ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መስከረም 1–7፦ “ለፅዮን ደህንነት”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94–97


“መስከረም 1–7፦ ‘ለፅዮን ደህንነት’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94–97፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94–97፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

የከርትላንድ ቤተመቅደስ

የከርትላንድ ቤተመቅደስ በአል ራውንድስ

መስከረም 1–7፦ “ለፅዮን ደህንነት”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94–97

በጥንት ጊዜ፣ ጌታ ድንኳን እንዲሠራ ሙሴን ባዘዘው ጊዜ፣ እርሱም “በተራራው [እንደተገለጠለት] ምሳሌ ሁሉን [ያደርግ] ዘንድ [ተጠንቅቆ] ነበር” (ዕብራውያን 8፥ 5፤ በተጨማሪም ፥ ዘፀአት 25፥8–9) ተመልከቱ። ድንኳኑም የእስራኤል ምድረበዳ ሰፈር ማዕከል ሊሆን ነበር (ዘኁልቁ 2፥1–2)።

በ1833 (እ.አ.አ)፣ ጌታ “በአለም በሚሰሩበት ሳይሆን”፣ ነገር ግን “በማሳያችሁ ሥርዓት ይሰራ” ሲል ጆሴፍ ስሚዝ ቤተመቅደሶችን እንዲሠራ አዞታል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥13–14፤ እንዲሁም 97፥10ን ተመልከቱ)። እንደ ምድረበዳው ድንኳን፣ ቤተመቅደሱ በከርትላንድ ውስጥ ዋነኛ ገፅታ ሆኖ እንዲያገለግል የታሰበ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94፥1 ተመልከቱ)።

ዛሬ ቤተመቅደሶች በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ። ምንም እንኳን በከተሞቻችን እምብርት የሚገኙ ባይሆኑም፣ የህይወታችን እምብርት መሆን ወደሚገባው ወደ ክርስቶስ ያመለክታሉ። እያንዳንዱ ቤተመቅደስ በመልክ የሚለያይ ቢሆንም፣ በውስጣቸው ተመሳሳይ መለኮታዊ ንድፎችን እንማራለን—እኛን ወደ እግዚአብሔር ፊት የሚመልስ ሰማያዊ እቅድ። ቅዱሥ ሥርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች “በአለም በሚሰሩበት ሳይሆን” ነገር ግን እግዚአብሔር በሚያሳየን ንድፍ መሠረት ከክርስቶስ ጋር ያገናኙናል እንዲሁም ቤተሰባችንን ያበረታታሉ።

Saints1፥169–70፤ “A House for Our God፣” Revelations in Context 165–73 ተመልከቱ፥።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 9497፥10–17

“[በ]ማንኛቸውም ነገሮች ሁሉ፣ [ለጌታ] [መ]ቀደስ” እችላለሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94 ውስጥ ጌታ የአስተዳደር ህንፃዎችን—ቢሮ እና ማተሚያ ቤት በከርትላንድ ውስጥ ስለመገንባት መመሪያ ሰጥቷል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 94፥2–12ጌታ ስለእነዚህ ህንፃዎች ከተናገረው የሚያስደንቃችሁ ምንድን ነው? ጌታ በ97፥10–17 ውስጥ ስለቤተመቅደስ ከተናገረው ጋር የሚነጻጸረው እንዴት ነው?

“[በ]ማንኛቸውም ነገሮች ሁሉ፣ [ለጌታ] [መ]ቀደስ” ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95

ጌታ የሚወዳቸውን ይቀጣል።

ክፍል 95 ውስጥ ያለው ራዕይ በመጣ ጊዜ፣ ቅዱሳን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲሠሩ ጌታ ካዘዛቸው አምስት ወራት ያህል አልፈው ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥117–19) እንዲሁም ገና አልጀመሩም ነበር። ጌታ በዚህ ራዕይ እንዴት ማስተካከያ እንደሠጣቸው አስተውሉ። በመንፈስ የተነሳሳ እርማት ለመስጠት የምታገኟቸውን የመርሆዎች ዝርዝር ማዘጋጀትም ትችላላችሁ። ቅዱሳኑን ካረመበት መንገድ ስለጌታ ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥43–44፤ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “የምወዳቸውን ያህል እቀጣለሁ እናም እገሥጻለሁ፣” ሊያሆና ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 97–100 ተመልከቱ።

8:40

God Loves His Children

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥8፣ 11–1797፥10–17

የሴሚናሪ ምልክት
ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።

በከርትላንድ የጌታን ቤት ባለመገንባታቸው ከተገሰጹ በኋላ፣ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች በስንዴ እርሻ ላይ የሚገነቡበትን ስፍራ መረጡ። የነቢዩ ወንድም የሆነው ኃይረም ስሚዝ ወዲያውኑ ረጅም ማጭድ ለማምጣት እና እርሻውን መመንጠር ለመጀመር ተጣደፈ። “የጌታን ቤት ለመገንባት በዝግጅት ላይ ነን፣ እና እኔ በሥራው የመጀመሪያ ለመሆን ቆርጫለሁ” አለ (በTeachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [2007] (እ.አ.አ) 271፣ 273)። ኃይረም ቤተመቅደሱን ለመገንባት በጣም የጓጓው ለምን ይመስላችኋል? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥8፣ 11–1797፥10–17ን ስታነቡ ይህንን አሰላስሉ።

በዘመናችን፣ ጌታ “ቤተ መቅደሶችን የምንገነባበትን ፍጥነት እያሳደገ ነው።” (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “በቤተመቅደሥ ላይ ማተኮር፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2022 (እ.አ.አ) 121)። አንድ ሠው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ብዙ ቤተመቅደሶችን የምትሰራው ለምንድን ነው ብሎ ቢጠይቃችሁ ምን ትላላችሁ? ሊሆኑ የሚችሉ መልሶችን በሚከተሉት ውስጥ ፈልጉ፦

5:40

What Is a Temple?

ቅዱሳን የከርትላንድ ቤተመቅደስን ለመገንባት ያደረጉትን ጥረት በቤተመቅደስ ውስጥ ከጌታ ጋር ትርጉም ያለው ተሞክሮ ታገኙ ዘንድ ለመዘጋጀት ከምታደርጉት ጥረት ጋር ልታወዳድሩት ትችላላችሁ። ሃይረም ስሚዝ ለጌታ ቅዱስ ቤት የሠጠውን ተመሳሳይ ክብደት እንዴት ማሳየት ትችላላችሁ? ለምሳሌ፣ ሃይረም እንዳደረገው ሜዳውን እንደመመንጠር ያለ ምን ነገር ማድረግ ትችላላችሁ? ጌታ ምን ዓይነት መስዋዕቶችን እንድትከፍሉ የሚፈልግ ይመስላችኋል? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥12ን ተመልከቱ)።

በተጨማሪም፣ “Holy Temples on Mount Zion፣” መዝሙር፣ ቁጥር 289፤ Topics and Questions፣ “Temples ፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ገበሬ እያጨደ

ኃይረም ስሚዝ ለከርትላንድ ቤተመቅደስ የሚሆን መሬትን እየመነጠረ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥8–9

“እኔ እቀበላቸዋለሁ።”

በአንድ ሥብሥብ ወይም ቡድን ውስጥ ተቀባይነት ያላገኛችሁበትን ወይም ተቀባይነት ያጣችሁበትን ጊዜ አስቡ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥8–9 በጌታ ተቀባይነትን ስለማግኘት ከሚያስተምረው ጋር የሚመሳሰለው ወይም የሚለየው እንዴት ነው? ጌታ በቁጥር 9 ውስጥ ባለው ምሠላ ሊያስተምራችሁ እየሞከረ ያለው ምን ይመስላችኋል?

ኤሪክ ደብልዩ.ኮፒሽክ፣ “በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ይኑራችሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ)፣ 104–6።

ለመማር እና ለማስተማር የሚሆን መንፈሳዊ አካባቢ ፍጠሩ። ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “መንፈስ ቅዱስ … ሁሉንም ያስተምራችኋል” (ዮሐንስ 14፥26) ሲል ቃል ገብቷል። ስለዚህ በግላችሁ እየተማራችሁም ሆነ ከሌሎች ጋር፣ መንፈስን መጋበዝን ቅድሚያ ስጡ። የተቀደሠ ሙዚቃ፣ ጸሎት እና ፍቅር ያሉበት ግንኙነቶች፣ መንፈስ ቅዱስ እውነትን ሊያስተምራችሁ የሚችልበትን ሰላማዊ፣ መንፈሳዊ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ይረዳሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥18–28

ፅዮን “ልበ ንጹህ” ናት።

በ1830ዎቹ (እ.አ.አ) ለነበሩት ቅዱሳን፣ ፅዮን ቦታ ነበረች። ጌታ በክፍል 97 ውስጥ በሠጠው ራዕይ ትርጉሙ “ልበ ንጹህ” የሆነውን ህዝብንም እንዲገልጽ በማድረግ አሰፋው (ቁጥር 21)። ቁጥር 18–28 በምታነቡበት ጊዜ፣ ፅዮን የሚለውን ቃል ስታነቡ ይህንን ትርጉም ልትተኩ ትችላላችሁ። ለእናንተ በልብ ንጹህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?

በተጨማሪም ሙሴ 7፥18 ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥897፥10–17

ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።

  • ክፍል 95 እና 97ን የተወሰነ ታሪካዊ ዳራ ለማግኘት፣ የሚከተለውን ለልጆቻችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ፦ “The Kirtland Temple” በDoctrine and Covenants Stories for Young Readers (የወንጌል ላይብረሪ፤ በተጨማሪም Saints1፥210 ተመልከቱ)። ልጆቻችሁ የከርትላንድ ቤተመቅደስን ለመገንባት እየረዱ (እንጨት መቁረጥ፣ ምስማር መምታት፣ ግድግዳዎችን ቀለም መቀባት እና የመሳሰሉትን እያደረጉ) እንደሆነ በማስመሰል ሊደሰቱ ይችላሉ። ጌታ ቤተመቅደሶችን እንድንገነባ ለምን እንደሚፈልግ ልጆቻችሁን ለማስተማር ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥8ን ስታነቡ፣ በዚህ መዘርዝር ውስጥ እንዳሉት ዓይነት የከርትላንድ ቤተመቅደስ ምስሎችን ልታሣዩዋቸውም ትችላላችሁ።

1:17

The Kirtland Temple

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥15–16 አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ ቤተመቅደስ ለእናንተ ለምን ልዩ እንደሆነ አንዳችሁ ለሌላችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ ለጌታ ቤት ጥልቅ አክብሮት እንዲሰማቸው ለመርዳት እንደ “I Love to See the Temple” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 95) ያለ መዝሙር አብራችሁ መዘመርም ትችላላችሁ። ቤተመቅደስ የተቀደሰ የሆነው ለምንድን ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥1–2፣ 8–9፣ 21

ፅዮን “ልበ ንጹህ” ናት።

  • ልጆቻችሁ ንፁህ የሚለው ቃል በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥21 ውስጥ ያለውን ትርጉም እንዲገነዘቡ ለመርዳት፣ አንድ ላይ ሆናችሁ አንድ ብርጭቆ ንጹህ ውሃን መመልከት እና ውሃውን ቆሻሻ የሚያደርገውን አንድ ነገር (እንደ ቆሻሻ ወይም በርበሬ) መጨመር ትችላላችሁ። ውሃ ንፁህ መሆን የሚያስፈልገው ለምንድን ነው? ከዚያም ልጆቻችሁ ቁጥር 21ን ማንበብ እና ጣታቸውን ንፁህ በሚለው ቃል ላይ ማድረግ ይችላሉ። ልቦቻችን ንፁህ ናቸው ሲባል ምን ማለት ነው? ቁጥር 1–2 እና 8–9 የተወሰነ ሃሳቦችን ሊሠጧችሁ ይችላል። አዳኙ ልቦቻችንን ንፁህ ለማድረግ የሚረዳን እንዴት ነው?

ቆሻሻ ውሃ እና ንፁህ ውሃ

የሰማይ አባት ልበ ንፁህ እንድሆን ይፈልጋል ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥8–9

ሠዎች ከእርሱ ጋር የገቧቸውን ቃል ኪዳኖች ሲጠብቁ ጌታ ይባርካቸዋል።

  • ልጆቻችሁ፣ በምንጠመቅበት ጊዜ ወይም በቤተመቅደስ ውስጥ፣ ከጌታ ጋር ምን አይነት ቃል ኪዳኖችን እንደምንገባ ያውቃሉ? ሞዛያ 18፥9–10፣ 13 ወይም አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ፣27.2ን ከእነርሱ ጋር በማንበብ እነዚያን ቃል ኪዳኖች መከለስን አስቡ። “ቃል ኪዳኖቻ[ችሁን] በመስዋዕት ለማክበር” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥8) እንዴት እንደምትጥሩ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

  • ልጆቻችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥9 ስለሚገልፀው ነገር ሥዕሎችን እንዲሥሉ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ሥዕሎቻቸውን ሲያሳዩ፣ ቃል ኪዳኖቻችሁን በመጠበቃችሁ ምክንያት ጌታ እንዴት እንደባረካችሁ ተናገሩ። እነዚያ በረከቶች “በንጹህ ወንዝ አጠገብ እንደተተከለ፣ … በጣም ፍሬአማ እንደሆነ ዛፍ” የሆኑት እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

የከርትላንድ ቤተመቅደስ ግንባታ

Building the Kirtland Temple [የከርትላንድ ቤተመቅደስን መገንባት] በዋልተር ሬን

የልጆች የአክቲቪቲ ገጽ