ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 18–24፦ “ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89–92


“ነሐሴ 18–24፦ ‘ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89–92፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89–92፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ጥንዶች አብረው ምግብ እያበሰሉ

ነሐሴ 18–24፦ “ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89–92

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በነቢያት ትምህርት ቤት ውስጥ የእስራኤል ሽማግሌዎችን የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ስለመገንባት አስተማረ። ስለመንፈሳዊ እውነቶች ተወያዩ፣ አብረው ጸለዩ፣ ጾሙ እንዲሁም ወንጌልን ለመስበክ ተዘጋጁ። ነገር ግን ስለሁኔታው ዛሬ ለእኛ እንግዳ የሚመስል አንድ ነገር ነበር፣ ይህም ለኤማ ስሚዝም እንዲሁ ትክክል አልመሰላትም ነበር። በስብሰባዎቹ ወቅት ወንዶቹ ትምባሆ ያጨሱ እና ያኝኩ ነበር፣ ይህም በወቅቱ እንግዳ ነገር አልነበረም፣ ነገር ግን የእንጨት ወለሉን በማጥቆር አበልዞት ነበር እንዲሁም አየሩን በመጥፎ ሽታ በክሎት ነበር። ኤማ ስጋቷን ለጆሴፍ ነገረችው፣ ጆሴፍም ጌታን ጠየቀው። መልሱም ከማጨስ እና በትንባሆ ምክንያት ከሚከሰት መበለዝ ልቆ የሚሄድ ራዕይ ነበር። ለቅዱሳኑ፣ ለሚመጣው ትውልድ፣ “ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ”—የአካላዊ ጤንነት፣ “ጥበብ፣” እና “ታላቅ የእውቀት ሃብቶች” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥3፣ 19) ተስፋ ሰጠ።

በተጨማሪም Saints 1፥166–68ን ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89

የሴሚናሪ ምልክት
ጌታ በአካል እና በመንፈሥ ጤነኛ እንድሆን ለመርዳት የጥበብ ቃልን ሠጠኝ።

በነቢያት ትምህርት ቤት የነበሩት ሽማግሌዎች፣ ጆሴፍ ስሚዝ የጥበብ ቃልን በመጀመሪያ ሲያነብ ሲሰሙት፣ ወዲያውኑ “ሲጋራቸውን እና ጥፍጥፍ የሚታኘክ ትንባሆ አሽቀንጥረው ጣሉ“ (ቅዱሳን፣1፥168)። ጌታን ለመታዘዝ ፈቃደኞች እንደሆኑ ለማሳየት ፈለጉ። ምናልባት የጥበብ ቃል አንዳትጠቀሙ የሚከለክሏችሁን ነገሮች ቀድሞውኑ ከህይወታችሁ “አሽቀንጥራችሁ” ጥላችሁ ይሆናል፣ ነገር ግን ከዚህ ራዕይ ውስጥ ሌላ ምን ነገር ልትማሩ ትችላላችሁ? እነዚህን ሃሳቦች ከግምት ውስጥ አስገቡ፦

  • ራዕዩ “ከተስፋ ጋር የሆነ መሰረታዊ መርህ” (ቁጥር 3)—ውሳኔ አሰጣጥን የሚመራ ፅኑ እውነት እንደሆነ አድርጋችሁ አስቡ። ውሳኔዎቻችሁን የሚመሩ ምን መርሆችን ታገኛላችሁ? ጌታ ምን አይነት በረከቶችን ቃል ይገባል? ( ቁጥር 18–21 ተመልከቱ)። እነዚያን ቃል ኪዳኖች በህይወታችሁ የፈፀመው እንዴት ነው?

  • ከጥበብ ቃል ጋር በተያያዘ “በሚያድሙ ሰዎች ልብ ውስጥ … ተንኮል እና አላማዎች” (ቁጥር 4) ምን ምሳሌዎችን አይታችኋል? ከዚህ ራዕይ በተጨማሪ እነዚህን ተንኮሎች ለማስወገድ ወይም ለማሸነፍ እንዲረዳችሁ ጌታ ምን ሰጥቷችኋል?

  • ይህ ራዕይ ስለጌታ ምን ያስተምራችኋል? የጥበብ ቃል ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥34–35 ጋር የሚዛመደው እንዴት ነው?

  • አካላችሁን በተሻለ ሁኔታ ለመንከባከብ ምን እንድታደርጉ ተነሳሳችሁት?

የጥበብ ቃልን ለምን እንደምትኖሩ ለሌሎች ለማስረዳት ዕድሎች ነበሯችሁ—እንዲሁም ወደፊት ብዙ እድሎች ሊኖሯችሁ ይችላሉ። ስለአዳኙ፣ ስለ ሰውነታችን ቅድስና እና ስለሌሎች መንፈሳዊ እውነቶች ለመመስከር እነዚህን እድሎች እንዴት መጠቀም እንደምትችሉ አስቡ። ሃሳቦችን ለማግኘት፣ “ሰውነታችሁ ቅዱስ ነው፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ፣ 22–29 ተመልከቱ።

በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 6፥19–20፤ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Principles and Promises ፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2016 (እ.አ.አ)፣ 78–79፤ Topics and Questions፣ “Word of Wisdom፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “The Word of Wisdom፣” በRevelations in Context፣ 183–91፤ “Addiction፣” “Physical Health፣” Life Help፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

4:39

መርሆች እና ቃልኪዳኖች

በመርህ ተማሩ እንዲሁም አስተምሩ አድርግ እና አታድርግ የሚሉ ዝርዝሮችን ከማዘጋጀት ይልቅ የመምረጥ ነፃነታችንን እና በክርስቶስ ያለንን እምነት ለመጠቀም በመርሆዎች መኖር እንችላለን። ለምሳሌ፣ የጥበብ ቃልን በተመለከተ እንደእነዚህ ያሉ በመርህ ላይ የተመሠረቱ ጥያቄዎችን አስቡ፦ የጥበብ ቃልን ለመታዘዝ እየተቸገረ ላለ ሠው ሊያበረታቱት የሚችሉት የትኞቹ መርሆዎች ናቸው? በጥበብ ቃል እየኖርኩኝም እንኳን የጤና ችግሮች በሚያጋጥሙኝ ጊዜ ሊያጽናኑኝ የሚችሉት የትኞቹ መርሆዎች ናቸው?

አንዲት ሴት ዮጋ እየሰራች

የሠማይ አባታችን ሰውነታችንን እንድንንከባከብ ይፈልጋል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥1–17

ቀዳሚ አመራር “የመንግስቱን ቁልፍ“ ይዘዋል።

ክፍል 90 ውስጥ ጌታ አሁን የቀዳሚ አመራር አባላት ብለን ለምንጠራቸው ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ለስድኒ ሪግደን እና ለፍሬድሪክ ጂ.ዊሊያምስ “ስለአገልግሎቱ እና ስለአመራሩ” (ቁጥር 12) መመሪያ ሰጥቷል። ከቁጥር 1–17 ስለቀዳሚ አመራር ምን ትማራላችሁ? የቀዳሚ አመራር አባላት የቅርብ ጊዜ መልዕክቶችን መከለስን አስቡ። “የዚህን ቤተክርስቲያን እና መንግስት ጉዳዮች በሥርዓት [ለ]ማደራጀት” (ቁጥር 16) ምን ያደርጋሉ? እነዚህ ለእናንተ “እንደ ቀላል ነገር” (ቁጥር 5) እንዳልሆኑ ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?

Come፣ Listen to a Prophet’s Voice” (መዝሙር፣ ቁጥር. 21) ወይም ሌላ ስለነቢያት የሚያወሳ፣ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ካሉ ትምህርቶች ጋር የሚዛመድ፣ መዝሙር መዘመርን ወይም ማንበብን አስቡ። ቀዳሚ አመራር የሚሰጡት አገልግሎት የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንድታውቁ የረዳችሁ እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥24

”ሁሉም ነገሮች [ለእኔ] በጎነት አብረው ይሰራሉ።”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥24 ውስጥ ስላለው የጌታ ቃል ኪዳን ምስክርነት የሚሰጡ ከዚህ በፊት የነበሯችሁን ማናቸውንም ተሞክሮዎች አሰላስሉ። ልምዶቻችሁን መመዝገብ እንዲሁም ለአንድ የቤተሰብ አባል ወይም ለምትወዱት ሠው—ምናልባት ማረጋገጫ ወይም ማበረታቻ ለሚፈልግ አንድ ሰው—ማጋራትን አስቡ። አሁንም የተወሰኑ በረከቶችን እየጠበቃችሁ ከሆነ፣ ”ሁሉም ነገሮች [ለእናንተ] በጎነት አብረው [እንደሚሠሩ]” ለማየት ስትጠባበቁ ታማኝ ለመሆን ምን ማድረግ እንደምትችሉ አሰላሥሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥28–31

ቪየና ዣክ ማን ነበረች?

ቪየና ዣክ በሰኔ 10 ቀን 1787 (እ.አ.አ) በማሳቹሴት ውስጥ ተወልዳ ነበር። የእምነት ሴት እና የብዙ ገንዘብ ባለቤት የነበረችው ቪየና፣ ከሚስዮናውያን ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘችው በ1831 (እ.አ.አ) ነበር። መልዕክታቸው እውነት ስለመሆኑ መንፈሳዊ ምስክርነት ከተቀበለች በኋላ፣ ነቢዩን ለማግኘት ወደ ከርትላንድ ኦሃዮ ተጓዘች፣ በዚያም ተጠመቀች።

ቪየና በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥28–31 ውስጥ ጌታ ለእርሷ የሰጠውን ምክር ታዘዘች። ቀደም ሲል በከርትላንድ ውስጥ ያደረገችውን መዋጮ ጨምሮ፣ ለጌታ የሰጠችው የተቀደሰ ስጦታ፣ መሪዎች የከርትላንድ ቤተመቅደስ የሚገነባበትን መሬት ለመግዛት በሚሞክሩበት ወሳኝ ጊዜ መጣ። ቪየና በህይወቷ ሙሉ “ታማኝ እና ስራ ፈት … ያልነበረች” ስትሆንም፣ በመጨረሻም በ96 አመቷ ባረፈችበት በሶልት ሌክ ሸለቆ ውስጥ ”በሰላም ልትሰፍር” (ቁጥር 31) ችላ ነበር።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 91

“መንፈሥ እውነትን ይገልጣል።”

ሁላችንም “እውነት የሆኑ አያሌ ነገሮች” እና “እውነት ያልሆኑ ብዙ ነገሮች[ን]” ያካተቱ መልዕክቶች ያጋጥሙናል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 91፥1–2)። በቁጥር 91 ውስጥ በምታገኟቸው መልዕክቶች ውስጥ ያለውን እውነት እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁ ምን ምክር ታገኛላችሁ? መንፈሱ እውነትን ከሥህተት እንድታውቁ የረዳችሁ እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89

የጥበብ ቃል በአካል እና በመንፈስ ጤናማ እንድሆን ይረዳኛል።

  • ክፍል 89ን ለማስተዋወቅ፣ ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ የቤተመቅደስ ምስልን ማየት ወይም ስለ አካላዊ ጤንነት የሚናገር እንደ “The Lord Gave Me a Temple” (የልጆች መዝሙር መፅሀፍ፣፣ 153) ያለ ሰውነታችን ለመንፈሳችን ቤተመቅደስ እንደሆነ የሚያስተምር መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ አካላቸውን መንከባከብ የሚችሉባቸውን መንገዶች እንዲተውኑ እርዷቸው።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥10–17 ውስጥ ስላሉት የጌታ ትዕዛዛት ለማወቅ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ አካላችንን ጤናማ ለማድረግ ልንመገባቸው ወይም ልናደርጋቸው የምንችላቸውን ጥሩ ነገሮች መሣል ወይም መመልከት ትችላላችሁ (በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ያለውን ሥዕል እና የመሳተፊያ ገፅ ተመልከቱ)። ጌታ እንዳንጠቀም ያስጠነቀቀን ምንድን ነው? አካላችንን እንድንንከባከብ የሚፈልገው ለምንድን ነው?

  • ሽማግሌ ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን፣ ወጣቶች በአልኮል ወይም በአደንዛዥ ዕፅ በሚፈተኑበት ጊዜ ስለሚያደርጉት ነገር አስቀድመው እንዲያቅዱ መክረዋል። እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፣ “ፈተና በእናንተ ላይ ያለው የመቆጣጠር ኃይል ያነሰ ሆኖ ታገኙታላችሁ። እንዴት ምላሽ እንደምትሰጡ እና ምን እንደምታደርጉ አሰቀድማችሁ ወስናችኋል። በእያንዳንዱ ጊዜ ውሳኔ መስጠት አያስፈልጋችሁም” (“የክህነት የጨዋታ መፅሀፋችሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 48)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥4ን እና የሽማግሌ ስቲቨንሰንን መግለጫ አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ፣ በቀሪው የህይወት ዘመናቸው የጥበብ ቃልን ለመጠበቅ እንዴት አሁን መወሰን እንደሚችሉ ከልጆቻችሁ ጋር ተማከሩ። አንድ ሰው፣ ጓደኛም ቢሆን፣ ከጥበብ ቃል ጋር የሚጻረር ነገር ቢያቀርብላቸው እንዴት ምላሽ ሊሰጡ እንደሚችሉ የሚያሳይ ትወና መተወንም ትችላላችሁ። የጥበብ ቃልን ስናከብር ጌታ የሚባርከን እንዴት ነው? (ቁጥር 18–21 ተመልከቱ)።

ልጆች በባህር ዳርቻ እየተጫወቱ

ሰውነታችን የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥5

እግዚአብሔር የሚመሩኝን እና ጥበቃ የሚያደርጉልኝን ነቢያት ሰጥቶኛል።

  • የጥንት ነቢያትን ሥዕሎች መመልከት ወይም እንደ “Follow the Prophet” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 110–11) ያለ መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ልጆቹን በነቢያቱ በኩል የባረከው እንዴት ነው? የእግዚአብሔርን ነቢያት መስማት ያለብን ለምንድን ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥5 ተመልከቱ)። ከዚያም እናንተ እና ልጆቻችሁ በህይወት ያለውን ነቢይ ምሥል ተመልከቱ እንዲሁም ጌታ በእርሱ በኩል ያስተማራችሁን ወይም ያስጠነቀቃችሁን አንዳንድ ነገሮችን አካፍሉ። ነቢዩን መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 91

መንፈሱ እውነት የሆነውን ነገር እንዳውቅ ሊረዳኝ ይችላል።

  • ልጆቻችሁ ይህ ራዕይ ለምን እንደተሰጠ እንዲገነዘቡ ለመርዳት የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 91ን የክፍል መግቢያ ማጠቃለያ ማቅረብ ትችላላችሁ። “እውነት የሆኑ አያሌ ነገሮች[ን]” እና “እውነት ያልሆኑ ብዙ ነገሮች[ን]” የምናገኝባቸውን፣ እንደ ሚዲያ ያሉ፣ ቦታዎችን ሊያስቡ ይችላሉ (ቁጥር 1–2)። ቁጥር 4–6 ስለመንፈስ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? መንፈስ ቅዱስ ትክክል የሆነውን እንድናውቅ የሚረዳን እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

ፍሬ

“የወይን ፍሬም፣ … ሁሉም እህል ለሰው ምግብ ጥሩ ነው።”

የመሳተፊያ ገጽ ለልጆች