“ሐምሌ 10–16 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 6–9፦ ‘ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) ([2022 (እ.አ.አ)]
“ሐምሌ 10–16 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 6–9፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 10–16 (እ.አ.አ)
የሐዋሪያት ስራ 6-9
“ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?”
የሐዋርያት ስራ 6–9ን በማንበብ ጀምሩ። በዚህ ረቂቅ ውስጥ የቀረቡት ሀሳቦች በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ አንዳንድ አስፈላጊ መርሆዎችን ለመለየት ይረዳሉ፤ ምንም እንኳን በራሳችሁ ጥናት ውስጥ ሌሎችን ብታገኙም።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ለመለወጥ የማይታሰብ እጩ የሚመስል ቢኖር ምናልባት ክርስቲያኖችን በማሳደድ ዝነኛ የነበረው ፈሪሳዊ ሳኦል ሳይሆን አይቀርም። ስለዚህ ጌታ ሐናንያ የሚባል ደቀ መዝሙር ሳኦልን ፈልጎ በረከትን እንዲሰጠው ሲነግረው ሐናንያ ማመንታቱ አልቀረም። “ጌታ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቼአለሁ“ (የሐዋርያት ስራ 9፥13) አለ። ነገር ግን ጌታ የሳኦልን ልብ እና አቅሙን ያውቅ ነበር፣ ለሳኦል የታሰበ ተልእኮ ነበረው፤ ”ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ” (የሐዋርያት ስራ 9፥15)። ስለዚህ ሐናንያ ታዘዘ፣ ይህን የቀድሞ አሳዳጅ ሲያገኝ “ወንድም ሳኦል” (የሐዋርያት ስራ 9፥17) ብሎ ጠራው። ሳኦል ሙሉ በሙሉ መለወጥ ከቻለ እና ሐናንያ በነፃነት ከተቀበለው ታዲያ እኛ እራሳችንን ጨምሮ ማንኛውንም የማይታሰብ የለውጥ እጩ አድርገን መቁጠር አለብን?
ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ልቤ “በእግዚአብሔር ፊት የቀና” መሆን አለበት።
እያደገች ያለች ቤተክርስቲያን ማለት ደቀመዛሙርቱ በመንግሥቱ ውስጥ የማገልገል ፍላጎትም ማደግ ማለት ነው። የሐዋርያት ስራ 6፥1–5፣ መሠረት አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አብረዋቸው በሚያገለግሉት ውስጥ ምን አይነት ባሕርያትን ይፈልጉ ነበር? የሐዋርያት ስራ 6–8ን በምታነብበት ጊዜ እነዚህ ባህርያት፣ እና ሌሎች፣ እንደ እስጢፋኖስ እና ፊልጶስ ባሉ ሰዎች ውስጥ እንዴት እንደታዩ ልብ በሉ። ስምዖን ውስጥ የጎደለው ምንድነው፣ ለመለወጥ ፈቃደኛ ስለመሆኑስ ምን እንማራለን?
ልባችሁ “በእግዚአብሔር ፊት የቀና” መሆኑን ለማረጋገጥ መለወጥ እንዳለባችሁ የሚሰማችሁ ነገር አለ? (የሐዋርያት ስራ 8፥21–22)። ይህን ለውጥ ማድረግ እግዚአብሔርን ስታገለግሉ እንዴት ሊባርካችሁ ይችላል?
መንፈስ ቅዱስን መቃወም አዳኙን እና አገልጋዮቹን እንዳንቀበል ሊያደርግ ይችላል።
የአይሁድ መሪዎች ሕዝቡ ለመሲሑ መምጣት የማዘጋጀት ኃላፊነት ነበረባቸው። ሆኖም ግን መሲሑን ማወቅ እንኳን ተስኗቸው እርሱን አልተቀበሉትም። ይህ እንዴት ሆነ? የዚህ መልስ ክፍል በእስጢፋኖስ ቃላት ውስጥ ሊገኝ ይችላል፤ “ሁል ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ” (የሐዋርያት ስራ 7፥51)። መንፈስ ቅዱስን መቃወም ማለት ምን ይመስላችኋል? መንፈስ ቅዱስን መቃወም አዳኙን እና አገልጋዮቹን ወደ አለመቀበል የሚመራው ለምንድነው?
የሐዋርያት ስራ 6–7ን በምታነብበት ጊዜ እስጢፋኖስ ለአይሁዶች ያስተማራቸውን ሌሎች መልእክቶችን ፈልጉ። ስለ የትኞቹን አመለካከቶች አስጠነቀቀ? በራሳችሁ ውስጥ ተመሳሳይ አመለካከቶችን ታገኛላችሁ? መንፈስ ቅዱስን መቃወም ስለሚያስከትለው ውጤት የእስጢፋኖስ ቃላት ምን ያስተምሯችኋል? በሕይወታችሁ ውስጥ ለመንፈስ ቅዱስ ተነሳሽነት ይበልጥ የተጋለጣችሁ እና ምላሽ ሰጪ መሆን የምትችሉት እንዴት ነው?
በተጨማሪ “የእስጢፋኖስ ሰማዕትነት” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።
መንፈስ ቅዱስ ሌሎችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድመራ ይረዳኛል።
በየሐዋርያት ስራ 8፥26–39፣ ላይ ካለው ወንጌልን ስለማካፈል ምን ትማራላችሁ? መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን እንዴት ረዳው? ወንጌልን ለሌሎች ማካፈል እንዴት እንደ መመሪያ ነው? (የሐዋርያት ስራ 8፥31ን ተመልከቱ)።
ሽማግሌ ዮልሲስ ሶሬስ ይህ ዘገባ “ሁላችንም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለመማር እና እርስ በእርስ ለማስተማር መፈለግ ያለብን መለኮታዊ ተልእኮን የሚያስታውስ ነው” ብለዋል። … እኛ አንዳንድ ጊዜ እንደ ኢትዮጵያዊው ነን—የታማኝ እና የተነሳሳ አስተማሪን እርዳታ እንፈልጋለን፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እንደ ፊሊጶስ ነን—ሌሎችን ማስተማር እና ሲለወጡ ማጠንከር አለብን። (“እንዴት ልረዳ እችላለሁ?፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ) 6)። የቀረውን የሽማግሌ ሶዋሬስን መልእክት ማንበብ እና መንፈስ ቅዱስ የተሻለ የወንጌል ተማሪ እና አስተማሪ እንድትሆኑ እንዴት እንደሚረዳ አስቡ።
ለጌታ ፈቃድ ስገዛ፣ በእጆቹ መሣሪያ መሆን እችላለሁ።
የሳኦል መለወጥ በጣም ድንገተኛ ይመስላል፤ ክርስቲያኖችን ከማሰር በፍጥነት በምኩራብ ስለ ክርስቶስ መስበክ ጀመረ። ታሪኩን በምታነቡበት ጊዜ ለመለወጥ እጅግ ፈቃደኛ የሆነበትን ምክንያት አስቡ። (ሳኦል ስለመለወጡ የገለጸውን ለማንበብ የሐዋርያት ስራ 22፥1–16 እና 26፥9–18ን ተመልከቱ። በእንዚህ ቁጥሮች ላይ የሳኦል ስም ጳውሎስ እንደሆነ ልብ በሉ [ የሐዋርያት ስራ 13፥9ን ተመልከቱ]።)
የሳኦል ተሞክሮ ያልተለመደ መሆኑ እውነት ቢሆንም ለአብዛኛው ሰዎች መለወጥ በጣም ረጅም ሂደት ነው—ስለ መለወጥ ከሳኦል የምትማሩት ነገር አለ? ሐናንያ እና ሌሎች ደቀ መዛሙርት ለሳኦል መለወጥ ምላሽ ከሰጡበት መንገድ ምን ትማራላችሁ? እነዚህን ትምህርቶች በሕይወታችሁ ውስጥ ለመተግበር ምን ታደርጋላችሁ? በጸሎት ልክ እንደ ጳውሎስ “ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” ብላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።
የሐዋርያት ስራ 9፥36–42ን በምታነቡበት ጊዜ ጣቢታ በእግዚአብሔር እጅ መሣሪያ እንዴት እንደነበረች አስቡ። ስለ እርሷ ምሳሌነት ምን ያነሳሳችኋል?
በተጨማሪ የዴተር ኤፍ. ኡክዶርፍ “በደማስቆ መንገድ ላይ መጠበቅ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2011 (እ.አ.አ) 70–77፤ “የደማስቆ መንገድ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
የሐዋርያት ስራ 6፥8፤ 7፥51–60።በየሐዋርያት ስራ 6፥8 እና የሐዋርያት ስራ 7፥51–60 ላይ ያለውን የእስጢፋኖስ ቃላትን በሉቃስ 23፥1–46፣ ላይ ካለው የአዳኙ ቃል ጋር አነጻጽሩ። እስጢፋኖስ የአዳኙን ምሳሌ እንዴት ተከተለ?
-
የሐዋሪያት ስራ 7፥51–60።እስጢፋኖስ ሲያሰቃዩት መንፈስ ቅዱስ እንዴት ባረከው? በአስቸጋሪ ጊዜያት ከመንፈስ ቅዱስ ኃይልን የተቀበልነው መቼ ነው?
-
የሐዋሪያት ስራ 9፥5። የመውጊያ ብረት የእንስሳትን መንጋ ለመንዳት የሚያገለግል ሹል ጦር ነው። ብዙውን ጊዜ እንስሳቱ በሚወጉበት ጊዜ ተመልሰው ይረግጡታል፣ ይህም ጦሩ በእንስሳቱ ሥጋ ውስጥ የበለጠ እንዲሰምጥ ያደርጋል። ይህ ምሳሌ አንዳንድ ጊዜ በእኛ ላይ እንዴት ሊሠራ ይችላል? ከጌታ እርማትን በተሻለ ለመቀበል ምን ማድረግ እንችላለን?
-
የሐዋርያት ስራ 9፥32–43።በየሐዋርያት ስራ 9፥32–43፣ ላይ ስላሉ ታሪኮች የቤተሰባችሁ አባላት ሥዕሎችን እንዲስሉ ለመጋበዝ አስቡ። ከእነዚህ ታሪኮች ስለ እውነተኛ ደቀመዝሙርነት ምን እንማራለን? እንደ ጣቢታ ያለ “መልካም ነገር [የሞላበት]” ሰው ሌሎች በጌታ እንዲያምኑ እንዴት ይረዳል? (የሐዋርያት ስራ 9፥36፤ “ምዕራፍ 60፦ ጴጥሮስ ጣቢታን ከሞት አስነሳት” (በአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 156–57፣ ወይም የሚመሳሰል ቪድዮ በChurchofJesusChrist.org፣ ላይ ተመልከቱ)።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።
በሃሳብ የሚቀርቡ መዝሙሮች፦ “አንተ ወደ ፈለግከው እሄዳለሁ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 270።