መንፈሳዊ ትምህርት ቤት እና ኢኒስቲትዩት
ምንም እያስተማራችሁ ብትሆኑ፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሩ


“ምንም እያስተማራችሁ ብትሆኑ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሩ፣” በአዳኙ መንገድ ማስተማር፦ በቤት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚያስተምሩ ሁሉ [2022 (እ.አ.አ)]

“ምንም እያስተማራችሁ ብትሆኑ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሩ” በአዳኙ መንገድ ማስተማር

ምስል
ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ በመጨረሻው እራት ላይ

ሰላምን እተውላችኋለሁ፣፣ በዋልተር ሬን

ምንም እያስተማራችሁ ብትሆኑ፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሩ

በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ እንደ መርሆዎች፣ ትዕዛዛት፣ ትንቢቶች እና የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ያሉ ማስተማር የሚቻሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉም የአንድ ዛፍ ቅርንጫፎች ናቸው፣ ሁሉም አንድ አላማ አላቸውና፦ ሁሉም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ እና በእርሱ ፍፁም እንዲሆኑ መርዳት ( ጄረም1፥11ሞሮኒ10፥32ይመልከቱ)። ስለሆነም፣ ምንም ብታስተምሩ በእርግጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና እንደ እርሱ እንዴት መሆን እንደሚቻል እያስተማራችሁ መሆኑን አስታውሱ። መንፈስ ቅዱስ ስለአዳኙ እውነቶችን እንዲሁም በእያንዳንዱ የወንጌል መርሆ፣ ትዕዛዝ እና የትንቢት ትምህርት ውስጥ ስላው የእርሱ የቤዛነት ኃይል ለመገንዘብ እንድትማሩ ሊረዳችሁ ይችላል ( ያዕቆብ 7፥10–11 ይመልከቱ)።

ስለመስዋዕትነት እያስተማራችሁ ነውን? የምንከፍለው መስዋዕትነት እንዴት ነፍሳችንን ወደአዳኙ “ታላቅ እና የመጨረሻ መስዋዕትነት” እንደሚጠቁም ከተማሪዎች ጋር መወያየትን አስቡ ( አልማ 34፥10 ይመልከቱ)። ስለአንድነት እያስተማራችሁ ነውን? ኢየሱስ ክርስቶስ ከአባቱ ጋር ስላሳካው አንድነት እና ከእነርሱ ጋር አንድ እንድንሆን ስላቀረበው ግብዣ መወያየትን አስቡ (ዮሐንስ 17ይመልከቱ)። እያንዳንዱን የወንጌል ርዕስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የማስተማር እና የመማር እድል አድርጋችሁ ተመልከቱ።

እያንዳንዱ ትዕዛዝም ይህን እድል ይሰጣል። በወንጌል ህግጋቱ ላይ ብቻ አታተኩሩ—ስለህግ ሰጪውም ተማሩ። ስለጥበብ ቃል ብትወያዩ እና ልክ ለጤናማ አኗኗር ሊደረጉ ስለሚገቡ እና ስለማይገቡ ነገሮች ላይ ብታቆሙ፣ ይህን ህግ በመስጠት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ የመንፈሳዊ እና አካላዊ ደህንነታችን እንዴት በጥልቀት እንደሚጨነቅ የማሰላሰል እድልን ታጣላችሁ። አዳኙ ህጎቹን መኖር እንችል ዘንድ እንዴት በኃይሉ ሊባርከን ፍቃደኛ እና ጉጉ እንደሆነ ትኩረት ስጡ። እርሱ የሚሰጠን እያንዳንዱ ትዕዛዝ ስለሃሳቡ፣ ስለፍቃዱ እና ስለልቡ የሆነ ነገር ይገልፃል—ይህን በጋራ በማግኘት ተደሰቱ።

ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ አጽንዖት ስጡ

የሁሉም ወንጌል መርሆዎች ፍፁም ምሳሌ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ በመገንዘብ እና አጽንዖት በመስጠት ኢየሱስ ክርስቶስን የመማር ማስተማሩ ማዕከል ማድረግ እንችላለን። እንደደቀመዛሙርት፣ ዝም ብለን መርሆዎችን ብቻ አንከተልም—ኢየሱስ ክርስቶስን እንከተላለን። በአዳኙ ፍፁም ምሳሌ ላይ ስናተኩር፣ መንፈስ ቅዱስ ስለእርሱ ይመሰክራል እንዲሁም እርሱን እንድንከተል ያነሳሳናል።

ለአፍታ እስከመጨረሻ የመፅናትን መርህ እያስተማራችሁ እንደሆነ አድርጋችሁ አስቡ። አዳኙ እንዴት እስከመጨረሻ የመፅናት ምሳሌ እንደሆነ መወያየት እርሱን በጥልቅ የማክበር ጣፋጭ ስሜቶችን ሊያመጣ ይችላል። ከእርሱ ምሳሌ የምታስተምሯቸው ሰዎች ምን ሊማሩ እና ሊሰማቸው ይችላል?

ምስል
አዳኙ በመሬት ላይ የተኛን ሰው ሲፈውስ

አዳኙ ለሁላችንም ፍፁም ምሳሌ አኖረ። ሁሉንም ፈወሳቸው፣ በማይክል ማልም

ስለኢየሱስ ክርስቶስ መጠሪያዎች፣ ሚናዎች እና ባህሪያት አስተምሩ

ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ብዙ መጠሪያዎች አሉት። እያንዳንዱ መጠሪያ በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ የእርሱን አንድ ሚና ያንፀባርቃል እንዲሁም ስለእርሱ መለኮታዊ ባህሪያት ያስተምረናል። የእግዚአብሔር በግ፣ ጠበቃ፣ የእምነታችን ፈጻሚ እና የዓለም ብርሃን የሚሉት መጠሪያዎች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደሚያስተምሩን ከተማሪዎች ጋር ልታስቡ ትችላላችሁ። እንዲሁም፣ ተማሪዎች ስለአዳኙ የበለጠ እያወቁ እንዲመጡ ስታግዙ፣ ከተናገረው እና ካደረገው አልፋችሁ ወደማንነቱ እና በሕይወታችን ውስጥ ምን ዓይነት ሚና መጫወት እንደሚፈልግ ወደማወቅ ሂዱ። ስለአዳኙ ተፈጥሮ እና ባህሪያት በጋራ ስትማሩ፣ መንፈስ ቅዱስ እርሱን መረዳታችሁን እና ለእርሱ ያላችሁን ፍቅር ጥልቅ ያደርገዋል።

ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ምልክቶችን ፈልጉ

ጌታ “ሁሉ[ን]ም ነገሮች” “የፈጠርኳቸው እና የሰራኋቸው ስለእኔ እንዲመሰክሩ ነው” ብሎ አወጀ፣( ሙሴ 6፥63፤ እንዲሁም 2ኛ ኔፊ 11፥4 ይመልከቱ)። ያንን እውነታ በአዕምሮ በማድረግ፣ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ስለአዳኙ የሚመሰክሩ ብዙ ምልክቶችን ማየትን መማር እንችላለን። እነዚህ ምልክቶች እንደዳቦ፣ ውኃ እና ብርሃን የመሳሰሉ ነገሮችን ያካትታሉ። እነዚህ ነገሮች ከአዳኙ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ከተረዳን፣ ስለኃይሉ እና ባህሪያቱ ሊያስተምሩን ይችላሉ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ በነብያት እና በሌሎች ታማኝ ወንዶች እና ሴቶች ሕይወት ውስጥ ከአዳኙ ሕይወት ጋር ተመሳሳይነትን ልታገኙም ትችላላችሁ። ምልክቶችን መሻት በማትጠብቁባቸው እና አልፋችሁ ልትሄዱ በምትችሉባቸው ቦታዎች ስለአዳኙ እውነታዎችን ይገልፃል።

አትም