አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ነሃሴ 28–መስከረም 3። 1 ቆሮንቶስ 8–13፦ “እናንተ የክርስቶስ አካል ናችሁ”


“ነሃሴ 28–መስከረም 3። 1 ቆሮንቶስ 8–13፦ ‘እናንተ የክርስቶስ አካል ናችሁ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ነሃሴ 28–መስከረም 3። 1 ቆሮንቶስ 8–13፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ

ነሐሴ 28––መስከረም 3 (እ.አ.አ)

1 ቆሮንቶስ 8–13

“እናንተ የክርስቶስ አካል ናችሁ”

1 ቆሮንቶስ 8–13ን በጸሎት ስታነቡ ፣ መንፈስ ቅዱስ በስውር መንገዶች ሊያናግራችሁ ይችላል (1 ነገሥት 19፥11–12ን ተመልከቱ )። እነዚህን ግንዛቤዎች መመዝገብ በጥናታችሁ ወቅት የነበራቸውን ስሜቶች እና ሀሳቦች ለማስታወስ ይረዳችኋል።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

በጳውሎስ ዘመን ቆሮንቶስ ከመላው የሮማ ግዛት ነዋሪዎች የነበሩባት ሀብታም የንግድ ማዕከል ነበረች። በከተማው ውስጥ ብዙ የተለያዩ ባህሎች እና ሃይማኖቶች በመኖራቸው፣ በቆሮንቶስ ያሉ የቤተክርስቲያን አባላት አንድነትን ለመጠበቅ ተቸግረዋል፤ ስለዚህ ጳውሎስ በክርስቶስ ባላቸው እምነት አንድነትን እንዲያገኙ ለመርዳት ፈለገ። ጳውሎስ የጠየቃቸው አንዳቸው የሌላውን ልዩነት እንዲታገሱ ብቻ አልነበረም፤ ይህ አንድነት በሰላም አብሮ ከመኖር በላይ መሆን ነበረበት። ይልቁንም እርሱ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ስትቀላቀሉ “አንድ አካል [እንድትሆኑ ተጠምቃችኋል]” በማለት አስተምሯል፣ እናም እያንዳንዱ የአካል ክፍል ያስፈልጋል (1 ቆሮንቶስ 12፥13)። አንድ የሰውነት አካል ሲጠፋ ልክ አንድ እጅና እግርን እንደ ማጣት ነው፣ በዚህም ምክንያት አካሉ ደካማ ይሆናል። አንድ አባል ሲቸገር ሁላችንም ሊሰማን እና ያን ለማቃለል የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል። በዚህ ዓይነት አንድነት ውስጥ ልዩነቶች እውቅና ማግኘት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ዋጋ ያላቸው ይሆናሉ፣ ምክንያቱም ያለ ልዩ ስጦታዎች እና ችሎታዎች አካል ውስን ስለሚሆን ነው። ስለዚህ ቤተክርስቲያኑ እንደ ቤት ቢሰማችሁ ወይም ደግሞ በእውነት እዚያ መሆን ይገባችሁ እንደሆን የምታስቡ ከሆነ፣ ለእናንተ የጳውሎስ መልእክት አንድነት ማለት ተመሳሳይነት እንዳልሆነ ነው። የእምነት ባልደረቦቻችሁ ያስፈልጓችኋል፣ እናንተም ለቅዱሳን ታስፈልጋላችሁ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

1 ቆሮንቶስ 10፥1–13

እግዚአብሔር ከፈተና ለማምለጥ መንገድን ያዘጋጃል።

መንፈሳዊ ልምዶች፣ ተአምራትም ቢሆኑ “ለሰው ሁሉ ከሚሆኑ” (1 ቆሮንቶስ 10፥13) ፈተናዎች አይለዩንም። ያ በሙሴ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን ታላላቅ ተአምራትን ቢያዩም ከፈተና ጋር እንዴት እንደታገሉ ጳውሎስ የጻፈበት አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል (ዘፀአት 13፥2114፥13–31ን ተመልከቱ)። 1 ቆሮንቶስ 10፥1–13ን በምታነቡበት ጊዜ በእስራኤላውያን ተሞክሮ ውስጥ የትኞቹ ማስጠንቀቂያዎች ናቸው ለእናንተም የሚሰሩ የሚመስሉት? የሰማይ አባት ከፈተና ምን ዓይነት “ማምለጫ” ሰጥቷችኋል? (በተጨማሪም አልማ 13፥27–303 ኔፊ 18፥18–19ን ተመልከቱ)

1 ቆሮንቶስ 10፥16–1711፥16–30

ቅዱስ ቁርባን እንደ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላትነት አንድ ያደርገናል።

ቅዱስ ቁርባን በእናንተ እና በጌታ መካከል የግል መሰጠትን የሚያካትት ቢሆንም፣ ለሌሎችም የምታጋሩት ተሞክሮ ነው። እኛ ሁል ጊዜ እንደ ቅዱሳን አካል በመሆን ቅዱስ ቁርባንን እንካፈላለን። ጳውሎስ ስለ ቅዱስ ቁርባን ያስተማረውን አንብቡ፣ እና ይህ ቅዱስ ሥርዓት “ብዙዎች” በክርስቶስ “አንድ” እንዲሆኑ እንዴት እንደሚረዳ አስቡ (1 ቆሮንቶስ 10፥17)። ቅዱስ ቁርባንን መካፈል ወደ ክርስቶስ እና ወደ ሌሎች አማኞች ይበልጥ ቅርበት እንዲሰማችሁ እንዴት ይረዳችኋል? እነዚህ ጥቅሶች ስለ ቅዱስ ቁርባን ያላችሁን ስሜት እና ለእዚያም በምትዘጋጁበት መንገድ ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራሉ?

1 ቆሮንቶስ 11፥11

በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ወንዶች እና ሴቶች እርስ በእርስ ይፈላለጋሉ።

1 ቆሮንቶስ 11፥4–15፣ ላይ ጳውሎስ እኛ ዛሬ የማንከተላቸውን ባህላዊ ልማዶች ጠቅሷል። ሆኖም፣ ጳውሎስ በቁጥር11፣ ላይ የሚገኘውን ለዘለአለም የሚሆን አስፈላጊ እውነት አስተምሯል። ይህ ጥቅስ ምን ማለት ነው ብላችሁ ታስባላችሁ፣ እናም ለምን አስፈላጊ ሆነ? ሽማግሌው ዴቪድ ኤ. ቤድናር “ወንድ እና ሴት አንዳቸው ከሌላው እንዲማሩ፣ እንዲያጠነክሩ፣ እንዲባርኩ፣ እና አንዳቸው ሌላውን ሙሉ ማድረግ እንዲችሉ የታቀዱ ናቸው” በማለት አስተምሯል (“ንፁህ በመሆን እናምናለን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ) 42)። ይህ እውነት በትዳር ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይገባል? በቤተክርስቲያን ውስጥ በምናገለግልበት መንገድ ላይ እንዴት ሊነካ ይገባል?

በተጨማሪም ጂን ቢ. ቢንጋም “የእግዚአብሔርን ስራ ለማከናወን የተባበርን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ) 60–63 ን ተመልከቱ።

1 ቆሮንቶስ 12–13

መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጡት የሰማይ አባት ልጆችን ሁሉ እንዲጠቅሙ ነው።

1 ቆሮንቶስ 12–13 ላይ ያሉት የመንፈሳዊ ስጦታዎች ዝርዝር የተሟላ አይደለም። ነገር ግን የሰማይ አባት የሰጣችሁን መንፈሳዊ ስጦታዎች ለይታችሁ ማሰላሰል ለመጀመር ጥሩ ቦታ ነው። በወንጌል ርዕሶች ውስጥ “መንፈሳዊ ስጦታዎች” የሚለው መጣጥፍ (topics.ChurchofJesusChrist.org) እነዚህን ስጦታዎች ይበልጥ ለመረዳት ይረዳችኋል። የጳውሎስን የስጦታዎች ዝርዝር በምታነቡበት ጊዜ አንዳንድ በሌሎች፣ በራሳችሁ ወይም በቅዱሳት መጻሕፍት ባሉ ሰዎች ላይ ልብ ያላችሁትን ማከል ትችላላችሁ። የፓትርያርክ በረከት ካላችሁ፣ አንዳንድ መንፈሳዊ ስጦታዎቻችሁን ሊጠቅስ ይችላል። እነዚህ ስጦታዎች ሌሎችን እንድትባርኩ እንዴት ይረዷችኋል? “የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ” እንዴት መፈለግ እንደምትችሉ አስቡ (1 ቆሮንቶስ 12፥31)።

በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 14ሞሮኒ 10፥8–21፣ 30ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 46፥8–26የእምነት አንቀጽ 1፥7ን ተመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

1 ቆሮንቶስ 9፥24–27ጳውሎስ ወንጌልን መኖር ከውድድር ጋር ስላነጻጸረ፣ የእርሱን ሃሳብ ለማሳየት የቤተሰብ ሩጫ ውድድር ሊኖራችሁ ይችላል። ሩጫውን ለጨረሰ ሁሉ አክሊል ስጡ፣ እናም በዚህ ሕይወት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ትጉ የሆኑ ሁሉ “የማይጠፋውን” ሽልማትን እንዴት እንደሚያገኙ ተወያዩ (1 ቆሮንቶስ 9፥25፤ በተጨማሪም 2 ጢሞቴዎስ 4፥7–8ን ተመልከቱ)። አንድ ሯጭ ለሩጫ ለመዘጋጀት ምን ያደርጋል? ወደ ሰማይ አባት ለመመለስ ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንችላለን?

በሩጫ ሜዳ ላይ ሯጮች

ጳውሎስ ወንጌልን መኖር ሩጫ ከመሮጥ ጋር አመሳስሎታል።

1 ቆሮንቶስ 12፥1–11እነዚህን ጥቅሶች አንድ ላይ ካነበባችሁ በኋላ ከላይ የሌላ የቤተሰብ አባል ስም ያለው ወረቀት ለሁሉም ሰው መስጠትን አስቡ። ያ ሰው ያለውን መንፈሳዊ ስጦታዎች እንዲዘረዝሩ ሁሉንም ጠይቁ። ከዚያ እያንዳንዱ ሰው ስለ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ስጦታዎች የመጻፍ ዕድል እስኪያገኝ ድረስ ወረቀቶቹን ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

1 ቆሮንቶስ 12፥3የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት ለማግኘት መንፈስ ቅዱስ ለምን አስፈለገ? ስለ እርሱ ምስክርነታችንን ለማጠናከር መንፈስ ቅዱስን ለመጋበዝ ምን እናድርግ?

1 ቆሮንቶስ 12፥12–27የጳውሎስ የአካል ምሳሌ በቤተሰብ አንድነት ላይ ለመወያየት የማይረሳ መንገድ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ የቤተሰብ አባላት በዓይኖች ወይም በጆሮዎች ብቻ የተሰራ አካል ለመሳል ሊሞክሩ ይችላሉ (ቁጥር 17ን ተመልከቱ)። እንደ ቤተሰብ አባላት አንዳችን ሌላችንን እንዴት መንከባከብ እንዳለብን እነዚህ ጥቅሶች ምን ይጠቁማሉ?

1 ቆሮንቶስ 13፥4–8የጳውሎስ የፍቅር ትርጉም ለቤተሰባችሁ የሚያነቃቃ መፈክር ሊሆን ይችላል። የቤተሰብ አባላት እያንዳንዱ በቁጥሮች 4–8 ውስጥ አንድ ሐረግ እንዲያጠና መመደብ እና ትርጓሜዎችን፣ ምሳሌዎችን እና የግል ልምዶችን በመጠቀም ምን ማለት እንደሆነ ማስተማር ትችላላችሁ። አዳኙ የእነዚህ ባሕርያት ምሳሌ የሆነው እንዴት ነው? ለእያንዳንዳቸው ለእነዚህ ሐረጎች ፖስተሮችን በጋራ መስራት እና በቤታችሁ ውስጥ ልታሳዩአቸው ትችላላችሁ። አዲስ ነገር ፈጣሪ ሁኑ!

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦“እዚህ ፍቅር ይወራል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 190–91።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ቅዱሳት መጻህፍትን አሳዩ። ያገኛችሁትን ትርጉም ያለው ጥቅስ ምረጡ፣ እናም የቤተሰብ አባላት ብዙውን ጊዜ በሚያዩበት ቦታ ላይ አስቀምጡት። ሌሎች የቤተሰብ አባላት አንድ የቅዱስ መጽሃፍ ጥቅስ ለማሳየት በየተራ እንዲመርጡ ጋብዙ።

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ

“የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? አንድ እንጀራ ስለ ሆነ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን” (1 ቆሮንቶስ 10፥16–17)።