ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 13–19 (እ.አ.አ)፦ “መስዋዕቱ ለእኔ ከፍሬው በላይ ቅዱስ ነው”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115–120


ጥቅምት 13–19፦ ‘መስዋዕቱ ለእኔ ከፍሬው በላይ ቅዱስ ነው’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115–120፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115-120፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ምስል
ፋር ዌስት፣ ሚዙሪ ሥዕል

ፋር ዌስት፣ ሚዙሪ በአል ራውንድስ

ጥቅምት 13–19 (እ.አ.አ)፦ “መስዋዕቱ ለእኔ ከፍሬው በላይ ቅዱስ ነው”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115–120

ቅዱሳን አዲሱ የመሰብሰቢያ ቦታቸው የሆነውን ሚዙሪ፣ ፋር ዌስትን፣ ተስፋ ለማድረግ ምክንያት ነበራቸው። ከተማዋ በፍጥነት እያደገች ነበር፣ ምድሪቱ ለጋስ ትመስል ነበር፣ እንዲሁም በአቅራቢያው የሚገኝ አዳም-ኦንዳይ-አማን የሚባል ላለፈውም ለወደፊቱም ታላቅ መንፈሳዊ ጠቀሜታ ያለው ቦታ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥53–56116 ተመልከቱ)። አሁንም፣ ቅዱሳኑ ስላጡት ነገር አለማሰብ አስቸጋሪ ሳይሆን አልቀረም። ቅዱሳን የፅዮን ማዕከል ከሆነው ከኢንዲፔንደንስ ከመባረራቸው በተጨማሪ፣ የሚወዱትን ቤተመቅደሳቸውን ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ብቻ በመተው ከከርትላንድም ለመሸሽ ተገድደው ነበር። እናም በዚህ ጊዜ ችግር የሚፈጥሩት ከቤተክርስቲያኗ ውጭ የነበሩ ጠላቶች ብቻ አልነበሩም—አራት የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን አባላትን ጨምሮ ብዙ ታዋቂ አባላት የጆሴፍ ስሚዝ ተቃዋሚ ሆነው ነበር።

ታማኝ አባላቱ ባጡት ነገር ላይ ከማተኮር ይልቅ አሁን ደግሞ በፋር ዌስት ጽዮንን መገንባታቸውን ቀጥለዋል። ለአዲስ ቤተመቅደስ ዕቅዶችን አወጡ። አራት አዳዲስ ሐዋርያት ተጠሩ። የእግዚአብሔርን ሥራ መሥራት ማለት በሂደቱ በጭራሽ መውደቅ የለም ማለት ሳይሆን “እንደገና መነሳት” ማለት እንደሆነ ተማሩ። እናም፣ ምንም እንኳን መስዋዕትነቶች መክፈል ቢኖርባችሁም፣ እነዚያ መስዋዕትነቶች ለእግዚአብሔር ቅዱስ ናቸው፣ እንዲያውም “[ከፍሬአቸው] በላይ ቅዱስ [ናቸው]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 117፥13)።

ቅዱሳን1፥296–99ን ተመልከቱ።

ምስል
የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥3–6

የቤተክርስቲያኗ ስም ለጌታ አስፈላጊ ነበር።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን የቤተክርስቲያኗ ስም “እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው” ብለዋል (“የቤተክርስቲያኑ ትክክለኛ ስም፣” ሊያሆና ፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ) 87)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥4–6ን በምታነቡበት ጊዜ ይህ ለምን እውነት እንደሆነ አስቡ። የቤተክርስቲያኗ ስም ከስራዋ እና ተልዕኮዋ ጋር ምን ግንኙነት አለው?

በተጨማሪም 3 ኔፊ 27፥1–11 ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥5–6

ፅዮን እና ካስማዋ “ከአውሎ ነፋስ መሸሸጊያ” ይሆናሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥5–6 ውስጥ ያሉትን ጠንካራ ሥዕላዊ ገለፃ ስታጠኑ፣ እንደ እርሱ ቤተክርስቲያን አባል ጌታ እንድታሟሉ የሚፈልገውን ሀላፊነት አስቡ። ለምሳሌ፣ “[ልትነሱ] እና [ልታበሩ]” ወይም “ለህዝቦች መመሪያ ትሆኑ ዘንድ” (ቁጥር 5) ምን ማድረግ ትችላላችሁ? በዙሪያችሁ ምን ዓይነት መንፈሣዊ አውሎ ነፋስ ታያላችሁ? የመልካሙን እረኛ ድምጽ እንዴት መለየት ትችላላችሁ? (ቁጥር 6)።

በተጨማሪም “Brightly Beams Our Father’s Mercy [የሰማይ አባታችን ምህረት እንደ ብሩህ ብርሀን ያበራል]፣” መዝሙር፣ ቁጥር 335 ተመልከቱ።

ምስል
አናቱ ላይ ብርሃን ያለው ማማ

የአዳኙ ቤተክርስቲያን አውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ ብርሃን እና መሸሸጊያ ሊሆን ይችላል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 117

የእኔ መስዋዕትነቶች በጌታ ዘንድ የተቀደሱ ናቸው።

በከርትላንድ የተደላደለ ህይወት እየኖራችሁ የነበራችሁ እና ከዚያ እንድትወጡ የተጠየቃችሁ ኑዌል ኬ ዊትኒን ወይም ሚስቱን ኤልዛቤትን እንደሆናችሁ አስቡ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 117፥1–11 ውስጥ ይህንን መስዋዕትነት እንድትከፍሉ ሊረዳችሁ ይችል የነበረ ምን ታገኛላችሁ? ለእግዚአብሔር ምን መስዋዕትነቶችን ትከፍላላችሁ? እነዚህ ጥቅሶች ስለእግዚአብሔር ምንነት እና ምን እንደሚሰራ ያስተምሯችኋል?

ኦሊቨር ግሬንጀር እንዲከፍል የተጠየቀው መስዋዕትነት የዊትኒ ቤተሰብ ከተጠየቁት የተለየ ነበር፦ በከርትላንድ ውስጥ እንዲቆይ እና የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ እንዲያስተካክል ጌታ የስራ ምደባ ሰጠው። ቤተክርስቲያኗን በታማኝነት ቢወክላትም፣ በመጨረሻም ብዙ ውጤታማ አልነበረም። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 117፥12–15 ውስጥ ያሉት የጌታ ቃላት ጌታ ለጠየቃችሁ ነገሮች እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ አስቡ።

በተጨማሪም “Far West and Adam-ondi-Ahman [ፋር ዌስት እና አዳም-ኦንዳይ-አማን]፣” በRevelations in Context [ራዕያት በአገባብ]፣ 239-40 ውስጥ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 119–20

ምስል
የሴሚናሪ ምልክት
አሥራቴ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት ይረዳል።

ክፍል 119 እና 120 ውስጥ ያሉት መመሪያዎች አሥራት ምን እንደሆነ ያብራራሉ፦ በየዓመቱ የትርፋችንን (ወይም የገቢያችንን) “አንድ አሥረኛ” እንለግሳለን (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 119፥4 ተመልከቱ)። ነገር ግን እነዚህ ራዕዮች ፍቺ ከመስጠት ያለፈ ጠቀሜታ አላቸው። አሥራትን መክፈል “የፅዮንን ምድር [እንደሚቀድስ]” ለቅዱሳኑ ነገራቸው። ይህ ህግ ከሌለ፣ “ለእናንተ ፅዮን … አይሆንላችሁም” (ቁጥር 6) ብሏል። አሥራትን በዚህ መንገድ አስባችሁት ታውቃላችሁ? አሥራትን መክፈል የበለጠ እንድትቀደሱ እና ለጽዮን ዝግጁ እንድትሆኑ የሚያደርጋችሁ እንዴት ነው?

የጌታ አገልጋዮች የአሥራት ገንዘብ ስለሚጠቀሙበት መንገድ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ተማራችሁ? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 120 ውስጥ ያለው “በምሰጣቸውም በራሴ ድምጽ” የሚለው ሐረግ ለእናንተ ምን ልዩ ትርጉም አለው?

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ አሥራት እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እና ይህን ህግ በመታዘዝ ስለሚገኘው በረከት በ“The Windows of Heaven [የሰማይ መስኮቶች]” (ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 19–20) ውስጥ ጠቃሚ መግለጫ ሰጥተዋል። የእርሳቸውን መልእክት ስታጠኑ የሚከተሉት ጥያቄዎች ሊረዷችሁ ይችሉ ይሆናል፦

  • አሥራት ለቤተክርስቲያኗ ከተከፈለ በኋላ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሚወስነው ማን ነው?

  • አሥራት ጥቅም ላይ የሚውለው በምን ላይ ነው?

  • አስራትን በመክፈል ምን ዓይነት በረከቶች ይመጣሉ? ለምሳሌ፣ አሥራትን መክፈል ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላችሁን ግንኙነት የሚያጠናክረው በምን ዓይነት መንገዶች ነው?

  • ከሽማግሌ ቤድናር ግብዣ ምን ልትማሩ ትችላላችሁ?

  • ሌሎች በጌታ የአሥራት ህግ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያሳድጉ መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው?

በተጨማሪም፣ ሚልክያስ 3፥8–12፤ “The Tithing of My People [የህዝቤ አስራት]፣” በRevelations in Context [ራዕይ በአገባብ]፣ 250–55 ተመልከቱ።

ሌሎች እየተማሯቸው ያሉትን እንዲተገብሩ እርዷቸው። አንድ ሰው አሥራት ለመክፈል በሚፈልግበት ጊዜም እንኳን፣ አንዳንድ ጊዜ እንዴት እንደሚደረግ አያውቅም። ቤተሰባችሁን ወይም ክፍላችሁን እያስተማራችሁ ከሆነ፣ በበይነመረብ ወይም የአሥራት እና የሌሎች ልገሣዎች ወረቀትን በመጠቀም እንዴት አሥራትን መክፈል እንደሚቻል ለማስረዳት የተወሰነ ጊዜ መመደብን አስቡ። (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 27ን ተመልከቱ።)

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

ምስል
የልጆች ክፍል ምልክት 02

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥4–5

እኔ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ነኝ።

  • ልጆቻችሁ የቤተክርስቲያኗን ስም እንዲያውቁ እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለመርዳት፣ ከእነርሱ መካከል የቤተክርስቲያኗን ሙሉ ስም መጥራት የሚችል ይኖር እንደሆነ ጠይቋቸው። ከዚያም በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥4 ውስጥ ሥሙን ልታሳዩዋቸው እና ከእናንተ ጋር እንዲደግሙት ልታደርጉ ትችላላችሁ። ይህን ስታደርጉበ ጉልህ የሆኑትን ቃላት እና ለምን አስፈላጊ እንደሆኑ ማመልከትን አስቡ። “Chapter 43: Jesus Christ Names His Church [ምዕራፍ 43፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን ሰየመ]” (በDoctrine and Covenants Stories [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 164፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ) ልትከልሱ ወይም “The Church of Jesus Christ [የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን]” (የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 77) ልትዘምሩ ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥4–6

የእኔ ምሳሌ ሌሎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ እና ጥበቃን እንዲያገኙ ሊረዳቸው ይችላል።

  • ልጆቻችሁ በችግር ውስጥ ያሉ እንዲሁም “ከህይወት አውሎ ንፋስ” “መሸሸጊያ” የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ሊያውቁ ይችላሉ (ቁጥር 6)። እነዚህን ሠዎች መርዳት የሚችሉት እንዴት ነው? ተነሱ የሚለውን ቃል በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥5 ውስጥ ስታነቡ ልጆቻችሁ እንዲቆሙ መጋበዝን አስቡ። አብሩ የሚለውን ቃል ስታነቡ ጣቶቻቸውን እንደ የፀሐይ ብርሃን ጨረር ሊዘረጉ ይችላሉ። ብርሃናችን የሚገኘው ከኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ልጆቻችሁን አስታውሷቸው፣ እንዲሁም ልክ እንደ እርሱ “[ማብራት]” የሚችሉባቸውን መንገዶች እንዲያስቡ እርዷቸው።

  • ልጆቿችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥6ን የሚገልፅ ሥዕል ሊሥሉ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ አውሎ ንፋስን እና በቤተክርስቲያኗ ህንፃ ውስጥ የተሸሸጉ ሰዎችን ሊሥሉ ይችላሉ። አውሎ ንፋሱ ምንን ሊወክል ይችላል? የአዳኙ ቤተክርስቲያን እርዳታ የምታቀርበው እንዴት ነው? ልጆቻችሁ አንድን ጓደኛ፣ የቤተሰብ አባል፣ ወይም የተቸገረ ጎረቤት እንዲያስቡ እርዷቸው። በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እርዳታ እንዲያገኙ ልንጋብዛቸው የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 117

የእኔ መስዋዕትነቶች በጌታ ዘንድ የተቀደሱ ናቸው።

  • ልጆቻችሁ ኒዌል ኬ. ዊትኒን እንደሆኑ እንዲያስመስሉ ጋብዟቸው። ጌታ ስኬታማ ሥራቸውን እንዲተው እና ወደ አዲስ ቦታ እንዲሔዱ ጠይቋቸው ቢሆን ኖሮ ምን ይሰማቸው ነበር? (“Chapter 41: Trouble in Kirtland [ምዕራፍ 41፦ ችግሮች በከርትላንድ ውስጥ]፣” በDoctrine and Covenants Stories [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 158–60፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ መከለስ ሊረዳ ይችል ይሆናል) ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 117፥1–11ን አብራችሁ ስታነቡ፣ ጌታን ለመታዘዝ እምነት እንዲኖራቸው የሚረዳ አንድ ነገር በሚሰሙበት ጊዜ እንዲያስቆሟችሁ ልጆቻችሁን ጠይቋቸው። ጌታን ለመታዘዝ ምን መስዋዕትነቶችን እንከፍላለን? የሚባርከን እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 119–20

የሰማይ አባት ልጆቹን ለመባረክ አሥራትን ይጠቀማል።

  • አብዛኞቹ የምታስተምሯቸው ልጆች ገንዘብ ለማግኘት እና አሥራት ለመክፈል ገና ትናንሽ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን አሥራት በመላው ዓለም በሚከናወነው የጌታ ሥራ ላይ እንዴት አስተዋፅዖ እንደሚያደርግ ቢገነዘቡ መልካም ነው። አሥራት ምን እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለመርዳት በዚህ መዘርዝር መጨረሻ ላይ ያሉትን ምሥሎች እና የአክቲቪቲ ገፅ መጠቀምን አስቡ። (“Chapter 44: Tithing [ምዕራፍ 44፦ አስራት]፣” በDoctrine and Covenants Stories [የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች]፣ 165-66፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ ተመልከቱ። የሰማይ አባት ልጆቹን ለመባረክ አሥራትን የሚጠቀመው እንዴት ነው? ስለአሥራት ህግ እና እናንተን ስለባረከበት መንገድ የሚሰማችሁን አካፍሉ።

ምስል
አንድ አሥራት እየከፈለ

አሥራት በምንከፍልበት ጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት እናሳያለን።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ተመልከቱ።

አትም