አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 21–27 (እ.አ.አ)። 1 ቆሮንቶስ 1–7፦ “የተባበራችሁ እንድትሆኑ”


“ነሐሴ 21–27 (እ.አ.አ)። 1 ቆሮንቶስ 1–7፦ ‘የተባበራችሁ እንድትሆኑ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 21–27 (እ.አ.አ)። 1 ቆሮንቶስ 1–7፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ጥንታዊ ቆሮንቶስ

ቆሮንቶስ፣ ደቡብ ግሪክ፣ የሸንጎ እና ህዝባዊ ማእከል፣ ስዕል በባላጅ Balogh/www.ArchaeologyIllustrated.com

ነሐሴ 21–27 (እ.አ.አ)

1 ቆሮንቶስ 1–7

“የተባበራችሁ እንድትሆኑ”

1 ቆሮንቶስ 1–7ን በምታነቡበት ጊዜ ግንዛቤዎቻችሁን መዝግቡ። እነዚህ ግንዛቤዎች አንድን ሀሳብ የበለጠ የማጥናት፣ የተማራችሁትን ነገር ለሌሎች የማካፈል፣ ወይም በሕይወታችሁ ውስጥ ለውጦችን የማድረግ ተነሳሽነቶችን ሊያካትቱ ይችላሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ጳውሎስ በቆሮንቶስ ባሳለፋቸው ወራት ፣ “ከቆሮንቶስ ሰዎች ብዙ በሰሙ ጊዜ አምነው ተጠመቁ” (የሐዋርያት ሥራ 18፥8)። ስለዚህ ጳውሎስ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በቆሮንቶስ ቅዱሳን መካከል “መለያየት” እና “ክርክር” እንደነበር እናም እሱ በሌለበት “የዚችን ዓለም [ጥበብን]” (1 ቆሮንቶስ 1፥10–11፣ 20) መስማት መጀመራቸውን መስማቱ ልብ የሚሰብር ሊሆን ይችላል። በምላሹ፣ ጳውሎስ አሁን 1ኛ ቆሮንቶስ ብለን የምንጠራውን ደብዳቤ ጻፈ። በጥልቅ ትምህርት የተሞላ ነው፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ፣ ጳውሎስ ቅዱሳኑ ሊሰጣቸው የሚፈልገውን ትምህርት ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸው ቅር ያሰኘው ይመስላል። “እኔ፣ ወንድሞች ሆይ፣ መንፈሳዊያን እንደመሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልኩም፣ … ገና ሥጋውያን ናችሁ” በማለት አዘነ (1 ቆሮንቶስ 3፥1–3)። የጳውሎስን ቃላት ለማንበብ ስንዘጋጅ፣ እውነትን ለመቀበል የራሳችንን ዝግጁነት መመርመር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል—መንፈስን ለመታዘዝ እና በቤተሰቦቻችን ውስጥ፣ ከባልንጀሮቻችን ቅዱሳን ጋር እና ከእግዚአብሔር ጋር በአንድነት ለመኖር ፈቃደኝነትን ጨምሮ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

1 ቆሮንቶስ 1፥10–173፥1–11

የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት አንድ ለመሆን ይጥራሉ።

በቆሮንቶስ ቅዱሳን መካከል ስላለው የአንድነት እጥረት ሁሉንም ዝርዝሮች አናውቅም፣ ነገር ግን በራሳችን ግንኙነቶች ውስጥ ያሉትን እናውቃለን። በሕይወታችሁ ውስጥ ይበልጥ አንድነት ሊጠቅም የሚችለውን ግንኙነት አስቡ፣ ከዚያም በ1 ቆሮንቶስ 1፥10–173፥1–11 ላይ በቆሮንቶስ ቅዱሳን መካከል ስለ አንድነት እጦት ጳውሎስ ያስተማረውን ፈልጉ። ከሌሎች ጋር ይበልጥ አንድነትን ለማዳበር ምን ግንዛቤዎችን ማግኘት ትችላላችሁ?

በተጨማሩም ሞዛያ 18፥214 ኔፊ 1፥15–17ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥23–27105፥1–5፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “አንድነት፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

1 ቆሮንቶስ 1፥17–31፤ 2

የእግዚአብሔርን ሥራ ለመፈጸም፣ የእግዚአብሔር ጥበብ ያስፈልገኛል።

ጥበብን ማግኘት በምንችልበት ቦታ ሁሉ መፈለግ ጥሩ ቢሆንም—እንዲያውም ቢበረታታም (2 ኔፊ 9፥29ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥118ነ ይመልከቱ)፣ ጳውሎስ “የዚህ ጥበብ ዓለም” ብሎ ስለጠራው ጉድለት ስላለው ሰብዓዊ ጥበብ አንዳንድ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥቷል። 1 ቆሮንሮስ 1፥17–25ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ይህ ሐረግ ምን ማለት እንደሆነ አስቡ። ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ጥበብ” ሲል ምን ማለቱ ይመስላችኋል? የእግዚአብሔርን ሥራ ለመፈጸም የእግዚአብሔር ጥበብ ለምን ያስፈልገናል?

የእግዚአብሔርን ሥራ ለመፈጸም ኃላፊነቶቻችሁን ለመወጣት በምታደርጉት ጥረት፣ ጳውሎስ የቆሮንቶስን ቅዱሳን ሲያስተምር የተሰማውን “ፍርሃትና … ብዙ መንቀጥቀጥ” አጋጥሟችሁ ያውቃልን? (1 ቆሮንቶስ 2፥3)። በ1 ቆሮንቶስ 2፥1–5 ላይ ድፍረት የሚሰጣችሁን ምን ታገኛላችሁ? “ከሰዎች ጥበብ” ይልቅ “በእግዚአብሔር ኃይል” እንደምትታመኑ እንዴት ማሳየት እንደምትችሉ አስቡ።

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥17–28ን ተመልከቱ።

1 ቆሮንቶስ 2፥9–16

የእግዚአብሔርን ነገሮች ለመረዳት መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገኛል።

ስለ አውቶሞቲቭ ሜካኒክስ ወይም የመካከለኛው ዘመን ሥነ ሕንፃ አንድ ነገር የበለጠ ለማወቅ ከፈለጋችሁ ምን ታደርጋላችሁ? በ1 ቆሮንቶስ 2፥9–16፣ መሠረት “[የእግዚአብሔርን ነገር]” መማር “[የሰውን ነገር]” ከመማር የሚለየው እንዴት ነው? የእግዚአብሔርን ነገር ለመረዳት መንፈስ ቅዱስ ለምን ያስፈልገናል? እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ መንፈሳዊ ነገሮችን ይበልጥ ለመረዳት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ይሰማችኋል? የጳውሎስ ቃላት ስለ ምስክርነቱ የሚታገልን ሰው እንዴት ሊረዳ ይችላል?

1 ቆሮንቶስ 6፥13–20

ሰውነቴ ቅዱስ ነው።

አብዛኞቹ የቆሮንቶስ ሰዎች የጾታዊ ብልግና ተቀባይነት ያለው እንደሆነና ሰውነታቸው በዋነኝነት የተሠራው ለደስታ እንደሆነ ይሰማቸው ነበር። በሌላ አገላለጽ፣ ቆሮንቶስ ከዛሬው ዓለም የተለየች አልነበረችም። በ1 ቆሮንቶስ 6፥13–20 ላይ ንጹሕ ሕይወት መኖር ለምን እንደምትፈልጉ ለሌሎች መግለጽ እንድትችሉ የሚረዳችሁን ጳውሎስ ምን አስተማረ?

እንደ ጳውሎስ፣ እህት ዌንዲ ደብሊው. ኔልሰን ቅዱሳን ንፁህ እንዲሆኑ አበረታታለች “ፍቅር እና ጋብቻ” (ዓለም አቃፋዊ የመንፈስ ስብሰባ ለመጣቶች፣ ጥር 8፣ 2017 (እ.አ.አ)፣ broadcasts.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ)። እንደ እህት ኔልሰን አነጋገር የጌታን የፍቅር እና የቅርብ ግንኙነት መመዘኛዎችን በመኖር ምን በረከቶች ይመጣሉ?

1 ቆሮንቶስ 7፥29–33

ጳውሎስ ከትዳር ይልቅ ያላገባ መሆን የተሻለ እንደሆነ አስተምሯል?

1 ቆሮንቶስ 7 ላይ ያሉት በርካታ ጥቅሶች ጋብቻ ተቀባይነት ያለው እንደሆነ ቢናገሩም ያላገባ ሆኖ መኖር እና ከጾታዊ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ መራቅ እንደሚመከር የሚጠቁሙ ይመስላሉ። ሆኖም ግን የ ጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም 1 ቆሮንቶስ 7፥29–33 (በመጽሃፍ ቅዱስ መጨረሻ ውስጥ) ጳውሎስ የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን እንዲሆኑ የተጠሩት፤ በምስዮናዊ አገልግሎቶቻቸው ወቅት ያላገቡ ሆነው ቢቆዩ እግዚአብሔርን በተሻለ ሁኔታ ማገልገል እንደሚችሉ እያመለከተ እንደነበረ እንድንረዳ ይረዳናል። ጳውሎስን ጨምሮ ጌታ በአገልጋዮቹ በኩል ጋብቻ የዘላለማዊ ዕቅዱ አካል እና ከፍ ከፍ ለመደረግ አስፈላጊ መሆኑን አስተምሯል (1 ቆሮንቶስ 11፥11ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፥1–4ን ተመልከቱ)።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

1 ቆሮንቶስ 1፥10–173፥1–11የቤተሰባችሁ አባላት እነዚህን ጥቅሶች ሲያነቡ፣ የበለጠ አንድነት እንዲኖራቸው የሚረዳ ግንዛቤ እንዲያገኙ ጋብዟቸው።

1 ቆሮንቶስ 3፥1–2ምናልባት ወተት እና ስጋ እየበላችሁ እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ ትችሉ ይሆናል። ሕፃናት ወደ አዋቂነት የሚያድጉበትን መንገድ ከመንፈሳዊ እድገት ጋር ማወዳደር ትችላላችሁ።

1 ቆሮንቶስ 3፥4–9ጳውሎስ የሚስዮናዊነት ጥረቱን ዘር ከመዝራት ጋር አነጻጽሯል። የእሱ ንጽጽር ወንጌልን ስለማካፈል ምን ያስተምረናል?

1 ቆሮንቶስ 6፥19–20ጳውሎስ እንዳደረገው ሰውነታችንን ከቤተ መቅደሶች ጋር ማወዳደር ስለ ሰውነታችን ቅድስና ለማስተማር ውጤታማ መንገድ ሊሆን ይችላል። ምናልባት ከዚህ ረቂቅ ጋር የሚዛመዱትን እንደ ቤተመቅደስ ሥዕሎችን ማሳየት ትችሉ ይሆናል። ቤተመቅደሶች ለምን ቅዱስ ናቸው? ሰውነታችን እንደ ቤተመቅደሶች የሚሆኑት እንዴት ነው? ሰውነታችንን እንደ ቤተመቅደስ እንዲሆን ምን እናድርግ? (በተጨማሪም የነሃሴ 2020 (እ.አ.አ) ስለጾታዊ ግንኙነት የ ሊያሆና ልዩ እትም ን ተመልከቱ።)

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ጌታ ቤተመቅደስን ሰጠኝ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 153።

የግል ጥናትን ማሻሻል

በራሳችሁ ትእግስተኛ ሁኑ። ጳውሎስ ወንጌልን ስንማር ከስጋ አስቀድሞ ወተት እንደሚመጣ አስተምሯል (1 ቆሮንቶስ 3፥1–2ን ተመልከቱ)። አንዳንድ አስተምሮቶችን አሁን ለመረዳት አስቸጋሪ እንደሆኑ ካገኛችሁ ታገሱ። እምነት ሲኖራችሁ እና በትጋት ስታጠኑ መልሶች እንደሚመጡ እመኑ።

አራት ቤተመቅደሶች

ጳውሎስ ሰውነታችንን ከቤተመቅደስ ቅድስና ጋር አመሳስሎታል። ከላይ በስተግራ በሰዓት አቅጣጫ፦ ቲኋና ሜክሲኮ ቤተመቅደስ፣ ታይፔ ታይዋን ቤተመቅደስ፣ ተጉጊጋልፓ ሆንዱራስ ቤተመቅደስ፣ የሂውስተን ቴክሳስ ቤተመቅደስ።