አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
መስከረም 18–24 (እ.አ.አ) 2 ቆሮንቶስ 8–13፦ “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል”


“መስከረም 18–24 (እ.አ.አ) 2 ቆሮንቶስ 8–13፦ ‘እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 18–24 (እ.አ.አ) 2 ቆሮንቶስ 8–13፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ ትንሽ ልጅ ሲያናግር

መስከረም 18–24 (እ.አ.አ)

2 ቆሮንቶስ 8–13

“እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል”

መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን መመዝገብ በቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ወቅት የተማራችሁትን ለማስታወስ ይረዳችኋል። በጥናት ደብተራችሁ ውስጥ መጻፍ፣ በቅዱሳት መጻህፍት ጠርዝ ላይ ማስታወሻዎችን ማድረግ፣ በወንጌል ቤተ መጽሐፍት መተግበሪያችሁ ውስጥ ማስታወሻዎችን ማከል ወይም የሐሳቦቻችሁን የድምፅ ቀረፃ ማድረግ ትችላላችሁ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በሌላ አካባቢ ያለ የቅዱሳን ጉባኤ በድህነት ውስጥ እየተሰቃየ መሆኑን ብትሰሙ ምን ታደርጋላችሁ? ይህ ሁኔታ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቅዱሳን በ2 ቆሮንቶስ 8–9፣ ላይ የገለጸው ነበር። ለተቸገሩት ቅዱሳን የተወሰነ እንዲለግሱ የቆሮንቶስን ቅዱሳን ለማሳመን ተስፋ አደረገ። ነገር ግን የጳውሎስ ቃላት መዋጮን ከመጠየቅ ባለፈ ስለመስጠት ጥልቅ እውነቶች ይዘዋል፤ “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም” (2 ቆሮንቶስ 9፥7)። በእኛ ዘመን፣ አሁንም በዓለም ዙሪያ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቅዱሳን አሉ ። አንዳንድ ጊዜ ለእነሱ ልናደርግላቸው የምንችለው መጾም እና የጾም በኩራት መለገስ ነው። በሌሎች ሁኔታዎች፣ የእኛ መስጠት ይበልጥ ቀጥተኛ እና ግላዊ ሊሆን ይችላል። የእኛ መስዋእትነት ምንም ይሁን ምን፣ ለመስጠት ያለንን ተነሳሽነት መመርመር ተገቢ ነው። መስዋእቶቻችን የፍቅር መግለጫዎች ናቸውን? ደግሞም ሰጪን ደስ የሚያሰኘው ፍቅር ነው።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

2 ቆሮንቶስ 8፥1–159፥5–15

ድሆችን እና ችግረኞችን ለመባረክ ያለኝን በደስታ ማካፈል እችላለሁ።

በዓለም ዙሪያ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ለውጥ ማምጣት እንዴት እንችላለን? ሽማግሌው ጄፍሪ አር. ሆላንድ ይህንን ምክር ሰጥተዋል፣ “ሀብታም ወይም ድሃ፥ ሌሎች እርዳታ ሲያስፈልጋቸው ‘የምንችለውን ማድረግ’ አለብን [ ማርቆስ 14፥6፣ 8ን ተመልከቱ]። … ከልብ የምትፈልጉ እና የምትጸልዩ እና እሱ የሰጣችሁን ትእዛዝ ደጋግማችሁ የምትጠብቁበትን መንገድ የምትፈልጉ ከሆነ [እግዚአብሔር] ይረዳችኋል፤ እናም ርህራሄ ባለው የደቀመዝሙርነት ሥራ ይመራችኋል”(“እኛ ሁላችንም ለማኞች አይደለንም?፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2014 (እ.አ.አ) 41)።

ጳውሎስ ድሆችን እና ችግረኞችን ስለመንከባከብ ያስተማረውን መሠረታዊ ሥርዓቶች በማስታወስ 2 ቆሮንቶስ 8፥1–159፥6–15ን አንብቡ። ስለ ጳውሎስ ምክር ምን ያነሳሳችኋል? የተቸገረን ሰው ለመባረክ ስለምታደርጉት ነገር ምሪት ለማግኘት መጸለይ ትችላላችሁ። የተቀበላችሁትን ማናቸውም ግንዛቤዎች መመዝገብ እናም በእነሱ ላይ እርምጃ መውሰዳችሁን አረጋግጡ።

በተጨማሪም ሞዛያ 4፥16–27አልማ 34፥27–29፤ ረስል ኤም. ኔልሰን “ሁለተኛይቱ ታላቅ ተእዛዝ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ) 96–100፤ ሄንሪ ቢ. ኡሪምግ “እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን?፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)፣ 22–25 ተመልከቱ።

2 ቆሮንቶስ 11፥1–6፣ 13–1513፥5–9

“በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ”

ዛሬ፣ ልክ እንደ ጳውሎስ ዘመን፣ “ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና” (2 ቆሮንቶስ 11፥3) እኛን ለማራቅ የሚሹ አሉ። በዚህ ምክንያት ጳውሎስ የጠቆመውን ማድረግ አስፈላጊ ነው፣ “በሃይማኖት ብትሆኑ ራሳችሁን መርምሩ” (2 ቆሮንቶስ 13፥5)። “በሃይማኖት [መሆን]” ምን ማለት እንደሆነ በማሰብ ይህንን ሂደት መጀመር ትችላላችሁ። በእምነት መሆናችሁን እንዴት ታውቃላችሁ? ራሳችሁን ለመመርመር እድሎችን ፈልጉ።

እንደ ምርመራችሁ አካል፣ “ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና” (2 ቆሮንቶስ 11፥3) የሚለውን ሐረግ ማሰላሰል ትችላላችሁ። በክርስቶስ እና በወንጌሉ ውስጥ ቅንነትና ንጽሕናን እንዴት አገኛችሁ? አዕምሯችሁ ከዚያ “ቅንነት እና ንጽህና” ተበላሽቶ ሚሆነው እንዴት ነው? በ2 ቆሮንቶስ 11፥1–6፣ 13–15ውስጥ ምን ጠቃሚ ምክርን ታገኛላችሁ?

እንዲሁም፣ ከፕሬዝደንት ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ የተሰጠውን ምክርም አስቡበት “ወንጌል ለእናንተ በደንብ እየሰራ እንዳልሆነ የምታስቡ ከሆነ፣ ወደ ኋላ እንድትመለሱ፣ ሕይወታችሁን ከፍ ካለ ቦታ እንድትመለከቱ እና የደቀ መዝሙርነት አቀራረባችሁን ቀለል አድርጉ። በወንጌሉ መሠረታዊ ትምህርቶች፣ መርሆዎች እና አተገባበር ላይ አተኩሩ። ወደ እርካታ ሕይወት በሚወስደው ጎዳናችሁ ላይ እግዚአብሔር እንደሚመራችሁ እና እንደሚባርካችሁ ፣ እናም ወንጌል በእርግጠኝነት ለእናንተ በተሻለ ሁኔታ እንደሚሠራ ቃል እገባለሁ” (“ድንቅ በሆነ መልኩ ይሰራል!፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 22)።

2 ቆሮንቶስ 12፥5–10

በድካሜ ውስጥ ብርታት እንዳገኝ የሚረዳኝ የአዳኙ ፀጋ በቂ ነው።

የጳውሎስ “[የሥጋ] መውጊያ” ምን እንደ ሆነ አናውቅም፣ ነገር ግን ሁላችንም እግዚአብሔር ከሕይወታችን እንዲያስወግድ የምንመኘው የራሳችን እሾህ አለን። 2 ቆሮንቶስ 12፥5–10ን በምታነቡበት ጊዜ ስለ እሾሃችሁን እና በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተማራችሁትን አስቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጳውሎስ ስለ ፈተናዎች እና ድክመቶች ምን አስተምሯል? የእግዚአብሔር “ጸጋ [ይበቃል]” ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው?

በተጨማሪም ሞዛያ 23፥21–2424፥10–15ኤተር 12፥27ሞሮኒ 10፥32–33ን ተመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

2 ቆሮንቶስ 8–9በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ለድሆች እና ለተቸገሩ ሌሎች እንድንደርስ የሚያነሳሳንን ምን እናገኛለን? ለተቸገረ ሰው እንደ ቤተሰብ አንድን አገልግሎት ለማቀድ ይህ ጥሩ ጊዜ ሊሆን ይችላል።

2 ቆሮንቶስ 9፥6–7ቤተሰባችሁ “በደስታ [የሚሰጥ]” ሊባል የሚችል ሰው ያውቃል? ለሌሎች የምንሰጠው አገልግሎት በደስታ የተሞላ እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ወጣት የቤተሰብ አባላት “እኔ በደስታ ሰጪ ነኝ” የሚሉ ባጆችን ማድረግ ይችላሉ። አንዳቸው ሌላውን በደስታ ሲያገለግሉ ባያችሁ ቁጥር ባጆቹን ለቤተሰብ አባላት መሸለም ትችላላችሁ።

2 ቆሮንቶስ 10፥3–7ከክፋት ጋር ስላለን “[ጦርነት]” ቤተሰባችሁን ማስተማር እንዴት ትችላላችሁ? በወንበሮች እና ብርድ ልብሶች ግድግዳ ወይም ምሽግ መገንባት ቤተሰባችሁን ሊያስደስት ይችላል? ይህ ከእግዚአብሔር የሚያርቁንን ነገሮች እንዴት መጣል እና “ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ [መማረክ]” እንደሚቻል ወደ ውይይት ሊያመራ ይችላል። ሀሳባችንን ለመቆጣጠር የምንጠቀምባቸው መንፈሳዊ “መሣሪያዎች” ምንድናቸው? (ኤፌሶን 6፥11–18ን ተመልከቱ)።

2 ቆሮንቶስ 11፥3“ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና” ላይ የበለጠ ለማተኮር ቤተሰባችሁ ምን ማድረግ ይችላል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “‘ትንሹ ወንዝ ስጡ ሲል ተናግሯል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 236።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ። ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስካት፣ “በጥንቃቄ የተመዘገበ እውቀት በተፈለገ ጊዜ የሚገኝ እውቀት ነው። … [መንፈሳዊ መመሪያን መመዝገብ] ተጨማሪ ብርሃን የመቀበል ዕድልላችሁን ያሰፋል” (“መንፈሳዊ እውቀትን ማግኘት፣” ኢንዛይን፣ ህዳር 1993 (እ.አ.አ)፣ 88፤ በተጨማሪም በአዳኙ መንገድ ማስተማር12፣ 30ን ይመልከቱ)።

ምስል
ወጣቶች በአገልግሎት ፕሮጀክት እየረዱ

“እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።” (2 ቆሮንቶስ 9፥7)።

አትም