ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 14–20፦ “እመራችኋለሁ”፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77–80


“ሐምሌ 14–20፦ ‘እመራችኋለሁ’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77–80፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]

“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77–80፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እረኛ

Going Home፣ በዮንግሱንግ ኪም

ሐምሌ 14–20፦ “እመራችኋለሁ”

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77–80

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዳግም ከተመለሰች ከሁለት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ2000 የሚልቁ አባላት ነበሯት እንዲሁም በፍጥነት እያደገች ነበር። መጋቢት 1832 (እ.አ.አ) ጆሴፍ ስሚዝ ከሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጋር “ ስለቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ለመወያየት” ተገናኘ፦ ይኼውም ራዕዮችን ስለማሳተም አስፈላጊነት፣ የሚሰባሰቡበት መሬት ስለመግዛት እና ድሆችን ስለመንከባከብ ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፣ የክፍል መግቢያ ተመልከቱ)። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት፣ በእነዚህ አካባቢዎች የጌታን “ምክንያት ወደፊት ለመግፋት” (ቁጥር 4) ጥረቶቻቸውን የሚያዋህዱበትን የትብብር ድርጅት ለመመሥረት ጌታ ትንሽ ቁጥር ያላቸውን የቤተክርስቲያን መሪዎችን ጠራ። ነገር ግን በእነዚህ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ውስጥም እንኳን፣ ጌታ በዘለዓለማዊ ነገሮች ላይ አተኩሯል። በመጨረሻም፣ የማተሚያ ቤት ወይም የጎተራ አላማ—በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እንደሚገኙት እንደ ሁሉም ሌሎች ነገሮች—ልጆቹ “በሰለስቲያል አለም ውስጥ ቦታ” እና “የዘለዓለም ባለጠግነት“ እንዲቀበሉ ለማዘጋጀት ነው (ቁጥሮች 7፣ 18)። እናም በየዕለት ተዕለት የሥራ ውጥረት ሣቢያ እነዚያን በረከቶች አሁን ለመገንዘብ ከባድ ከሆነ፣ “ተደሰቱ፣ እንደሚገባችሁ እመራችኋለሁ“ በማለት አረጋግጦልናል (ቁጥር 18)።

የጥናት ምልክት

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77

እግዚአብሔር እውቀትን ለሚፈልጉ ሰዎች እውቀትን ይሰጣል።

ጆሴፍ ስሚዝ እና ሲድኒ ሪግደን በመንፈስ አነሳሽነት የሚዘጋጀውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሲያዘጋጁ፣ እንደ ብዙ ሰዎች ስለዮሀንስ ራዕይ መጽሐፍ ጥያቄዎች ነበሯቸው። እናም ጆሴፍ ጠንቅቆ እንደሚያውቀው፣ ጥበብ ቢጎድለው፣ እግዚአብሔርን መጠየቅ ይችላል። ያገኛቸው ግንዛቤዎች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77፥41 ውስጥ ይገኛሉ። ይህን ክፍል ስታነቡ፣ በዮሀንስ ራዕይ መጽሐፍ ውስጥ በሚገኙት ተያያዥ ምዕራፎች ውስጥ የምታገኟቸውን ግንዛቤዎች መመዝገብን አስቡ። ከጥናታችሁ ራዕይን ስለመቀበል ምን ትማራላችሁ?

ጆሴፍ ስሚዝ እና ስድኒ ሪግደን መጽሐፍ ቅዱስ እያነበቡ

የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም በሊዝ ሌሞን ስዊንድል

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78

የትብብር ድርጅቱ ምን ነበር?

የትብብር ድርጅቱ በኦሃዮ እና በሚዙሪ ውስጥ የቤተክርስቲያኗን የህትመት እና የንግድ ጉዳዮች ለማስተዳደር የተቋቋመ ነበር። ይህም በማደግ ላይ ያለችውን ቤተክርስቲያን ሥጋዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ሀብቶቻቸውን ያዋሃዱትን ጆሴፍ ስሚዝን፣ ኑዌል ኬ. ውትኒን እና ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎችን ያካትታል። እንዳለመታደል ሆኖ፣ የትብብር ድርጅቱ እዳ ውስጥ ገባ እናም እዳው ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑም በ1834 (እ.አ.አ) ፈረሰ።

በተጨማሪም “Newel K. Whitney and the United Firm ፣” Revelations in Context፣ 142–47፤ Church History Topics፣ “United Firm (‘United Order’)፣” የወንጌል ላይብረሪ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥1–7

የክርስቶስን እና የእርሱን ቤተክርስቲያን “ምክንያት ወደፊት ለመግፋት” መርዳት እችላለሁ።

ጌታ፣ ጎተራውን እና ማተሚያ ቤቱን ማስተዳደር “ራሳችሁ የተቀበላችሁትን ምክንያት ወደፊት ለመግፋት” ይረዳል ሲል ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ነገራቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥4)። የአዳኙ ቤተክርስቲያን “ምክንያት“ ምንድን ነው ትላላችሁ? ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥1–7ን ስታነቡ ይህንን አሰላስሉ። በቤተሰባችሁ ውስጥ ጨምሮ ያንን ምክንያት ወደፊት በመግፋት ልትረዱ የምትችሉባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

በተጨማሪም አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ1.2ን ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥17–18

ጌታ ይመራኛል።

ጌታ ተከታዮቹን አንዳንድ ጊዜ “ትንሽ ልጆች“ ብሎ የሚጠራው ለምን ይመስላችኋል? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥17)። ምናልባት “ገና ያልተረዳችሁት” ወይም “መሸከም ያልቻላችሁ“ (ቁጥር 17–18) አንድ ነገር በመኖሩ ሣቢያ ትንሽ ልጅ የሆናችሁ ያህል የተሰማችሁ መቼ ነው? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንዲህ ባሉ ጊዜያት “እንድትደሰቱ“ (ቁጥር 18) የሚረዳችሁን ምን ታገኛላችሁ? የልጅነት ፎቷችሁን መፈለግን አስቡ እንዲሁም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በመንፈሳዊ እንዴት እንዳደጋችሁ አሰላስሉ። ወይም በልጅነታችሁ ከባድ የነበረ ነገር፣ ግን አሁን ቀላል የሆነን ነገር አስቡ። የሰማይ አባት አሁንም እንደ ልጅ እንድትሆኑ የሚፈልገው በምን በምን መንገዶች ነው? (ሞዛያ 3፥19 ተመልከቱ)። እርሱ “እየመራችሁ” ያለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥19

የሴሚናሪ ምልክት
ሁሉንም ነገሮች በአመስጋኝነት መቀበል እችላለሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥19ን ለማጥናት ለመዘጋጀት፣ ዛሬ ያጋጠሟችሁን መልካም ነገሮች ዝርዝር ማዘጋጀት ትችላላችሁ። ከዚያ ለእናንተ በእርግጥ በረከት የማይመስሉ ነገሮችን ዝርዝር አዘጋጁ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥19ን ስታነቡ እነዚህን ዝርዝሮች አሰላስሉ። “ሁሉንም ነገር”፣ በረከት የማይመስሉ ነገሮችን እንኳን፣ በአመስጋኝነት ብትቀበሉ በህይወታችሁ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?

ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ በህይወታችሁ ላይ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖ የበለጠ ለማወቅ፣ እነዚህን የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶች መርምራችሁ የምታገኟቸውን እውነቶች ዝርዝር አዘጋጁ፦ መዝሙር 107፥8–9ሉቃስ 17፥11–19ፊልጵስዩስ 4፥6–7ሞዛያ 2፥19–24አልማ 34፥3837፥37ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥3259፥7፣ 15–21

አመስጋኝ ስለመሆን ምክሮችን ለማግኘት፣ በፕሬዚዳንት ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ “በማንኛውም ሁኔታ አመስጋኝ፣” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 70–77) መልዕክት ውስጥ መፈለግን አስቡ። በ“President Russell M. Nelson on the Healing Power of Gratitude” (ወንጌል ላይብረሪ) ቪዲዮ ላይ ተመሳሳይ ምክርን መፈለግ ትችላላችሁ። ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባላችሁ ግንኙነት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?

11:38

President Russell M. Nelson on the Healing Power of Gratitude​

መርምሩ እና አካፍሉ። እንድታስተምሩ ከተመደባችሁ፣ ሰዎች በግላቸው ወይም በትናንሽ ቡድኖች ሆነው ቅዱሳት መጻህፍትን ወይም የነቢያትን ቃል እንዲመረምሩ እና የተማሩትንም እንዲያካፍሉ መርዳት የምትችሉባቸውን መንገዶች ፈልጉ። ለምሳሌ፣ በዚህ አክቲቪቲ ውስጥ ለእያንዳንዱ ግለሰብ ወይም ቡድን የፕሬዚዳንት ኡክዶርፍ መልዕክትን አንድ ክፍል መስጠትና እርሳቸው ያስተማሩትን አሳጥሮ እንደሚገልፅ የሚሰማቸውን አንድ ሀረግ ወይም ዓረፍተ ነገር እንዲያካፍሉ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ።

በተጨማሪም፣ “Count Your Blessings፣” መዝሙር፣ ቁጥር 241፤ Topics and Questions፣ “Gratitude፣” የወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 79–80

ከማገለግልበት ቦታ ይልቅ እግዚአብሔርን ለማገልገል የተሰጠኝ ጥሪ ይበልጥ ትርጉም ያለው ነው።

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 80ን አስመልክተው እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፣ “ምናልባትም አዳኙ በዚህ ራዕይ ውስጥ እያስተማረን ያለው አንድ ትምህርት፣ በአንድ የተወሰነ ቦታ ላይ ተመድቦ ማገልገል አስፈላጊ እና ጠቃሚ ቢሆንም ለሥራው ከመጠራት ቀጥሎ የሚመጣ ነገር ነው” (“ለስራው መጠራት፣” ሊያሆና ግንቦት ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 68)። የሽማግሌ ቤድናር ቃላት እውነት እንደሆኑ እንድትማሩ ምን ልምዶች ረድተዋችኋል? በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 79–80 ውስጥ አንድ አዲስ ጥሪ የተቀበለን ሰው ሊረዳ የሚችል ምን ተጨማሪ ትምህርቶችን ልታገኙ ትችላላችሁ?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የሊያሆና እና የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሄቶች ዕትሞችን ተመልከቱ።

የልጆች ክፍል ምልክት 03

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77፥2

እግዚአብሔር በምድር ላይ ያለውን ፍጥረት ሁሉ ፈጠረ።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77፥2ን አብራችሁ ስታነቡ፣ ነፍሳትንና ወፎችን ጨምሮ የእንስሳትን ሥዕሎች ልትመለከቱ ትችላላችሁ። እናንተ “አውሬዎች፣” “የሚሳቡ ነገሮች” እና “የሰማይ ወፎች” የሚሉትን ቃላት ስታነቡ ልጆቻችሁ ወደ ሥዕሎቹ ሊጠቁሙ ይችላሉ። የእግዚአብሔር ፍጥረታት፣ የእርሱ ፍቅር እንዲሰማችሁ እንዴት እንደሚረዷችሁ አንዳችሁ ለሌላችሁ አካፍሉ።

ቢራቢሮ

እግዚአብሔር በምድር ላይ ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ ፈጠረ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥4

የኢየሱስ ክርስቶስን “ምክንያት ወደፊት ለመግፋት” መርዳት እችላለሁ።

  • ልጆቻችሁ በጌታ ሥራ ውስጥ ስላሏቸው ሚናዎች እንዲያስቡ ለመርዳት፣ በተጠመቅንበት ጊዜ “የተቀበልነውን” (የተቀበልነውን ወይም ልንደግፈው የመረጥነውን) “ምክንያት” ለመለየት ከእነርሱ ጋር ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥4ን ማንበብን አስቡ። ሊሆኑ የሚችሉ መልሶችን ለማግኘት እንደነዚህ ባሉት የቅዱሳት መጻህፍት ምንባቦች ውስጥ እንዲመለከቱ እርዷቸው፦ ሞዛያ 18፥8–10ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37ሙሴ 1፥39። ልጆቻችሁ በጌታ ሥራ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ የሚያሣይ ትወና በመተውን ሊደሰቱ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ “አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸክም መሸከም” ወይም “የኢየሱስ ክርስቶስን ስም [በላያችን] ላይ መውሰድ” ማለት ምን ማለት ነው? ይህ የኢየሱስ ክርስቶስን “ምክንያት ወደፊት [የሚገፋው]” እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥6

ያለኝን ለሌሎች ለማካፈል እችላለሁ።

  • “በምድራዊ ነገሮች እኩል” መሆን (ቁጥር 6) ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማስተማር፣ የተቸገሩ ሰዎችን ምስሎች (የተራቡ፣ የተጎዱ፣ ወይም የበረዳቸው) እና ለዚያ የሚረዱ (እንደ ምግብ፣ የቁሥል ማሰሪያ ወይም ብርድ ልብስ) ያሉ ነገሮችን ለልጆቻችሁ ልትሰጧቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ልጆቻችሁ ሥዕሎቹን ከተጠቀሱት ነገሮች ጋር ማዛመድ ይችላሉ። የተቸገሩ ሰዎችን ለመርዳት ምን ማካፈል እንችላለን?

  • ክፍል 78ን የተወሰነ አውድ ለማግኘት በ“Chapter 28፦ The Prophet Joseph Goes to Missouri Again” ውስጥ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሥዕሎች ስር ያሉትን ዓረፍተ ነገሮች ከልጆቻችሁ ጋር አንብቡ (በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች፣ 108፣ ወይም ተዛማጅ ቪዲዮውን በወንጌል ላይብረሪ) ውስጥ ተመልከቱ። ከዚያም ልጆቻችሁ አንድን ግለሠብ ቤት በመገንባት፣ ምግብ በማካፈል ወይም በሌላ መንገድ እያገለገሉ እንደሆነ ሊያስመስሉ ይችላሉ።

    2:39

    Chapter 28: The Prophet Joseph Goes to Missouri Again: March–May 1832

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥18

ኢየሱስ ክርስቶስ ይመራኛል።

  • ልጆቻችሁ መሪ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ መናገር ከዚያም አንድን አክቲቪቲ መምራት ሊያስደስታቸው ይችላል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥18 አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ ኢየሱስ እንዲመራን ስለምንፈልግበት ጊዜ ልትወያዩ ትችላላችሁ። “I Will Walk with Jesus” (የወንጌል ላይብረሪ) ያለ መዝሙር መዘመርን አስቡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥19

“ሁሉንም ነገሮች በአመስጋኝነት” መቀበል እችላለሁ።

  • ጌታ አመስጋኝ ለሆኑ ሰዎች ስለገባቸው ቃል ኪዳኖች ለማወቅ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥19ን ከልጆቻችሁ ጋር አንብቡ። ልጆቻችሁ “መቶ እጥፍ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲገነዘቡ፤ ምናልባትም አንድን ትንሽ ነገር እና የዚያን ተመሳሳይ 100 ነገሮች በማሳየት እርዷቸው። ምናልባት “በአመስጋኝነት” ከእግዚአብሔር የተቀበሏቸውን ነገሮች ምስሎች ሊስሉ ይችላሉ።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር የጓደኛ መጽሄት ዕትም ይመልከቱ።

እንስሳት ያሉበት የአትክልት ስፍራ

የእግዚአብሔር የአትክልት ስፍራ፣፣ በሳም ሎውሎር

የመሳተፊያ ገጽ ለልጆች