“ሐምሌ 24–30 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 16–21፦ ‘ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናል’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]
“ሐምሌ 24–30 (እ.አ.አ)። የሐዋሪያት ስራ 16–21፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ሐምሌ 24–30 (እ.አ.አ)
የሐዋሪያት ስራ 16-21
“ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናል”
ጳውሎስ ወንጌልን ለመስበክ ስላደረገው ጥረት በምታነቡበት ጊዜ፣ መንፈስ በሀሳቦች ወይም በስሜት ሊያነሳሳችሁ ይችላል። እነዚህን ማበረታቻዎች ፃፉ እና በእነሱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እቅድ አውጡ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ጌታ ለሐዋርያቱ ከተናገራቸው የመጨረሻ ቃሎች መካከል “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ [አስተምሯቸው]” (ማቴዎስ 28፥19–20) የሚል ትእዛዝ ነበር። ሐዋርያት አሕዛብን ሁሉ ባያዳርሱም፣ የሐዋሪያት ስራ 16–21 ጳውሎስ እና ጓደኞቹ ቤተክርስቲያንን በማቋቋም አስደናቂ መሻሻል እንዳሳዩ ያሳያል። እነሱ አስተምረዋል፣ አጥምቀዋል እናም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታን ሰጥተዋል። አንድን ሰው ከሞት እስከማስነሳት ተአምራትን ሠርተዋል፣ እናም ስለ ታላቁ ክህደት ትንቢት ተናግረዋል (የሐዋሪያት ስራ 20፥7–12፣ 28–31)። እናም የጀመሩት ሥራ ጳውሎስ ባላሰበው መንገድ ዛሬ የአዳኙን ተልእኮ ለመፈጸም ከሚረዱ፥ እንደ እናንተ ካሉ ደቀ መዛሙርት ጋር በሕይወት ካሉ ሐዋርያት ጋር ይቀጥላል። ምናልባት የሰማዩን አባታቸውን ወይም የእርሱን ወንጌል የማያውቁ ሰዎችን ታውቁ ይሆናል። ስለ እሱ የምታውቁትን ለእነሱ ለማካፈል “[መንፈሳችሁ በእናንተ ውስጥ እንደተነቃቃ]” ተሰምቷችሁም ይሆናል (የሐዋሪያት ስራ 17፥16)። ወንጌልን በማካፈል የጳውሎስን የትሕትና እና የድፍረት ምሳሌ ከተከተላችሁ፣ “[ጌታ ልቡን የከፈተለትን]” (የሐዋርያት ስራ 16፥14) ልታገኙ ትችላላችሁ።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ወንጌልን ለማካፈል በማደርገው ጥረት መንፈስ ይመራኛል።
ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ “ማንም ሰው ያለ መንፈስ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አይችልም” በማለት ተናግሯል (የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች፡ ጆሴፍ ስሚዝ [2007 (እ.አ.አ)]፤ 332)። የሐዋርያት ሥራ 16–21ን በምታነቡበት ጊዜ የነቢዩ ቃል ለምን እውነት እንደሆነ አስቡ። መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስንና ጓደኞቹን የረዳባቸውን አጋጣሚዎች ልብ በሉ። መንፈስን ሲከተሉ ምን በረከቶች ተገኙ? ወንጌልን ለማካፈል በምታደርጉት ጥረት መንፈስ ሲገፋፋችሁ መቼ ተሰማችሁ?
በሁሉም ሁኔታዎች ወንጌልን ማወጅ እችላለሁ።
ወንጌልን በመስበክ ምክንያት እስር ቤት መወርወር መስበክ ለማቆም ጥሩ ምክንያት ሊመስል ይችላል። ለጳውሎስና ለሲላስ ግን የእስር ቤቱን ጠባቂ ለመለወጥ አጋጣሚ ሆነ (የሐዋርያት ሥራ16፥16–34ን ይመልከቱ)። በ ሐዋርያት ሥራ 16–21፣ ላይ በሙሉ ጳውሎስ ምስክርነቱን ለሁሉም ለማካፈል ፈቃደኛ ስለመሆኑ ሌሎች ምሳሌዎችን ፈልጉ። እሱ በጣም ደፋር እና ፍርሃት አልባ የነበረው ለምን ብላችሁ ታስባላችሁ? ከጳውሎስ ምሳሌነት ምን ትማራላችሁ?
በ የሐዋርያት ሥራ16–21፣ ውስጥ ወንጌልን ስለማካፈል ብዙ ተጨማሪ መልእክቶች አሉ። እነዚህን ምዕራፎች በምታጠኑበት ጊዜ በተለይ ለእናንተ የሚጠቅሙትን ፈልጉ።
በተጨማሪም ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “የሚስዮናዊነት ሥራ፤ በልባችሁ ያለውን ማካፈል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 15–18 ተመልከቱ።
“የእግዚአብሔር [ልጆች ነን]።”
በአቴንስ፣ ጳውሎስ የተለያዩ አስተያየቶች እና ሃይማኖታዊ አመለካከቶች ያላቸውን ሰዎች አገኘ። እነሱ ሁልጊዜ “አዲስ ነገርን … መስማት” ይፈልጉ ነበር፣ እናም ጳውሎስ ያቀረበላቸው በእርግጠኝነት ለእነሱ አዲስ ነበር (የሐዋርያት ሥራ 17፥19–21ን ተመልከቱ)። እነሱ “[የማይታወቅ] አምላክ” (የሐዋርያት ሥራ 17፥23) የሚለውን ጨምሮ ብዙ አማልክትን ያመልኩ ነበር፣ ነገር ግን አማልክት ኃይሎች፣ ሕያው እና የግል ፍጥረታት ያልሆኑ፣ በእርግጥ የእኛ አባት አይደሉም ብለው ያምኑ ነበር። አምላክን እንዲያውቁ ለመርዳት ጳውሎስ የተናገረውን አስቡ። “የእግዚአብሔር [ልጆች]” መሆን ለእናንተ ምን ማለት ነው? (የሐዋርያት ስራ 17፥29)። በእናንተ አስተያየት የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ከፍጡሮቹ አንዱ ብቻ ከመሆኑ በምን ይለያል? ይህንን እውነት መረዳት እናንተን እና ሌሎችን በምታዩበት መንገድ ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራል?
ጳውሎስ በሚመሰክርበት ጊዜ ከጎኑ ቆማችሁ ቢሆን ኖሮ ስለ ሰማይ አባታችን ለጥንቶቹ ግሪኮች ምን ትነግሩ ነበር? ምስክርነታችሁን በመስማት ሊጠቀም የሚችል ሰው ታውቃላችሁ?
በተጨማሪም ሮሜ 8፥16፤ 1 ዮሐንስ 5፥2፤ “የእግዚአብሄር ልጆች ነን” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
የሐዋሪያት ስራ 16–21።የ የሐዋርያት ሥራ 16–21፣ ላይ የቤተሰባችሁን ግንዛቤ ጥልቅ ለማሳደግ፣ በዚህ ረቂቅ መጨረሻ ላይ ባለው ካርታ ጳውሎስ ወንጌልን የሰበካቸውን ከተሞች በመፈለግ ማጥናት ትችላላችሁ። ወንጌልን ለአህዛብ ሁሉ ለማድረስ ዛሬ ምን ግብአቶች አሉን?
ወንጌልን እንዲያካፍሉ ቤተሰባችሁን ለማነሳሳት፣ በወንጌል ላይብረሪ ላይ “ወንጌልን ማካፈል” ክፍል ውስጥ አንድ ወይም ተጨማሪ ቪዲዮዎችን ማሳየት ትችላላችሁ።
-
የሐዋሪያት ስራ 17፥10–12፤ 18፥24–28።በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንዳሉት ቅዱሳን እንዴት ልንሆን እንችላለን? “ልበ ሰፊዎች ነበሩና … ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ” ምን ማለት ሊሆን ይችላል? (የሐዋሪያት ስራ 17፥11)። “በመጻሕፍት እውቀት [የበረታን]” ለመሆን ምን ማድረግ እንችላለን? (የሐዋሪያት ስራ 18፥24)።
-
የሐዋሪያት ስራ 19፥1–7።እነዚህ ጥቅሶች ቤተሰባችሁ ስለ መጠመቅ እና መንፈስ ቅዱስ መቀበል አስፈላጊነት ውይይት እንዲያደርግ ሊረዷችሁ ይችላሉ። በ የሐዋሪያት ስራ 19፥1–7፣ ላይ ያሉትን እውነቶች የተሻለ ለመረዳት፣ ያለ ሌላ ነገር የማይጠቅሙ አንዳንድ ነገሮችን፣ ለምሳሌ ባትሪ የሌለውን ሞባይል ስልክን፥ መወያየት ትችላላችሁ። ወይም ይህንን ትምህርት ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ማጋራት ትችላላችሁ፤ “በውኃ ጥምቀት ግማሽ ጥምቀት ብቻ ነው፣ ያለ ሌላኛው ግማሽ ማለትም ያለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምንም አይጠቅምም” (ትምህርቶች ጆሴፍ ስሚዝ፣ 95)። የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ሳይቀበሉ ጥምቀት “[የማይጠቅም]” የሚሆነው ለምንድነው? (3 ኔፊ 27፥19–20፤ ሙሴ 6፥59–61ን ተመልከቱ)።
-
የሐዋሪያት ስራ 19፥18–20። የሐዋሪያት ስራ 19፥18–20ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ወንጌልን ለመቀበል ሕዝቡ ለመተው ፈቃደኛ የነበረውን የንብረት ዋጋ አስተውሉ (ቁጥር 19ን ተመልከቱ)። ሰማያዊ በረከቶችን ለማግኘት መተው ያለብን ዓለማዊ ንብረቶች ወይም እንቅስቃሴዎች አሉን?
-
የሐዋሪያት ስራ 20፥32–35።ቤተሰባችሁ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው” የሚለውን የክርስቶስን ትምህርት የቀመሰው መቼ ነው? (የሐዋሪያት ስራ 20፥35)። ቤተሰባችሁ ሊሰጥ ከሚችለው አገልግሎት፣ ጊዜ ወይም ስጦታ ሊጠቅም የሚችል ሰው አለ? እንደ ቤተሰብ፣ አንዳንድ ሀሳቦችን ተወያዩና አንድን ሰው ለማገልገል እቅድ አውጡ። ሌሎችን ስናገለግል ምን ይሰማናል? ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ለምን ይባርካል?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።
በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣፣ 2–3።