“መስከረም 4–10 (እ.አ.አ) 1 ቆሮንቶስ 14–16፦ ‘እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]
“መስከረም 4–10 (እ.አ.አ) 1 ቆሮንቶስ 14–16፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
መስከረም 4–10 (እ.አ.አ)
1 ቆሮንቶስ 14–16
“እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም”
1 ቆሮንቶስ 14–16ን በምታነቡበት ጊዜ ግንዛቤዎቻችሁን መዝግቡ። መንፈስ ስላስተማራችሁ ነገር ጸልዩ፣ እናም እናንተ ተጨማሪ እንድትማሩ የሚፈልገው ነገር ካለ የሰማይ አባትን ጠይቁ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
በቆሮንቶስ ቤተክርስቲያኗ እና ትምህርቶቿ በአንጻሩ አዲስ ስለነበሩ፣ የቆሮንቶስ ቅዱሳን ግራ መጋባት አጋጥሟቸው እንደነበረ መረዳት ይቻላል። ጳውሎስ ቀደም ሲል የወንጌልን መሠረታዊ እውነት “ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ … እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ” (1 ቆሮንቶስ 15፥3–4) በማለት አስተምሯቸዋል። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ አንዳንድ አባላት “ትንሣኤ ሙታን የለም” (1 ቆሮንቶስ 15፥12) እያሉ ማስተማር ጀመሩ። ጳውሎስ የተማሩትን እውነት “[እንዲያስቡ]” (1 ቆሮንቶስ 15፥2) ተማጸናቸው። በወንጌል እውነቶች ላይ እርስ በርስ የሚጋጩ የሚመስሉ አስተያየቶች ሲያጋጥሙን “እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም” (1ቆሮንቶስ 14፥33) የሚለውን ማስታወስ ጥሩ ነው። የጌታን የተሾሙ አገልጋዮችን ማዳመጥ እና በተደጋጋሚ የሚያስተምሩትን ቀላል እውነቶች መያዛችን ሰላምን እንድናገኝ እና “በሃይማኖት [እንድንቆም]” (1 ቆሮንቶስ 16፥13) ይረዳናል።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
የትንቢትን ስጦታ መፈለግ እችላለሁ።
የትንቢት ስጦታ ምንድነው? የወደፊቱን የመተንበይ ችሎታ ነው? ለነቢያት ብቻ ነው? ወይም ይህን ስጦታ ማንም ሊቀበል ይችላል?
1 ቆሮንቶስ 14፥3፣ 31፣ 39–40ን ስታጠኑ እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ። በተጨማሪም ራዕይ 19፥10 እና በቅዱሳት መጻህፍት መመርያ ላይ “ትንቢት” (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) አንብቡ። በተማራችሁት መሠረት የትንቢት ስጦታን እንዴት ትገልጻላችሁ? ጳውሎስ ቆሮንቶስን “ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ” በማለት ሲጋብዝ ምን ማለቱ ሊሆን ይችላል? (1 ቆሮንቶስ 14፥39)። ይህንን ግብዣ እንዴት መቀበል ትችላላችሁ?
በተጨማሪም ኢዮኤል 2፥28–29፤ አልማ 17፥3፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥23–28ን ተመልከቱ።
በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለ ሴቶች ያለው መግለጫ ዛሬ እንዴት ይሠራል?
በጳውሎስ ዘመን ሴቶች በቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች ውስጥ ጨምሮ በማህበረሰቡ ውስጥ እንዴት መሳተፍ እንዳለባቸው የተለያዩ አመለካከቶች ነበሩ። በጳውሎስ ዘመን በ1 ቆሮንቶስ 14፥34–35 ላይ ያለው አስተምሮት ምንም ቢሆን ምን፣ ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሴቶች መናገር እና መምራት እንደሌለባቸው እየተናገረ እንደሆነ መረዳት አይገባም (ጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ 1 ቆሮንቶስ 14፥34 [በ1 ቆሮንቶስ 14፥34፣ የግርጌ ማስታወሻ ለ] ላይ ተመልከቱ)። ፕሬዘደንት ረስል ኤም. ኔልሰን ዛሬ ለቤተክርስቲያኗ ሴቶች “እኛ… ጥንካሬያችሁን፣ መለወጣችሁን፣ ጽኑ እምነታችሁን፣ የመምራት ችሎታችሁን፣ ጥበባችሁን እና ድምጻችሁን እንፈልጋለን። ቅዱስ ቃልኪዳኖችን የሚገቡ፣ ከዚያም የሚጠብቁ፣ በእግዚአብሔር ሀይል እና ስልጣን መናገር የሚችሉ ሴቶች በሌሉበት የእግዚአብሔር መንግስት ሙሉ አይደልም፣ ሊሆንም አይችልም!”። (“ለእህቶቼ ልመና፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 96)።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አደረገ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ለክርስትና በጣም መሠረታዊ ነው፣ አንድ ሰው ያለ እሱ ክርስትና የለም ሊል ይችላል፤ የጳውሎስን ቃላት ለመጠቀም፣ “እንግዲያውስ ስብከታችን ከንቱ ነው፣ እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት” (1 ቆሮንቶስ 15፥14)። ሆኖም አንዳንድ የቆሮንቶስ ቅዱሳን “ትንሣኤ ሙታን የለም” ብለው ያስተምሩ ነበር (1 ቆሮንቶስ 15፥12)። በ1 ቆሮንቶስ 15፣ ውስጥ የጳውሎስን ምላሽ በምታነቡበት ጊዜ፣ ትንሣኤን ባታምኑ ኖሮ ህይወታችሁ እንዴት የተለየ ሊሆን እንደሚችል ለማሰብ ትንሽ ጊዜ ውሰዱ (2 ኔፊ 9፥6–19፤ አልማ 40፥19–23፤ ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 93፥33–34)። “ክርስቶስ ካልተነሳ እምነታችሁ ከንቱ ናት” የሚለው ሐረግ ለእናንተ ምን ማለት ነው? (ቁጥር 17)።
በተጨማሪም ጳውሎስ ለሙታን ጥምቀትን ለትንሣኤው እውነት ማስረጃ አድርጎ መጥቀሱ ልብ ሊባል የሚገባው ነው (1 ቆሮንቶስ 15፥29ን ተመልከቱ)። የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ በትንሳኤ ትምህርት ላይ እምነታችሁን እንዴት አጠንክሯል?
በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 138፥11–37ን ተመልከቱ።
ከሞት የተነሱ አካላት ከሟች አካላት የተለዩ ናቸው።
የትንሣኤ አካል ምን እንደሆነ አስባችሁ ታውቃላችሁ? በ1 ቆሮንቶስ 15፥35፣ መሠረት አንዳንድ የቆሮንቶስ ሰዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ነበራቸው። በቁጥር 36–54፣ ውስጥ የጳውሎስን መልስ አንባቡ፣ እናም በሚሞቱ አካላት እና በትንሣኤ አካላት መካከል ያለውን ልዩነት የሚገልጹ ቃላትን እና ሀረጎችን ልብ በሉ። ይህን ስታደርጉ ቁጥሮች 40–42 ን ከ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥50–112፣ ጋር ማነጻጸር ትችላላችሁ። ይህ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የመጣው መገለጥ ግንዛቤያችሁ ላይ ምን ይጨምራል? (በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ 1 ቆሮንቶስ 15፥40 [በ1 ቆሮንቶስ 15፥40፣ የግርጌ ማስታወሻ ሃ] ተመልከቱ)። እነዚህ እውነቶች ለእናንተ ዋጋ ያላቸው የሆኑት ለምንድን ነው?
በተጨማሪም ሉቃስ 24፥39፤ አልማ 11፥43–45፤ ትምህርት እና ቃልኪዳ ኦች 88፥14–33ን ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
1 ቆሮንቶስ 15፥29።ከ ቁጥር 29 ልክ እንደዛሬው የጥንት ክርስቲያኖች በሙታን ጥምቀት እንደተሳተፉ እንማራለን። ለቅድመ አያቶቻችን ለምን እንደምንጠመቅ ለሌሎች እንዴት እንገልፃለን? (“የሙታን ጥምቀት ምንድነው?”) [ቪዲዮ]፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ)። ለሟች ቅድመ አያቶቻችን የቤተመቅደስ ስርዓቶችን ለመፈጸም እንደ ቤተሰብ ምን እያደረግን ነው? በዚህ ርዕስ ላይ ተጨማሪ ምንጮችን በወንጌል ርዕሶች ” “ለሙታን ጥምቀት” (topics.ChurchofJesusChrist.org) እና በFamilySearch.org፣ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።
-
1 ቆሮንቶስ 15፥35–54።ቤተሰባችሁ ጳውሎስ ሟች አካላት ከትንሣኤ አካላት እንዴት እንደሚለዩ የገለጸውን አንዳንድ ቃላትን እንዲረዱ ለማገዝ ምን ዓይነት ዕቃዎች ወይም ስዕሎች ልታሳዩ ትችላላችሁ? ለምሳሌ በሚበሰብሰው እና በማይበሰብሰው መካከል ያለውን ልዩነት ለማሳየት (ቁጥር 52–54ን ተመልከቱ) የዛገ ብረትን እና የማይዝግ ብረትን ማሳየት ትችላላችሁ። ወይም ደካማ ነገርን ከኃይለኛ ነገር ጋር ማነጻጸር ትችላላችሁ (ቁጥር 43ን ተመልከቱ)።
-
1 ቆሮንቶስ 15፥55–57።ቤተሰባችሁ በህይወት የሌለን ሰው የሚያውቅ ከሆነ ስለእነዚህ ጥቅሶች የሚደረግ ውይይት ትርጉም ያለው ሊሆን ይችላል። የቤተሰብ አባላት ኢየሱስ ክርስቶስ “የሞትን መውጊያን” እንዴት እንደወሰደ ምስክርነት ሊሰጡ ይችላሉ (ቁጥር 56)።
-
1 ቆሮንቶስ 16፥13።የቤተሰብ አባላት ከዚህ ጥቅስ ጋር እንዲዛመዱ ለማገዝ፣ መሬት ላይ ክብ መሳል እና አንድ የቤተሰብ አባል ዓይኖቹን ጨፍኖ በውስጡ “[እንዲቆም]” ማዘዝ ትችላላችሁ። ከዚያ ሌሎች እሱን ወይም እሷን ከክቡ ለመግፋት ወይም ለመሳብ ሊሞክሩ ይችላሉ። በክቡ ውስጥ ያለው ሰው ዓይኖቹ ሲከፈቱ እና “ንቁ” ሲሆኑ ምን ልዩነት አለው? መጥፎ ምርጫዎችን ለማድረግ ስንፈተን “[ጠንክረን ለመቆም]” ምን እናድርግ? (በተጨማሪ “በጀልባው ውስጥ ቆዩ እና ጠብቁ!፣” [ቪዲዮ] ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ)።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።
በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ተነስቷል፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 199።