“መሥከረም 8–14፦ ‘ዕረፉ፣ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98–101፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98–101፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
መሥከረም 8–14፦ “ዕረፉ፣ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98–101
በ1830ዎቹ (እ.አ.አ) ለነበሩት ቅዱሳን፣ ኢንዲፐንደንስ፣ ሚዙሪ፣ ቃል በቃል የተስፋ ቃል ምድር ነበር። ይህም የፅዮን “አማካዩ ስፍራ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 57፥3)—በምድር ላይ ያለ የእግዚአብሔር ከተማ—እናም የቅዱሳን በዚያ መሰባሰብ ለዳግም ምጽአቱ አስደሳች ቅድመ ሁኔታ ነበር። በአካባቢው የነበሩ ጎረቤቶቻቸው ግን ነገሮችን በተለየ መንገድ አይተውታል። እግዚአብሔር ምድሪቱን ለቅዱሳኑ ሰጥቷል የሚለውን ተቃወሙ፣ እንዲሁም ወደ አካባቢው በፍጥነት እጅግ ብዙ ሰዎች በመምጣታቸው የተነሳ የሚኖረው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ውጤቶች ምቾት አልሠጣቸውም ነበር። ብዙም ሳይቆይ ምቾት ማጣታቸው ወደ ስደትና ብጥብጥ ተለወጠ። በ1833 (እ.አ.አ)፣ የቤተክርስቲያኗ ማተሚያ ቢሮ ወደመ፣ ቅዱሳንም ከቤቶቻቸው ተገደው ወጡ።
ጆሴፍ ስሚዝ ከ800 ማይል በላይ ርቆ በከርትላንድ ውስጥ ነበር፣ እናም ይህ ዜና እሱ ጋር ለመድረስ ሳምንታትን ወስዶ ነበር። ነገር ግን ጌታ ምን እየተደረገ እንዳለ ያውቅ ነበር፣ እናም ቅዱሳንን የሚያጽናኑ የሰላም እና የማበረታቻ መርሆዎችን፣ እንዲሁም ስደት በሚያጋጥመን ጊዜ፣የጽድቅ ፍላጎቶቻችን ሳይፈጸሙ በሚቀሩበት ጊዜ፣ ወይም የዕለት ተዕለት መከራችን ውሎ አድሮ በሆነ መንገድ “ለመልካም ነገር አብረው እንደሚሠሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥3) ማስታወሻ በሚያስፈልገን ጊዜ የሚረዱ መርሆችን ለነቢዩ ገልጦለታል።
Saints 1፥171–93፤ “Waiting for the Word of the Lord፣” Revelations in Context፣ 196–201 ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥1–3፣ 11–14፣ 22፣ 101፥1–16፣ 22–31፣ 36
ፈተናዎቼ ለእኔ ጥቅም አብረው ሊሠሩ ይችላሉ።
በህይወታችን ውስጥ አንዳንድ ፈተናዎች የሚከሰቱት በራሳችን ምርጫዎች ምክንያት ነው። ሌሎቹ ደግሞ የሚከሰቱት በሌሎች ምርጫዎች ነው። እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ የምድራዊ ህይወት አካል ክፍል የሆኑ ነገሮች ይከሰታሉ። ምክንያቱ ምንም ቢሆን፣ ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር ስንመልሥ፣ መከራ መለኮታዊ ዓላማዎችን ለመፈፀም ሊረዳ ይችላል።
ይህ በ1833 (እ.አ.አ) በሚዙሪ ለነበሩት ቅዱሳን እውነት ነበር፣ ለእኛም ዛሬ እውነት ነው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98 እና 101 ውስጥ ጌታ ለቅዱሳን የነገራቸውን ስታነቡ፣ መልእክቱ ሊኖሯችሁ ለሚችሉት የተለያዩ ፈተናዎች ወይም ችግሮች እንዴት እንደሚሰራ አሰላስሉ። እናንተን ለመርዳት የቀረቡ ጥያቄዎች እና ግብዓቶች እነሆ።
ፈተናዎቹ የምን ውጤት ናቸው፦
-
የግል ምርጫዎች፦ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥11–12 101፥1–9 ውስጥ ምን ምክሮችን—እና ተስፋዎችን—ታገኛላችሁ? ከእነዚህ ጥቅሶች ስለሰማያዊ አባት እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ትማራላችሁ? እግዚአብሔር ምን እንድታደርጉ የሚፈልግ ይመስላችኋል?
-
የሌሎች ምርጫዎች፦ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥1–3፣ 22፤ 101፥10–16፣ 22 ውስጥ ምን ዓይነት መፅናናትን ታገኛላችሁ? ጌታ ለጥቃት፣ ለሚያበሽቁ ወይም ለጠበኝነት እንዴት ምላሽ እንድንሰጥ ይፈልጋል? (የህይወት እርዳታ፣ “ጥቃት፣ ” የወንጌል ላይብረሪ፤ Topics and Questions፣ “Abuse፣” የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።) እነዚህ ጥቅሶች እምነታችሁን በጌታ ላይ ማድረግ ስለምትችሉበት መንገድ ምን ያስተምራሉ?
-
የምድራዊ ህይወት አስቸጋሪ ሁኔታዎች፦ ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥1–3፤ 101፥22–31፣ 36 ውስጥ ምን ዓይነት ዕይታን ታገኛላችሁ? ከፈተናዎቻችሁ ምን እየተማራችሁ ነው? የእግዚአብሔርን እርዳታ ለመጋበዝ ምን እያደረጋችሁ ነው? እየረዳችሁ ያለውስ እንዴት ነው?
እግዚአብሔር “የተሰቃያችሁባቸው ነገሮች ሁሉ … ለጥቅማችሁ አብረው [እንዲሰሩ]” እንዴት እንደሚያደርግ የበለጠ ለማወቅ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥3)፣ የሽማግሌ አንቶኒ ዲ. ፐርኪንስን መልዕክት አምላክ ሆይ፣ የሚሠቃዩትን ቅዱሳንህን አስታውስ” (ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 103–5) ማጥናትን አስቡ። በመልዕክቱ ውስጥ አዳኙ ፈተናዎቻችሁን እንዴት እንድትመለከቱ እንደሚጋብዛችሁ እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁን ምንባብ ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ፈተናዎቻችሁ ለእናንተ ጥቅም አብረው የሠሩት ወይም የእግዚአብሔርን ዓላማዎች ያከናወኑት በምን መንገዶች ነው?
በተጨማሪም ሮሜ 8፥28፤ 2 ኔፊ 2፥2፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 90፥24፤ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “ወደ ፅዮን ኑ፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2008 (እ.አ.አ)፣ 37–40፤ “Trial of Adversity፣” “Feeling the Lord’s Love and Goodness in Trials፣” “The Refiner’s Fire” (ቪዲዮዎች)፣ ChurchofJesusChrist.org.ተመልከቱ።
ጌታ በእሱ መንገድ ሰላምን እንድፈልግ ይፈልጋል።
ፕሬዚዳንት ራስል ኤም.ኔልሰን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፦ “የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች አለም ሁሉ ሊከተለው የሚገባ ምሳሌ መተው ይኖርባቸዋል። በልባችሁ እና በህይወታችሁ ውስጥ በአሁኑ ወቅት እየተነሱ ያሉትን የግል ግጭቶች ለማስወገድ ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ እንድታደርጉ እማጸናችኋለሁ” (“ የመንፈሳዊ ፍጥነት ሃይል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 97)።
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥23–48 ውስጥ ያለው ሁሉም ነገር ከሌሎች ጋር ባላችሁ የግል ግንኙነቶች ላይ ተፈፃሚ ባይሆኑም፣ በህይወታችሁ ያሉ የግል ግጭቶችን ወደማስወገድ ሊመሯችሁ የሚችሉ ምን መርሆዎችን ታገኛላችሁ? እንደ “Truth Reflects upon Our Senses” (መዝሙር ቁጥር 273) ባሉ ስለ ሰላም ወይም ስለይቅር ባይነት በሚያወሱ መዝሙሮች ውስጥ ተጨማሪ እውነቶችን ልታገኙም ትችላላችሁ።
ጌታ እርሱን የሚያገለግሉትን ሠዎች ይንከባከባል።
በክፍል 99 እና 100 ውስጥ የሚገኙት ራዕዮች የተሰጡት አስፈላጊ የቤተክርስቲያን ኃላፊነቶች ለነበሯቸው ነገር ግን የቤተሰቦቻቸው ነገር ለሚያሳስባቸው ሰዎች ነው። በእነዚህ ራዕዮች ውስጥ ሊረዳቸው ይችል የነበረ ምን ታገኛላችሁ? በእነዚህ ራዕዮች ውስጥ ጌታ ለእናንተ ምን መልእክት አለው?
በተጨማሪም “John Murdock’s Missions to Missouri” በ“‘I Quit Other Business’: Early Missionaries” እና “A Mission to Canada፣” በRevelations in Context፣ 87–89፣ 202–7 ውስጥ ተመልከቱ።
የእግዚአብሔርን ምክር መከተል ጥበቃ እንዳገኝ ይረዳኛል።
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥43–62 ውስጥ ያለው ምሳሌ ቅዱሳኑ ከፅዮን እንዲባረሩ ጌታ ለምን እንደፈቀደ ያብራራል። እነዚህን ጥቅሶች በምታነቡበት ጊዜ፣በምሳሌው ውስጥ እንደሚገኙት አገልጋዮች የሆናችሁባቸውን የተወሰኑ መንገዶች ታያላችሁን? “በትክክል እና በተገቢ መንገድ ወደ [ደህንነታችሁ] ለመመራት እንደምፈል[ጉ]” ( ቁጥር 63–65 ተመልከቱ) ለእግዚአብሔር የምታሳዩት እንዴት ነው?
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ኢየሱስ ክርስቶስ ፈተናዎቼን ወደ በረከቶች መቀየር ይችላል።
-
ልጆቻችሁን፣ የእድሜ አቻዎቻቸው የሚያጋጥሟቸውን አንዳንድ ችግሮች በመጠየቅ ውይይት ልትጀምሩ ትችላላችሁ። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥1–3ን አብራችሁ ልታነቡ እና ኢየሱስ ክርስቶስ መከራዎችን እንዴት ወደበረከቶች እንደሚቀይራቸው ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ፈተናዎቻችሁን ወደ በረከቶች እንዴት እንደለወጠ የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ለልጆቻችሁ ልታካፍሉ ትችላላችሁ።
አዳኙ ይቅር እንድል ይረዳኛል።
ማስታወሻ፦ ልጆቻችሁን ስለይቅርታ አስፈላጊነት በምታስተምሩበት ጊዜ፣ አንድ ሰው ጉዳት ሲያደርስባቸው ሁል ጊዜ እምነት ለሚጣልበት አዋቂ መንገር እንዳለባቸው መረዳታቸውንም አረጋግጡ።
-
ምዕራፍ 34 እና 35 በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች (128–34) የሚገኙት ትምህርቶች በ1833 (እ.አ.አ) ቅዱሣኑ በሚዙሪ እንዴት እንደተያዙ እንድታስተምሩ ሊረዳችሁ ይችላል እናንተ እና ልጆቻችሁ እነዚህ ቅዱሣን እንዴት ተሰምቷቸው ሊሆን እንደሚችል ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ከዚያም ጌታ ምን እንዲያደርጉ ፈልጎ እንደነበር ለማወቅ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥39–40 አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። እናንተ እና ልጆቻችሁ አንድን ሰው ይቅር ማለት አስፈልጓችሁ ስለነበሩ ጊዜያት እና አዳኙ እንዴት እንደረዳችሁ ልትናገሩ ትችላላችሁ።
-
እንዲሁም ለልጆቻችሁ የደስታ ፊት እና የሀዘን ፊት ምሥሎችን ልታሳዩዋቸው ትችላላችሁ። አንድ ሰው ደግነት የጎደለው ስለሆነባቸው ሁኔታዎች ተናገሩ ከዚያም ምላሽ የሚሰጥባቸውን መንገዶች ጠቁሙ። ልጆቻችሁ እያንዳንዱ ምላሽ ደስ የሚያሰኛቸው ወይም የሚያሳዝናቸው ከሆነ ወደ ተጓዳኙ የፊት ምሥል በመጠቆም እንዲመርጡ እርዷቸው። ኢየሱስ ለእኛ ጥሩ ያልሆኑትን ሠዎች ሳይቀር ይቅር እንድንል የሚፈልገው ለምንድን ነው?
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥16፣ 23–32
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ሊሰጠኝ ይችላል።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥16ን ካነበባችሁ በኋላ፣ ልጆቻችሁ ፀጥ በምንልበት እና ስለ ኢየሱስ በምናስብበት—ለምሳሌ ስንጸልይ ወይም ቅዱስ ቁርባንን በምንወወስድበት ጊዜ—የሚመጡትን ሰላማዊ ስሜቶች እንዲለዩ እርዷቸው። እንደ “Reverently, Quietly]” ወይም “To Think about Jesus” (የልጆች የመዝሙር መፅሀፍ፣፣ 26፣ 71) ያሉ ስለ ጥልቅ አክብሮ የሚያወሱ መዝሙሮችን ልትዘምሩም ትችላላችሁ። የእርሱን ሠላም በቤታችን ውስጥ መገንባት የምንችለው እንዴት ነው?
-
ልጆቻችሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና ሲመጣ ህይወት ምን እንደምትመስል ለማወቅ ይፈልጉ ይሆናል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥23–32ን አብራችሁ አንብቡ፣ ከዚያም በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለሚያገኟቸው እርሱ በሚመጣበት ጊዜ ደስታን ስለሚሰጡን ነገሮች ተነጋገሩ። አስቸጋሪ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ ስለእነዚህ ነገሮች ማወቃችን የሚረዳን ለምንድን ነው?