ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መስከረም 22–28፦ “[የ]እግዚአብሔር ልጅ ሥርዓት”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106–108


“መስከረም 22–28፦ ‘[የ]እግዚአብሔር ልጅ ሥርዓት’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106–108፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106–108፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ የክህነት ሥልጣን እየሰጠ

መስከረም 22–28፦ “[የ]እግዚአብሔር ልጅ ሥርዓት”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106–108

በመጀመሪያ ሲታይ፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107 የጌታን ቤተክርስቲያን የክህነት ክፍሎች በአመራር መዋቅር ስለማደራጀት ብቻ የሚናገር ሊመስል ይችላል። ይህ ራዕይ በታተመ ጊዜ፣ የቤተክርስቲያኗ አባልነት፣ ከነበሩት ጥቂት መሪዎች አቅም በላይ እያደገ ነበር። ስለዚህም የቀዳሚ አመራርን፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድንን፣ የሰባዎችን፣ የኤጲስ ቆጶሳትን፣ እና የቡድኖች አመራሮችን ሚናዎች እና ሀላፊነቶች መዘርዘር በእርግጥ አስፈላጊ እና የሚረዳ ነበር። ነገር ግን፣ በክፍል 107 ውስጥ ያለው መለኮታዊ መመሪያ የቤተክርስቲያን አመራር እንዴት መደራጀት እንዳለበት ከመደንገግም እጅግ የላቀ ጠቀሜታ ያለው ነው። እዚህ፣ ጌታ ኃይሉ እና ሥልጣኑ ስለሆነው፣ “[የ]እግዚአብሔር ልጅ ሥርዓት ቅዱስ ክህነት” ያስተምረናል (ቁጥር 3)። የክህነት ዓላማ ለእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ “ሰማያት ለእነርሱ እንዲከፈቱላቸው” እና “ከእግዚአብሔር አብ እና [የ]አዲስ ኪዳን አማላጅ ከሆነው ከኢየሱስ ጋር መገናኘት እና በእነርሱም መገኘት መደሰት” እንዲችሉ “የቤተክርስቲያኗ[ን] መንፈሳዊ በረከቶች ሁሉ” መክፈት ነው።(ቁጥር 18–19)። አዳኙ፣ ስለክህነቱ በማስተማር ስለእራሱ እና እንዴት ወደ እርሱ እንደምንመጣ እያስተማረን ነው።

Restoring the Ancient Order፣ በ” Revelations in Context፣ 208–12 ውስጥ ተመልከቱ።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106፤ 108

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
ጌታ እንዳገለግል ሲጠራኝ ይደግፈኛል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106 እና 108 ውስጥ፣ ጌታ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እንዲያገለግሉ ተጠርተው ለነበሩ ሁለት አባላት ምክር እና የተስፋ ቃል ሰጥቷል። ምክሩን ስታጠኑ፣ ጌታን ለማገልገል ስላላችሁ ስለራሳችሁ ዕድሎች—ምናልባት የአገልግሎት ምደባን፣ የቤተክርስቲያን ጥሪን፣ በቤተሰባችሁ ውስጥ ሃላፊነት መውሰድን ወይም መልካም ለማድረግ የመንፈስ መነሳሳትን ልታስቡ ትችላላችሁ።

በእነዚህ ራዕዮች ውስጥ አዳኙ ለእናንተ ያለው መልዕክት ምን ይመስላችኋል? ለእናንተ በተለይ ትርጉም ያላቸው የሚመስሉት የትኞቹ ሃረጎች ናቸው? ግምት ውስጥ የምታስገቧቸው ጥቂቶቹ እነሆ፦

ሽማግሌ ካርል ቢ. ኩክ ከባድ የቤተክርስቲያኗ ስራ ምደባ ሲሠጣቸው፣ ከአንድ ቅድመ አያታቸው ተሞክሮ ጥንካሬን አግኝተዋል። ስለሱ፣ “Serve፣” (ሊያሆና፣ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 110–12) በተሠኘው መልዕክት ውስጥ አንብቡ። ለእናንተ የወደፊት ትውልዶች—ወይም ለወደፊቱ ለእናንተ—ጌታን ለማገልገል የምታገኟቸውን ዕድሎች እንድትቀበሉ ለማበረታታት ደብዳቤ መጻፍን አስቡ። ከሽማግሌ ኩክ መልዕክት፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 106 እና 108 እንዲሁም ከራሳችሁ ተሞክሮዎች የተማራችኋቸውን እውነቶች በደብዳቤያችሁ ውስጥ አካቱ።

በተጨማሪም ሄንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “ከእኔ ጋር ተራመድ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 82–85፤ Topics and Questions፣ “Serving in Church Callings፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “Warren Cowdery” እና “‘Wrought Upon’ to Seek a Revelation፣” በRevelations in Context፣ 219–23፣ 224–28 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥1–4፣ 18–20

ክህነቱ “እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሥርዓት” ነው።

ጌታ “ስለክህነት የሰጠው ራዕይ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፣ የክፍል መግቢያ) ስለመልከ ጼዴቅ ክህነት የመጀመሪያ ሥያሜ በማስተማር ይጀምራል (ቁጥር 1–4 ተመልከቱ)። ያንን ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? ይህ ሥም ስለክህነት በሚሰማችሁ ስሜት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?

በተለይም በቁጥር 18–20 ውስጥ ስለክህነት ስታነቡ፣ እነዚህን ሃሳቦች በአዕምሯችሁ ያዙ። “ሰማያት … እንዲከፈቱ” ማለት ምን ማለት ነው? “ከእግዚአብሔር አብ እና … ከኢየሱስ ጋር [መገናኘት] እና በእነርሱም መገኘት መደሰት” ማለት ምን ማለት ነው? የአዳኙ የክህነት ሃይል እና ሥልጣን ይህን ሁሉ እንድታገኙ የሚያደርገው እንዴት ነው?

በተጨማሪም አልማ 13፥2፣ 16ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–27 ተመልከቱ።

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አተኩሩ። “በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ እንደ መርሆዎች፣ ትዕዛዛት፣ ትንቢቶች እና የቅዱሳት መፃህፍት ታሪኮች ያሉ ማስተማር የሚቻሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉም የአንድ ዛፍ ቅርንጫፎች ናቸው፣ ሁሉም አንድ አላማ አላቸው፦ ይኸውም፣ ሁሉም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ እና በእርሱ ፍፁም እንዲሆኑ መርዳት ነው (ጄረም 1፥11ሞሮኒ 10፥32 ተመልከቱ)። ስለሆነም፣ ምንም ብታስተምሩ በእርግጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም እንዴት እንደ እርሱ መሆን እንደሚቻል እያስተማራችሁ መሆኑን አስታውሱ” (በአዳኙ መንገድ ማስተማር6)። ለምሳሌ፣በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107 ውስጥ ስላለው ስለክህነት ስታስተምሩ—እና ስትማሩ— ደጋግማችሁ፣ “ስለ አዳኙ ምን እየተማርን ነው?” እያላችሁ ጠይቁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥22

የጌታ አገልጋዮች “በቤተክርስቲያኗ እምነት፣ ታማኝነት፣ እና ጸሎት [ይደገፋሉ]”።

የጌታን አገልጋዮች በእምነት፣ በታማኝነት፣ እና በጸሎት መደገፍ ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል?

በተጨማሪም፣ “God Bless Our Prophet Dear፣” መዝሙር፣ ቁጥር 24 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥23–24፣ 33–35፣ 38፣ 91–92

ነቢያትና ሐዋርያት ስለኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራሉ።

ጆሴፍ ስሚዝ ክፍል 107ን ለአዲሱ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን በ1835 (እ.አ.አ) አካፍሏል (የክፍል መግቢያውን ተመልከቱ)። በቁጥር 23–24፣ 33–35፣ 38 ውስጥ ጌታ ስለጥሪያቸው ምን አስተማራቸው? በህይወት ባሉ ሐዋርያቱ ትምህርት እና አገልግሎት የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነታችሁ የተጠናከረው እንዴት ነው?

ቁጥር 91–92 ውስጥ ጌታ ስለ ታላቁ ሐዋርያ፣ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት ያስተምራል። “እንደ ሙሴ” የሆነው እንዴት ነው? (በቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “ሙሴ፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ)።

በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር “Chosen to Bear Testimony of My Name፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 128–31 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥27–31፣ 85–89

ጌታ ሥራውን የሚፈፀመው በምክር ቤቶች በኩል ነው።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥27–31 ውስጥ ጌታ ስለ ምክር ቤቶች ያስተማረውን አስተውሉ። ምክር ቤትን ውጤታማ የሚያደርገው ምንድን ነው? እነዚህን መርሆዎች በቤተክርስቲያን ጥሪያችሁ፣ በቤታችሁ ወይም በሌሎች ሀላፊነቶቻችሁ ውስጥ ልትተገብሯቸው የምትችሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም ኤም. ራስል ባላርድ፣ “Family Councils፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 63–65፤ አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ4.3–4.4፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ምስል
ቤተሰብ በአንድ ላይ እያቀዱ

ጌታ፣ ቤተሰቦች አንድ ላይ እንዲማከሩ ይጋብዛል።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ይመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥18–20

ኢየሱስ ክርስቶስ በክህነት ሃይሉ በኩል ይባርከኛል።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥18–19ን አብራችሁ ስታነቡ፣ “መንፈሳዊ በረከቶች ላይ ሁሉ” ለሚለው ሃረግ አፅንዖት ሥጡ። ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ ከክህነት የሚገኙትን በረከቶች ልትዘረዝሯቸው ትችላላችሁ። ይህንንም እንደ ጨዋታ ልታደርጉት ትችላላችሁ—ረጅሙን ዝርዝር ሊሰራ የሚችለው ማን እንደሆነ ተመልከቱ። ልጆቻችሁ እነዚህን በረከቶች የሚወክሉ ሥዕሎችን መሳል ወይም መፈለግም ይችላሉ (የዚህን ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ ተመልከቱ)። ከዚያም የክህነት ሥርዓቶች (እንደ ጥምቀት ወይም ቅዱስ ቁርባን) ያሉ የእግዚአብሔር በረከቶችን እንዴት እንድንቀበል እንደሚረዱን መነጋገር ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥21–26፣ 33–35፣ 91–92

የጌታ የተመረጡ አገልጋዮች የእርሱን ቤተክርስቲያን ይመራሉ።

  • እያንዳንዱ የሊያሆና የጉባኤ ዕትም የአጠቃላይ ባለስልጣናት ምሥሎች ገጽን ያካትታል። ስላላቸው ሀላፊነት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥21፣ 33–35 ውስጥ ስታነቡ፣ እነዚህን ምስሎች ከልጆቻችሁ ጋር ማየትን አስቡ። ጌታ እነዚህን ኃላፊነቶች ስለሰጣቸው እናንተ እና ልጆቻችሁ ለምን አመስጋኝ እንደሆናችሁ መነጋገር ትችላላችሁ።

  • ልጆቻችሁ ስለጌታ አገልጋዮች በ“General Church Leadership”ውስጥ በChurchofJesusChrist.org.ላይ የበለጠ መማር ይችላሉ። ምናልባት እያንዳንዱ ልጆቻችሁ ከእነዚህ መሪዎች ስለአንዱ ሊማሩ እና ስለእርሱ ወይም ስለእርሷ አንዳቸው ለሌላቸው ያስተምሩ ይሆናል። እነዚህ መሪዎች የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አገልጋዮች መሆናቸውን እንዴት እንደምታውቁ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥22ን አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ ተራ በተራ የቀዳሚ አመራርን ምሥል ልትይዙ እና እንደ ጌታ አገልጋዮች ልትደግፏቸው የምትችሉባቸውን መንገዶች ልታካፍሉ ትችላላችሁ።

ምስል
ቀዳሚ አመራር

ቀዳሚ አመራር

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 108፥3

ቃል ኪዳኖቼን በመኖር ረገድ ጠንቃቃ መሆን እችላለሁ።

  • ስለዚህ ጥቅስ ውይይት ለመጀመር፣ ልጆቻችሁ ሳያፈሱ ኩባያን እንደመሙላት ያለ ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረት የሚሻ አንድ ነገርን እንዲያደርጉ መጋበዝ ትችላላችሁ። ጠንቃቃ ባልሆንን ጊዜ ምን ይከሰታል? ከዚያም ጌታ ምን በጥንቃቄ እንድናደርግ እንደሚፈልግ ለማወቅ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 108፥3 አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። ለእግዚአብሔር የምገባቸው “ቃል ኪዳኖች” (ተስፋዎች ወይም ቃል ኪዳኖች) ምንድን ናቸው? እነሱን ለመጠበቅ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? Careful versus Casual” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 9–11) የተሠኘውን ልጆቻችሁ ቃል ኪዳናቸውን እንዲጠብቁ ሊያነሳሳቸው እንደሚችል የሚሰማችሁን የእህት ቤኪ ክራቨን መልዕክት ክፍሎችን ልታካፍሉ ትችላላችሁ። እንዲሁም ቃል ኪዳንን ስለመጠበቅ የሚናገር እንደ “I Will Be Valiant” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 162) ያለ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ።

ምስል
አንዲት ልጅ ውሃ እየቀዳች

ውሃ በጥንቃቄ መቅዳት ቃል ኪዳናችንን በጥንቃቄ ከመጠበቅ ጋር ሊመሳሰል ይችላል።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም