በአዳኙ መንገድ ማስተማር፦ በቤት እና በቤተክርስቲያን ለሚያስተምሩ ሁሉ መግቢያ የቀዳሚ አመራር መልዕክትይህ የመረጃ ምንጭ አዳኙ እንዴት እንዳስተማረ ለመማር መመሪያችሁ ሊሆን ይችላል። በእርሱ መንገድ ለማስተማር ስትጥሩ፣ እርሱ መሆን እንደምትችሉት የሚያውቀውን አስተማሪ እንድትሆኑ ይረዳችኋል። የ በአዳኙ መንገድ ማስተማር ዓላማበዚህ የመረጃ ምንጭ ውስጥ የተገለፁት መርሆዎች እያንዳንዱ የወንጌል አስተማሪ በአዳኙ መንገድ እንዲያስተምር ሊረዱ ይችላሉ። የክርስቶስ መሰል ትምህርት አጠቃላይ ዕይታበዚህ የመረጃ ምንጭ ውስጥ የተገለፁት መርሆዎች እያንዳንዱ የወንጌል አስተማሪ በአዳኙ መንገድ እንዲያስተምር ሊረዱ ይችላሉ። ክፍል 1፦ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ማተኮር ክፍል 1፦ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ማተኮር ምንም ነገር በምታስተምሩበት ጊዜ ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሩምንም ነገር እያስተማራችሁ ብትሆኑ በእርግጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም እንዴት እንደእርሱ መሆን እንደሚቻል እያስተማራችሁ መሆኑን አስታውሱ። ተማሪዎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጡ እርዱእንደ አስተማሪ የምታደርጉት ምንም ነገር የሰማይ አባትን እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቁ እና ፍቅራቸው እንዲሰማቸው ከመርዳት በበለጠ ተማሪዎችን አይባርክም። ክፍል 2፦ የክርስቶስ መሰል ትምህርት መርሆዎች ክፍል 2፦ የክርስቶስ መሰል ትምህርት መርሆዎች የምታስተምሯቸውን ውደዱየአዳኙ ፍቅር በልባችን ውስጥ ሲኖር ሌሎች ስለክርስቶስ እንዲማሩ እና ወደ እርሱ እንዲመጡ ለመርዳት እያንዳንዱን መንገድ እንሻለን። ፍቅር የትምህርታችን ማነሳሻ ይሆናል። በመንፈስ አስተምሩየኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስታስተምሩ፣ መንፈስ ቅዱስ ሊመራችሁ እና እውነታውን ለምታስተምሯቸው ሰዎች አእምሮዎች እና ልቦች ሊመሰክር አብሯችሁ ሊሆን ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥2 ይመልከቱ)። ትምህርቱን አስተምሩአዳኙ እንዳደረገው የአብን ትምህርት ስታስተምሩ በኃይል ማስተማር ትችላላችሁ። በትጋት መማርን ጋብዙየአዳኙን ምሳሌ ስንከተል የምናስተምራቸው ሰዎች እንዲጠይቁ፣ እንዲሹ እና እንዲያንኳንኩ ከዛም እንዲያገኙ እንጋብዛለን (ማቴዎስ 7፥7–8 ይመልከቱ)። ክፍል 3፦ ተግባራዊ እርዳታዎች እና ሃሳቦች ክፍል 3፦ ተግባራዊ እርዳታዎች እና ሃሳቦች ለተለያዩ የማስተማር ሁኔታዎች እና ተማሪዎች ሃሳቦችይህ ክፍል ለብዙ ተማሪዎች እና የትምህርት ሁኔታዎች የተለዩ የሆኑ ተጨማሪ ሃሳቦችን ይሰጣል። የትምህርት እቅድ አወጣጥ ናሙናየትምህርት ዕቅድ የናሙና ንድፍ ሊሆን የሚችል ምሳሌ እነሆ። እንደ ክርስቶስ መሰል አስተማሪነትን ማሻሻል—የግል መመዘኛእንደ አስተማሪዎች ተማሪዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን እንዲገነቡ እና የበለጠ እንደሱ እንዲሆኑ የመርዳት ችሎታችንን ለማዳበር እንችል ዘንድ በየጊዜው ጥንካሬያችንን እና ድክመታችንን መመዘን አለብን። ለመሪዎች—አስተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ መርዳትከአስተማሪዎች ጋር ስትገናኙ ለሚያበረክቱት አገልግሎት በደግነት እና በምስጋና ለማጠናከር እና ለማበረታታት መንገዶችን አስቡ።