“ሐምሌ 7–13፦ ‘ዋጋቸውም ታላቅ እና ክብራቸውም ዘለአለማዊ ይሆናል’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 7–13፦ “ዋጋቸውም ታላቅ እና ክብራቸውም ዘለአለማዊ ይሆናል”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76
“ከሞትኩኝ በኋላ ምን እሆናለሁ?” ከሞላ ጎደል እያንዳንዱ ግለሠብ ይህንን ጥያቄ በአንድ ወይም በሌላ መልክ ይጠይቃል። ለብዙ መቶ አመታት፣ ብዙ የክርስቲያን ባህሎች በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ላይ በመመርኮዝ፣ ስለመንግስተ ሰማይ እና ስለገሃነም ይኼውም ገነት ለጻድቃን እንዲሁም ሥቃይ ለክፉዎች እንደሆነ አስተምረዋል። ነገር ግን፣ በእውነት መላው የሰው ልጅ ቤተሰብ እንደዚያ በጥብቅ ሊከፈል ይችላል? በየካቲት 1832 (እ.አ.አ)፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን ስለጉዳዩ ብዙ ሊታወቅ የሚችል ነገር ይኖር እንደሆነ የማወቅ ፍላጎት አደረባቸው (ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 76 ተመልከቱ)።
በእርግጥም ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን በእነዚህ ነገሮች ላይ እያሰላሰሉ ሳሉ፣ ጌታ “የመረዳት አይኖቻ[ቸውን] ነካ እናም ተከፈቱ” (ቁጥር 19)። ጆሴፍ እና ስድኒ በጣም አስደናቂ፣ በጣም ሰፋ ያለ እንዲሁ በጣም ገላጭ የሆነ ራዕይ ተቀበሉ እና ቅዱሳኑም “ራዕዩ” ብለው ጠሩት። የሰማይን መስኮቶች ወለል አድርጎ ከፈተ እናም ለእግዚአብሔር ልጆች አእምሮን የሚያሰፋ የዘለአለማዊነት እይታ ሰጣቸው። ራዕዩ መንግስተ ሰማይ ታላቅ እና ሰፋ ያለ፣ እንዲሁም ብዙ ሰዎች ከዚያ በፊት ከሚያስቡት የበለጠ አካታች መሆኑን ገልጿል። እግዚአብሔር ከምንረዳው በላይ ይቅር ባይ እና ፍትሃዊ ነው። እናም የእግዚአብሔር ልጆች፣ ከምናስበው በላይ የላቀ ክብራማ ዘለአለማዊ ፍጻሜ አላቸው።
Saints፣ 1፥147–50፤ “The Vision፣” በRevelations in Context፣ 148–54 ውስጥ ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
መዳን የሚገኘው የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው።
ክፍል 76 ስለዘለዓለማዊ ፍፃሜያችን ጠቃሚ እውነቶችን ይገልፃል፣ ነገር ግን ይህ መገለጥ የሚናገረው ስለሦስቱ የክብር መንግስታት ወይም ስለደህንነት ዕቅዱ ብቻ ነው ብሎ መናገር ጎዶሎ ያደርገዋል። ይበልጥ በትክክል ለመናገር፣ ክፍል 76 የሚገልጸው የእግዚአብሔርን ዕቅድ፣ ለደህንነታችን እና ለዘለዓለማዊ ክብራችን የሚቻል ስለሚያደርገው ስለኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በምታነቡበት ጊዜ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና የተለያዩ የክብር መንግስታትን በሚወርሱ ሰዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚገልጹ ቃላትን ወይም ሀረጎችን ልትፈልጉ ትችላላችሁ። ምናልባት እንደሚከተለው ያለ ሰንጠረዥ የምታገኙትን እንድትመዘግቡ ሊረዳችሁ ይችላል።
የክብር መንግስት |
ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለው ግንኙነት |
ዘለዓለማዊ በረከቶች |
---|---|---|
የክብር መንግስት | ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለው ግንኙነት
| ዘለዓለማዊ በረከቶች
|
የክብር መንግስት | ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለው ግንኙነት | ዘለዓለማዊ በረከቶች |
የክብር መንግስት | ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለው ግንኙነት | ዘለዓለማዊ በረከቶች |
ከአዳኙ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማጠናከር ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል?
ውልፈርድ ውድረፍ ይህንን ራዕይ ሲያነቡ፣ እንዲህ አሉ፣ “ከዚህ በፊት በህይወቴ ወድጄው ከማውቀው በላይ ጌታን የመውደድ ፍላጎት አደረብኝ” (“የዳግም የመመለስ ድምጾች፥ ‘የራዕዩ’ ምስክርነቶች” ተመልከቱ)። በቁጥር 1–5፣ 20–24፣ 39–43፣ 107–8 ውስጥ እርሱን ይበልጥ እንድትወዱት ምክንያት የሆናችሁን ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ትማራላችሁ?
በተጨማሪም 1ኛ ጴጥሮስ 3፥18–19፤ 4፥6፤ ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “What Has Our Savior Done for Us?፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021(እ.አ.አ)፣ 75–77፤ “I Stand All Amazed፣” መዝሙር፣ ቁጥር. 193 ተመልከቱ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥5–10፣ 114–18
“በመንፈስ ቅዱስ ኃይል” የእግዚአብሔርን ፈቃድ መረዳት እችላለሁ።
በክፍል 76 ውስጥ ያለውን ራዕይ ተቀበሉት ሁሉም የቤተክርስቲያን አባላት አልነበሩም፣ ምክንያቱም ሁሉም እንደሚድኑ እና የተወሰነ የክብር ደረጃ እንደሚቀበሉ ያስተምር ነበርና። ለምሳሌ፣ ብሪገም ያንግ እንዲህ ብለዋል፦ “የእኔ ልምዶች እንደዚህ ነበሩ፣ ራዕዩ በመጀመሪያ ወደ እኔ ሲመጣ፣ ቀድሞ የተማርኩትን በቀጥታ የሚቃረን እንዲሁም የሚቃወም ነበር። እንዲህ አልኩኝ፣ ትንሽ ቆይ። ውድቅ አላደረኩትም፤ ሆኖም ልረዳው አልቻልኩም ነበር።” “እኔ ራሴ እስካውቀው እና ሙሉ በሙሉ እስክገነዘበው ድረስ ማሰብ እና መጸለይ፣ ማንበብ እና ማሰብ” አለብኝ ሲል ገለጸ(በ“The Vision፣” በRevelations in Context፣ 150)። እግዚአብሔር አሁን ካላችሁ ግንዛቤ የተለየ ነገሮችን በሚገልጥበት ጊዜ ሊረዳችሁ የሚችል ከእርሳቸው ተሞክሮ ምን ትማራላችሁ? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥5–10፣ 114–18 ውስጥ ስለእግዚአብሔር ምን ትማራላችሁ? እነዚህ ጥቅሶች “[የእግዚአብሔርን] በጎ ፈቃድ” እንዴት መገንዘብ እንደምትችሉ ምን ያስተምራሉ? (ቁጥር 7)።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥39–44፣ 50–70
በዘለአለም ህይወት ከፍ ከፍ መደረግ እጅግ ከፍተኛው የደህንነት ደረጃ ነው።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥39–44፤ ስለደህንነት በአጠቃላይ ይገልፃል። ቁጥሮች 50–70 የተለየ የደህንነት ዓይነት ስለሆነው በዘለአለም ህይወት ከፍ ከፍ ስለመደረግ ይገልፃል። በደህንነት እና በዘለዓለም ህይወት ከፍ ከፍ በመደረግ መካከል ያለውን ልዩነት እንዴት ትገልፁታላችሁ? በሁለቱም ውስጥ የአዳኙ ሚና ምንድን ነው? በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ በዘለዓለም ህይወት ከፍ ከፍ መደረግን እንድትሹ የሚያነሳሷችሁን ምን ታገኛላችሁ?
በተጨማሪም ዮሐንስ 3፥16–17፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥20–25 ተመልከቱ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥50–70፣ 92–95
ሰማያዊ አባቴ በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ዘለአለማዊ ህይወትን እንድቀበል ይፈልጋል።
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥50–70፣92–95 ውስጥ እንደተገለፀው፣ የሰለስቲያል ክብርን የሚቀበል አይነት ሰው መሆን ስለመቻላችሁ አስባችሁ ወይም ተጨንቃችሁ ታውቃላችሁን? እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀውን ማወቅ አስፈላጊ ቢሆንም፣ እርሱን እንድንመስል ለመርዳት እግዚአብሔር ለእኛ ያደረገልንን እና እያደረገልን ያለውን በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ መመልከትን አስቡ። ጥረታችሁ ለእርሱ አስፈላጊ እንደሆነ የሚሰማችሁ ለምንድነው?
ይህ የሰለስቲያል ክብር ዕይታ ኑሯችሁን ለመኖር በምትፈልጉበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?
በተጨማሪም ሙሴ 1፥39፤ ጄ. ዴቭን ኮርኒሽ፣ “Am I Good Enough?ተመልከቱ። Will I Make It?፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2016(እ.አ.አ)፣ 32–34።
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ሁላችንም የእግዚአብሔር ልጆች ነን።
-
ልጆቻችሁ መለኮታዊ አቅማቸውን እንዲገነዘቡ ለመርዳት፣ የልጆችን እና የእነርሱን ወላጆች ምሥሎች ልታሳዩዋቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥24 ልታነቡ እና እኛ ሁላችንም “የእግዚአብሔር ወንዶች እና ሴቶች ልጆች” መሆናችንን በማወቃችሁ ለምን ደስተኛ እንደሆናችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ አጋሩ።
-
“I Am a Child of God” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ ፣ 2–3) አብራችሁ ልትዘምሩ እና “እኔ” የሚለውን ሲዘምሩ ልጆቻችሁ ወደራሳቸው እንዲጠቁሙ ልጋብዟቸው ትችላላችሁ። ከዚያም፣ ወደ ሌላ ሰው እየጠቆሙ “እኔ” የሚለውን “አንተ” በሚለው በመተካት መዝሙሩን እንደገና ዘምሩ።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥5፣ 41–42፣ 69
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ ነው።
የሰማይ አባት ተመልሼ ለዘለአለም ከእሱ ጋር እንድኖር ይፈልጋል።
-
እናንተ እና ልጆቻችሁ “Chapter 26፥ The Three Kingdoms of Heaven” በሚለው (በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 97–103፣ ውስጥ ማንበብ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ) መመልከት ትችላላችሁ፣ ከዚያም ስለ ጆሴፍ ስሚዝ ራዕይ የምትወዱትን አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ። ልጆቻችሁ በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ከሰማይ አባት ጋር መኖር ምን እንደሚመስል ያላቸውን ሀሳብ እና ስሜት እንዲያካፍሉ ፍቀዱላቸው።
-
እንዲሁም፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥62ን ማንበብ እና ልጆቻችሁ ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ሆነው የሚያሳዩ የራሳቸውን ምስሎች እንዲሥሉ መጋበዝ ትችላላችሁ (የዚህን ሣምንት የአክቲቪቲ ገፅ ተመልከቱ)።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥12፣ 15–19፣ 114–16
ቅዱሣት መፃህፍትን ማጥናት “የእግዚአብሔርን ነገሮች [እንድረዳ]” ሊያግዘኝ ይችላል።
-
ልጆቻችሁ ከቁጥሮች 15–19 በማንበብ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሲድኒ ሪግደን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76 ውስጥ ያለውን ራዕይ ሲረከቡ ምን እያደረጉ እንደነበር እንዲያውቁ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ መነሣሣትን ስላገኛችሁበት ጊዜ ለልጆቻችሁ ንገሯችው፣ እንዲሁም ልጆቻችሁ ተመሳሳይ ተሞክሮዎች እንደነበሯቸው ጠይቋቸው።