መንፈሳዊ ትምህርት ቤት እና ኢኒስቲትዩት
የቀዳሚ አመራር መልዕክት


“የቀዳሚ አመራር መልዕክት፣” በአዳኝ መንገድ ማስተማር፦ በቤት እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚያስተምሩ ሁሉ [2022 (እ.አ.አ)]

“የቀዳሚ አመራር መልዕክት፣” በአዳኙ መንገድ ማስተማር

የቀዳሚ አመራር መልዕክት

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማስተማር ያላችሁ እድል ምንኛ ክቡር ነው! ለማስተማር የተለየ ጥሪ ይኑራችሁ አይኑራችሁ፣ እናንተ አስተማሪ ናችሁ ። እንደ ዋናው መምህር እንደኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙርነታችሁ፣ በምትሄዱበት ቦታ ሁሉ—በቤት ውስጥ፣ በቤተክርስቲያን፣ ሌሎችን እና ጓደኞቻችሁን ስታገለግሉ የእርሱን ብርሃን የማካፈል እድሎች አሏችሁ። ወንጌልን ማስተማር የተቀደሰ ሃላፊነት ነው። ወንጌልን ማስተማር የጌታ ስራ አስፈላጊው አካል ነው እናም በእርሱ መንገድ ስናደርገው የተሻለ ይሰራል።

ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌልን እንዴት እንዳስተማረ የበለጠ እንድትማሩ እንጋብዛችኋለን። ቃላቱን፣ ተግባሮቹን እና ባህሪያቱን በጸሎት መንፈስ አጥኑ እንዲሁም እርሱን የበለጠ በቅርበት ለመከተል ጣሩ። በአዳኙ መንገድ ማስተማር መመሪያችሁ ሊሆን ይችላል።

ቀዳሚ አመራር