ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 20–26 (እ.አ.አ)፦ “እግዚአብሔር ሆይ፣ የት ነህ?”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121–123


“ጥቅምት 20-26 (እ.አ.አ)፦ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ የት ነህ?’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121–123፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121–123፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ጆሴፍ ስሚዝ በሊበርቲ እስር ቤት

ሊበርቲ እስር ቤት በዌልደን አንደርሰን

ጥቅምት 20–26 (እ.አ.አ)፦ “እግዚአብሔር ሆይ፣ የት ነህ?”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121–123

በሊበርቲ፣ ሚዙሪ ውስጥ የነበረው እስር ቤት የታችኛው ክፍል “ጉድጓዱ” በመባል ይታወቅ ነበር። ግድግዳዎቹ ወፍራም ነበሩ፣ የድንጋይ ንጣፉ ቀዝቅዛ እና ቆሻሻ ነበር፣ ምግቡ የተበላሸ ነበር፣ እና ብቸኛው ብርሃንም በጣሪያው አጠገብ ባሉ ሁለት ጠባብ በብረት የተዘጉ መስኮቶች የሚገባው ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች ጥቂቶች በ1838–39 (እ.አ.አ) ክረምት ላይ አራት ቀዝቃዛ ወራትን ያሳለፉት በዚህ ነበር። በዚህን ጊዜ ጆሴፍ ዘወትር ስለ ቅዱሳን ስቃይ ዜና ይሰማ ነበር። በፋር ዌስት የታየው ሰላምና ብሩህ ተስፋ የቆየው ለጥቂት ወራት ብቻ ነበር፣ አሁንም ቅዱሳኑ እንደገና ቤት አልባ ሆነውና ሌላ ቦታ ለመፈለግ እንዲሁም ከመጀመርያ ለመጀመር ወደ ምድረ በዳ ተሰድደው ነበር—በዚህ ጊዜ ነቢያቸው እስር ቤት ነበር።

ሆኖም፣ በዚያ አሳዛኝ እስር ቤት ውስጥ እንኳን፣ “ከሰማይ እውቀ[ት]” “[በመ]ፍሰሥ” ይመጣ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥33)። “እግዚአብሔር ሆይ፣ የት ነህ?” የሚለው የጆሴፍ ጥያቄ በግልፅ እና በሃይል ተመልሰውን ነበር፦“አትፍራ፣ እግዚአብሔር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ከአንተ ጋር ነውና” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች121፥1122፥9)።

ቅዱሳን1፥323-96፤ “Within the Walls of Liberty Jail [በሊበርቲ እስር ቤት ውስጥ]፣” Revelations in Context [ራዕያት በአገባብ]፣ 256-63 ተመልከቱ።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–10፣ 23–33፤ 122

በእግዚአብሔር እርዳታ መከራ “[ለእኔ] ጥቅም” ሊሆን ይችላል።

በእኛ ወይም በምንወዳቸው ሠዎች ላይ መከራ ሲደርስ፣ እግዚአብሔር ስላለንበት ሁኔታ ያውቃልን ብሎ መጠየቅ አይደንቅም። እናንተ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 121፥1–6ን ስታነቡ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የነበሩትን ዓይነት ጥያቄዎች ወይም ስሜቶች ስለነበሯችሁ ጊዜ አስቡ። በጌታ ምላሽ ውስጥ እነዚያ ጥያቄዎች ወይም ስሜቶች ሲኖሯችሁ ሊረዳችሁ የሚችል ምን ታገኛላችሁ? ለምሳሌ፣ በቁጥር 7–1026–33 ውስጥ ቃል የገባቸውን በረከቶች አስተውሉ። “በመልካም … [መፅናት]” ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? አዳኙ ይህንን እንድታደርጉ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?

እናንተ ክፍል 122ን ስታነቡ፣ ጌታ መከራችሁን እንዴት እንድትመለከቱ እንደሚፈልግ አስቡ። ከፈተናዎቻችሁ የተገኙትን ልምዶች እንዲሁም “[ለእናንተ] ጥቅም]” ሊሆኑ ስለሚችሉበት መንገድ ማሰብ ትችላላችሁ (ቁጥር 7)።

በተጨማሪም ክውንተን ኤል. ኩክ፣ “Personal Peace in Challenging Times [በአስቸጋሪ ጊዜዎች ያለ የግል ስላም]፣” ሊያሆናህዳር 2021 (እ.አ.አ) 89-92፤ “Where Can I Turn for Peace? [ለሰላም ወደየት መዞር እችላለሁ]፣” መዝሙር፣ ቁ. 129 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥34–46

የሴሚናሪ ምልክት
እውነተኛ ኃይል እና ተጽዕኖ የተመሠረቱት “በጽድቅ መሠረታዊ መርሆዎች” ላይ ነው።

ዓለማዊ ኃይል ቅዱሳንን ከሚዙሪ እንዲወጡ አስገደዳቸው እንዲሁም ጆሴፍ ስሚዝን ወደ እስር ቤት እንዲገባ አደረገው። ነገር ግን ጆሴፍ በዚያ ሳለ፣ ጌታ ለየት ስላለ ዓይነት ኃይል አስተማረው፦ ስለ እርሱ ኃይል፣ ስለ“ሰማይ ኃይላት”። በትምህርትና ቃል ኪዳኖች 121፥34-46 ውስጥ ስለዚያ ሃይል ስታነቡ፣ ያንን ሃይል እንዴት እንደምትቀበሉ እንዲሁም ሌሎችን ለመባረክ እንዴት እንደምትጠቀሙት እንድትማሩ ሊረዳችሁ ይችላል። ምናልባት የምትማሩትን የሠማይ ኃይላት እና ዓለማዊ ኃይል.የሚል ሥያሜ የተሠጣቸው ረድፎች ባሉት ሠንጠረዥ ውስጥ ልትመዘግቡ ትችላላችሁ። እነዚህ ሁለት ዓይነት ሃይላት የሚለያዩት እንዴት ነው? እነዚህ የጌታ ኃይል መግለጫዎች ስለእርሱ ምን ያስተምሯችኋል?

ምናልባት በቁጥር 41 ውስጥ ባለው ተፅዕኖ በሚለው ቃል ላይ ልታሰላስሉም ትችላላችሁ። በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለመሆን የምትፈልጉባቸው አንዳንድ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው—ምናልባት በቤተሰብ ግንኙነት፣ በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ ወይም በቤተክርስቲያን የሥራ ምደባ ውስጥ? ከቁጥር 41–46 እግዚአብሔር በልጆቹ ላይ ተፅዕኖ ስለሚያደርግበት መንገድ ምን ተማራላችሁ? እንደሚከተለው ዓይነት አረፍተ ነገርን በማሟላት የተማራችኋቸውን አሳጥራችሁ ልታስቀምጡ ትችላላችሁ፦ “በጎ ተፅዕኖ ለመፍጠር አደርጋለሁ።”

በተጨማሪም ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “Not as the World Giveth [አለም እንደሚሰጠው አይደለም]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 35–38፤ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “The Powers of Heaven [የሰማይ ሀይላት]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት (እ.አ.አ)፣ 48–51፤ “The Powers of Heaven [የሰማይ ሀይላት]” (ቪዲዮ)፣ የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

9:13

"The Powers of Heaven"

አንድን ሃረግ ምረጡና በጥልቀት አጥኑት። በቁጥር 45–46 ውስጥ ስለተገለጹት አስደናቂ በረከቶች የበለጠ ለማወቅ፣ ለእናንተ ጎልቶ የሚታያችሁን ሀረግ ልትመርጡ እና በጥልቀት ልታጠኑት ትችላላችሁ። ለምሳሌ ማሳመር የሚለው ቃል ለእናንተ ምን ማለት ነው፣ እንዲሁም፣ በጎነት ሃሳባችሁን ማሳመር የሚችለው እንዴት ነው? ወይም ምናልባት የጤዛ ምስል ልትፈልጉና ጤዛ በእፅዋት ላይ እንዴት እንደሚፈጠር ልትማሩ ትችላላችሁ። ይህ ጌታ ትምህርቱን ከሚያስተምርበት መንገድ ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ያገኛችሁትን በቤተክርስቲያን ለሚገኙ ጓደኞቻችሁ ጨምሮ ለቤተሰባችሁ ወይም ለጓደኞቻችሁ አካፍሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥8

ኢየሱስ ክርስቶስ እኔን ይረዳኝ ዘንድ ከሁሉም ነገሮች በታች ወርዷል።

ኢየሱስ ክርስቶስ “ከሁሉም [ነገሮች] በታች ወርዷል” ማለት ምን ማለት ይመስላችኋል? ይህንን ሐረግ እንድትረዱ የሚያግዟችሁ አንዳንድ ተጨማሪ ጥቅሶች እነሆ፦ ኢሣይያስ 53፥3–4ዕብራውያን 2፥17–181 ኔፊ 11፥16–33አልማ 7፥11–13። በተማራችሁት ላይ በመመሥረት፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥8ን በራሳችሁ አባባል መግለፅን አስቡ። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉ ነገሮች በታች ስለወረደ ምስጋናችሁን ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?

ይህ ከፕሬዚዳንት ዳሊን ኤች. ኦክስ የተገኘው ግንዛቤ በእናንተ ግንዛቤ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል? “ከሁሉም ነገሮች በታች በመውረድ፣ [ኢየሱስ ክርስቶስ] እኛን ከፍ ለማድረግ እና በመከራዎቻችን እንፀና ዘንድ የሚያስፈልገንን ጥንካሬ ሊሰጠን ትክክለኛ ቦታ ላይ ሆኗል እንላለን።” (“Strengthened by the Atonement of Jesus Christ [በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጥያት ክፍያ በኩል መጠናከር]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 64)።

ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴሴማኒ እየተሰቃየ

ዝርዝር ከ Not My Will But Thine [የእኔ ፈቃድ አይሁን፣ የአንተ እንጂ]፣ በዋልተር ሬን

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 123

“በሀይላችን ያሉትን ነገሮች ሁሉ በደስታ እናድርግ።”

ጆሴፍ ስሚዝ የቅዱሳንን ስደት ጨምሮ ወደ ስቃይ ያመሩ የሐሰት እምነቶችን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 123፥7–8 ውስጥ ጠቅሷል። መጋቢት 1839 (እ.አ.አ)፣ ቅዱሳን ያጋጠማቸውን አስከፊ ሁኔታ ለመቀየር ብዙ ሊያደርጉ ይችሉ የነበረ ነገር የሌለ ይመስል ነበር። ሆኖም፣ በሊበርቲ እስር ቤት እያለ በፃፋቸው ደብዳቤዎች ውስጥ፣ ጆሴፍ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ነግሯቸው ነበር፦ “ተጨባጭ ነገሮች እውቀት ሁሉ [ሰብስቡ]” እና “በእርግጠኝነት እግዚአብሔር የሚያደርገውን ማዳን ለማየት [ቁሙ]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 123፥1፣ 17)። በዛሬው ጊዜ በዓለም ውስጥ ያሉትን ችግሮች] ስታስቡ፣ ለማድረግ ስለምትችሏቸው “[በኃይላችሁ] [ስላ]ሉት” መንገዶች አስቡ (ቁጥር 12፣ 17)። እንዲሁም “እንደ ትንሽ ነገሮች” (ቁጥር 15) የሚመስሉትን ችላ አትበሏቸው። እነዚህን ነገሮች “በደስታ” ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ቁጥር 17)።

በዚህ ደብዳቤ ውስጥ ጆሴፍ የጠየቃቸው አብዛኞቹ ጥያቄዎች ለመንግሥት ቀርበው ነበር፤ እንዲሁም፣ Times and Seasons [ጊዜያት እና ወቅቶች] (“A History, of the Persecution, of the Church of Jesus Christ, of Latter Day Saints in Missouri, December 1839–October 1840 [በሚዙሪ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የስደት ታሪክ፣ ታህሳስ 1839–ጥቅምት 1840 (እ.አ.አ)],” [josephsmithpapers.org] ተመልከቱ)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–9122፥7–9

ከእግዚአብሔር ጋር መከራዎቼ “[ለእኔ] ጥቅም” ሊሆኑ ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁ፣ የሊበርቲ እስር ቤት ለጆሴፍ ስሚዝ እና ጓደኞቹ ምን እንደሚመስል እንደነበር እንዲያስቡ ለመርዳት፣“Chapter 46: Joseph Smith in Liberty Jail [ምዕራፍ 46፦ ጆሴፍ ስሚዝ በሊበርቲ እስር ቤት]” (በDoctrine and Covenants Stories [የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 172–74) ወይም “Voices of the Restoration: Liberty Jail [የዳግም መመለስ ድምጾች፦ ሊበርቲ እስር ቤት]” አብራችሁ ልታነቡ ወይም “Joseph Smith: Prophet of the Restoration [ጆሴፍ ስሚዝ፦ የዳግም መመለስ ነቢይ]” የሚለውን ቪዲዮ ክፍል (የወንጌል ላይብረሪ፣ ከ41፥30 ጀምሮ) ልትመለከቱ ትችላላችሁ። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥1–9ን አብራችሁ ስታነቡ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ሠላም እንዲሠማው አዳኙ እንዴት እንደረዳው መናገር ትችላላችሁ። በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ብሆንም እንኳን በጌታ ሠላም ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

    1:51

    Chapter 46: Joseph Smith in Liberty Jail: November 1838–April 1839

    62:4

    Joseph Smith: The Prophet of the Restoration

  • ፈተናዎቻችን “ለእኛ ጥቅም” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥7) ሊሆኑ እንደሚችሉ እንዲገነዘቡ ልጆቻችሁን ለመርዳት፣ ከባድ ነገር ስንሸከም ጡንቻዎቻችን እንዴት እንደሚዳብሩ ከእነሱ ጋር መነጋገር ትችላላችሁ። ከባድ ነገርን እንዲያነሱ ልትጠይቋቸውም ትችላላችሁ። ከዚያም በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ማለፍ እርዳታ ለማግኘት ፊታችንን ወደ ጌታ ስንመልስ፣ መንፈሳችን እንዲያድግ ስለሚረዳበት መንገድ መናገር ትችላላችሁ። ከህይወታችሁ አንዳንድ ምሳሌዎችን አጋሩ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥34–46

ፅድቅ “የሰማይ ኃይላትን” ያመጣል።

  • ምናልባት ለልጆቻችሁ “የሰማይ ሀይላትን” ለማስረዳት ንፅፅር መጠቀም ሊረዳ ይችላል። ለምሳሌ፣ የእግዚአብሔርን ኃይል ከኤሌክትሪክ ሀይል ጋር ማነፃፀር ትችላላችሁ። አንድ የኤሌክትሪክ መሣሪያ ሃይል ከመቀበል ምን ሊያግደው ይችላል? የእኛን መንፈሳዊ ሃይል ሊቀንሰው የሚችለው ምንድን ነው? ሊጨምረው የሚችለውስ? (በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥34–46 ውስጥ ቃላቶችን እና ሃረጎችን ፈልጉ፤ በተጨማሪም፣ አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ3.53.6፣ በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ ተመልከቱ።)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥7–9

ኢየሱስ ክርስቶስ እያለፍኩባቸው ያሉትን አስቸጋሪ ጊዜያት ያውቃል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥7–9ን ካነበባችሁ በኋላ፣ አዳኙ በከባድ መከራ ወቅት ከእናንተ ጋር እንዳለ የተሠማችሁን አንድ ተሞክሮ ልታካፍሉ ትችላላችሁ። እንዲሁም እንደ “Jesus Once Was a Little Child [ኢየሱስ ትንሽ ልጅ ነበረ]” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 55) የመሠለ መዝሙር አብራችሁ መዘመር እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደሚሰማን ስለሚያውቅ ሊረዳን እንደሚችል መሥክሩ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 123፥15–17

ትናንሽ ነገሮችም እንኳ በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ።

  • ልጆቻችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 123፥15–17ን እንዲገነዘቡ ለመርዳት፣ የአንድ ትልቅ መርከብን እና የአንድ ትንሽ መሪ ፎቶን ልታሳዩዋቸው ትችላላችሁ፣ ወይም ከእነርሱ ጋር በThe Principles of My Gospel [የወንጌሌ መርሆዎች]” ውስጥ ያለውን የሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር ማብራሪያ (ሊያሆና ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 125–26) አካፍሏቸው። ከዚያም ቤተሰባችንን እና ጓደኞቻችንን በደስታ ስለምናገለግልባቸው ትናንሽ መንገዶች መናገር ትችላላችሁ።

15:0

“The Principles of My Gospel”

በባህር ላይ ያለ መርከብ ምሥል

ልክ እንደ አንድ የትልቅ መርከብ ትንሽ መሪ፣ ትናንሽ ጥረቶቻችን ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሔት ዕትም ተመልከቱ።

ጆሴፍ ስሚዝ በሊበርቲ እስር ቤት ውስጥ ራዕይ እየመዘገበ

Joseph Smith in Liberty Jail [ጆሴፍ ስሚዝ ሊበርቲ እስር ቤት ውስጥ]፣ በግሬግ ኦልሰን

የአክቲቪቲ ገጽ ለልጆች