ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
የዳግም መመለስ ድምጾች፦ የጽዮን ካምፕ


“የዳግም የመመለስ ድምጾች፦ የጽዮን ካምፕ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“የፅዮን ካምፕ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

የዳግም መመለስ ድምጾች ምልክት

የዳግም መመለስ ድምጾች

የፅዮን ካምፕ

የፅዮን ካምፕ ቅዱሳንን በጃክሰን ካውንቲ ወደሚገኘው መሬታቸው በጭራሽ ስላልመለሳቸው ብዙ ሰዎች ጥረታቸው ከንቱ እንደሆነ ተሰምቷቸው ነበር። ሆኖም፣ በርካታ የፅዮን ካምፕ ተሳታፊዎች ልምዶቻቸውን ወደ ኋላ ተመልሰው በመመልከት፣ ጌታ በህይወታቸው እና በመንግሥቱ እንዴት ከፍ ያለ ዓላማ እንደፈፀመ አይተዋል። የተወሰኑ ምስክርነቶቻቸው እነሆ።

ጆሴፍ ስሚዝ

One drawing in pencil, charcoal and ink on paper.  A left profile, head/shoulders portrait of Joseph Smith; drawn basically in charcoal, highlighted with white paint and black ink.  titled at bottom "Jospeh Smith the Prophet."  Signed at left shoulder "Drawn from the most authentic sources by Dan Weggeland"  A drawn border surrounds it.  No date apparent.

የፅዮን ካምፕ ከተደረገ ከ40 ዓመታት በላይ በኋላ፣ የካምፑ አባል የነበረው ጆሴፍ ያንግ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የሚከተሉትን እንደተናገረ ዘግቧል፥

“ወንድሞች፣ አንዳንዶቻችሁ በሚዙሪ ስላልተዋጋችሁ ተናዳችሁብኛል፣ ነገር ግን ልንገራችሁ፣ እግዚአብሔር እንድትዋጉ አልፈለገም። ልክ እንደ አብርሐም ህይውታቸውን ለመሰዋት ካዘጋጁት እና ታላቅ መስዋትነት ከከፈሉ ሰዎች ካልወሰደ በቀር፣ በአስራ ሁለት ሰዎች እንዲሁም የእነርሱን መሪነት በሚከተሉ በስራቸው በሚገኙ ሰባዎች ለምድር ህዝብ የወንጌልን በር ለመክፈት አይችልም።

“አሁን ጌታ አሥራ ሁለቱን እና ሰባዎቹን አግኝቷል፣ እንዲሁም መስዋዕትነት የሚከፍሉ፣ ሌሎች የሰባዎች ቡድኖችም ይጠራሉ፣ እንዲሁም መስዋዕትነቶቻቸውን እና መስዋዕቶቻቸውን አሁን ያላደረጉ ከዚህ በኋላ መስዋዕትን ያደርጋሉ።”

ብሪገም ያንግ

Photograph of Brigham Young in stately side pose.

“ወደ ሚዙሪ ስንደርስ ጌታ አገልጋዩን ጆሴፍ ስሚዝን ‘መሰዋዕትህን ተቀብያለሁ’ ሲል አነጋገረው፣ ስለዚህም እንደገና የመመለስ መብት አግኝተን ነበር። ስመለስ ብዙ ጓደኞቼ ከሥራቸው ወደ ሚዙሪ እንዲሄዱ መጥራትና ከዚያም ምንም ሳያሳኩ ተመልሶ መምጣት ስለነበረው ጥቅም ጠየቁኝ። ‘ማንን ጠቀመ?’ ብለው ጠየቁ። ‘ጌታ ይህን እንዲከናወን አዝዞ ከነበረ፣ ይህን ሲያደርግ ምን ዓላማ ነበረው?’ … ለእነዚያ ወንድሞች፣ ጥሩ እንደተከፈለኝ—ከከፍተኛ ወለድ ጋር እንደተከፈለኝ—አዎን ከነቢዩ ጋር በመጓዝ ያገኘሁት እውቀት ተትረፈርፎ እስኪፈስ ድረስ መለኪያዬ ሞልቶልኝ እንደነበር ነገርኳቸው።”

ውልፈርድ ውድረፍ

Photograph of Brigham Young in stately side pose.

“በፅዮን ካምፕ ከእግዚአብሔር ነቢይ ጋር ነበርኩኝ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያደረገውን ግንኙነት አየሁ። የእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር እንደነበረ አየሁ። እርሱ ነቢይ እንደነበረ አየሁ። በዚያ ተልዕኮ ላይ በእግዚአብሔር ኃይል ለእርሱ የተገለጠለት ነገር ለእኔ እና መመሪያውን ለተቀበሉ ሁሉ ትልቅ ዋጋ ነበረው።”

“የፅዮን ካምፕ አባላት በተጠሩ ጊዜ ብዙዎቻችን ተያይተን አናውቅም ነበር፤ አንዳችን ለሌላችን እንግዳ ነበርን እንዲሁም ብዙዎቹ ነቢዩን በጭራሽ አይተውት አያቁም ነበር። እንዲሁም ልክ በወንፊት እንደተነፋ በቆሎ፣ በመላ አገሪቱ ወደ ውጪ ተበታትነን ነበር። እኛ ወጣት ወንዶች ነበርን፣ እና በዚያ በመጀመሪያው ጊዜ ሄደን ፅዮንን እናድን ዘንድ ተጠርተን ነበር፣ እናም ማድረግ ያለብንን በእምነት ማድረግ ነበረብን። ከተለያዩ ግዛቶች ወደ ከርትላንድ ተሰባሰብን ከዚያም የእግዚአብሔር ትዕዛዝ በእኛ ላይ ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ ፅዮንን ለማዳን ሄድን። እግዚአብሔር፣ የአብርሃምን ሥራ እንደተቀበለው የእኛንም ሥራዎች ተቀበለ። ከሃዲዎች እና የማያምኑ ብዙ ጊዜ ‘ምን ሠራችሁ?’ በለው ቢጠይቁም እንኳ፣ እኛ ብዙ ነገሮችን አከናወንን። በሌላ መንገድ ፈፅሞ ማግኘት የማንችለውን ተሞክሮ አግኝተናል። የነቢዩን ፊት የማየት እድል ገጥሞን ነበር፣ እንዲሁም አንድ ሺህ ማይሎችን ከእርሱ ጋር አብረን የመጓዝ እድል አግኝተን ነበር፣ ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን መንፈስ ሥራዎች፣ የኢየሱስ ክርስቶስን ለእርሱ መገለጥ፣ እንዲሁም የእነዚያን ራዕዮች ፍጻሜን አይተን ነበር። ደግሞም በዚያች በመጀመሪያ ቀን ሁለት መቶ የምንሆን ሽማግሌዎችን ከመላ አገሩ ሰበስቦን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንድንሰብክ ወደ ዓለም ሁሉ ላከን። ከፅዮን ካምፕ ጋር ባልሄድ ኖሮ፣ ዛሬ እዚህ [በአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን ውስጥ በማገልገል፤ በሶልት ሌክ ሲቲ] ውስጥ ባልሆንኩኝ ነበር። ወደዚያ በመሄዳችን ወንጌልን ለመስበክ ወደ ወይኑ አትክልት ተላክን፣ እናም ጌታ ሥራችንን ተቀበለ። እንዲሁም በሥራዎቻችን እና በሥደታችን ሁሉ፣ ህይወታችን ብዙውን ጊዜ ለአደጋ የተጋለጠ ሆኖ፣ በእምነት መስራት እና መኖር ነበረብን።”

“በፅዮን ካምፕ በመጓዝ ያገኘነው ተሞክሮ ከወርቅ የላቀ ዋጋ ነበረው።”

ማስታወሻዎች

  1. ጆሴፍ ያንግ፣ ቀዳማዊ፣ History of the Organization of the Seventies [1878 (እ.አ.አ)]፣ 14።

  2. “Discourse፣” ዴዘረት ኒውስ፣ ታህሳስ 3፣ 1862 (እ.አ.አ)፣ 177።

  3. በጉባኤ ሪፖርት፣ ሚያዝያ 1898 (እ.አ.አ)፣ 29–30፤ በተጨማሪም Teachings of Presidents of the Church: Wilford Woodruff (2004)፣ 135 ተመልከቱ።

  4. “Discourse፣” ዴዘረት ኒውስ፣ ታህሳስ 22፣ 1869 (እ.አ.አ)፣ 543፤ እንዲሁም eachings: Wilford Woodruff 138 ተመልከቱ።

  5. Deseret News: Semi-Weekly፣ ነሃሴ 27፣ 1880 (እ.አ.አ)፣ 2፤ እንዲሁም Teachings: Wilford Woodruff፣ 138 ተመልከቱ።