ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የዳግም መመለስ ድምጾች፦ የሊበርቲ እስር ቤት


“የዳግም መመለስ ድምጾች፦ ሊበርቲ እስር ቤት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“የሊበርቲ እስር ቤት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
የዳግም መመለስ ድምጾች ምልክት

የዳግም መመለስ ድምጾች

ሊበርቲ እስር ቤት

በሊበርቲ፣ ሚዙሪ ውስጥ ታስሮ በነበረበት ጊዜ ጆሴፍ ስሚዝ በአገረ ገዢው ትእዛዝ ከክልሉ እየተባረሩ ስላሉት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሁኔታ የሚገልጽ ደብዳቤ ደረሰው። ከባለቤቱ ከኤማ የሚነካ ደብዳቤም መጣ። የእርሷ ቃላቶች፣ እና በምላሹ የጆሴፍ ደብዳቤዎች፣ በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ስቃያቸውን እና እምነታቸውን ይገልፃሉ።

ምስል
ሊበርቲ እስር ቤት

ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች በዚህ እስር ቤት ውስጥ ከ1838–39 (እ.አ.አ) በነበሩት የበጋ ወራትታስረው ነበር።

ከኤማ ስሚዝ ወደ ጆሴፍ ስሚዝ የተላከ ደብዳቤ፣ መጋቢት 7፣ 1839 (እ.አ.አ)

ውድ ባሌ

በጓደኛ ለመላክ አጋጣሚ ሳገኝ፣ ለመጻፍ ሙከራ አደርጋለሁ፣ ግን ሁሉንም ስሜቴን ለመፃፍ አልሞክርም፣ ምክንያቱም ባለህበት ሁኔታ፣ ግድግዳዎች፣ መወርወሪያዎች እና መቀርቀሪያዎች፣ ወንዞቹ፣ የሚሽከረከሩ ጅረቶች፣ ከፍ ያሉ ኮረብቶች፣ ተንሸራታቾች ሸለቆዎች እና የሚለያዩን ውዳሴዎች፣ እና በመጀመሪያ አንተን በእስር ቤት ውስጥ የጣለህን እና በዚያ የሚያስቆይህ በጭካኔ የተሞላው ኢፍትሀዊነት፣ ከብዙ ሌሎች ጉዳዮች ጋር፣ ስሜቴን ለመግለፅ እጅግ ከባድ ያደርገዋል።

በንጹህ ቅንነት እና መለኮታዊ ምህረት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ባይሆን ኖሮ፣ ያለፍኩትን የመከራ ትዕይንቶች መቼም ቢሆን በጽናት መቋቋም እንደማልችል እርግጠኛ ነኝ … ፤ ነገር ግን ለአንተ ስል እንዲህ እንድሰቃይ የደጉ ሰማይ ፍቃድ ከሆነ እኖራለሁ እና አሁንም ለመከራዬ የበለጠ መከራን ለመቀበል ፈቃደኛ ነኝ።

በጣም ታማሚ ከሆነው ፍሬድሪክ በስተቀር አሁን ሁላችንም ደህና ነን።

አሁን በእጄ ውስጥ ያለው ትንሹ አሌክሳንደር በህይወትህ ውስጥ ከተመለከትካቸው በጣም ደስ የሚሉ ትንሽ ሰዎች አንዱ ነው። እሱ በጣም ጠንካራ ስለሆነ በአንድ ወንበር እገዛ በክፍሉ ዙሪያ ዙሪያውን በሙሉ ይሮጣል። …

ከትንሽ ልጆቻችን በስተቀር ቤታችንን እና መኖሪያችንን ያገኘናቸውን ነገሮች ሁሉ ትተን፣ አንተንም ለብቻህ በዛ እስር ቤት ውስጥ እንደተዘጋብህ ትቼ ከምዙሪ ግዛት በምጣበት ጊዜ፣ የአእምሮዬን አስተሳሰብ እና የልቤን ስሜት ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም አያውቅም። ነገር ግን መታሰቢያው የሰው ልጅ ሊሸከም ከሚችለው በላይ ነው። …

… አሁንም ወደ እኛ የሚመጡ የተሻሉ ቀናት እንደሚኖሩ ተስፋ አለኝ። … [እኔ] ሁል ጊዜ በፍቅር የአንተ ነኝ።

ኤማ ስሚዝ

ከጆሴፍ ስሚዝ ወደ ኤማ ስሚዝ የተላከ ደብዳቤ፣ ሚያዚያ 4፣ 1839 (እ.አ.አ)

ውድ—እና ተወዳጅ—ሚስቴ።

ሐሙስ ምሽት፣ በዚህ የብቸኝነት እስር ቤት ውስጥ አሾልከን የጸሃይን መጥለቅ ስንመለከት፣ ያለሁበትን ሁኔታ ለአንቺ ለማሳወቅ ደብዳቤ ለመጻፍ ቁጭ አልኩኝ። እኔ በሌሊትና በቀን በጠባቂ በጥላቻ እየታየሁ፣ የሚሰቀጥጥ ድምጽ ያለው የብረት በር ባለው የተነጠለ፣ ጨለማ እና ቆሻሻ እስር ቤት ግድግዳዎች ውስጥ ከሆንኩኝ አሁን አምስት ወር ከስድስት ቀናት ያህል እንደሆነኝ አምናለሁ። ይህንን ደብዳቤ የምጽፈው እግዚአብሔር ብቻ በሚያውቃቸው ስሜቶች ነው። በእነዚህ ሁኔታዎች ስር ያለው የአዕምሮ እይታ እኛ የሚያጋጥመንን በጭራሽ ላላጋጠመው የሰው ልጅ ለመግለጽ፣ ወይንም ለመሳል ብዕርን ወይም ምላስን፣ ወይ መላዕክትን ይከላከላል። እኛ ለማዳን በያህዌኽ ክንድ ላይ እንመካለን፣ እና በማንም አንመካም፣ እናም እሱ ካላደረገው አይከናወንም፣ በማንኛውም ነገር ጥፋተኞች ባንሆንም፣ በዚህ ስቴት ውስጥ ለደማችን ታላቅ ጥማት እንዳአለ እርግጥኛ ሁኚ። … ውዴ ኤማ ሁል ጊዜም ስለአንቺ እና ስለ ልጆቹ አስባለሁ። … ትንሹ ፍሬደሪክን፣ ጆሴፍን፣ ጁሊያን፣ አሌክሳንደርን፣ ጆአናን እና ኦልድ ሜጆርን (የቤተሰብ ውሻውን) ማየት እፈልጋለሁ። ከዚህ አንቺን ለማየት በባዶ እግሬ፣ በተጋለጠ ጭንቅላቴ፣ እንዲሁም ግማሽ ዕራቁቴን በመሆን ለመጓዝ ፈቃደኛ ነኝ እንም ይህን እንደ ታላቅ ደስታ እንጂ እንደ ስቃይ አላስበውም። … የእኔን ጭቆና ሁሉ በፅናት እሸከማለሁ፣ ከእኔ ጋር ያሉትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ ማንኛችንም ብንሆን ገና አልተንቀሳቀስንም። [ልጆቻችን] እንዳይረሱኝ እንድታደርጊ እፈልጋለሁ። አባታቻው በፍጹም ፍቅር እንደሚወዳቸው፣ እናም ከወንበዴዎች በማምለጥ ወደ እነርሱ ለመምጣት የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው ብለሽ ንገሪያቸው። … አባታቸውም ጥሩ ልጆች መሆን አለባችሁ እና እናታቸውንም ማክበር አለባችሁ ብሏል በያቸው። …

“የአንቺው፣

ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ

ማስታወሻዎች

  1. ከኤማ ስሚዝ የተላከ ደብዳቤ፣ 7 መጋቢት 1839 (እ.አ.አ)፣” የደብዳቤ መጽሃፍ 2፣ 37፣ josephsmithpapers.org፤ የፊደል አጻጻፍ፣ ሥርዓተ-ነጥብ፣ እና የሰዋሰው ዘመናዊነት ተሻሽሏል።

  2. ለኤማ ስሚዝ የተላከ ደብዳቤ፣ 4 ሚያዚያ 1839 (እ.አ.አ)፣” 1–3፣ josephsmithpapers.org፤ የፊደል አጻጻፍ፣ ሥርዓተ-ነጥብ ፣ እና ሰዋሰው ተሻሽሏል።

  3. ጆሴፌ እና ጓደኞቹ ጥቅምት 31 ቀን 1838 (እ.አ.አ) ተያዙ፤ ከዚያም ቀን እና ሌሊት ከባድ ጥበቃ ይደረግባቸው ነበር። በሪችመንድ፣ ምዙሪ ከተደረገው የመጀመሪያ የፍርድ ሂደት በኋላ፣ ታህሳስ 1 ቀን ወደ ሊበርቲ እስር ቤት ተወሰዱ።

አትም