ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 11–17፦ “የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88


“ነሐሴ 11–17፦ ‘የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች –88፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
በትንሽ ቤት ውስጥ የተዘጋጀ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ

የነቢያት ትምህርት ቤት የተካሄደው በዚህ ክፍል ውስጥ ነበር።

ነሐሴ 11–17፦ “የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88

አልፎ አልፎ ጌታ ለነቢያቱ አስደናቂ መገለጦችን በመስጠት ማለቂያ ስለሌለው “ሞገሱ እና ክብሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥47) ትንሽ ፍንጭ ይሰጠናል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88ም እንዲህ ያለ ራዕይ ነው—ስለ ብርሃን እና ስለክብር እንዲሁም ስለመንግስታት የሚናገር፣ በንጽጽር ምድራዊ ፍላጎቶቻችን አነስተኛ መስለው እንዲታዩ ሊያደርግ የሚችል ራዕይ ነው። ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ ልንረዳው ባንችልም በዘለዓለማዊነት ውስጥ ቢያንስ እስካሁን ከምናውቀው እጅግ የሚልቅ ነገር እንዳለ ሊሰማን ይችላል። በእርግጥ ጌታ እነዚህን ታላላቅ እውነቶች የተናገረው እኛን ለማስፈራራት ወይም ትንሽ እንደሆንን እንዲሰማን ለማድረግ አይደለም። በእርግጥ፣ “እግዚአብሔርን የምትረዱበት ቀን ይመጣል” በማለት ተስፋ ሰጥቷል (ቁጥር 49፤ አጽንዖት ተጨምሮበታል)። ምናልባት ጌታ የከርትላንድ ቅዱሳን የነቢያት ትምህርት ቤትን እንዲመሰርቱ ያሳሰበው ያ አስደናቂ ውጤት እንዲመጣ ይሆናል። “ራሳችሁን አደራጁ” ብሏል። “አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ አዘጋጁ፤ … እንዲሁም … የእግዚአብሔርን ቤት መስርቱ” (ቁጥር 119)። እይታችንን ከሥጋዊው አለም ባሻገር ከፍ የሚያደርገው፣ “ፊቱን ለእኛ [የሚገልጠው]፣” እንዲሁም “በሰለስቲያል መንግስት ህግ እንድንጸና” [የሚያዘጋጀን] (ቁጥር 68፣ 22) ከማንኛውም ቦታ በላይ በእግዚአብሔር ቅዱስ ቤት ውስጥ—እንዲሁም በቤታችን ውስጥ ነው።

Saints1፥164–66ን ተመልከቱ።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88

ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን ይሰጠኛል።

ጦርነት “በሁሉም ህዝብ ላይ እንደሚፈስ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 87፥2) ካስጠነቀቀ ከቀናት በኋላ፣ ጌታ የሠላም ባህላዊ ምልክት የሆነውንና ጆሴፍ ስሚዝ “የወይራ ቅጠል” ሲል የጠራውን ራዕይ ሰጠው (የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88የክፍል መግቢያ፤ በተጨማሪም ዘፍጥረት 8፥11ን ተመልከቱ)። በዚህ ሳምንት መላውን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88ን ስታጠኑ፣ ጌታ ለእናንተ ያለውን የሠላም መልዕክት ፈልጉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6–67

ብርሃን እና ህግ ከኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል።

ብርሃን እና ህግ የሚሉት ቃላት በክፍል 88 ውስጥ ብዙ ጊዜ ተደጋግመዋል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6–67 ውስጥ እነዚህን ቃላት በምታገኙባቸው ቁጥሮች ላይ ምልክት አድርጉ ወይም ማስታወሻ ያዙ እንዲሁም ስለብርሐን እና ስለህግ—እንዲሁም ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደምትማሩ ጻፉ። እነዚህ ጥቅሶች ብርሃንን ለመቀበል እና “የክርስቶስን ህግ” (ቁጥር 21) ለመኖር ምን የማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

በተጨማሪም ኢሳይያስ 60፥19ዮሐንስ 1፥1–93 ኔፊ 15፥9፤ ቲሞቲ ጄ. ዳይክ፣ “Light Cleaveth unto Light፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 112–15፤ ሼረን ዩባንክ፣ “ክርስቶስ፦ በጨለማው የሚያበራው ብርሀን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 73–76 ተመልከቱ።

ምስል
ቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍትን በአንድ ላይ እያነበቡ

ቅዱሳት መጻህፍት የክርስቶስን ህግ ይይዛሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥62–64

“ወደ እኔ ቅረቡ።”

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉት ተስፋዎች እውነት መሆናቸውን ያሳዩአችሁ ተሞክሮዎች የትኞቹ ናቸው? ወደ ክርስቶስ “ለመቅረብ” ቀጥሎ የምትወስዱት እርምጃ ምንድን ነው? “Nearer፣ My God፣ to Thee፣” (መዝሙር፣ ቁጥር 100) የሚለውን መዝሙር የጥናታችሁ እና የአምልኳችሁ ክፍል ማድረግን አስቡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥67–76

በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ንፁህ መሆን እችላለሁ።

“ራሳችሁን ቀድሱ” የሚለው የጌታ ትዕዛዝ በክፍል 88 (ቁጥር 68፣ 74) ውስጥ ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል። የዚህ ሐረግ ትርጉም ምን ይመስላችኋል? በቅዱሳት መፃህፍት መመሪያ (የወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ ቅድስና በሚለው ሥር ያሉትን የተወሰኑትን ምንባቦች ልትከልሱ ትችላላችሁ። የተቀደስን መሆን የምንችለው እንዴት ነው? ይህ ጥያቄ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥67–76 ጥናታችሁን ይምራው እንዲሁም የምትቀበሏቸውን ማናቸውንም መንፈሳዊ ግንዛቤዎች መዝግቡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥77–80፣ 118–26

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
“እውቀትን፣ እንዲሁም በጥናትና ደግሞም በእምነት፣ እሹ።”

ቅዱሳን “የነቢያት ትምህርት ቤት” በከርትላንድ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችs 88፥137) እንዲያቋቁሙ ጌታ ነገራቸው። በክፍል 88 ውስጥ ያለው አብዛኛው መመሪያ እንዴት እንደሚያቋቁሙ አስተምሯቸዋል። ይህ መመሪያ በራሳችሁ ህይወት “የእውቀትን ቤት… [እንድትመሰርቱ]” (ቁጥር 119) ሊረዳችሁም ይችላል። በእርግጥ፣ ቁጥር 77–80 እና 118–26ን “ቤታችሁን [ወይም ህይወታችሁን] የወንጌል መማሪያ ማዕከል ለማድረግ ለማስተካከል ” እና “የእምነት ቅዱስ ቦታ” ለማድረግ እንደሚረዱ ሥዕላዊ ንድፎች አድርጋችሁ ልታዩዋቸው ትችላላችሁ (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Becoming Exemplary Latter–day Saints፣”ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ) 113)። ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ተግባራዊ ልታደርጓቸው እንደሚያስፈልጋችሁ የሚሰማችሁን ሐረጎች ጨምሮ የእናንተ የግል “ማስተካከያ” ምን ሊመስል እንደሚችል የሚያሣይ ሥዕል መሣል አስደሳች ሊሆን ይችላል።

እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎችን መመርመር የሚረዳ ሊሆን ይችላል፦ መማር እና ትምህርት ለጌታ አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? ምን እንዳጠና ይፈልጋል? እንዴት እንድማር ይፈልጋል? የእነዚህን ጥያቄዊች መልሶች በቁጥር 77–80 እና በ “እውነት ነጻ ያወጣችችኋል” ውስጥ ፈልጉ (ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ፣ 30–33)።

“በጥናትና ደግሞም በእምነት” (ቁጥር 118) መማር ምን ማለት ይመስላችኋል? “Seeking Knowledge by the Spirit” ከሚለው የሽማግሌ ማትያስ ሄልድ መልዕክት ምን ግንዛቤዎችን ታገኛላችሁ? (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 31–33)።

በተጨማሪም፣ Topics and Questions፣ “Seeking Truth and Avoiding Deception፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “A School and an Endowment፣” በ Revelations in Context 174–82 ውስጥ ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥33

የሰማይ አባት መልካም ሥጦታዎችን ይሠጣል።

  • ልጆቻችሁ፣ ደስ ብሏቸው ስለተቀበሏቸው እና ስለሌሎች ደስ ሣይላቸው ስለተቀበሏቸው ስጦታዎች እንዲናገሩ በመጠየቅ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥33 ውይይትን መጀመር ትችላላችሁ። ምናልባት ስጦታን በደስታ ሲቀበሉ የሚያሳይ ትወና ሊተውኑ ይችላሉ። ከዚያም የሠማይ አባት ስለሚሰጠን ስጦታዎች (ለምሣሌ ስለመንፈስ ቅዱሥ ሥጦታ) መናገር ትችላላችሁ። እነዚህን ሥጦታዎች በደሥታ የምንቀበለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥63

አዳኙን ብፈልገው፣ አገኘዋለሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥63 ልጆቻችሁ በህይወታቸው ውስጥ የጌታን መገኘት እንዲፈልጉ ለማበረታታት የሚረዱ አንዳንድ የሚያስደስቱ መሳተፊያዎችን እንድታደርጉ የሚያነሳሱ የድርጊት ቃላትን ይዟል። ለምሳሌ “ተግታችሁም ፈልጉኝ እናም ታገኙኝማላችሁ” (አጽንዖት ተጨምሯል) ወይንም “አንኳኩ ይከፈትላችሁማል” በሚለው ሐረግ ላይ ለመወያየት የሚያስችል ጨዋታ ልታስቡ ትችላላችሁ?

ልጆች የተለያዩ ነገሮችን ይፈልጋሉ። “አብዛኞቹ ልጆች ብዙ የስሜት ህዋሳትን ሲጠቀሙ ከሁሉም በተሻለ ሁኔታ ይማራሉ። ልጆች በሚማሩበት ጊዜ የማየት፣ የመስማት እና የመንካት የስሜት ህዋሳቶቻቸውን እንዲጠቀሙ ለመርዳት መንገዶችን ፈልጉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ፣ የማሽተት እና የመቅመስ የስሜት ህዋሳቶቻቸውን ለማካተት መንገዶችን ልትፈልጉም ትችላላችሁ!” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 32)።

  • “ወደ እኔ ቅረቡ” በሚለው የአዳኙ ግብዣ ላይ አፅንዖት ለመስጠት፣ አንድ ልጅ በአንደኛው የክፍሉ ወገን በመሆን የኢየሱስን ምስል (በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ እንዳለው ዓይነት ምስል) እንዲይዝ፣ ሌሎቹ ልጆች ደግሞ በሌላኛው ወገን እንዲቆሙ መጠየቅ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ወደ አዳኙ ለመቅረብ ማድረግ ስለሚችሏቸው ነገሮች በሚያስቡ ጊዜ፣ ወደ ሥዕሉ አንድ እርምጃ ሊራመዱ ይችላሉ፣ እንዲሁም ሥዕሉን የያዘው ልጅ ወደ ሌሎቹ ልጆች አንድ እርምጃ ሊራመድ ይችላል። እናንተ እንዴት ወደ አዳኙ እንደምትቀርቡ እንዲሁም እርሱ እንዴት ወደ እናንተ እንደሚቀርብ ከልጆቻችሁ ጋር ተነጋገሩ። እንደ “I Feel My Savior’s Love” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 74–75) ያለ ስለዚህ ርዕስ የሚወሳ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥77–80፣ 118

የሰማይ አባት እንድማር ይፈልጋል።

  • ልጆቻችሁ በትምህርት ቤት ወይም በመጀመሪያ ክፍል እየተማሯቸው ስላሉት ነገሮች እንዲነግሯችሁ ጠይቋቸው። እናንተም እየተማራችኋቸው ስላላችሁት አንዳንድ ነገሮች ማካፈልም ትችላላችሁ። ከዚያም ምንለምን፣ እና እንዴት.የሚሉትን ቃላት ለልጆቻችሁ ልታሳዩዋቸው ትችላላችሁ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥77–79 ውስጥ ጌታ ስለምን እንድንማር እንደሚፈልግ ለማወቅ እንዲፈልጉ እርዷቸው። ከዚያም አንድ ላይ በመሆን በቁጥር 80 ውስጥ ለምን እንድንማር እንደሚፈልግ እንዲሁም በቁጥር 118 ውስጥ እንዴት መማር እንዳለብን ለማወቅ ተመልከቱ።

ምስል
ቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍትን በአንድ ላይ እያነበቡ

“እውቀትን … በጥናትና ደግሞም በእምነት፣ እሹ።”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥119

ቤታችን ልክ እንደ ቤተመቅደስ ቅዱስ ሊሆን ይችላል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች88፥119ን ለልጆቻችሁ ስታነቡ፣ “ቤት” የሚለውን ቃል ሲሰሙ የቤተመቅደስ አናት ቅርፅን በእጃቸው መስራት ይችላሉ። የሰማይ አባት፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ቅዱሳኑ ቤተመቅደስ ወይም “የእግዚአብሔርን ቤት” እንዲገነቡ ይፈልግ እንደነበረ አብራሩ።

  • ልጆቻችሁ ቤታቸውን የሚገልጹ ሰባት ቃላትን እንዲመርጡ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ጌታ ቤቱን ለመግለፅ የተጠቀመባቸውን ሰባት ቃላት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥119 ውስጥ እንዲፈልጉ እርዷቸው። ቤታችንን “የእግዚአብሔርን ቤት” ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

አትም