አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 14–20 (እ.አ.አ)። ሮሜ 7–16፦ “ክፉውን በመልካም አሸንፍ”


“ነሐሴ 14–20 (እ.አ.አ)። ሮሜ 7–16፦ ‘ክፉውን በመልካም አሸንፍ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 14–20 (እ.አ.አ)። ሮሜ 7–16፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
የጥንታዊ ሮም ጥፋት

ነሐሴ 14–20 (እ.አ.አ)

ሮሜ 7–16

“ክፉውን በመልካም አሸንፍ”

ሮሜ 7–16 ላይ ካሉት የወንጌል መርሆዎች ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው በዚህ ረቂቅ ውስጥ ሊካተቱ የቻሉት፣ ስለዚህ እዚህ በተገለጸው ላይ ብቻ ራሳችሁን አትገድቡ። በምታጠኑበት ጊዜ ለምትቀበሉት መነሳሳት ትኩረት ስጡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ጳውሎስ ለሮሜ መልእክቱን በጀመረበት ወቅት፣ “በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ” በማለት ለቤተክርስቲያኑን አባላት ሰላምታ ሰጠ። እሱ “[እምነታቸው] በዓለም ሁሉ [እንደተሰማች]” ተናግሯል(ሮሜ 1፥7–8)። ምንም እንኳን ጳውሎስ ብዙ መልእክቱን የሐሰት ሀሳቦችን እና የተሳሳቱ ባህሪያትን በማረም ያሳለፈ ቢሆንም፣ ለእነዚህ አዲስ የክርስትና እምነት ተከታዮች በእውነት በእግዚአብሔር የተወደዱ ቅዱሳን መሆናቸውን ለማረጋገጥ የፈለገ ይመስላል። የእርሱ የርህራሄ ምክር የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማን የምንታገለውን እና ቅዱስ መሆን የማይደረስበት ሆኖ የሚሰማንን ባርኳል። በትህትናና ርኅራሄ፣ ጳውሎስ አንዳንድ ጊዜ እንደ “ጎስቋላ ሰው” (ሮሜ 7፥24) እንደሚሰማው አምኗል፣ ነገር ግን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ኃጢአቱን ለማሸነፍ ኃይል ሰጥቶታል (የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ሮሜ 7፥22–27 ን ተመልከቱ [በመጽሐፍ ቅዱስ መግለጫ ላይ)። (ሮሜ 12፥21) በዚያ ኃይል፣ በአዳኙ የማዳን ኃይል፣ በዓለም ውስጥ እና በእኛም ያለውን “ክፉን” “በመልካም” ማሸነፍ” እንችላለን።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሮሜ 7–8

መንፈስን የሚከተሉ “ከክርስቶስ ጋር [አብረው] ወራሾች” ሊሆኑ ይችላሉ።

ወደ “[አዲስ] ሕይወት” (ሮሜ 6፥4) ከገባችሁ በኋላም እንኳን፣ ምናልባት ጳውሎስ በሮሜ 7፣ ላይ የገለፀውን አይነት አንዳንድ ውስጣዊ ውዝግቦች—በተፈጥሯዊው ሰው እና በጽድቅ ፍላጎቶችሁ መካከል “[ውግያ]” (ሮሜ 7፥23) ተሰምቷችሁ ያውቅ ይሆናል። ጳውሎስ ግን በሮሜ 8፥23–25ላይ ስለ ተስፋ ተናግሯል። በምዕራፍ 8ላይ ለዚህ ተስፋ ምን ምክንያቶች አገኛችሁ? እንዲሁም “የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ [በመኖሩ]” (ሮሜ 8፥9) የሚመጡ በረከቶችን ፈልጉ። በህይወታችሁ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን አብሮነት ይበልጥ እንዴት መፈለግ እችላላችሁ?

ሮሜ 8፥16–39

የዘላለም ክብር ስጦታ በምድር ላይ ከሚያጋጥሙኝ ፈተናዎች እጅግ ይበልጣል።

ጳውሎስ ይህንን መልእክት ከጻፈ ከጥቂት ዓመታት በኋላ፣ በሮም የነበሩ ቅዱሳን አሰቃቂ መከራ ደርሶባቸዋል። በሮሜ 8፥16–39 ላይ እነዚህ ቅዱሳን መከራ ሲመጣባቸው የረዳቸውን ምን ታገኛላችሁ? እነዚህ ቃላት ለእናንተ እና አሁን በገጠማችሁ ፈተናዎች ላይ እንዴት ሊተገበሩ ይችላሉ?

በእነዚህ ጥቅሶች እና በዚህ የእህት ሊንዳ ኤስ. ሪቭስ ምክር መካከል ያለውን ግንኙነት ፈልጉ፤ “እኛ ያሉን ብዙ ፈተናዎች ለምን እንዳሉን አላውቅም፣ ነገር ግን ሽልማቱ በጣም ትልቅ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሆነ፣ እጅግ አስደሳች እና ከመረዳት በላይ እንደሚሆን፤ እንዲሁም በዚያ የሽልማት ቀን፣ መሐሪ ለሆነው አፍቃሪ አባታችን ‘የሚያስፈልገው ሁሉ ይህ ነበር?’ ማለት ሊሰማን እንደሚችል ግላዊ ስሜቴ ነው። የሰማይ አባታችን እና አዳኛችን ለእኛ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር በየቀኑ ማስታወስ እና ማስተዋል ብንችል፣ ከእነርሱ ጋር ተመልሰን ለመኖር የጠየቁንን ሁሉ ለማድረግ ፍቃደኞች እንሆናለን። ምናልባት … በመጨረሻ እነዚህ ፈተናዎች ለአባታችን እና ለአዳኛችን በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ለዘላለማዊ ሕይወት እና ከፍ ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉን ነገሮች ቢሆኑን?” (“የተስፋችን በረከቶች የሚገባን፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 11)። እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን ፍቅር “በየቀኑ ለማስታወስ እና ለመለየት” ምን እንደምታደርጉ ወስኑ።

ሮሜ 8፥29–309–11

ጳውሎስ “አስቀድሞ … ወስኗል፣” “መመረጥ” እና “አስቀድሞ ያወቃቸው” ሲል ምን ማለቱ ነበር?

ጳውሎስ ከዚህ ሕይወት አስቀድሞ፣ እግዚአብሔር አንዳንድ ልጆቹ የእስራኤል፣ የቃል ኪዳኑ ሕዝቦች እንዲሆኑ መምረጡን ለማስተማር “አስቀድሞ … ወስኗል፣” “ምርጫ” እና “አስቀድሞ አወቀ” የሚሉትን ቃላት ተጠቅሟል። ይህ ማለት ሁሉንም የዓለም ሰዎች ይባርኩ ዘንድ ልዩ በረከቶችን እና ኃላፊነቶችን ይቀበላሉ ማለት ነው (የቅዱሳት መጻሕፍት መመሪያን፤ “ምርጫ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ)። ሆኖም፣ ጳውሎስ ሮሜ 9–11 ላይ ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች የቃል ኪዳኑ ህዝቦች ሊሆኑ እንደሚችሉ አበክሮ ገልጿል፣ እናም ሁላችንም የዘላለም ሕይወትን በተመሳሳይ መንገድ እንቀበላለን—በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና ትእዛዛቱን በመጠበቅ።

በተጨማሪም ኤፌሶን 1፥3–41 ጴጥሮስ 1፥2አልማ 13፥1–5፤ የወንጌል ርዕሶች “አስቀድሞ መመረጥ፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

ሮሜ 12–16

ጳውሎስ እውነተኛ ቅዱስ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ እንድሆን ይጋብዘኛል።

የሮሜ የመጨረሻዎቹ አምስት ምዕራፎች እንደ ቅዱሳን መኖርን በተመለከተ በደርዘን የሚቆጠሩ የተወሰኑ መመሪያዎችን ይዘዋል። እነዚህን መመሪያዎች ለማጥናት አንዱ መንገድ የሚደጋገሙ ርዕሶችን መፈለግ ነው። የጳውሎስን ምክር እንዴት ታጠቃልላላችሁ?

ይህንን ምክር ሁሉ በአንድ ጊዜ ተግባራዊ ማድረግ ላትችሉ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን መንፈስ ዛሬ መስራት የምትጀምሩትን አንድ ወይም ሁለት መርሆዎችን እንድታገኙ ይረዳችኋል። ምኞቶቻችሁን ለሰማይ አባታችሁ በጸሎት አካፍሉ፣ እና የእርሱን እርዳታ ጠይቁ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሮሜ 8፥31–39የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ስለ እኛ ምን እንደሚሰማቸው የሚያስተምረንን ከ ሮሜ 8፥31–39 ላይ ምን እናገኛለን? የእግዚአብሔር ፍቅር መቼ ተሰማን?

ቁጥሮች 38–39ን ለማብራራት፣ የቤተሰብ አባላት እንደ እኛ እና እንደ እግዚአብሔር ፍቅር ሊነጣጠሉ የማይችሉ ነገሮችን ምሳሌዎችን ማግኘት ይችላሉ።

ምስል
አባት እና ሴት ልጅ ሲጨፍሩ

ሽማግሌ ዊልፎርድ ደብሊው አንደርሰን “የወንጌል ሙዚቃ [አስደሳች] መንፈሳዊ ስሜት ነው” ብለው አስተምረዋል።

ሮሜ 9፥31–32የሽማግሌ ዊልፎርድ ደብሊው አንደርሰን መልዕክት “የወንጌል ሙዚቃ” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ) 54–56፤ በተጨማሪም ቪድዮውን በChurchofJesusChrist.orgላይ ተመልከቱ) ጳውሎስ ስለ ሕግ፣ ሥራ እና እምነት የሚያስተምረውን በምሳሌ ለማስረዳት ሊረዳ ይችላል። ስለ ንግግሩ ከተወያያችሁ በኋላ ቤተሰባችሁ በሙዚቃ እና ያለ ሙዚቃ ለመደነስ ሊሞክር ይችላል። የወንጌልን ደስታ እንድናገኝ እምነት እንዴት ሊረዳን ይችላል?

ሮሜ 10፥17የእግዚአብሔር ቃል ምንጮችን (እንደ ቅዱሳት መጻህፍት፣ የግል መገለጥ እና አጠቃላይ ጉባኤ) በብዙ የውሃ ብርጭቆዎች ላይ ምልክት አድርጉ። እያንዳንዱን ብርጭቆ “እምነት” ተብሎ በተሰየመ መያዣ ውስጥ ስታፈሱ የእግዚአብሔር ቃል እንዴት እምነታችንን እንደሚጨምር ተወያዩ።

ሮሜ 12እራሳችንን “እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት” ማድረግ ምን ማለት ነው? (ቁጥር 1)።

ሮሜ 14፥13–21በግል ምርጫዎች ላይ ስለመፍረድ እና ስለመከራከር የጳውሎስን ምክር በማጥናት ቤተሰባችሁ ሊጠቀም ይችላል። ምናልባት ሌሎች ሰዎች፣ የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ፣ ከእናንተ የሚለዩ ምርጫዎችን ሲመርጡ ተገቢውን ምላሽ ስለመስጠት ልትወያዩ ትችላላችሁ። “ሰላም የሚቆምበት.[መከተል]” እንዴት እንችላለን? (ቁጥር 19)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “የአዳኜ ፍቅር ይሰማኛል፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 74–75።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ልጆች የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲገልጹ ፍቀዱ። ልጆች ከወንጌል መርሆ ጋር የሚዛመድን ነገር እንዲፈጥሩ ስትጋብዙ መርሆውን የበለጠ እንዲገነዘቡት ይረዳቸዋል። … እንዲገነቡ፣ እንዲስሉ፣ ቀለም እንዲቀቡ፣ እንዲጽፉ እና እንዲፈጥሩ ፍቀዱላቸው” ((በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 25)።

ምስል
ክርስቶስ በተዘረጋ እጆች

ከእኔ ጋር ሁን፣ በዳል ፓርሰን

አትም