አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 17–23 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 10–15፦ “የእግዚአብሔር ቃል … ያድግና ይበዛ ነበር”


“ሐምሌ 17–23 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 10–15፦ ‘የእግዚአብሔር ቃል … ያድግና ይበዛ ነበር’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) ([2022 (እ.አ.አ)]

“ሐምሌ 17–23 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 10–15፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ጴጥሮስ ከቆርኔሌዎስ ጋር ሲነጋገር

ሐምሌ 17–23 (እ.አ.አ)

የሐዋሪያት ስራ 10-15

“የእግዚአብሔር ቃል… ያድግና ይበዛ ነበር”

መንፈስ በሐሳቦች እና በስሜቶች እንዲመራችሁ ጊዜ በመፍቀድ የሐዋርያት ስራ 10–15 በጥንቃቄ አንብቡ። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ልትማሩት የምትችሉት ምን አለ?

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

በሥጋዊ አገልግሎቱ ወቅት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የቆዩ የሰዎችን ወጎች እና እምነቶች ይገዳደር ነበር። ወደ ሰማይ ካረገ በኋላም በመገለጥ ቤተክርስቲያኑን መምራቱን ስለቀጠለ ይህ አልቆመም። ለምሳሌ፣ በኢየሱስ ሕይወት ወቅት ደቀ መዛሙርቱ ወንጌልን የሰበኩት ለአይሁድ ወገኖቻቸው ብቻ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ አዳኙ ከሞተ እና ጴጥሮስ በምድር ላይ የቤተክርስቲያን መሪ ከሆነ በኋላ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አይሁድ ላልሆኑ ሰዎች የሚሰበክበት ጊዜ መሆኑን ለጴጥሮስ ገለጸለት። ወንጌልን ለአህዛብ የማካፈል ሀሳብ ዛሬ የሚገርም አይመስልም፣ ስለዚህ በዚህ ታሪክ ውስጥ ለእኛ ያለው ትምህርት ምንድነው? ምናልባት አንዱ ትምህርት በጥንታዊም ሆነ በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ አፍቃሪው አዳኝ የተመረጡ መሪዎቹን እንደሚመራቸው ነው (አሞጽ 3፥7ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 1፥38ን ተመልከቱ)። ቀጣይነት ያለው መገለጥ የእውነተኛ እና ህያው ቤተክርስትያን አስፈላጊ ምልክት ነው። እንደ ጴጥሮስ፣ ቀጣይ የሆነን መገለጥ መቀበል እና “በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ” (ሉቃስ 4፥4) መኖር ያስፈልገናል፤ “የእግዚአብሔርን መንግሥት በተመለከተ … [እርሱ] የገለጣቸውን፣ አሁንም በሚገልጣቸው ሁሉ” እና “ብዙ ታላቅ እና አስፈላጊ ነገሮች” (የእምነት አንቀጽ 1፥9) ጨምሮ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

የሐዋሪያት ስራ 10

“እግዚአብሔር ለሰው ፊት [አያደላም]።”

ለዘመናት አይሁዶች “የአብርሃም ዘር” ወይም በቀጥታ ከአብርሃም የዘር ሃረግ መሆን ማለት አንድ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው እና የተመረጠ ነው ብለው ያምኑ ነበር (ሉቃስ 3፥8ን ተመልከቱ)። ሌላን ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሌለው “ርኩስ” አሕዛብ አድርገው ይቆጥራሉ። በየሐዋርያት ስራ 10፣ ላይ ጌታ “በእርሱ የተወደደ [ስለሆነው]” ጴጥሮስን ምን አስተማረ?(የሐዋሪያት ስራ 10፥35)። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የቆርኔሌዎስ ሕይወት በጌታ ዘንድ ተቀባይነት እንዳገኘ ምን ማስረጃ ታገኛላችሁ? “እግዚአብሔር ለሰው ፊት [አያዳላም]” የሚለው ቃል ምን ማለት እንደሆነ አስቡ (ቁጥር 34፤ በተጨማሪም 1 ኔፊ 17፥35ን ተመልከቱ)። ይህንን እውነት ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?

የአብርሃም ዘር ያልሆኑትን ዝቅ አድርገው እንደሚመለከቱት አይሁዶች፣ ከእናንተ የተለየ ስለሆነ ሰው ደግነት የጎደለው ወይም መረጃ የለሽ ግምቶችን ስታደርጉ ራሳችሁን አግኝታችሁ ታውቃላችሁ? ይህንን ዝንባሌ እንዴት ማሸነፍ ትችላላችሁ? ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ቀላል ጨዋታን መሞከር አስደሳች ሊሆን ይችላል፤ በማንኛውም ጊዜ ከአንድ ሰው ጋር በምትገናኙበት ጊዜ “ይህ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው” ብላችሁ ለራሳችሁ ለማሰብ ሞክሩ። ይህን በምታደርጉበት ጊዜ እናንተ ስለ ሌሎች በምታስቡበት እና ከሌሎች ጋር በምትገናኙበት መንገድ ላይ ምን ለውጦች ታስተውላላችሁ።

በተጨማሪም 1 ሳሙኤል 16፥72 ኔፊ 26፥13፣ 33፤ ረስል ኤም. ኔልሰን “እግዚአብሄር ያሸንፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ) 92–95፤ “ወንጌልን ለአህዛብ ለመውሰድ የጴጥሮስ መገለጥ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ይመልከቱ።

የሐዋርያት ስራ 1011፥1–18፤ 15

የሰማይ አባት በራዕይ በኩል ቀስ በቀስ ያስተምረኛል።

ጴጥሮስ የሐዋርያት ስራ 10፣ ላይ የተገለጸውን ራእይ ባየ ጊዜ፣ በመጀመሪያ ለመረዳት ተቸገረና “ምን ይሆን ብሎ በልቡ [አመነታ]” (ቁጥር 17)። ሆኖም ጴጥሮስ እንደፈለገው ጌታ የበለጠ ግንዛቤን ሰጠው። የሐዋርያት ስራ 1011፣ እና 15ን በምታነብበት ጊዜ፣ ጴጥሮስ ስለ ራእዩ ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ እንደሄደ ልብ በሉ። ጥያቄዎች ሲኖሯችሁ ከእግዚአብሔር የበለጠ ግንዛቤን እንዴት ፈልጋችሁ አገኛችሁ?

የሐዋርያት ስራ 1011፣ እና 15 ጌታ አገልጋዮቹን በራዕይ የመራባቸውን አጋጣሚዎች ይዘረዝራል። እነዚህን ምዕራፎች በምታነቡበት ጊዜ ስለ ራዕይ የተማራችሁትን መመዝገብ ሊረዳ ይችላል። መንፈስ ለእናንተ በምን መንገድ ይናገራል?

የወንጌል ርዕሶች፣ “መገለጥ፣” topics.ChurchofJesusChrist.org፤ ኩዊንተን ኤል ኩክ “ለነቢያት ቀጣይነት ያለው መገለጥ በረከት እና ህይወታችንን ለመምራት ግላዊ መገለጥ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 96–100፤ “የኢየሩሳሌም ጉባኤ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

ከሐዋርያት ስራ 11፥26

በኢየሱስ ክርስቶስ ስለማምን እና ስለምከተለው እኔ ክርስቲያን ነኝ።

አንድ ሰው ክርስቲያን ተብሎ መጠራቱ ምን ትርጉም አለው? (የሐዋርያት ሥራ 11፥26ን ተመልከቱ)። ክርስቲያን በመባል መታወቅ ለእናንተ ምን ማለት ነው? የስሞችን አስፈላጊነት ግምት ውስጥ አስገቡ። ለምሳሌ፣ የቤተሰብ ስም ለእናንተ ምን ማለት ነው? የቤተክርስቲያኗ ስም ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች115፥4ን ተመልከቱ)። የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በራሳችሁ ላይ በቃል ኪዳን መውሰድ ለአንተ ምን ማለት ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77ን ተመልከቱ)።

በተጨማሪም ሞዛያ 5፥7–15አልማ 46፥13–153 ኔፊ 27፥3–8፤ ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “የቤተክርስትያኗ ትክክለኛ ስም፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 87–90ን ተመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

የሐዋርያት ስራ 10፥17፣20መንፈሳዊ ልምዶች አጋጥመውን ኋላ ላይ ግን ምን እንደተሰማን ወይም እንደተማርን ተጠራጥረን እናውቃለን? ጥርጣሬዎቻችንን ለማሸነፍ የሚረዱንን ምን ምክሮች እርስ በእርስ መሰጣጠት እንችላለን? (ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “Spiritually Defining Memories፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 18–22ን ተመልከቱ።)

የሐዋርያት ስራ 10፥34–35“እግዚአብሔር ለሰው ፊት [እንደማያዳላ]” ቤተሰባችሁን እንዴት ማስተማር ትችላላችሁ? (የሐዋሪያት ስራ 10፥34)። ምናልባት ቤተሰባችሁ እነዚህን ጥቅሶች በሚያነብበት ጊዜ ከተለያዩ አስተዳደግ እና ባህሎች የመጡ ሰዎችን ስዕሎች ማሳየት ትችሉ ይሆናል። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉት እውነቶች በድርጊታችን ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይገባል? (ለምሳሌ “ከእናንተ ጋር እራመዳለሁ” [የልጆች የመዝሙር መጻፍ፣ 140–41]ን ተመልከቱ)።

የሐዋርያት ስራ 12፥1–17ጴጥሮስ ወደ እስር ቤት እንደተጣለ እና የቤተክርስቲያኑ አባላት ተሰብስበው ስለ እርሱ ሲጸልዩ የሚናገረውን ታሪክ ቤተሰባችሁ ሊተውን ይችላል። በጸሎት መቼ ተባርከናል? በመንፈስ አነሳሽነት እንድንጸልይለት የተሰማን እንደ የቤተክርስቲያን መሪ ወይም የምንወደው ሰው አለ? “ሳታቋርጡ መጸለይ” ማለት ምን ማለት ነው? (የሐዋርያት ስራ 12፥5፤ በተጨማሪም አልማ 34፥27ን ተመልከቱ)።

ምስል
ጴጥሮስ ከእስር ቤት ነፃ ወጣ

ጴጥሮስ ከእስር ቤት ነፃ ወጣ፣ በኤ ኤል ኖኪያስ

የሐዋርያት ስራ 14ይህን ምዕራፍ አብራችሁ ስታነቡ፣ አንዳንድ የቤተሰብ አባላት ለደቀመዛሙርቱ እና ለቤተክርስቲያኑ የመጡትን በረከቶች ማስታወሻ ሊይዙ ይችላሉ። ሌሎች የቤተሰብ አባላት ደግሞ ደቀ መዛሙርት ያጋጠሟቸውን ተቃውሞ ወይም ፈተናዎች ልብ ሊሉ ይችላሉ። እግዚአብሔር ጻድቃን ሰዎች አስቸጋሪ ነገሮች እንዲደርሱባቸው ለምን ይፈቅዳል?

የሐዋርያት ስራ 15፥1–21እነዚህ ጥቅሶች የሚገልጹት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መገረዝን ጨምሮ የሙሴን ሕግ መጠበቅ አስፈላጊ ስለመሆን አለመሆኑ አለመግባባትን ነው። ስለ እነዚህ አለመግባባት ሐዋርያት ምን አደረጉ? የቤተክርስቲያን መሪዎች የቤተክርስቲያኗን ሥራ እንዴት እንደሚመሩ ከዚህ ምሳሌ ምን እንማራለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “ከእናንተ ጋር እራመዳለሁ፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣፣ 140–41።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ስዕል ሳሉ። ሥዕሎች የቤተሰብ አባላት የቅዱስ መጻህፍት ትምህርቶችን እና ታሪኮችን በዓይነ ሕሊናቸው እንዲመለከቱ ሊያግዙ ይችላሉ። እናንተ ያነበባችሁትን ሥዕሎች እንዲስሉ የቤተሰብ አባላትን መጋበዝ ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ በየሐዋርያት ስራ 10፣ ላይ እንደ ጴጥሮስ ራእይ።

ምስል
ጴጥሮስ እና ቆርኔሌዎስ

የጴጥሮስ እና ቆርኔሌዎስ ተሞክሮዎች “እግዚአብሔር ለሰው ፊት [እንደማያዳላ]” ያሳያሉ፣(የሐዋርያት ስራ 10፥34)።

አትም