ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መስከረም 15–21፦ “ከብዙ ሥቃይ በኋላ … በረከት ይመጣል”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–105።


“መስከረም 15–21፦ ‘ከብዙ ስቃይ በኋላ … በረከት ይመጣል፣’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–105 ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–105፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

የፅዮን ካምፕ

ሲ.ሲ.ኤ. ክሪስቲያንሰን [1831–1912 (እ.አ.አ)]፣ የፅዮን ካምፕ፣ በ1878 (እ.አ.አ) አካባቢ፣ tempera on muslin፣ 78 ×114 ኢንች፡፡ ብሪንግሀም ያንግ ዩኒቨርሲቲ የሥነጥበብ ሙዚየም፣ የ ሲ. ሲ. ኤ. ክሪስቸንሰን የልጅ ልጆች ስጦታ፣ 1970 (እ.አ.አ)

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15–21፦ “ከብዙ ስቃይ በኋላ … በረከት ይመጣል”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–105

በከርትላንድ የሚገኙት ቅዱሳን፣ በጃክሰን ካውንቲ፣ ሚዙሪ ውስጥ ያሉ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ከቤታቸው እየተባረሩ እንደሆኑ ሲሰሙ እጅግ አዝነው ነበር። እንግዲያውስ ጌታ “የፅዮን መዳን” “በኃይል ይመጣል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥ 15) ብሎ ሲናገር አበረታች የነበረ መሆን አለበት። ያንን ተስፋ በልባቸው ይዘው፣ ከ200 በላይ ወንዶች፣ እና ወደ 25 የሚጠጉ ሴቶች እና ልጆች፣ በኋላ ላይ የፅዮን ካምፕ ብለው በጠሩት በእስራኤል ካምፕ ለመሣተፍ ተመዘገቡ። ተልዕኮው ወደ ሚዙሪ በመሄድ ፅዮንን ማዳን ነበር።

ለካምፑ አባላት፣ ፅዮንን ማዳን ቅዱሳንን ወደ መሬታቸው መመለስ ማለት ነበር። ነገር ግን ልክ ጃክሰን ካውንቲ ከመድረሣቸው በፊት፣ ጌታ የፅዮን ካምፕን እንዲበትን ለጆሴፍ ስሚዝ ነገረው። አንዳንድ የካምፑ አባላት ግራ ተጋቡ እንዲሁም ተበሳጩ፤ የዘመቻው ጉዞ ያልተሳካና የጌታ ቃል ኪዳን ያልተፈፀመ መሠለ። ነገር ግን ሌሎች በተለየ መንገድ አዩት። ግዞተኞቹ ቅዱሳን መሬታቸውን እና ቤታቸውን ባያገኙም፣ ተሞክሮው ለፅዮን በተወሰነ ደረጃ “መዳን” አመጣ፣ ይህም “በኃይል የመጣ” ነበር። ታማኝ የፅዮን ካምፕ አባላት፣ ብዙዎች ከጊዜ በኋላ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ሆነዋል፣ ልምዱ በእግዚአብሔር ሀይል፣ በጆሴፍ ስሚዝ መለኮታዊ ጥሪ እና በፅዮን—ቦታ በሆነችው ፅዮን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ህዝብ በሆኑት ፅዮን—ያላቸውን እምነት እንዳጠነከረ መስክረዋል። ያልተሳካ የሚመስለውን የዚህን ሥራ ጠቀሜታ ከመጠራጠር ይልቅ፣ ሁሉንም ነገር ባልተረዳንበት ጊዜም እንኳን እውነተኛው ተግባር አዳኙን መከተል እንደነበር ተምረዋል። በመጨረሻም ፅዮን የምትድነው በዚህ መንገድ ነው።

Saints1፥194–206፤ “The Acceptable Offering of Zion’s Camp፣” Revelations in Context፣ 213–18 ውስጥ ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102፥12–23

የአባልነት ምክር ቤት ዓላማ ምንድን ነው?

ክፍል 102 የመጀመሪያው የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ምክር ቤት በተደራጀበት በከርትላንድ ኦሃዮ ውስጥ የተካሄደውን ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ይዟል። በቁጥር 12–23 ውስጥ ጌታ፣ ከፍተኛ ምክር ቤቶች ከባድ መተላለፍ ለፈፀሙ ሰዎች የአባልነት ምክር ቤቶችን ሲያካሂዱ የሚከተሏቸውን ሂደቶች ይገልጻል።

ፕሬዚዳንት ኤም. ራስል ባላርድ እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፦ “አንዳንድ ጊዜ አባላት የቤተክርስቲያን [የአባልነት] ምክር ቤት ለምን እንደሚካሄድ ይጠይቃሉ። ዓላማው ሦስት እጥፍ ነው፦ የተላለፈውን ነፍስ ለማዳን፣ ንጹሁን ለመጠበቅ፣ እንዲሁም የቤተክርስቲያኗን ንፅህና፣ ታማኝነት እና መልካም ስም ለመጠበቅ.ነው (”A Chance to Start Over: Church Disciplinary Councils and the Restoration of Blessings፣” ኤንዛይን፣ መስከረም 1990 [እ.አ.አ]፣ 15)።

በተጨማሪም Topics and Questions፣ “Membership Councils፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥1–12፣ 36105፥1–19

ፅዮን መገንባት የምትችለው በፅድቅ መርሆዎች ላይ ብቻ ነው።

ቅዱሳን በሚዙሪ የነበረውን የቃል ኪዳን ምድር ለምን አጡ? ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ—ቢያንስ አንደኛው፣ ጌታ “የህዝቤ መተላለፍ ነው” ብሏል። ያ ባይሆን ኖሮ ፅዮን “[ትድን] ነበር” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 105፥2)። እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች103፥1–2 ፤ 36105፥1፟–19ን በምታነቡበት ጊዜ፣ በሚዙሪ ውስጥ ፅዮንን ለማቋቋም እንቅፋት የሚሆኑ እና ሌሎች ሊረዱ ይችሉ የነበሩ አንዳንድ ነገሮችን አስተውላችሁ ይሆናል። ፅዮንን በልባችሁ፣ በቤታችሁ እና በማህበረሰባችሁ ውስጥ ለመመስረት ሊረዳችሁ የሚችል ምን ትማራላችሁ?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥12–13፣ 36105፥1–6፣ 9–19

የሴሚናሪ ምልክት
በረከቶች ከእምነት ፈተናዎች በኋላ ይመጣሉ።

በብዙ መንገዶች፣ በፅዮን ካምፕ ውስጥ መሳተፍ የእምነት ፈተና ነበር። ጉዞው ረጅም ነበር፣ አየሩም ሞቃት ነበር፣ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ የምግብ እና የውሃ እጥረት ነበረ። እናም ከዚህ ሁሉ ፅናት በኋላ፣ የፅዮን ካምፕ አሁንም ቅዱሳንን ወደ መሬታቸው መመለስ አልቻለም። በነበረው/ራት ተሞክሮ ምክንያት በጌታ ላይ ያለው/ላት እምነት ለተናወጠበት/ባት የጽዮን ካምፕ አባል ደብዳቤ የመጻፍ እድል እግኝታችሁ እንደነበረ አስቡ። ይህንን ግለሠብ ለማበረታታት ምን ትሉ ነበረ? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥5–7፣ 12–13፣ 36 105፥1–6፣ 9–19 ውስጥ ሊረዳ የሚችል ምን እውነቶችን ታገኛላችሁ?

ከዚያም ይበልጥ የዘመኑ የሆነ እንደ ጽዮን ካምፕ ያለ ፈተና ምሳሌን፣ ለምሳሌ፣ አንድ ሚስዮናዊ ጠንክሮ የሚሰራ/ምትሰራ ቢሆንም/ብትሆንም፣ እርሱ ወይም እርሷ ባደረጉት ጥረቶች አማካኝነት ማንም ቤተክርስቲያኗን እንዳልተቀላቀለ—ልታስቡ ትችላላችሁ። ባጠናችሁት መሠረት፣ ሚስዮናዊው/ሚስዮናዊዋ የእርሱ ወይም የእርሷ ተልዕኮ አሁንም ስኬታማ መሆኑን እንዲገነዘብ/እንድትገነዘብ እንዴት ትረዱታላችሁ/ትረዷታላችሁ?

ጌታ “ከብዙ ሥቃይ” በኋላ የባረካችሁ እንዴት ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥12)።

በተጨማሪም 1 ኔፊ 11፥16–17አልማ 7፥11–12ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥33–3684፥88101፥35–36፤ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “On the Lord’s Side: Lessons from Zion’s Camp፣” ኤንዛይን፣ ሐምሌ 2017 (እ.አ.አ)፣ 26–35፣ ወይም ሊያሆና፣ ሐምሌ 2017 (እ.አ.አ)፣ 14–23፤ Topics and Questions፣ “Endure to the End፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “How Firm a Foundation፣” መዝሙር፣ ቁጥር 85።

የራዕዮቹን ታሪካዊ አውድ በማጥናት ተዘጋጁ። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ያሉት ራዕዮች የመጡበትን ጊዜ እና ቦታ መረዳታችሁ የሚያስተምሯቸውን መርሆዎች እንድትገነዘቡ እና እንድትተገብሩ ሊረዳችሁ ይችላል። ኑ፣ ተከተሉኝ ለእነዚህ ብዙ ግብዓቶች አገናኞችን ያቀርባል። ለትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102–5Saints1፥194–206፤ “The Acceptable Offering of Zion’s Camp፣” በሚለው በRevelations in Context፣ 213–18 ፤ እና “የዳግም መመለስ ድምፆች፦ የፅዮን ካምፕ” ውስጥ ተመልከቱ።

ወንዝ በሚዙሪ ዩኤስኤ

የእስራኤል ካምፕ በትንሽ የዓሣ ማጥመጃ ወንዝ ዳርቻ ሠፈረ።

የፈተናዎች አላማ ምንድን ነው?

ሽማግሌ ኦርሰን ኤፍ. ዊትኒ የፈተናዎችን ዓላማ በተመለከተ የሠጡትን ምክርን አስቡ፦ “ምንም አይነት የምንሠቃይበት ህመም፣ የሚያጋጥመን ፈተና በከንቱ አይቀርም። እንደ ትዕግስት፣ እምነት፣ ጥንካሬ እና ትህትና የመሳሰሉ ባህሪያትን ለማዳበር ለትምህርታችን ያገለግላል። የሚደርስብን እና የምንታገሰው መከራ ሁሉ፣ በተለይም በትዕግስት ስንጸና፣ ባህሪያችንን ያንጻል፣ ልባችንን ያጸዳል፣ ነፍሳችንን ያሰፋልናል፣ እና የበለጠ ሩህሩህ እና በጎ አድራጊ እንድንሆን ያደርገናል፣ የበለጠ የእግዚአብሔር ልጆች ለመባል ብቁ እንሆናለን … እንዲሁም ወደዚህ የመጣነው በኀዘን እና በሥቃይ፣ በድካምና በመከራ አማካኝነት በሰማያት ያሉትን አባታችንና እናታችንን እንድንመስል የሚያደርገንን ትምህርት ለማግኘት ነው (ስፔንሰር ደብልዩ. ኪምባል፣ Faith Precedes the Miracle [1972(እ.አ.አ)]፣ 98)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 104፥11–18፣ 78–83

ጌታ “ለምድር በረከቶች በመጋቢነት [ተጠያቂ]” አድርጎኛል።

በሚዙሪ ከነበሩት ፈተናዎች በተጨማሪ፣ በ1834 (እ.አ.አ) ቤተክርስቲያኗ፣ ከባድ እዳዎችን እና ወጪዎችን ጨምሮ፣ የገንዘብ ችግሮች አጋጥመዋት ነበር። በክፍል 104 ውስጥ ጌታ በቤተክርስቲያኗ የገንዘብ ሁኔታ ላይ ምክር ሰጥቷል። የራሳችሁን የገንዘብ ውሳኔዎች ስታደርጉ በቁጥር 11፟፟–18 እና 78–83 ውስጥ ያሉትን መርሆዎች እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ትችላላችሁ?

በተጨማሪም “Treasure in Heaven: The John Tanner Story” and “The Labor of His Hands” (ቪዲዮዎች)፣ የወንጌል ላይብረሪ፣ ተመልከቱ።

2:3

Treasure in Heaven: The John Tanner Story

3:42

The Labor of His Hands

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥9

ኢየሱስን በመከተል “ለዓለም ብርሃን” መሆን እችላለሁ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥9ን በምታነብበት ጊዜ፣ ልጆቻችሁ የአምፖል፣ የሻማ ወይም የሌላ የብርሃን ምንጭ ሥዕሎችን እንዲይዙ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ኢየሱስን በምንከተልበት ጊዜ ለሌሎች እንደ ብርሃን መሆን የምንችለው እንዴት ነው? በተጨማሪም “Jesus Wants Me for a Sunbeam፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 60–61) ተመልከቱ።

የተለኮሰ ሻማ

ኢየሱስን በምከተልበት ጊዜ ለሌሎች እንደ ብርሃን መሆን እችላለሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 104፥13–18

ጌታ ያለኝን እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እንዳካፍል ይፈልጋል።

  • እግዚአብሔር የሰጣቸውን (እንደ ምግብ፣ ልብስ፣ ችሎታ፣ እምነት እና ቤት ያሉ) የበረከቶችን ዝርዝር እንዲያዘጋጁ ለልጆቻችሁ ጥቂት ደቂቃዎችን ልትሰጧቸው ትችላላችሁ። የቻሉትን ያህል እንዲዘረዝሩ አበረታቷቸው። ከዚያም፣ የሁሉም ነገሮች እውነተኛ ባለቤት ማን ነው? ለመሣሠሉ ጥያቄዎች መልሶችን እየፈለጋችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 104፥13–18ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። በእነዚህ ነገሮች ምን እንድናደርግ ይፈልጋል? እናንተ እና ልጆቻችሁ አንድ ሰው የሚያስፈልጋችሁን ነገር የሠጠበትን ተሞክሮ ልታካፍሉ ትችላላችሁ(በተጨማሪም “The Coat” [ቪዲዮ]፣ በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ)።

    2:7

    The Coat

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 104፥42

ጌታ የእርሱን ትዕዛዛት ስጠብቅ ይባርከኛል።

  • ክፍል 104 ውስጥ፣ ጌታ ትዕዛዛቱን በታማኝነት ለሚጠብቁ ሰዎች “የተትረፈረፉ በረከቶች” እንደሚሰጥ ብዙ ጊዜ ቃል ገብቷል። ልጆቻችሁ “መትረፈረፍ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለመርዳት አንድ ክብን ሳሉ ከዚያም ልጆቻችሁ የክቦቹን ቁጥር—ሁለት ከዚያም አራት ከዚያም ስምንት ከዚያም አስራ ስድስት ወዘተ እያደረጉ በማብዛት እንዲያግዟችሁ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ክቦችን በምትጨምሩበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ ልጆቻችሁ የሰማይ አባት ስለሰጣቸው አንድ በረከት እንዲያስቡ እርዷቸው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 105፥38–40

አስታራቂ መሆን እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ ስለፅዮን ካምፕ እንዲማሩ ለመርዳት፣ “Chapter 36: Zion’s Camp” (በየትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 135–39፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ) ልታካፍሉ ት ችላላችሁ። ከጽዮን ካምፕ ልንማር ስለምንችላቸው—ለምሳሌ፣ ጌታ ሰላማዊ እንድንሆን እንዲሁም ከመጨቃጨቅ እና ከመጣላት ይልቅ እንድንሰራ እንደሚፈልግ የሚያስተምሩ—ትምህርቶችን ለመናገር በየጊዜው ለአፍታ ቆም በሉ (በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን. “አስታራቂዎች ይፈለጋሉ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 98–101 ተመልከቱ)።

    3:30

    Chapter 36: Zion’s Camp: February–June 1834

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 105፥38–40ን ልታነቡ እና “ሰላም” የሚለውን ቃል በሚሰሙበት በእያንዳንዱ ጊዜ ልጆቹን እንዲቆሙ ልትጠይቋቸውም ትችላላችሁ። ቅዱሳኑ ደግነት ከጎደላቸው ሰዎች ጋር እርቅ እንዲፈጥሩ ጌታ ይፈልግ እንደነበረ አስረዱ። ልጆቻችሁ አስታራቂዎች ለመሆን ሊያደርጓቸው ስለሚችሏቸው ነገሮች እንዲያስቡ እርዷቸው እንዲሁም አንዳንድ ሁኔታዎችን አስመስለው እንዲተውኑ ጋብዟቸው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

የፅዮን ካምፕ ምሥል

Zion’s Camp (Zion’s Camp at Fishing River)፣ በጁዲት ኤ. መኸር

የልጆች የአክቲቪቲ ገፅ