አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
መስከረም 11–17 (እ.አ.አ)። 2 ቆሮንቶስ 1–7፦ “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ”


“መስከረም 11–17። (እ.አ.አ) 2 ቆሮንቶስ 1–7፦ ‘ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 11–17 (እ.አ.አ)። 2 ቆሮንቶስ 1–7፣ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ

መስከረም 11–17 (እ.አ.አ)

2 ቆሮንቶስ 1–7

“ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ”

ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የጻፋቸውን ደብዳቤዎች ስታጠኑ፣ ያገኛችሁትን አንዳንድ የወንጌል መርሆዎች ጻፉ እናም በሕይወታችሁ ውስጥ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

አንዳንድ ጊዜ፣ የቤተክርስቲያን መሪ መሆን ማለት አንዳንድ አስቸጋሪ ነገሮችን መናገር ማለት ነው። ልክ እንደዛሬው በጳውሎስ ዘመን ይህ እውነት ነበር። ከዚህ ቀደም ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቅዱሳን የጻፈው ደብዳቤ ተግሳጽ ስለነበረው ስሜቶችን ጎድቷል። ሁለተኛ ቆሮንቶስ በሆነው ደብዳቤ ውስጥ ከባድ ቃላትን እንዲጠቀም ያደረገውን፤ “በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበርና፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም” (2 ቆሮንቶስ 2፥4)፣ ብሎ ለማብራራት ሞክሯል። ከአንዳንድ መሪዎች የተወሰኑ እርማቶችን በምትቀበሉበት ጊዜ፣ እነሱ እንደ ክርስቶስ ባለ ፍቅር ተነሳስተው መሆኑን ማወቅ ይረዳል። እንደዚያም ባልሆነባቸው ሁኔታዎች እንኳን፣ ጳውሎስ እንደተሰማው ዓይነት ፍቅር ሌሎችን ለማየት ፈቃደኞች ከሆንን፣ ለማንኛውም ጥፋቶች ተገቢውን ምላሽ መስጠት ቀላል ይሆናል። ሽማግሌው ጄፍሪ አር. ሆላንድ ሲመክሩ፣ “ለሰው ደካማነት ደጎች ሁኑ—ለራሳችሁ እንዲሁም በበጎ ፈቃደኛ፣ ሟች ወንዶች እና ሴቶች በሚመራ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከእናንተ ጋር ለሚያገለግሉ። አንድያ ከሆነው ከፍጹሙ ልጁ በቀር፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ፍጹም ካልሆኑ ሰዎች ጋር አብሮ መሥራት ነበረበት” (“ጌታ ሆይ፥ አምናለሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ) 94)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

2 ቆሮንቶስ 1፥3–74፥6–10፣ 17–187፥4–7

የእኔ ፈተናዎች በረከት ሊሆኑ ይችላሉ።

ጳውሎስ በሕይወቱ ያጋጠሙትን ነገሮች ሁሉ ሲታሰቡ ስለ መከራ ዓላማዎች እና በረከቶች ብዙ መፃፉ አያስገርምም። 2 ቆሮንቶስ 1፥3–74፥6–10፣ 17–187፥4–7ን በምታነቡበት ጊዜ ፈተናዎቻችሁ በረከት ሊሆኑ ስለሚችሉባቸው መንገዶች አስቡ። ለምሳሌ እግዚአብሔር “[በመከራችሁ ሁሉ እንዴት እንደሚያጽናናችሁ]” ማሰብ እናም በተራ “በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት” (2 ቆሮንቶስ 1፥4) እንደምትችሉ ልታስቡ ትችላላችሁ። ወይም “[ስትገፉ]” እና “[ስታመነቱ]” (2 ቆሮንቶስ 4፥6፣ 8) እንኳን የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን በልባችሁ ውስጥ እንዴት “[እንደበራ]” ታተኩሩ ይሆናል።

በተጨማሪም ሞዛያ 24፥13–17፤ ሄንሪ ቢ.አይሪንግ “የተፈተነ፣ የተረጋገጠ እና የጠራ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ) 96–99፤ የወንጌል ርዕሶች “ጠላት፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

2 ቆሮንቶስ 2፥5–11

ይቅርታ እኔ መስጠትም መቀበልም የምችለው በረከት ነው።

ጳውሎስ በ2 ቆሮንቶስ 2፥5–11፣ ላይ ስለጠቀሰው ሰው ብዙም አናውቅም—እሱ መተላለፉን ብቻ (ቁጥር 5–6ን ተመልከቱ) እና ጳውሎስ ቅዱሳኑ ይቅር እንዲሉት መፈለጉን ብቻ ነው የምናውቀው (ቁጥር 7–8ን ተመልከቱ)። አንዳንድ ጊዜ የምንወደው ሰው ሲበድለን “[ፍቅራችንን ማጽናት]” ለምን ያቅተናል? (ቁጥር 8)። ይቅርታን አለመቀበል ሌሎችን እና እራሳችንን እንዴት ይጎዳል? (ቁጥር 7፥10–11ን ተመልከቱ)። ይቅርታን አለመቀበል “[በሰይጣን እንድንታለል]” የሚያደርገው እንዴት ነው? (ቁጥር 11)።

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥9–11ን ተመልከቱ።

2 ቆሮንቶስ 5፥14–21

በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ እችላለሁ።

እንደማንኛውም ሰው፣ ጳውሎስ “አዲስ ፍጥረት” (2 ቆሮንቶስ 5፥17)፣ መሆን ምን እንደሚመስል ያውቅ ነበር። እርሱ ከክርስቲያኖችን አሳዳጅነት ወደ ደፋር የክርስቶስ አስከባሪነት ተለወጠ። 2 ቆሮንቶስ 5፥14–21ን በምታነቡበት ጊዜ እንደነዚህ ያሉትን ጥያቄዎች አስቡ፤ ማስታረቅ ማለት ምን ማለት ነው? ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ምን ማለት ነው? ከእግዚአብሔር የሚለያችሁን ነገር አስቡ። ከእሱ ጋር ሙሉ በሙሉ ለመታረቅ ምን ማድረግ አለባችሁ? አዳኙ ያንን እንዴት የሚቻል ያደርጋል?

እንዲሁም “የማስታረቅም አገልግሎት” ውስጥ “[የክርስቶስ] መልዕክተኞች” (ቁጥሮች 18፣ 20) መሆን ምን ማለት እንደሆነ ልታስቡ ትችላላችሁ። ከሽማግሌው ጄፍሪ አር. ሆላንድ “የእርቅ አገልግሎት” መልእክት ምን ግንዛቤዎችን ታገኛላችሁ? (ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 77–79ን ተመልከቱ)።

በተጨማሪም 2 ኔፊ 10፥23–25ን ተመልከቱ።

2 ቆሮንቶስ 7፥8–11

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ወደ ንስሐ ይመራል።

እኛ ብዙውን ጊዜ ሀዘንን እንደ ጥሩ ነገር አንቆጥረውም፣ ነገር ግን ጳውሎስ “እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን” (2 ቆሮንቶስ 7፥10) እንደ አስፈላጊ የንስሐ ክፍል አድርጎ ተናግሯል። ከሚከተሉት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነ ኀዘን ምን እንደምትማሩ አስቡ፦ 2 ቆሮንቶስ 7፥8–11አልማ 36፥16–21ሞርሞን 2፥11–15፤ እና የእህት ሚሼል ዲ. ክሬግ መልእክት “መለኮታዊ ቅሬታ” (ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ) 52–55)። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን መቼ ተሰማችሁ፣ እናም በሕይወታችሁ ውስጥ ምን ተጽዕኖ አሳደረ?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

2 ቆሮንቶስ 3፥1–3የቤተሰባችሁ አባላት አንድ ሰው የሥራ ወይም የትምህርት ቤት የምስክር ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው ጠይቀው ያውቃሉ? ስለዚህ ተሞክሮ እንዲናገሩ ጠይቋቸው። የቅዱሳን ሕይወት ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንደ የምክር ደብዳቤዎች እንደነበር፣ “በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም” አልተጻፈም በማለት ጳውሎስ አስተምሯል። 2 ቆሮንቶስ 3፥1–3 ን አብራችሁ ስታነቡ ምሳሌዎቻችን የወንጌልን እውነት እና ዋጋ የሚያሳዩ “ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት” ደብዳቤዎች እንዴት እንደሚሆኑ ተወያዩ። ምናልባት እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሌላ የቤተሰብ አባል የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ጥሩ ምሳሌ መሆኑን የሚያብራራ ደብዳቤ ወይም “መልእክት” ሊጽፍ ይችላል። ለቤተሰባችሁ ደብዳቤዎቻቸውን አንብበው ለጻፉት የቤተሰብ አባል ሊሰጧቸው ይችላሉ። ሕይወታችን “የክርስቶስ መልእክቶች” መሆኑን መረዳት ለምን አስፈላጊ ነው?

2 ቆሮንቶስ 5፥6–7“በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስም” ማለት ምን ማለት ነው? አዳኙን ማየት ባንችልም እርሱን እንደምናምን ለማሳየት ምን እያደረግን ነው?

2 ቆሮንቶስ 5፡17አስደናቂ ለውጦች በሚያልፉ እና አዲስ ፍጥረታት የሚሆኑ ነገሮች ቤተሰባችሁ ሊያስብ ወይም ምሳሌዎችን ሊያገኝ ይችላል? (በዚህ ረቂቅ መጨረሻ ላይ ስዕሉን ተመልከቱ)። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እኛን እንዴት ሊለውጠን ይችላል?

2 ቆሮንቶስ 6፥1–102 ቆሮንቶስ 6፥1–10፣ መሠረት “እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች” ማለት ምን ማለት ነው? (ቁጥር 4)። የእግዚአብሔር አገልጋይ ምን ባሕርያት አሉት?

2 ቆሮንቶስ 6፥14–18በዙሪያችን ያሉትንም እየወደድን “ከመካከላቸው [ከአመጸኞች] ውጡና የተለያችሁ ሁኑ” የሚለውን የጳውሎስን ምክር መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “ውድ አባቴ፣ እርዳኝ፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ 99።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

በተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ትምህርቶችን አጋሩ። አንዳንድ የወንጌል ጽንሰ–ሐሳቦች፣ ለምሳሌ የኃጢያት ክፍያ፣ ለመረዳት አዳጋች ሊሆኑ ይችላሉ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ያገኛችሁትን መርሆዎች ቤተሰባችሁ እንዲረዳ የሚያግዙ ስዕሎችን ወይም ዕቃዎችን ለመጠቀም አስቡ።

ምስል
አባጨጓሬ፣ የእጭ ሽፋን እና ቢራቢሮ

ወደ ክርስቶስ ወንጌል ስንለወጥ፣ የእኛ መለወጥ በጣም ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ ጳውሎስ “አዲስ ፍጥረት” በማለት ገልጾታል (2 ቆሮንቶስ 5፥17)።

አትም