መንፈሳዊ ትምህርት ቤት እና ኢኒስቲትዩት
የክርስቶስ መሰል ትምህርት አጠቃላይ ዕይታ


“የምታስተምሯቸውን ውደዱ፣” በአዳኙ መንገድ ማስተማር(2022) [እ.አ.አ]

የክርስቶስ መሰል ትምህርት አጠቃላይ ዕይታ

2:19

የሚከተሉት ሰንጠረዦች በዚህ የመረጃ ምንጭ ውስጥ የሚሰጡትን የመርሆዎች ትምህርት አጠቃላይ ዕይታ ይሰጣሉ።

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አተኩሩ

ምንም ነገር በምታስተምሩበት ጊዜ ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሩ

  • የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ አጉሉ።

  • ስለኢየሱስ ክርስቶስ መጠሪያዎች፣ ሚናዎች እና ባህሪያት አስተምሩ።

  • ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ምልክቶችን ፈልጉ።

ተማሪዎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጡ እርዱ

  • ተማሪዎች የጌታን ፍቅር፣ ኃይል እና ምህረት በሕይወታቸው ውስጥ እንዲገነዘቡ እርዱ።

  • ተማሪዎች ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠነክሩ እርዱ።

  • ተማሪዎች በፍቃደኝነት የበለጠ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን እንዲጥሩ እርዱ።

የክርስቶስ መሰል የማስተማር መርሆዎች

የምታስተምሯቸውን ውደዱ።

  • ተማሪዎችን እግዚአብሄር በሚያያቸው መልኩ እዩዋቸው።

  • እነሱን ለማወቅ እሹ—ያሉበትን ሁኔታ፣ ፍላጎታቸውን፣ እና ጥንካሬያቸውን ተረዱ።

  • ለእነርሱ በስም ጸልዩላቸው።

  • ሁሉም የሚከበሩበት እና የሚያበረክቱት ነገር ዋጋ እንዳለው የሚያውቁበት ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ፍጠሩ።

  • ፍቅራችሁን ለመግለጽ ተገቢ መንገዶችን ፈልጉ።

በመንፈስ አስተምሩ

  • በመንፈስ እራሳችሁን አዘጋጁ።

  • ተማሪዎቹ ስለሚያስፈልጓቸው ነገሮች መንፈሳዊ ሀሳቦችን ስታገኙ ምላሽ ለመስጠት ሁሌም ዝግጁ ሁኑ።

  • በመንፈስ ቅዱስ የሚማሩበትን ቦታ እና እድል ፍጠሩ።

  • ተማሪዎች የግል ራእይን እንዲሹ፣ እንዲያውቁ፣ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ አግዙ።

  • ብዙ ጊዜ ምስክርነታችሁን ስጡ፣ እናም ተማሪዎች ስሜታቸውን፣ ልምዳቸውን፣ እና ምስክርነታቸውን እንዲያካፍሉ ጋብዙ።

ትምህርቱን አስተምሩ

  • የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ለራሳችሁ ተማሩ።

  • ከቅዱሳት መጻህፍትና ከኋለኛው ቀን ነቢያት ቃሎች አስተምሩ።

  • ተማሪዎች ቅዱሳት መጻህፍትን እንዲሹ፣ እንዲያውቁ እና ውስጡ ያሉትን እውነቶች እንዲረዱ አግዟቸው።

  • ወደመለወጥ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን ወደመገንባት በሚመሩ እውነታዎች ላይ አተኩሩ።

  • ተማሪዎች ከኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮ ውስጥ ከነሱ ጋር የግል ዝምድና ያለውን ነገር እንዲያገኙ አግዙ።

በትጋት መማርን ጋብዙ

  • ለትምህርታቸው ሀላፊነት እንዲወስዱ አግዙ።

  • ወንጌሉን በየቀኑ በማጥናት አዳኙን ወደማወቅ እንዲመጡ ተማሪዎችን አበረታቱ።

  • ለመማር እንዲዘጋጁ ተማሪዎችን ጋብዙ።

  • ተማሪዎች እየተማሯቸው ስላሉት እውነቶች እንዲያጋሩ አበረታቱ።

  • ተማሪዎች እየተማሯቸው ያሉትን እንዲኖሩ ጋብዙ።

የክርስቶስ መሰል ትምህርት አጠቃላይ ዕይታ