ ወይም በጠበቅነው መንገድ አይከናወንም። ወደ 30 ከሚጠጉ ዓመታት በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ሰማዕት ከሆነ ከረዥም ጊዜ በኋላ፣ ሳውዝ ካሮላይና አመፀች ከዚያም የእርስ በእርስ ጦርነት ተከተለ። ዛሬ በዓለም ዙሪያ ያለው ጦርነት “ምድር [እንድታዝን]“ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥6) ምክንያት መሆኑን ቀጥሏል። የዚህ ራዕይ ዋጋ፣ ጥፋቱ መቼ እንደሚመጣ በመናገር ረገድ ያለው ጠቀሜታ አነስ ያለ ሲሆን፣ በሚመጣበት ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለብን ለማስተማር ያለው ዋጋ ከፍ ያለ ነው። በ1831ም ሆነ፣ በ1861 ወይም በ2025 ምክሩ ያው ነው፦ “በተቀደሱ ስፍራዎች ቁሙ፣ እናም አትነቃነቁ“ (ቁጥር 8)።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥1–2

ጌታ “ታሪክን [እንድጠብቅ]” ይሻል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥1–2 ውስጥ በተገለፀው “ታሪክ” ውስጥ ጌታ እንዲካተት የፈለገውን አስተውሉ። ቅዱሳኑ ታሪክ እንዲጠብቁ የሚፈልገው ለምን ይመስላችኋል? ለእናንተ እና ለወደፊቱ ትውልድ በረከት ሊሆን የሚችል፣ ስለአኗኗሯችሁ፣ ስለእምነታችሁ፣ እና ስለስራችሁ ምን ልትመዘግቡ ትችላላችሁ? የግል ታሪካችሁን መመዝገብ ወደ ክርስቶስ እንድትመጡ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?

እንዲሁም “Journals: ‘Of Far More Worth than Gold፣’” Teachings of Presidents of the Church: Wilford Woodruff (2011)፣ 125–33፤ “Turning Hearts” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥6

መንፈስ “በአነስተኛ ለስላሳ ድምጽ” ይናገራል።

ጆሴፍ ስሚዝ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥6 ውስጥ መንፈስን ለመግለጽ የተጠቀማቸውን ቃላቶች አሰላስሉ። የመንፈስ ድምጽ “አነስተኛ” እና “ለስላሳ” የሚሆነው በምን መንገድ ነው? በጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጡትን እነዚህን ተጨማሪ መግለጫዎች አስቡ፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥22–248፥2–39፥7–911፥12–13128፥1። መንፈስ ለእናንተ የሚናገረው በምን መንገድ ነው?

በተጨማሪም ሉቃስ 24፥32ሞዛያ 5፥2አልማ 32፥28ሄለማን 5፥30ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥22–2311፥12–13 ተመልከቱ።

የተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ትምህርቶችን ተጠቀሙ። ሰዎች እየተማሩት ካለው ነገር ጋር የሚዛመድ የተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ትምህርትን ሲያዩ ወይም በዚያ ላይ ሲሳተፉ የወንጌል ትምህርትን በተሻለ ሁኔታ ያስታውሳሉ። ለምሣሌ ስለመንፈስ አነስተኛ እና ለስላሳ ድምጽ በምታስተምሩበት ጊዜ ምናልባት ለስላሳ፣ የተቀደሰ የሙዚቃ ቅጂ ልታጫውቱ ትችላላችሁ፣ እንዲሁም ተማሪዎች፣ ሙዚቃው እንዴት እንዲሰማቸው እንዳደረጋቸው እና ትኩረት የሚከፋፍሉ ድምፆች ቢኖሩ ኖሮ ምን ያህል ለመስማት አዳጋች እንደሚሆን ሊናገሩ ይችላሉ። ይህም፣ አነስተኛ እና ለስላሳ ድምጽን እንዳንሰማ ስለሚያደርጉ በህይወታችን ውስጥ ስላሉ ትኩረትን የሚከፋፍሉ ጉዳዮች አስመልክቶ ወደሚደረግ ውይይት ሊያመራ ይችላል።

ምስል
ወጣት ሴት ቅዱሳት መጻህፍትን እያነበበች

ቅዱሳት መፃህፍት፣ የመንፈስ ድምጽ አነስተኛ እና ለስላሳ እንደሆነ ይገልፃሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86

በመጨረሻው ቀን ጻድቃን ወደ ክርስቶስ ይሰበሰባሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86ማቴዎስ 13፥24–30፣ 37–43 ውስጥ የሚገኘውን የስንዴ እና የእንክርዳድ ምሳሌ ትርጉም ይዟል። ስለዚህ ምሣሌ ትርጉም ስትማሩ እንደዚህ ዓይነት ሰንጠረዥን መሙላትን አስቡ፦

ምልክቶች

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

ምልክቶች

ዘሩን ዘሪዎች

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ነቢያት እና ሐዋርያት

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

ነቢያት እና ሐዋርያት የሚዘሩት ምን ዓይነት “ዘሮችን” ነው?

ምልክቶች

ጠላት

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ሰይጣን

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

ጠላት የጌታን ሥራ ለማቆም የሚሞክረው እንዴት ነው?

ምልክቶች

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

ምልክቶች

ሊሠጡ የሚችሉ ትርጉሞች

ማሰላሰያ ጥያቄዎች

የምታስቡባቸው ጥቂት ተጨማሪ ጥያቄዎች እነሆ፦

  • ምሳሌውን ከተረጎመ በኋላ፣ ጌታ ስለ ክህነት፣ ስለዳግም መመለሥ እና ስለ ህዝቡ ደህንነት ተናገረ (ቁጥሮች 8–11 ተመልከቱ)። በእነዚህ ጭብጦች እና በስንዴና በእንክርዱ ምሳሌ መካከል ምን ግንኙነት ታያላችሁ?

  • “ለአህዛብ ብርሐን” እንዲሁም “[ለጌታ ህዝቦች እንደ] አዳኝ” በመሆን ረገድ ያላችሁ ሚና ምንድን ነው? (ቁጥር 11)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
“በተቀደሱ ስፍራዎች“ ሰላም ይገኛል።

ክፍል 87 ውስጥ የሚገኘው ትንቢት በመጨረሻው ቀናት ስለሚኖሩት ከጦርነት ጋር የተያያዙ አካላዊ አደጋዎችን ያስጠነቅቃል። ሆኖም በዚህ ራዕይ ውስጥ ያሉት ምክሮች ለመንፈሳዊ አደጋዎችም ጭምር ይሆናሉ። እንደሚከተሉት ባሉ ጥያቄዎች ላይ አሰላስሉ፦

  • ትንቢት ከእግዚአብሔር ለአንድ ነቢይ የሚሠጥ ራዕይ ሲሆን፣ ብዙ ጊዜ የሚናገረውም ስለወደፊቱ ጊዜ ነው። የጥንት እና የዘመናችን ነቢያት የተናገሯቸው አንዳንድ የትንቢቶች ምሳሌዎች ምን ምን ናቸው? (ዮሐንስ 3፥14ሞዛያ 3፥5ሔለማን 14፥2–6 ተመልከቱ)። የተፈፀሙትስ እንዴት ነው? ( ሉቃስ 23፥33ማቴዎስ 15፥30–313 ኔፊ 1፥15–21 ተመልከቱ)።

  • የእግዚአብሔር ነቢያትን ትንቢቶች መቀበል የሚያመጧቸው በረከቶች ምን ምን ናቸው?

እነዚያን ሃሳቦች በአዕምሯችሁ በመያዝ ክፍል 87ን አንብቡ። (የታሪኩን የተወሰነ አውድ ለማወቅ፣ የዚህን መዘርዝር መግቢያ ማንበብ ትፈልጉም ይሆናል።) ከዚህ ራዕይ ስለትንቢት እና ስለተፈፀመበት መንገድ ምን ትማራላችሁ? አንድ ትንቢት ወዲያው ባለመፈፀሙ ምክንያት ለሚጠራጠር ሰው ምን ትሉታላችሁ?

ቁጥር 8 ውስጥ ጌታ ምን አይነት ምክር ሰጥቷል? ሰላም እና ጥበቃ የምታገኙባቸው የእናንተ “የተቀደሱ ስፍራዎች” ምን ምን ናቸው? አንድን ቦታ ቅዱስ የሚያደርገው ምንድን ነው? ምናልባት ከአካላዊ ስፍራዎች በተጨማሪ ሰላምን ሊያመጡ የሚችሉ የተቀደሱ ጊዜያት፣ የተቀደሱ ተግባራት ወይም የተቀደሱ ሃሳቦች አሉ። ለምሳሌ፣ የእግዚአብሔር ነቢያት ቃላት የተቀደሰ ሥፍራ ሊሆኑላችሁ የሚችሉት እንዴት ነው? በእነዚህ ቦታዎች “መቆም” እና “አለመነቃነቅ” ማለት ምን ማለት ነው?

በተጨማሪም “Where Love Is፣” የልጆች መዝሙር መፅሀፍ፣፣ 138–39፤ Saints1፥163–64፤ “Peace and War፣” በRevelations in Context፣ 158–64 ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥6

መንፈስ “በአነስተኛ ለስላሳ ድምጽ” ይናገራል።

  • መንፈሥ ቅዱሥ እንዳናገራቸው እንዴት እንዳወቁ ልጆቻችሁን የሆነ ሰው ቢጠይቃቸው ምን ብለው ይመልሳሉ? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 85፥6 ውስጥ ጆሴፍ ስሚዝ የመንፈሥን ድምፅ ስለገለፀበት አንድ መንገድ እንዲያነቡ ጋብዟቸው። ከዚያም “በለሥላሣ ድምፅ” ማዳመጥን እና መናገርን ሊለማመዱ ይችላሉ። መንፈስ እናንተን በለሥላሣ ድምፅ ያነጋገረበትን ተሞክሮዎች ልታካፍሉም ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ “በለሥላሣ ድምፅ” የሚለውን ሐረግ እንዲገነዘቡ ለመርዳት እንደ “The Holy Ghost” (የልጆች መዝሙር፣ 105) የመሰለ የልጆች መዝሙርን በአነስተኛ ድምጽ ልታጫውቱ ትችላላችሁ። ሌሎች ልጆች ትኩረትን የሚከፋፍሉ ድምፆችን ሲያሰሙ፣ ከልጆቹ አንዱን ምን መዝሙር እንደሆነ እንዲገምት ጠይቁ። ከዚያም ትኩረትን የሚከፋፍሉ ድምፆች በሌሉበት መዝሙሩን ልትደግሙት ትችላላችሁ። መንፈሱን ይበልጥ በተደጋጋሚ ለመሰማት ምን አይነት ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን ከህይወታችን ማስወገድ እንችላለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86

የእግዚአብሔርን ህዝብ ለመሰብሰብ መርዳት እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ በክፍል 86 ውስጥ የተገለጸውን ምሳሌ እንዲገነዘቡ ለመርዳት ብዙ ትናንሽ የስንዴ ምስሎችን ወይም ሥዕሎችን ልታዘጋጁ እና በክፍሉ ዙሪያ ልትደብቋቸው ትችላላችሁ። የስንዴውን እና የእንክርዳዱን ምሳሌ ለልጆቻችሁ አስረዱ (ማቴዎስ 13፥24–30 ተመልከቱ)፣ ከዚያም የጌታን አስተያየት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86፥1–7 ውስጥ አብራችሁ አንብቡ። ከዚያም ልጆቻችሁ የተደበቁትን የስንዴ ሥዕሎች ሊሠበስቧቸው እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ “መሰብሰብ” የሚችሉትን ሰው ስም በላያቸው ላይ ሊጽፉ ይችላሉ። ሠዎችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሠብሠብ ማለት ምን ማለት ነው? ይህንን ማድረግ የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምን ምን ናቸው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86፥11

ለሌሎች እንደ ብርሀን ለመሆን እችላለሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86፥11 ላይ ስትወያዩ ልጆቻችሁን ልትጠይቋቸው የምትችሏቸው አንዳንድ ጥያቄዎች እነሆ፦ ብርሃን የሚባርከን እንዴት ነው? ብርሃን በማይኖረን ጊዜ ምን ይመስላል? ለሌሎች ሠዎች ብርሀን ለመሆን የምንችለው እንዴት ነው? ልጆቻችሁ “[በኢየሱስ] መልካምነት መቀጠል” የምንችልባቸውን መንገዶች እንዲያስቡና ለሌሎች እንዲያካፍሉት እርዷቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥6፣ 8

“በተቀደሱ ሥፍራዎች መቆም” እችላለሁ።

  • ጌታ በኋለኛው ቀናት ይፈፀማሉ ስላላቸው ነገሮች ለማወቅ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥6ን አብራችሁ አንብቡ። ከዚያም እናንተ እና ልጆቻችሁ ስለሚያጋጥሟችሁ አንዳንድ ፈተናዎች መናገር ትችላላችሁ። በቁጥር 8 ውስጥ፣ በአስቸጋሪ ጊዜያት ልናደርጋቸው ስለምንችላቸው ነገሮች ጌታ ምን ተናግሯል?

  • ልጆቻችሁ መንፈሳዊ አደጋን እንዲጋፈጡ የሚረዷቸውን የተቀደሱ ቦታዎች፣ የተቀደሱ ሃሳቦች እና የተቀደሱ ድርጊቶች ዝርዝር እንዲያዘጋጁ እርዷቸው። ሃሳቦችን ለማግኘት፣ “Standing in Holy Places” እና “Stand Ye in Holy Places—Bloom Where You’re Planted” (የወንጌል ላይብረሪ) የሚሉትን ቪዲዮዎች ተመልከቱ።

ምስል
አንዲት እናት ቤተመቅደስን ለህፃን ልጇ እያሳየች

ቤተመቅደስ የተቀደሰ ቦታ ነው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ምስል
የስንዴ ማሳ

ጌታ ህዝቡን እንደ ስንዴ ይሰበስባል።

ምስል
የመሳተፊያ ገጽ ለልጆች

አትም