“ሰኔ 16–22፦ ‘ጌታ ልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ ይሻል’፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64–66፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2025 (እ.አ.አ) [2025 (እ.አ.አ)]
“ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64–66፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2025 (እ.አ.አ)
ሰኔ 16–22፦ “ጌታ ልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ ይሻል”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64–66
በጣም ሞቃት በሆነው በነሀሴ 1831 (እ.አ.አ)፣ ጌታ እንዳዘዘው በሚዙሪ ከነበረው የፅዮን የመሬት ይዞታ ብዙ ሽማግሌዎች ወደ ከርትላንድ በመመለስ ላይ ነበሩ። ተጓዦቹም፣ በሙቀት ቀልጠውና ድካም አዝሏቸው ነበር፣ ከዚያም ውጥረቶች ብዙም ሳይቆይ ወደ ጠብ ተቀየሩ። የፍቅር፣ የአንድነት እና የሰላም ከተማ የሆነችውን ፅዮንን መገንባት ረዥም ጊዜ የሚወስድ ሳይመስል አልቀረም።
እንደ እድል ሆኖም—በ1831 (እ.አ.አ) ሚዙሪ ውስጥ ወይም ዛሬ በልቦቻችን፣ በቤተሰቦቻችችን እና በአጥቢያዎቻችን ውስጥ—ፅዮንን መገንባት ፍጹም መሆንን አይጠይቅብንም። ከዚያ ይልቅ “እናንተ ለሁሉም ሰዎች ይቅርታን ታደርጉ ዘንድ ይጠበቅባችኋል” ብሏል ጌታ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥10)። እርሱ “ልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ” ይሻል (ቁጥር 34)። ፅዮን የምትገነባው “በትንንሽ ነገሮች” መሠረትነት “በመልካም [ሥራ … በማይታከቱ]” ሰዎች በመሆኑ ምክንያት እርሱ ትዕግስት እና ትጋት እንዲኖር ይጠብቃል (ክፍል 33)።
በተጨማሪም Saints፣ 1፥133–34፣ 136–37ን ተመልከቱ።
በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች
“እርስ በርሳችሁ [ይቅር ተባባሉ]።”
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥1–11ን ስታነቡ የሚከተለውን አስቡ።
-
ጌታ ይቅር ብሏችሁ የነበረበትን ጊዜ አስቡ። እንዴት ነበር የተሰማችሁ?
-
ይቅር ልትሉት የሚያስፈልጋችሁ ሰው አለ? ሌሎችን ይቅር ማለት በጣም አስቸጋሪ ሊሆን የሚችለው ለምንድን ነው? እነዚህን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ማሸነፍ የምትችሉት እንዴት ነው?
-
በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥1–11 ውስጥ ስለ ይቅርታ የትኞቹ እውነቶች ለእናንተ ጠቃሚ ይመስሏችኋል? ጌታ “ሁሉንም ይቅር [እንድንል]” ያዘዘን ለምን ይመስላችኋል? (ቁጥር 10)።
ይቅር ማለትን አስቸጋሪ ሆኖ ካገኛችሁት የሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድን መልዕክት “The Ministry of Reconciliation” (ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 77–79) ወይም የክርስቲን ኤም. ዪን መልዕክት “Beauty for Ashes: The Healing Path of Forgiveness” (ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 36–38) ማጥናትን አስቡ። ክርስቶስ ይቅር እንድትሉ እናንተን ስለሚረዳበት መንገድ ምን ትማራላችሁ?
የቤተሰብ ግንኘነቶች ይቅር ለማለት ብዙ አጋጣሚዎችን ሊፈጥሩ ይችላሉ። ስለቤተሰባችሁ አባላት አስቡ። ማንን ይቅር ልትሉ ያስፈልጋችኋል? እርስ በርሳችን ይቅር በማንባባልበት ጊዜ “[የምንሰቃየው]” (ቁጥር 8) እንዴት ነው? ይቅርታ ከቤተሰባችሁ ጋር ያላችሁን ግንኙነት የሚነካው እንዴት ነው?
በተጨማሪም Topics and Questions፣ “Forgiveness፣” የወንጌል ላይብረሪ፤ “Forgiveness: My Burden Was Made Light” (ቪዲዮ)፣ ወንጌል ላይብረሪ ተመልከቱ።
ጌታ የእኔን “ልብ እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ” ይጠይቀኛል።
“መልካም ስራ” ልታከናውኑ በምትሞክሩበት ጊዜ “ድካም” ተሰምቷችሁ ያውቃልን? ጌታ ለእናንተ ያለውን መልዕክት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥31– 34 ውስጥ ፈልጉ። ጌታ የእርሱን “ታላቅ ስራ” ትሠሩ ዘንድ ምን እንድታደርጉ ይፈልጋል?
ቁጥር 33ን የሚያብራሩ እንደ ሞዛይክ ወይም የብሎኬት ህንፃ ያሉ ከትናንሽ ነገሮች የተሠሩ ትልቅ ነገሮችን የሚገልጹ ተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮችን አስቡ። ለእግዚአብሔር ታላቅ ሥራ “መሠረት ለመጣል” በእያንዳንዱ ቀን ምን “ትናንሽ ነገሮችን” ማድረግ ትችላላችሁ? ጌታ የሰጣችሁ “ታላቅ ሥራ” አንዳንድ ምሳሌዎች ምን ምን ናቸው?
“ልብ እና መልካም ፈቃድ ያለው አዕምሮ”
ሽማግሌ ዶናልድ ኤል. ሃልስትረም “ልብ እና መልካም ፈቃድ ያለው አዕምሮ” ለሚለው ሐረግ ይህንን ሊሆን የሚችል ትርጉም ጠቁመዋል፦
“ልብ የፍቅር እና የመስዋዕትነት ምልክት ነው። በሌላ በምንም ምክንያት በፅናት የማናደርገውን ለምንወዳቸው ሰዎች ስንል መስዋዕትነት እንከፍላለን እንዲሁም ሸክሞችን እንሸከማለን። ፍቅር ከሌለ ቁርጠኝነታችን ይቀንሳል። …
“‘ፈቃደኛ አዕምሮ’ መያዝ የተቻለንን ጥረት ማድረጋችንን እና ጥሩ አስተሳሰብ መያዛችንን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ጥበብ መፈለጋችንን ያመለክታል። እጅግ በትጋት የምናደርገው የህይወት ዘመን ጥናታችን ዘለአለማዊ ተፈጥሮ ያላቸው ነገሮች መሆን እንዳለባቸው ይጠቁማል። የእግዚአብሔርን ቃል በመስማትና በመታዘዝ መካከል የማይነጣጠል ግንኙነት ሊኖር ይገባል ማለት ነው” (“The Heart and a Willing Mind፣” ኤንዛይን፣ ሰኔ 2011 (እ.አ.አ)፣ 31–32)።
ፅዮን “ለህዝብ ምልክት” ሆና ትቆማለቸ።
ምልክት ማለት “ሠዎች በዓላማ ወይም በማንነት የሚሰባሰቡበት ሰንደቅ ዓላማ ወይም መሥፈርት” ነው (የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “Ensign፣” ወንጌል ላይብረሪ)። ፅዮን—ወይም የጌታ ቤተክርስቲያን—እንደ ምልክት የሆነችላችሁ እንዴት ነው? ህዝቡን ለመባረክ እንደ ምልክት ወደላይ የሚያዙ እነዚህን ሌሎች ምሳሌዎችን አስቡ፦ ዘኍልቁ 21፥6– 9፤ ማቴዎስ 5፥14–16፤ አልማ 46፥11– 20። ጌታ ፅዮንን የገለጸባቸውን ሌሎች መንገዶች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥41–43 ውስጥ ፈልጉ።
በተጨማሪም፣ “Let Zion in Her Beauty Rise፤” መዝሙር፣ ቁጥር 41 ተመልከቱ።
በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሔር መንግሥት ዓለምን ለአዳኙ መመለሥ ያዘጋጃል።
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65 በኋለኛው ቀን የጌታ ቤተክርስቲያን ስለሚኖራት ተልዕኮ የሚያነሳሳ ገለፃ ይሰጣል። እንደነዚህ ለመሣሠሉ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት በዚህ ክፍል ውስጥ መፈለግን አስቡ፦ ጌታ፣ መንግሥቱ በምድር ላይ ምን እንድታከናውን ይፈልጋል? ለመርዳት ምን እንዳደርግ ይፈልጋል?
በተጨማሪም “Prepare Today for the Second Coming” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።
ጌታ የልቤን ሃሳብ ያውቃል።
የቤተክርስቲያኗ አባል ከሆነ ከአጭር ጊዜ በኋላ፣ ዊሊያም ኢ. መክለለን እግዚአብሔር ለእሱ ያለውን ፈቃድ እንዲገለፅለት ጆሴፍ ስሚዝን ጠየቀው። ጆሴፍ አላወቃቸውም ነበር፣ ነገር ግን ዊልያም እግዚአብሔር በነቢዩ አማካኝነት እንዲመልስለት ተስፋ ያደረገባቸው አምስት የግል ጥያቄዎች ነበሩት። የዊልያም ጥያቄዎች ምን እንደነበሩ አናውቅም፣ ነገር ግን ስለእርሱ የመጣው አሁን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 66 የሆነው ራዕይ እያንዳንዱን ጥያቄ ለዊልያም “በሙሉ እና በሚያረካው መልኩ” መለስ እንደሰጠ እናውቃለን (“William McLellin’s Five Questions፣” በ Revelations in Context፣ 138)።
ክፍል 66ን ስታነቡ፣ ጌታ ስለ ዊልያም መክለለን እና ስላሳሰበውና በልቡ ስለያዘው አላማው ምን እንደሚያውቅ አስቡ። ጌታ እንደሚያውቃችሁ ያሳያችሁ እንዴት ነዉ? የፓትርያርክ በረከቶችን ተቀብላችሁ ከሆነ፣ እርሱን ማጥናትን አስቡ። ያንን ስታደርጉ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ስላለው አላማ መንፈስ ቅዱስ ምን እንድትገነዘቡ ረዳችሁ?
ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች
ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ይቅር እንድል ይፈልጋል።
ማስታወሻ፦ “ሁሉንም ይቅር [በሉ]” የሚለውን የጌታ ትዕዛዝ ለልጆቻችሁ ስታስተምሩ ይቅር ማለት ሰዎች እንዲጎዱን መፍቀድ ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ማድረግ ትፈልጉ ይሆናል። አንድ ሰው ቢጎዳቸው ወይም ተገቢ ባልሆነ መንገድ ቢነካቸው እምነት ለሚጥሉበት አዋቂ ሠው እንዲናገሩ አበረታቷቸው።
-
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥10ን ከልጆቻችሁ ጋር ካነበባችሁ በኋላ፣ አንድን ሰው ይቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከእነርሱ ጋር ተነጋገሩ። ጥቂት ቀላል ምሳሌዎችን ማጋራት ትችሉ ይሆናል። ምናልባት ይቅር ማለትን ለመለማመድ እነዚህን ምሳሌዎች በትወና መልክ ሊያቀርቡ ይችላሉ።
-
ልጆቻችሁ—ለምሳሌ ታናሽ ወንድም ወይም እህት ሊሆን ይችላል—ሌሎችን ይቅር ስለማለት አንድን ሰው እንዴት እንደሚያስተምሩ እንዲያቅዱ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። በሚያስተምሩበት ጊዜ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው ሀረጎችን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥7–10 ውስጥ እንዲፈልጉ እርዷቸው።
-
እንደ “Help Me, Dear Father፣” (የልጆች መዝሙር መፅሐፍ 99) ያለ ስለይቅርታ የሚናገር መዝሙር ዘምሩ። ይህ መዝሙር ሌሎችን ይቅር ስለማለት ምን ያስተምረናል?
የእግዚአብሔር “ታላቅ ሥራ” “በትትንሽ ነገሮች” ይገነባል።
-
እንደመገጣጠም ጨዋታ ወይም እንደምንጣፍ ያሉ ከትናንሽ ክፍሎች የተሰሩ አንዳንድ ነገሮችን ለልጆቻችሁ ማሳየት ትችላላችሁ። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥33ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። የእግዚአብሔር “ታላቅ ሥራ” ምንድን ነው? ልናደርጋቸው የምንችላቸው የሚረዱ “ትትንሽ ነገሮች” ምን ምን ናቸው?
ኢየሱስ ክርስቶስን በልቤ እና በአዕምሮዬ መከተል እችላለሁ።
-
ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥33 ለልጆቻችሁ ስታነቡ፣ “ልብ” እና “አዕምሮ” የሚለውን በምታነቡበት ጊዜ ወደ ልባችሁ እና ወደ እራሳችሁ ልትጠቁሙ፣ እንዲሁም ልጆቹም ከእናንተ ጋር እንዲሁ እንዲያደርጉት ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። ልቦቻችንን (ፍላጎቶቻችንን) እና አዕምሮአችንን (ሀሳቦቻችንን) ለአዳኙ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው?
ጌታ ማን እንደሆንኩኝ ያውቃል እንዲሁም ይወደኛል።
-
ዊልያም ኢ. መክለለን ለጌታ አምስት ጥያቄዎች እንደነበሩት ልጆቻችሁ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። የዊልያም ጥያቄዎች ምን እንደነበሩ የማያውቅ የነበረ ቢሆንም፣ ጆሴፍ ስሚዝ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ተቀብሏል። ጌታ እንድታደርጉ የሚፈልገውን ነገር ስላሳያችሁ ጊዜ ለልጆቻችሁ ንገሯቸው እንዲሁም የእርሱን መመሪያ በመከተላችሁ ስተቀበላችኋቸው በረከቶች ተናገሩ። ከዚያም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 66፥4ን አብራችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ እንዲሁም ጌታ እንዲያደርጉ የሚፈልገውን ለመገንዘብ እድሎችን እንዲፈልጉ ልጆቻችሁን ጋብዟቸው። ።
ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲቀበል ልረዳ እችላለሁ።
-
ልጆቻችሁ የአዳኙን የዳግም ምጽዓት ምስል ሲመለከቱ ምን እንደሚያዩ ወይም ስለዚህ ክስተት ምን እንደሚያውቁ እንዲገልጹ ጠይቋቸው። በትምህርትና ቃል ኪዳኖች 65 ውስጥ ስለዳግም ምጽዓት እንዲፈልጉ ቃላትን እና ሀረጎችን ለልጆቻችሁ ልትሰጧቸውም ትችላላችሁ። እነዚህ ቃላት እና ሃረጎች ምን ያስተምሩናል? ለአዳኙ ዳግም መመለሥ መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?