“ነሐሴ 25–31፦ ‘የእርሱን ሙላት መቀበል’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 25–31፦ “የእርሱን ሙላት መቀበል”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93
ጆሴፍ ስሚዝ፣ “መሰላል ላይ ስትወጡ፣ እላይ እስክትደርሱ ድረስ ከስሩ መጀመር እና ደረጃ በደረጃ መውጣት አለባችሁ፤ እና የወንጌል መሰረታዊ መርሆዎችም እንዲሁ ናቸው— ከመጀመሪያው መጀመር እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግን መርሆዎች እስክትማሩ ድረስ መቀጠል አለባችሁ” ሲል አስተምሯል (Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [2007 (እ.አ.አ)] 268)።
አንዳንድ ጊዜ ያ በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ መሰላል ከሚገባው በላይ ከፍ ያለ መስሎ ሊታየን ይችላል፣ ሆኖም የተወለድነው በአዳኙ የማያቋርጥ እርዳታ ወደ ላይኛው ጫፍ ለመውጣት ነው። እኛ ምንም ዓይነት ውስንነቶችን በራሳችን ላይ ብናይም፣ የሰማይ አባት እና ልጁ በእኛ ውስጥ እንደ አምላክ ያለ ታላቅ ነገርን ያያሉ። ልክ ኢየሱስ ክርስቶስ “በመጀመሪያ ከአብ ጋር እንደነበረ”፣ “እናንተም እንዲሁ ነበራችሁ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥21፣ 23)። ልክ እርሱ ”ሙላትን እስከሚቀበል ድረስ ከጸጋ ወደ ጸጋ” እንደ ቀጠለ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ”እናንተም በጸጋ ላይ ጸጋን ትቀበላላችሁ” (ቁጥር 13፣ 20)። ዳግም የተመለሰው ወንጌል ስለ እግዚአብሔር እውነተኛ ተፈጥሮ ያስተምረናል፣ እንዲሁም ስለእናንተ እውነተኛ ተፈጥሮ እና ፍፃሜም ያስተምረናል። “በጊዜው የእርሱን ሙላት” ለማግኘት የሚያስችል አቅም ያላችሁ ቃል በቃል የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ” (ቁጥር 19)።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ልክ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እከብራለሁ እንዲሁም የእግዚአብሔርን “ሙላት” አቀበላለሁ።
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ፣ “ሰዎች የእግዚአብሔርን ባህርይ ካልተረዱ እራሳቸውን አይረዱም” ሲል አስተምሯል (Teachings: Joseph Smith 40)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93ን በማጥናት ስለአዳኙ ስትማሩ፣ ስለራሳችሁ ምን እንደምትማሩም ፈልጉ። ለምሳሌ፣ ከቁጥር 3፣ 12–13፣ 21 እና 26ስለእርሱ ምን ትማራላችሁ? በቁጥር 20፣ 23 እና 28–29 ውስጥ (በተጨማሪም 1 ዮሐንስ 3፥2፤ 3 ኔፊ 27፥27 ተመልከቱ) ስለራሳችሁ ምን ተመሳሳይ እውነቶችን ታገኛላችሁ? ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ጥያቄዎች በዚህ ክፍል ውስጥ ያሉትን እውነቶች እንድትገነዘቡ ሊረዷችሁ ይችሉ ይሆናል።
-
“ጸጋ በጸጋ” መቀበል እና “ከጸጋ ወደ ጸጋ” መቀጠል ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? (ቁጥር 12–13)። የሚረዳ ከሆነ “ጸጋ” የሚለውን ቃል በቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ (የወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ ልታነቡ ትችላላችሁ።
-
በዚህ ራዕይ ውስጥ እግዚአብሔር እንድታድጉ እና እንድትማሩ ሊረዳችሁ ስለሚችልበት መንገድ ምን ታገኛላችሁ? ይህንን ማወቃችሁ ሌሎችን—እና እራሳችሁን በምትይዙበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?
-
“እንዴት እንደምታመልኩ እና ምን እንደምታመልኩ” በተመለከተ ምን ትማራላችሁ? (ቁጥር 19፤ በተጨማሪም በቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “ማምለክ፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ)።
የእግዚአብሔር ክብር ብርሀንና እውነት ነው።
በዚህ ራዕይ ውስጥ እንደ ክብር፣ ብርሃን እና እውነት የመሣሠሉት ቃላት እንደተደጋግሙ ልታስተውሉ ትችላላችሁ። በተለይ ቁጥር 20–39ን በምታጠኑበት ጊዜ፣ ስለእነዚህ ሃሳቦች የምትማሯቸውን እውነቶች ዝርዝር ጻፉ። እንደዚህ ያለ ሠንጠርዥ ማዘጋጀትሊረዳችሁ ይችላል፦
ቁጥር |
የተማርኩት ነገር |
ማሰላሰያ ጥያቄዎች |
---|---|---|
ቁጥር | የተማርኩት ነገር | ማሰላሰያ ጥያቄዎች በዓለም ዙሪያ ብዙ ማታለያዎች አሉ። እውነቱን እንዴት ላውቅ እችላለሁ? (በተጨማሪም ያዕቆብ 4፥13 ተመልከቱ)። |
ቁጥር | የተማርኩት ነገር | ማሰላሰያ ጥያቄዎች |
ቁጥር | የተማርኩት ነገር እግዚአብሔር የብርሀን እና የእውነት አካል ነው። | ማሰላሰያ ጥያቄዎች |
ቁጥር | የተማርኩት ነገር | ማሰላሰያ ጥያቄዎች ክፉ ተፅዕኖዎችን መቋቋም የሚችል የሚመሥል ማንን አውቃለሁ? ይህንን ማድረግ የቻሉት ለምንድን ነው? |
ቁጥር | የተማርኩት ነገር | ማሰላሰያ ጥያቄዎች |
ቁጥር | የተማርኩት ነገር | ማሰላሰያ ጥያቄዎች |
ቁጥር በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥24 ተመልከቱ። | የተማርኩት ነገር | ማሰላሰያ ጥያቄዎች |
በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የላቀ ብርሐንን እና እውነትን እንድትሹ የሚያነሳሷችሁ ምን ታገኛላችሁ? ብርሐን እና እውነት ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥሩ መጠሪያዎች የሆኑት ለምንድን ነው? (ዮሀንስ 8፥12፤ 14፥6 ተመልከቱ)። እነዚያ እውነቶች በህይወታችሁ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩት እንዴት ነው?
በቁጥር 20፣ 22፣ 28፣ 33–35 ውስጥ ስለ ዘለአለማዊ ፍፃሜያችሁ የተሠጡ ተሥፋዎችን ማስታወሻ ልትይዙም ትችላላችሁ። በእነዚህ ተሥፋዎች እና ብርሃን በማግኘት መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው?
ብርሃን ለማግኘት ምን ማድረግ እንደምትችሉ እና ጌታ እንዴት እንደሚባርካችሁ ቃል እንደገባ ለማወቅ ፣“በእግዚአብሔር ብርሀን ተራመዱ” (ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ፣ 18–21) ውስጥ መፈለግን አስቡ። “Light and Truth ክፍል 1” እና “ክፍል 2” (የወንጌል ላይብረሪ) የተሠኙት ቪዲዮዎች ተጨማሪ ሃሳቦችን ሊሠጡ ይችላሉ።
በተጨማሪም “Teach Me to Walk in the Light፣መዝሙር፣ ቁጥር. 304፤ Topics and Questions፣ “Holy Ghost፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።
“ቤትህን በሥርዓት አደራጅ።”
“ቤትህን በሥርዓት አደራጅ” (ቁጥር 43) የሚለው ትዕዛዝ ቁም ሳጥንንና መደርደሪያን ስለማደራጀት ሳይሆን “ብርሃንና እውነትን” ስለማስተማር—እና ስለመማር ነው (ቁጥር 42)። ይህን ምክር ለመከተል ምን እያደረጋችሁ እንደሆነ አስቡ። ምን ፈተናዎች አጋጠሟችሁ? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93 ውስጥ የትኛው እውነት ሊረዳ ይችላል?
ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር ከሰጧቸው ከእነዚህ ትምህርቶች ምን ግንዛቤዎችን አገኛችሁ?
“ቢሮዬ ውስጥ የሚያምር የስንዴ ማሳ ሥዕል አለ። ሥዕሉ በጣም ብዛት ያላቸው ነጠላ የብሩሽ ጭረቶች ስብስብ ሲሆኑ—አንዳቸውም ቢሆኑ በተናጥል በጣም የሚስቡ ወይም አስደናቂ አይደሉም። እንዲያውም ወደ ሸራው ጠጋ ብላችሁ ከቆማችሁ የምታዩት የማይገናኙ የሚመስሉ እና የማይስቡ የሚመስሉ ቢጫ፣ ወርቃማ እና ቡናማ ቀለም ያላቸውን ጭረቶች ነው። ነገር ግን፣ ከሥዕል ሸራው ቀስ በቀስ እየራቃችሁ ስትሄዱ፣ ሁሉም ነጠላ የብሩሽ ጭረቶች አንድ ላይ በመሆን የሚያምር የስንዴ ማሣ መልክዓ ምድርን ይፈጥራሉ። ብዙ ተራ፣ ነጠላ የብሩሽ ጭረቶች አንድ ላይ በመሆን ማራኪ እና የሚያምር ሥዕል ይፈጥራሉ።
“እያንዳንዱ የቤተሰብ ጸሎት፣ እያንዳንዱ የቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና እያንዳንዱ የቤተሰብ ምሽት በነፍሳችን ሸራ ላይ የብሩሽ ጭረቶች ናቸው። ምንም ሌላ ክስተት በጣም አስደናቂ እና የሚታወስ ሆኖ ሊታይ አይችልም። ነገር ግን፣ ልክ ቢጫ እና ወርቃማ እና ቡኒ የሥዕል ጭረቶች እርስ በእርሳቸው እንደሚደጋገፉ እና አስደናቂ ሥዕል እንደሚፈጥሩ፣ የእኛም ትንንሽ የሚመስሉ ወጥነት ያላቸው ድርጊቶች ወደ ጉልህ መንፈሳዊ ውጤቶች ይመራሉ። ‘ስለዚህ፣ መልካም ሥራን ትሰሩ ዘንድ አትታክቱ፣ የታላቅ ስራን መሰረት እየገነባችሁ ነውና። እናም ከትንንሾቹ ነገሮች ታላቅ የሆነው ይወጣል’ [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥33]። በየግል ህይወታችን ውስጥ የታላቅ ስራን መሰረት ስንጥል እና ለራሳችን ቤት የበለጠ በትጋት ስንሠራ እና ስንጨነቅ ወጥነት ቁልፍ መርህ ነው” (“በቤት ውስጥ የበለጠ ታታሪ እና የሚያገባው መሆን፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2009 [እ.አ.አ]፣ 19–20)።
በተጨማሪም ሄንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “A Home Where the Spirit of the Lord Dwells፣” ሊያሆና ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 22–25 ተመልከቱ።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ብርሃን እና ህይወት ነው።
-
የአዳኙን ምስል ለልጆቻችሁ ማሳየትን አስቡ፣ ከዚያም ስለኢየሱስ ክርስቶስ መማር እና እርሱን መከተል አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ጠይቋቸው። ከዚያም አንዱን አስፈላጊ ምክንያት ለማወቅ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥19ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ።
-
ከክፍል 93 ውስጥ እናንተን የሚያነሳሱ ስለክርስቶስ ብዙ እውነቶችን ልትመርጡ ትፈልጉ ይሆናል፣ ከዚያም ልጆቻችሁ እንዲያውቋቸው እና እንዲገነዘቧቸው እርዷቸው (በተጨማሪም “Chapter 33: A Revelation about Jesus Christ፣” በየትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 126–27፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ)። ጥቅሱን አብራችሁ ስታነቡ፣ የመረጣችሁትን እያንዳንዱን እውነት የሚወክል ልጆቻችሁ የሚያደምጡት አንድ ቃል ወይም ሐረግ ልትሰጧቸው ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፦
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥23፣ 29፣ 38
ወደ ምድር ከመምጣቴ በፊት ከሰማይ አባት ጋር እኖር ነበር።
-
አዳኙ በክፍል 93 ውስጥ “በመጀመሪያ” ከእግዚአብሔር ጋር እንኖር እንደነበር ሶስት ጊዜ አጽንዖት ሰጥቷል (ቁጥር 23፣ 29፣ 38)። ልጆቻችሁ ይህንን እንዲገነዘቡ ለመርዳት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥23፣ 29፣ 38ን እንዲያነቡ ልትጋብዟቸው እና በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተደገመን አንድ እውነት እንዲፈልጉ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። የሰማይ አባት እነዚህን እውነቶች እንድናውቅ የሚፈልገው ለምንድን ነው? ከመወለዳችን በፊት ከሰማይ አባት ጋር ስለነበረን ህይወት ልጆቻችሁ ምን እንደሚያውቁ ልትጠይቋቸውም ትችላላችሁ። ይበልጥ እንዲማሩ ለመርዳት፣ ከሚከተሉት ቅዱሳት መጻህፍት ምንባቦች ውስጥ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑትን ከእነርሱ ጋር አንብቡ፦ ኤርምያስ 1፥5፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥53–56፤ ሙሴ 3፥5፤ አብርሃም 3፥22–26።
-
“I Am a Child of God” ወይንም “I Lived in Heaven” (የልጆች መዝሙር መፅሀፍ፣፣ 2–3፣ 4) የሚሉ መዝሙሮችን አብራችሁ ልትዘምሩ እና ወደ ምድር ስለመጣንበት ዓላማ ከእነዚህ መዝሙሮች የምንማራቸውን እውነቶች ልትወያዩ ትችላላችሁ።
እግዚአብሔርን ስታዘዝ ብርሃንን እና እውነትን እቀበላለሁ።
-
ልጆቻችሁ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93 ውስጥ ያሉትን የመታዘዝ እውነታዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለመርዳት፣ ከዚህ ክፍል ውስጥ የተወሰኑ የቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻዎችን በትናንሽ ወረቀት ላይ መጻፍን አስቡ። እያንዳንዳቸው እነዚህ ጥቅሶች የሚያስተምሩትን እውነቶች በተለያዩ ትናንሽ ወረቀቶች ላይ ጻፉ። ልጆቻችሁ በአንድነት ጥቅሶቹን ማንበብ እና እውነቱን ከቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻዎች ጋር ማዛመድ ይችላሉ። ምሣሌዎቹ እነዚህን ሊያካትቱ ይችላሉ፦
-
ቁጥር 24፦ እውነት በፊት፣ አሁን እና ወደፊት እውን የሆኑ ነገሮችን ማወቅ ነው።
-
ቁጥር 28፦ ትዕዛዛቱን ስጠብቅ ብርሃንን እና እውነትን መቀበል እችላለሁ።
-
ቁጥር 37፦ ብርሃንና እውነት ሲኖረኝ ክፋትን መቋቋም እችላለሁ።
-
ቁጥር 39፦ በማልታዘዝ ጊዜ ብርሃን እና እውነት አይኖረኝም።
የጌታን ትእዛዛት በመጠበቃችሁ ያወቃችኋቸውን የእውነቶች ምሳሌዎች ልታካፍሉ ትፈልጉ ይሆናል።
-