አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 3–9 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 1–5፦ “ምስክሮቼ ትሆናላችሁ”


“ሐምሌ 3–9 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 1–5፦ ‘ምስክሮቼ ትሆናላችሁ’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ሐምሌ 3–9 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 1–5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ብዙ ሰዎች በወንዝ ዳርቻ ላይ እና በወንዝ ውስጥ እየተጠመቁ

በዓለ ኀምሳ ቀን፣ በሲድኒ ኪንግ

ሐምሌ 3–9 (እ.አ.አ)

የሐዋሪያት ስራ 1–5

“ምስክሮቼ ትሆናላችሁ”

የሐዋርያት ስራ 1–5ን በምታጠኑበት ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ለሕይወታችሁ የሚስማማውን እውነት እንድታገኙ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። የሚያስደንቋችሁን ጥቅሶች ልብ በሉ፣ እና የተማራችሁትን ለማካፈል እድሎችን ፈልጉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ኢየሱስ ወደ አባቱ ሲያርግ ጴጥሮስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ወደ ሰማይ “ትኵር [ብሎ ሲመለከት]” ምን እንደሚያስብ እና ምን እየተሰማው እንደሆነ አስባችሁ ታውቃላችሁ? የሐዋሪያት ስራ 1፥10። በእግዚአብሔር ልጅ የተመሠረተችው ቤተክርስቲያን አሁን በጴጥሮስ እንክብካቤ ውስጥ ሆነች። “አሕዛብን ሁሉ … [የማስተማር]” (ማቴዎስ 28፥19) ጥረትን የመምራት ተግባር አሁን በእሱ ላይ አረፈ። ነገር ግን እሱ በቂ እንዳልሆነ ወይም የፍርሃት ስሜት እንደተሰማው በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ምንም ማስረጃ የለም። እኛ የምናገኘው በድፍረት የመመስከር እና የመለወጥ፣ የተአምራዊ ፈውሶች፣ መንፈሳዊ መገለጫዎች፣ እና የቤተክርስቲያን ጉልህ እድገት ምሳሌዎችን ነው። ይህ አሁንም በአዳኙ የሚመራ የእርሱ ቤተክርስቲያን ነበር። በእርግጥ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በሐዋርያቱ በኩል የኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ተብሎ ሊጠራ ይችላል። ከዚያን በኋላ በመንፈስ ፍሰት በመመራት፣ ጴጥሮስ በገሊላ ባሕር ዳርቻ ኢየሱስ ያገኘው ያልተማረ ዓሣ አጥማጅ አልነበረም። ወይም ከሳምንታት በፊት የናዝሬቱን ኢየሱስን አላውቀውም ብሎ በመካዱ መራራ ለቅሶ አልቅሶ የነበረ የተረበሸ ሰውም አልነበረም።

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ወንጌሉ ኃይለኛ መግለጫዎችን ታነባላችሁ። እንዲሁም ያ ወንጌል ሰዎች—እናንተንም ጨምሮ—እግዚአብሔር መሆን እንደሚችሉ ወደሚያውቀው ደቀ መዛሙርትነት እንዴት እንደሚለውጥ ታያላችሁ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

የሐዋርያት ስራ 1፥1–8፣ 15–262፥1–424፥1–13፣ 31–33

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ይመራል።

የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ከአዳኙ ዕርገት በኋላ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለማቋቋም የሐዋርያትን ጥረት ይዟል። ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ባይኖርም፣ ቤተክርስቲያንን በመንፈስ ቅዱስ በኩል በመገለጥ መርቷል። የሚከተሉትን ምንባቦች ስትገመግሙ መንፈስ ቅዱስ አዲሶቹን የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሪዎችን እንዴት እንደመራቸው አስቡ የሐዋርያት ስራ 1፥1–8፣ 15–262፥1–424፥1–13፣ 31–33

ዛሬ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት እንደመሆናችን መጠን፣ እያንዳንዳችን በመዳን እና ከፍ በማድረግ ሥራ የመሳተፍ ሀላፊነት አለብን—የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የመኖር፣ የተቸገሩትን የመንከባከብ፣ ሌሎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ የመጋበዝ፣ እና ቤተሰቦችን ለዘለአለም የማዋሃድ (አጠቃላይ የእጅ መጽሐፍ፣ 1.2ን ተመልከቱ)። ጥረቶቻችሁን ለመምራት በመንፈስ ቅዱስ እንዴት መታመን እንደምትችሉ ከነዚህ ቀደምት ሐዋርያት ምን ትማራላችሁ?

በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “መንፈስ ቅዱስን” ተመልከቱ።

የሐዋርያት ስራ 2፥36–473፥12–21

የወንጌል መርሆዎች እና ሥርዓቶች ወደ ክርስቶስ እንድመጣ ይረዱኛል።

በበዓለ ሃምሳ ቀን እንደ አይሁዶች “[ልባችሁ ተነክቶ]” ያውቃል? (የሐዋሪያት ስራ 2፥37)። ምናልባት እናንተ የሚጸጽታችሁን አንድ ነገር አድርጋችኋል ወይም እንዲሁ ሕይወታችሁን መለወጥ ትፈልጉ ይሆናል። እነዚህ ስሜቶች ሲኖራችሁ ምን ማድረግ ይጠበቅባችኋል? ጴጥሮስ ለአይሁድ የሰጠው ምክር የሐዋርያት ስራ 2፥38፣ ላይ ይገኛል። የሐዋርያት ስራ 2፥37–47፣ ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው የመጀመሪያዎቹ የወንጌል መርሆዎች እና ሥርዓቶች (እምነት፣ ንስሐ፣ ጥምቀት፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ—ወይም አንዳንድ ጊዜ የክርስቶስ ትምህርት ተብለው የሚጠሩትን) በእነዚህ አማኞች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንዳሳደሩ ልብ በሉ።

አስቀድማችሁ ተጠምቃችሁ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብላችሁ ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህ የክርስቶስን ትምህርት መተግበር እንዴት ትቀጥላላችሁ? የሽማግሌ ዴል ጂ. ረንለንድ እነዚህን ቃላት አስቡ፤ “በተደጋጋሚ በክርስቶ እምነትን በመለማመድ፣ ንስሀ በመግባት፣ ቃል ኪዳኖችን እና የጥምቀት በረከቶችን ለማሳደስ ቅዱስ ቁርባንን በመውሰድ፣ እና መንፈስ ቅዱስን ሁሌ እንደሚገኝ ጓደኛ በመቀበል … ፍጹም መሆን እንችላለን። ይህን ስናደርግ፣ እንደ ክርስቶስ እንሆናለን እና ከሚከተለው ሁሉ ጋር እስከመጨረሻው መጽናት እንችላለን” (“የኋላኛው ቀን ቅዱሳን ጥረታችሁን ቀጥሉ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ) 56)።

የሐዋርያት ስራ 3፥19–21

“የመጽናናት ዘመን” እና “ነገር ሁሉ [የሚታደስበት] ዘመን” ምንድናቸው?

“የመጽናናት ዘመን” የሚያመለክተው ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የሚመለስበትን ሺህ ዓመት ነው። “ነገር ሁሉ [የሚታደስበት] ዘመን” የሚያመለክተው ዓለምን ለሚሊኒየም የሚያዘጋጀውን የወንጌልን ዳግም መቋቋምን ነው።

የሐዋርያት ስራ 34፥1–315፥12–42

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በስሙ ተአምራትን የማድረግ ኃይል ተሰጥቷቸዋል።

አንካሳው ሰው ወደ ቤተመቅደስ ከሚመጡ ሰዎች ገንዘብ ለመቀበል ተስፋ አድርጎ ነበር። የጌታ አገልጋዮች ግን ከዚያ የበለጠ ብዙ ሰጡት። የሐዋርያት ስራ 34፥1–31 እና 5፥12–42ን ስታነቡ የተከተለው ተአምር እነዚህን ሰዎች እንዴት እንደነካ አስቡ።

  • አንካሳው ሰው

  • ጴጥሮስ እና ዮሐንስ

  • በቤተ መቅደሱ ውስጥ ምስክሮችን

  • ሊቀ ካህናትና ገዢዎች

  • ሌሎች ቅዱሳን

ጴጥሮስ አንድን ሰው እየፈወሰ

ይህን ያለኝን እሰጥሃለሁ፣ በዋልተር ሬን

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

የሐዋርያት ስራ 1፥21–26 የሐዋርያት ስራ 1፥21–26 ን ማንበብ ቤተሰባችሁ ዛሬ በምድር ላይ ሐዋርያትን በመኖራቸው የሚገኘውን በረከቶች እንዲወያዩ ሊረዳቸው ይችላል። የአሁን ጊዜ ሐዋርያት እና ነቢያት በእግዚአብሔር እንደተጠሩ ምስክርነት እንዴት እንዳገኙ የቤተሰብ አባላት ማጋራት ይችላሉ። ይህ ምስክርነት ለምን አስፈላጊ ነው?

የሐዋሪያት ስራ 2፥37“ልባቸው ተነካ” የሚለው ሐረግ ምን ማለት ሊሆን ይችላል? ከዚህ ጋር የሚመሳሰል ነገር መቼ ተሰምቷችሁ ያውቃል? እንደዚህ ዓይነት ስሜቶች ሲኖሩን “ምን እናድርግ?” ማለት አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው?

የሐዋርያት ስራ 3፥1–10በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያለውን ታሪክ ቤተሰባችሁ በመተወን ሊደሰት ይችላል። ወይም “ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ከተወለደ ጀምሮ የአካል ጉዳተኛ የሆነውን ሰው ፈውሱ” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪዲዮ ማየት ይችላል። በቤተመቅደስ ውስጥ የነበረው ሰው ከጠበቀው በተለየ እንዴት ተባረከ? የሰማይ አባት በረከቶች ወደ እኛ ባልታሰበ መንገድ ሲመጡ እንዴት አየን?

የሐዋርያት ስራ 3፥12–264፥1–215፥12–42ስለ ጴጥሮስ እና በዮሐንስ ታማኝነት ምን ያስደንቃችኋል? (በተጨማሪም ChurchofJesusChrist.org) ላይ “ጴጥሮስ ሰበከ እናም ታሰረ” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከቱ)። በኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነቶቻችን ላይ እንዴት ደፋር መሆን እንችላለን? ትናንሽ ልጆች ምስክርነቶቻቸውን ማካፈል እንዲለማመዱ መርዳትን አስቡ።

የሐዋሪያት ስራ 4፥315፥4ቤተሰባችን፣ ቅርንጫፋችን ወይም ማህበረሰባችን በየሐዋርያት ስራ 4፥31–37፣ እንደተገለጸው ይበልጥ እንዲሆኑ እንዴት መርዳት እንችላለን? “አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ” መሆን ማለት ምን ማለት ነው? የእኛን አስተዋፅዖ አንዳንድ ጊዜ “[የምናስቀረው]” በምን አይነት መንገዶች ነው? ያንን ማድረግ “እግዚአብሔርን መዋሸት” የሚሆነው ለምንድነው? (የሐዋርያት ስራ 5፥2፣4)። አለመታመን መንፈሳዊነታችንን እንዴት ነው የሚጎዳው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “መንፈስ ቅዱስ ይምራ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 143።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ርዕሶችን ምረጡ። የቤተሰብ አባላት በአንድነት ለማጥናት ከ የሐዋርያት ስራ 1–5 ተራ በተራ ርዕስ እንዲመርጡ አድርጉ።

ወደ ላይ እያመለከቱ ባሉ ሁለት መላእክት ዙሪያ ያሉ ሐዋርያት

እርገት፣ በሃሪ አንደርሰን