ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 6–12፦ “ሁሉንም ነገሮች ለእናንተ መልካምነት አዝዛለሁ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111–114


“ጥቅምት 6–12፦ ‘ሁሉንም ነገሮች ለእናንተ መልካምነት አዝዛለሁ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111–114፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111–114፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ በከርትላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ እያስተማረ

ጥቅምት 6–12፦ “ሁሉንም ነገሮች ለእናንተ መልካምነት አዝዛለሁ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111–114

በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ እምነት ልበ ሙሉ እና ጥብቅ የመሆን ስሜት እንዲሰማችሁ የሚያደርግ — ሆኖም ከዚያ በኋላ የህይወት ችግሮች እምነታችሁን በመፈተናቸው ከዚህ በፊት ወደተሰማችሁ ሰላም ለመመለስ ስትታታገሉ ራሳችሁን ያገኛችሁበት መንፈሳዊ ተሞክሮ አጋጥሟችህ ያውቃልን? በከርትላንድ ውስጥ ቅዱሳን ተመሳሳይ ነገር አጋጥሟቸው ነበር። ከከርትላንድ ቤተመቅደስ ምረቃ ጋር የተገናኘው የመንፈስ ፍስት ከሆነ ከአንድ አመት በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ችግሮች ተነሱ። የገንዘብ ቀውስ፣ በአስራ ሁለቱ ቡድን ውስጥ አለመግባባት፣ እና ሌሎች ፈተናዎች፣ ቀድሞ ከነበሯቸው ተሞክሮዎች በተቃራኒ አንዳንዶች በእምነታቸው እንዲንገዳገዱ አደረጓቸው።

ፈተናዎችን ለማስወገድ አንችልም፣ ስለዚህ በእምነታችን እና በምስክርነታችን ላይ ስጋት እንዳይፈጥሩ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ምናልባት የመልሱ ክፍል፣ በከርትላንድ የነበረው ፈተና እየተባባሰ በነበረበት ጊዜ ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112 ውስጥ በሰጠው ምክር ውስጥ ሊገኝ ይችላል። ጌታም “በፊቴ ልባችሁን አፅዱ” (ቁጥር 28)፣ “አታምጹ” (ቁጥር 15)፣ “ለስራውም ወገ[ባችሁን] አጥብ[ቁ]” (ቁጥር 7)፣ እና “ትሁት ሁ[ኑ]” (ቁጥር 10) አለ። ይህንን ምክር ስንከተል፣ ጌታ ከችግር ውስጥ ወደ ፈውስ እና ሰላም “[እጃችንን] ይዞ ይመራናል” (ቁጥር 10፣ 13 ተመልከቱ)።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111

ጌታ “ሁሉንም ነገሮች [ለእኔ] መልካምነት [ለማዘዝ]” ይችላል።

በ1836 (እ.አ.አ)፣ የጌታን ሥራ ለማከናወን ቤተክርስቲያኗ ከባድ ዕዳዎች ተጭነውባት ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች ስለእነዚህ ዕዳዎች ሲጨነቁ እና እነሱን ለመክፈል የሚቻልባቸውን መንገዶች ሲያስቡ ነበር (የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111ን የክፍል መግቢያ ተመልከቱ)።

ቁጥር 111ን ስታነቡ፣ ጌታ ለጆሴፍ የሠጠው ምክር ለእናንተ—እና ለሚያስጨንቋችሁ ነገሮች—እንዴት እንደሚሠራ አስቡ። ለምሳሌ፣ “ስህተተኞች ብትሆኑም” የእግዚአብሔር ፍቅር የተሰማችሁ መቼ ነው? (ቁጥር 1ን ተመልከቱ)። ጌታ ያልተጠበቁ “ሀብቶችን” እንድታገኙ የረዳችሁ እንዴት ነው (ቁጥር 10)? “ሁሉንም ነገሮች ለእናንተ መልካምነት” እንዲሆኑ ምን አድርጓል (ቁጥር 11)? “እናንት ልትቀበሉ በምትችሉት ፍጥነት፣” የሚለው ሐረግ ስለሰማይ አባት ምን ያስተምራችኋል?

በተጨማሪም ማቴዎስ 6፥19–21፣ 33፤ “More Treasures Than One [ከአንድ በላይ የሆኑ ሀብቶች]፣” Revelations in Context [ራዕያት በአገባብ]፣ 229–34 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥3–15፣ 22

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
በትህትና ፈቃዱን ስፈልግ ጌታ ይመራኛል።

የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን ፕሬዚዳንት የነበረው ቶማስቢ. ማርሽ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እርሱን ሳያማክር ሁለቱን የቡድኑን አባላት ወንጌልን ለመስበክ ወደ እንግሊዝ አገር እንዲሄዱ ጥሪ ስለሠጣቸው ተበሳጭቶ ነበር። ቶማስ የተጎዳ ስሜቱን እንዲረሳ የረዳውን ራዕይ ከተቀበለው ከነቢዩ ጋር ተገናኘ። ያ ራዕይ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112 ውስጥ ተመዝግቧል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112ን በምታጠኑበት ጊዜ ይህንን አውድ አስታውሱ። የቶማስን የተጎዳ ስሜት ያከመለት ሊሆን የሚችል ምን ታገኛላችሁ? በቁጥር 3–15 እና 22 ውስጥ ትህትና ማለት ምን ማለት ነው? ለሚለው እና ለመሣሠሉ ጥያቄዎች መልሶችን ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ጌታ “እ[ጃችሁ]ን ይዞ ይመራ[ችኋል]” ማለት ምን ማለት ነው? ትህትና የጌታን ምሪት እንድትቀበሉ የሚረዳችሁ ለምን ይመስላችኋል? ተጨማሪ መልሶችን በ“Pattern of Humility [የትህትና ንድፍ]” በሽማግሌ ጆሴፍ ደብልዩ. ሲታቲ መልዕክት “Patterns of Discipleship [የደቀመዝሙርነት ንድፎች]” (ሊያሆና፣ ህዳር 2022(እ.አ.አ)፣ 87–88).ውስጥ ልታገኙ ትችላላችሁ።

ትሁት እንደሆነ የምታውቁትን አንድ ሠው አስቡ። ይህ ሰው ትህትናውን ለማሳየት የሚያደርገው ምንድን ነው? ትሑት ስለመሆን ከአዳኙ ምን ትማራላችሁ? ምናልባት በህይወቱ ትህትናውን ያሳየበት ጊዜ የሚገልፁ ሥዕሎችን ልትፈልጉ ትችላላችሁ።

ትሑት ስትሆኑ ጌታ እየተመራችሁ እንደሆነ የተሰማችሁ መቼ ነው?

በተጨማሪም ዩሊሰስ ሶሬስ፣ “Be Meek and Lowly of Heart [የዋህ እና በልብ ትሁት ሁኑ]፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2013 (እ.አ.አ)፣ 9–11፤ “The Faith and Fall of Thomas Marsh [የቶማስ ማርሽ እምነት እና ውድቀት]፣” በ Revelations in Context [ራዕያት በአገባብ]፣ 54–60፤ Topics and Questions [ርዕሶች እና ጥያቄዎች]፣ “Humility [ትህትና]፣” ወንጌል ላይብረሪ “Be Thou Humble [ትሁት ሁኑ]፣” መዝሙር፣ ቁ. 130 ተመልከቱ።

ተማሪዎችን አሳትፉ። የምታስተምሯቸው ሰዎች በቅዱሣት መፃህፍት ውስጥ ያሉትን እውነቶች ሲማሩ በንቃት እንዲሣተፉ እንዴት ልትረዷቸው እንደምትችሉ አስቡ። ለምሳሌ፣ ጌታ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥10 ውስጥ የተናገረውን እንዲገነዘቡ ለመርዳት፣ የአንድን ሰው ዐይኑን/ኗን ልትጨፍኑና በጥንቃቄ እጁን/ጇን በመያዝ በወንበሮች ወይም በሌሎች ነገሮች አነስተኛ መሰናክሎች መካከል ልትመሩት/ሯት ትችላላችሁ። ከዚህ ገለፃ ስለትህትና ምን ልንማር እንችላለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥12–26፣ 28፣ 33–34

በእውነት የተለወጡ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማወቅ ይመጣሉ።

በ1837 (እ.አ.አ) የአንዳንድ ሐዋርያት ነቢዩን መደገፍ የማቆም እውነታ የቤተክርስቲያን ጥሪያችን ምንም ይሁን ምን ወይም ስለ ወንጌሉ ምንም ያህል ብናውቅ፣ በግለሰብ ደረጃ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መለወጣችንን ማጠናከራችንን ማረጋገጥ እንዳለብን ጥሩ አስታዋሽ ነው። ምናልባት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥12–26፣ 28፣ 33–34.ን ልታነቡ እና የእምነት ፈተናን እንድታሸንፉ ወይም ሙሉ ለሙሉ ወደ ጌታ እንድትለወጡ የሚረዷችሁን እውነቶች ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ሌሎች ሰዎች ወደ ክርስቶስ መለወጣቸውን ያጠናክሩ ዘንድ ያገኛችኋቸውን ለማካፈል መነሳሳት ሊሰማችሁ ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 113

ጆሴፍ ስሚዝ “የክርስቶስ እጆች አገልጋይ” ነበር።

ነቢዩ ኢሳይያስ ከእሴይ ዘር መካከል አንዱን “በትር” እና “ሥር” ሲል ጠርቶታል (ኢሳይያስ 11፥1፣ 10)። በክፍል 113 ውስጥ፣ የክርስቶስ አገልጋይ የሆነው ይህ ዘር፣ በመጨረሻው ቀናት የጌታን ህዝቦች ለመሰብሰብ በጣም አስፈላጊ እንደሚሆን ጌታ ገልጿል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 113፥4፣ 6ን ተመልከቱ)። ይህም ትንቢት ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝን በትክክል ይገልፃል። ይህ እና ሌሎች በክፍል 113 ውስጥ የሚገኙ እውነቶች በከርትላንድ ውስጥ ሁከት በገጠማቸው ጊዜ ቅዱሳኑን ያበረታታቸው እንዴት ነበር? በዚህ ራዕይ ውስጥ በጥንካሬ ለመዝለቅ እና ዛሬ በጌታ ሥራ ውስጥ በመሳተፍ ለመቀጠል የሚያነሳሳችሁ ምን ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “እሴይ፣” ወንጌል ላይብረሪ፤ 2 ኔፊ 21፥10–12ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥40 ተመልከቱ።

ምስል
የኢሳይያስ 11፥1 ሥዕላዊ መግለጫ

ኢሳይያስ “ከእሴይ ግንድ” “በትር” እና “ሥር” እንደሚወጣ ፅፏል (ኢሳይያስ 11፥1)።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 01

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111፥2፣ 10–11።

የእግዚአብሔር ነገሮች ለእኔ ውድ ሀብት ሊሆኑ ይችላሉ።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ ውድ ሀብትየሚለውን ቃል ስትሰሙ ወደ አዕምሯችሁ የሚመጣውን ነገር ልትሥሉ ትችላላችሁ። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 111፥2፣ 10–11ን አብራችሁ ልታነቡ እና ምድራዊ ውድ ሃብቶችን ጌታ ውድ ሃብቶች አድርጎ ከሚያያቸው ነገሮች ጋር ልታነፃፅሩ ትችላላችሁ። (የዚህን ሣምንትየአክቲቪቲ ገፅተመልከቱ)። የእግዚአብሔርን ነገሮች ይበልጥ ውድ ሃብቶች ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥10

ጌታ እጆቼን ይዞ ይመራኛል እንዲሁም ፀሎቴን ይመልሣል።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥10ን አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ “Be Thou Humble [ትሁት ሁኑ]” (መዝሙር፣ ቁ. 130) አብራችሁ ልትዘምሩ ትችላላችሁ። “እጅ በመያዝ” አንዱ ሌላውን መምራትን የሚያካትትን ጨዋታ (ለምሣሌ፣ በመሠናክል መካከል እንደማለፍ ያለ) መጫወትም ትችላላችሁ። ጌታ በአካል ከእኛ ጋር ባይሆንም፣ “እ[ጃችንን] ይዞ” የሚመራን እንዴት ነው? ጌታ እንዲረዳን የምንፈልገው ምንድን ነው? ጌታ እየረዳን እንዳለ የተሰማን መቼ ነው?

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥10 ቃላትን ልትፅፏቸው እና ፊታችንን በትህትና ወደ እርሱ በምንመልስበት ጊዜ ጌታ በሚሠጠን በረከቶች ላይ ልታሠምሩባቸው ትችላላችሁ። ልጆቻችሁ የጌታን እርዳታ በትህትና ስለጠየቁበት እና ለጸሎታቸው መልስ ስላገኙበት ወይም አንድ ጥሩ ነገር ወደ ማድረግ ስለተመሩበት ጊዜ እንዲያካፍሉ አበረታቷቸው(ሞሮኒ 7፥13፣16 ተመልከቱ)።

ምስል
ኢየሱስ አንድን ልጅ ሲፈውስ

ዝርዝር ከArise and Walk [ተነሳና ሂድ] በሳይመን ዲዊ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥11

ኢየሱስ ሁሉንም እንድወድ ይፈልጋል።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ Chapter 41: Trouble in Kirtland [ምዕራፍ 41፦ በከርትላንድ ቤተመቅደስ የነበረ ችግር]ን (በ Doctrine and Covenants Stories [የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 158–60) ውስጥ ተራ በተራ ማንበብ ትችላላችሁ። በታሪኩ ውስጥ በከርትላንድ የነበሩትን ችግሮች ያባባሳቸው ማን ነው? እንዲሻሻሉ ሲጥር የነበረውስ ማን ነበር? ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥11ን ልታነቡ እና አዳኙ ለምን ሁሉንም እንድንወድ እንደሚፈልግ ልትናገሩ ትችላላችሁ። ለእርሱ ደግነት ላልነበራቸው ሰዎች ፍቅር ያሳየው መቼ ነበር? (ለምሳሌ፣ ሉቃስ 23፣10ን ተመልከቱ)። እንዲሁም ሌሎችን ስለመውደድ የሚያወሳ እንደ “I’ll Walk with You [ከአንተ ጋር እራአመዳለሁ]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 140–41) ያለ መዝሙር መዘመርም ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥11–14፣ 24–26።

በእውነት የተለወጡ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማወቅ ይመጣሉ።

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥24–26ን ካነበባችሁ በኋላ፣ እናንተ እና ልጆቻችሁ የአንድን ሠው ሥም በማወቅ እና እራሱን በማወቅ መካከል ስላለው ልዩነት ልትነጋገሩ ትችላላችሁ። ከቁጥር 11–14 ውስጥ፣ ጌታን ማወቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንድናውቅ የሚረዳን የትኛው ትምህርት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም