መንፈሳዊ ትምህርት ቤት እና ኢኒስቲትዩት
በአዳኙ መንገድ የማስተማር አላማ


በአዳኙ መንገድ ማስተማር አላማ፣” በአዳኙ መንገድ ማስተማር፦ በቤት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚያስተምሩ ሁሉ [2022 (እ.አ.አ)]

በአዳኙ መንገድ ማስተማር አላማ፣” በአዳኙ መንገድ ማስተማር

በአዳኙ መንገድ ማስተማር አላማ

በዚህ የመረጃ ምንጭ ውስጥ የተገለፁት መርሆዎች እያንዳንዱ የወንጌል አስተማሪ በአዳኙ መንገድ እንዲያስተምር ሊረዱ ይችላሉ። ያ ወላጆችን፣ የአገልግሎት ወንድሞችን እና እህቶችን፣ ሚስዮናውያንን፣ የሴሚነሪ እና የኢኒስቲቲዩት አስተማዎችን እና የቤተክርስቲያን ጥሪያቸው ለማስተማር እድሎችን የሚሰጣቸውን ሰዎች ሁሉ ያካትታል።

ይህን የመረጃ ምንጭ በራሳችሁ ማጥናት ወይም የተሻለ አስተማሪ መሆን ስለሚቻልበት ሁኔታ ከሌሎች ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን ለመምራት መጠቀም ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ ይህ የመረጃ ምንጭ በቤት ለቤት ምሽት፣ በአመራር ስብሰባዎች፣ በአጥቢያ ወይም በካስማ የምክር ቤት ስብሰባዎች፣ በሴሚናሪ እና በኢኒስቲቲዩት አገልግሎት ስብሰባዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል (“ለመሪዎች—አስተማሪዎችን ውጤታማ እንዲሆኑ መርዳት” ይመልከቱ)።

ይህ የመረጃ ምንጭ እንዴት እንደተደራጀ

ክፍል 1 የእርሱን ወንጌል መርሆዎች በምናስናስተምርበት ጊዜ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ትኩረት የማድረግን አስፈላጊነት አጽንዖት ይሰጣል። ይህ ክፍል ምን እንደምናስተምር ይገልፃል።

ክፍል 2፦ ለክርስቶስ መሰል ትምህርት መርሆዎች አጽንዖት ይሰጣል። ይህ ክፍል እንዴት እንደምናስተምር ይገልፃል።

ክፍል 3 አስተማሪዎች የክርስቶስ መሰል ትምህርት መርሆዎችን እንዲተገብሩ ለመርዳት ተግባራዊ ሃሳቦችን ይሰጣል።

የክርስቶስ መሰል ትምህርት አጠቃላይ እይታ

የሚከተሉት ሰንጠረዦች በዚህ የመረጃ ምንጭ ውስጥ የሚሰጡትን የመርሆዎች ትምህርት አጠቃላይ እይታ ይሰጣሉ።

ምስል
የትምህርት አስተቃቀድ ቢጋር ናሙና

አትም