መሥከረም 29–ጥቅምት 5፦ ‘ይህም ቤትህ፣ የቅድስናህ ስፍራ [ነው]፣’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ)” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109–110፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
መስከረም 29–ጥቅምት 5፦ “ይህም ቤትህ፣ የቅድስናህ ስፍራ [ነው]”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109–110
የከርትላንድ ቤተመቅደስ በሮች እስከ መጋቢት 27 ቀን 1836 (እ.አ.አ) ከጠዋቱ 2፥00 ሰዓት ድረስ መከፈት አልነበረባቸውም። ነገር ግን በምረቃው አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ተስፋ ያደረጉ የነበሩ ቅዱሳን ከማለዳው 1፥00 ሰዓት ጀምሮ መሰለፍ ጀመሩ። የተረፉትን ሠዎች የማሳረፊያ ቦታ እና ሁሉንም ሠዎች ለማስተናገድ ደግሞ ሁለተኛ ዙር አስፈልጎ ነበር። እናም በቦታው ለመገኘት ጓጉተው የነበሩት በህይወት ያሉ ሠዎች ብቻ አልነበሩም። በምርቃቱ ወቅት እና ከዚያ በኋላ በቤተመቅደሱ ውስጥ እና በቤተመቅደሱ ጣራ ላይ ሳይቀር ብዙ ምስክሮች መላዕክትን እንዳዩ መስክረዋል። “የሰማይ ሠራዊቱ” ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጋር “ለመዘመር እና ለመጮህ” የመጡ ይመስልም ነበር (“The Spirit of God [የእግዚአብሔር መንፈስ]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 2)።
በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ታላቅ ደስታ የነበረው ለምንድን ነበር? ከክፍለ ዘመናት በኋላ የጌታ ቤት እንደገና በምድር ስለተሠራ ነበር። ጌታ፣ “ከላይ ሚመጣ ኃይል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥32) ለቅዱሳኑ ለመስጠት የገባውን ቃል እየፈፀመ ነበር። እና ይህም “የበረከት መጀመሪያ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥10) እንደሆነ ተናግሯል። የተፋጠነ የቤተመቅደስ ሥራ እና ሥርዓቶች በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ በህይወት ላሉ እና ለሙታን የሚገኙበት አሁን የምንኖርበት ዘመን፣ ጅማሬውን ያደረገው “ምድርን የሸፈናት መጋረጃ መቀደድ በጀመረበት” (“The Spirit of God [የእግዚአብሔር መንፈስ]”) በከርትላንድ ነበር።
በተጨማሪም ቅዱሳን፣፣ 1፥232-41፤ “A House for Our God [የአምላካችን ቤት]፣” Revelations in Context [ራዕይ በአገባብ] 169–72ን ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
ጌታ በቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖች አማካኝነት የተትረፈረፉ በረከቶችን ይሠጠኛል።
የከርትላንድ ቤተመቅደስ ዛሬ ከምናውቃቸው ቤተመቅደሶች የተለየ ነበር። ለምሳሌ፣ መሠዊያዎች እና የመጠመቂያ ገንዳ አልነበረም። ነገር ግን የከርትላንድ ቤተመቅደስ የምረቃ ጸሎት አካል የነበሩት፣ በከፍል 109 ውስጥ የተገለጹት በረከቶች ዛሬም በጌታ ቤት ውስጥ የሚገኙ ናቸው። እነዚህን የሚከተሉትን የተወሰኑ በረከቶች ለማግኘት የሚከተሉትን ጥቅሶች ከልሱ፣ ከዚያም ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማጠናከር እንዴት እንደሚረዷችሁ አሰላስሉ።
ቁጥር 5፣ 12–13 (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥6–8 ተመልከቱ፡)፦ በጌታ ቤት ውስጥ ጌታ እራሱን ለእኔ መግለጥ ይችላል እኔም የእርሱ ሀይል ሊሰማኝ ይችላል።
ሌሎች በረከቶች፦
ወደ ጌታ ቤት ገብታችሁ የምታውቁ ከሆነ፣ እነዚህ ቃልኪዳኖች በህይወታችሁ ውስጥ እንዴት እንደተፈፀሙ አስቡ።
“The Spirit of God [የእግዚአብሔር መንፈስ]” (መዝሙር፣ ቁጥር 2) የተሠኘው መዝሙር የተፃፈው ለከርትላንድ ቤተመቅደስ ምረቃ ነበር፣ እናም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በእያንዳንዱ የቤተመቅደስ ምረቃ ላይ እየተዘመረ ይገኛል። እሱን የጥናታችሁ ወይም የአምልኳችሁ አካል አድርጋችሁ መዘመርን ወይም ማዳመጥን አስቡ። በመዝሙሩ ውስጥ የተገለፁ ምን የቤተመቅደስ በረከቶችን ታገኛላችሁ?
ፀሎት ማለት ከሰማይ አባት ጋር መነጋገር ማለት ነው።
ክፍል 109 ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በራዕይ የተሰጠው የምረቃ ጸሎት ነው (የክፍል መግቢያውን ተመልከቱ)። ከዚህ ክፍል ስለ ፀሎት ምን ትማራላችሁ? ለምሳሌ፣ ነቢዩ ስለምን ምሥጋና እንዳቀረበ እና ምን ዓይነት በረከቶችን እንደጠየቀ ማስታወሻ ልትይዙ ትችላላችሁ። እርሱ በዚህ ፀሎት ውስጥ ሌላ ምን አለ? በምታጠኑበት ጊዜ፣ ከሰማይ አባት ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለመገመግም ትችሉ ይሆናል። ከዚህ ፀሎት ስለእርሱ እና ስለልጁ ምን ተማራችሁ?
በአቅራቢያችሁ የሚገኘውን ቤተመቅደስ ጨምሮ፣ የሌሎች ቤተመቅደሶችን የምረቃ ፀሎት ለማንበብ የምትወዱ ከሆነ፣ በ temples.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ የሚገኘውን የቤተመቅደስ ገፅ ጎብኙ።
ጌታ በቤቱ እራሱን ለእኔ ለመግለጥ ይችላል።
በክፍሉ መግቢያ ላይ ያለውን ጨምሮ፣ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥1-10 ውስጥ ያሉትን ስለጌታ የቀረቡ ገለፃዎች ስታነቡ፣ እነዚህ ጥቅሶች ስለእርሱ ምን እንደሚጠቁሙ አሰላስሉ።
ኢየሱስ ክርስቶስ—በቤቱ ውስጥ ራሱን የሚገልፀው —ወይንም ራሱን ለእናንተ የሚያሣውቀው እንዴት ነው? መስዋዕቶቻችሁን እንደተቀበለ እንድታውቁ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?
አዳኙ በክህነት ቁልፎች አማካኝነት ሥራውን ይመራል።
ልክ ሙሴ፣ ኤሊያስ እና ኤልያ የክህነት ቁልፎችን ዳግም ለመመለስ ከመገለጣቸው በፊት፣ ጌታ “ይህም በህዝቤ ራሶች ላይ የሚፈሰው የበረከት መጀመሪያም ነው” አለ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፡10)። ቁጥር 11–16ን ስታነቡ፣ አዳኙ በእዚህ ቁልፎች በሚመራ ሥራ በእናንተ ላይ እያፈሠሠ ስላለው በረከቶች አስቡ። ለምሳሌ፦
-
ቁጥር 11፦ ሙሴ እና እስራኤልን የመሰብሰብ ቁልፎች (ወይንም የሚስዮናዊ ሥራ)። ጌታ በቤተክርስቲያኗ የሚስዮናዊ ጥረቶች እናንተን እና ቤተሰባችሁን የባረከው እንዴት ነው?
-
ቁጥር 12፦ የአብርሐም ቃል ኪዳንን ጨምሮ፣ ኤልያስ እና የአብርሐም ወንጌል ቁልፎች። ጌታ፣ በቃል ኪዳኖቻችሁ ምክንያት እናንተን እና “[ከእናንተ] በኋላ የሚመጣውን ትውልድ” ሊባርክ የሚችለው እንዴት ነው? (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለዓአለማዊ ቃል ኪዳን፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ)፣ 4–11፤ የቅዱሣት መፃህፍት መመሪያ፣ “ኤሊያስ፣” ወንጌል ላይብረሪ።)
-
ቁጥር 13–16፦ ኤልያ እና የማተም ኃይል የሚገለጠው በቤተመቅደስ እና በቤተስብ ታሪክ ሥራ አማካኝነት ነው። የሰማይ አባት በቤተመቅደስ ሥርዓቶች ከቅድመ አያቶቻችሁ ጋር እንድትገናኙ የሚፈልገው ለምን ይመስላችኋል? (ጌሪት ደብልዩ.ጎንግ፣ “Happy and Forever [ደስታ እና ዘለአለም]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 83–86 ተመልከቱ።)
በእነዚህ ቁልፎች እና በእግዚአብሔር የደህንነት እና በዘለዓለም ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ውስጥ (በወንጌል መኖር፣ የተቸገሩትን መንከባከብ፣ ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ እና ቤተሰቦችን ለዘለዓለም ማጣመር) ባሉን ኃላፊነቶች መካከል ምን ግንኙነቶችን ታያላችሁ?
በእግዚአብሔር የደህንነት እና በዘለዓለም ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ምን ተሞክሮዎች ነበሯችሁ? እነዚህ ተሞክሮዎች ስለአዳኙ፣ ስለቤተክርስቲያኑ እና ስለ ሥራው ምን ያስተምሯችኋል?
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥12–13፤ 110፥1–7
ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ ስለቤታችሁ የምትወዱትን ነገር ለመናገር ትችላላችሁ። ከዚያም የከርትላንድ ቤተመቅደስን ምሥል ልትመለከቱ እና ቤተመቅደሱ እንዴት እንደተመረቀ እና እንዴት የጌታ ቤት እንደሆነ ለመናገር ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥12–13፤ 110፥1–7ን ልትጠቀሙ ትችላላችሁ (በተጨማሪም “Chapter 39: The Kirtland Temple Is Dedicated [ምዕራፍ 39፦ የከርትላንድ ቤተመቅደስ መመረቅ]፣” በDoctrine and Covenants Stories [በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 154፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ)። ስለጌታ ቤት የምትወዱትን ነገር አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።
-
ምናልባት እናንተ እና ልጆቻችሁ አንድ ጓደኛችሁ ቤታችሁን ለማግኘት እየሞከረ የሆነ ያህል ማሠብ ትችላላችሁ። ጓደኛችን የትኛው ቤት የእኛ እንደሆነ እንዲያውቅ የምንረዳው እንዴት ነው? ቤተመቅደስ የጌታ ቤት እንደሆነ ያወቅነው እንዴት ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥12–13ተመልከቱ)።
አዳኙ ህዝቡን በክህነት ቁልፎች አማካኝነት እየባረከ ነው።
-
ቤተመቅደሱን ስለጎበኙት የሰማይ አካላት ለልጆቹ ለመንገር የዚህን ሣምንት የአክቲቪቲ ገፅ ወይም “Chapter 40: Visions in the Kirtland Temple [ምዕራፍ 40፦ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ የነበሩ ራዕዮች]” (በDoctrine and Covenants Stories [የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 155–57 ውስጥ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን ከወንጌል ላይብረሪ) ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ያለውን ምሥል ልትጠቀሙም ትችላላችሁ።
-
በከርትላንድ ቤተመቅደስ ስለሆነው ነገር አስፈላጊነት ለማወቅ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ ቁልፎች ምን እንደሚሠሩ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ምናልባት ልጆቻችሁ ተራ በተራ ቁልፎችን ሊይዙ እና የተቆለፈ በር እንደሚከፈቱ ሊያስመስሉ ይችላሉ። ቁልፎች የሚለውን ቃል በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥11–16 ውስጥ እንዲፈልጉ እርዷቸው፣ ከዚያም እነዚህ ቁልፎች ስለሚከፍቷቸው በረከቶች ተናገሩ። የክህነት ቁልፎች የእርሱን ቤተክርስቲያን ለመምራት የሚያስችሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆኑ ልታብራሩ ትችላላችሁ። ጌታ የክህነት ቁልፎችን ስለሰጠን ያላችሁን አመስጋኝነት አካፍሉ።
አዳኙ የእኔን ልብ ወደ አባቶቼ እንድመልስ ይፈልጋል።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥15ን አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ ልባችሁን ወደ ቅድመ ዓያቶቻችሁ እንድትመልሱ የረዳችሁን አንድ ተሞክሮ ለልጆቻችሁ ንገሯቸው። እንደ “Family History—I Am Doing It [የበተሰብ ታሪክ—እያደረኩት ነው]” (የልጆች የመዝሙር መፅሐፍ፣ 94).የመሠለ መዝሙርን አብራችሁ ልትዘምሩም ትችላላችሁ።
-
የልጆቻችሁን “ልብ ወደ” ቅድመ አያቶቻቸው “[ለመመለስ]” ምን ሊረዳ ይችላል? በFamilySearch.org/discovery ውስጥ አንዳንድ የሚያዝናኑ ሀሳቦችን ልታገኙ ትችላላችሁ። የቤተመቅደስ ሥርዓቶች የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ዓያቶች ለመለየት አብራችሁ መሥራተ ትችላላችሁ። ኢየሱስ ይህንን ሥራ እንድንሠራ የሚፈልገው ለምንድን ነው?