አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
መስከረም 25–ጥቅምት 1 (እ.አ.አ)። ገላትያ፦ “በመንፈስ ተመላለሱ”


“መስከረም 25–ጥቅምት 1 (እ.አ.አ)። ገላትያ፦ ‘በመንፈስ ተመላለሱ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“መስከረም 25–ጥቅምት 1 (እ.አ.አ)። ገላትያ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ክርስቶስ ለጳውሎስ በእስር ቤት ተገለጠ

ትንሳኤ ያደረገው አዳኝ ለጳውሎስ በእስር ቤት ተገለጠ (የሐዋርያት ስራ 23፥11ን ይመልከቱ)። ኢየሱስ ክርስቶስ ”[ከ]ባርነት ቀንበር” (ገላትያ 5፥1) ነጻ ያወጣናል።

መስከረም 25–ጥቅምት 1 (እ.አ.አ)

ገላትያ

“በመንፈስ ተመላለሱ”

ገላትያን በምታነቡበት ጊዜ የተቀበላችሁትን ግንዛቤዎች መዝግቡ። እንዲህ ማድረጉ ወደፊት እንድታስታውሷቸው እና እንድታሰላስሏቸው ይረዳችኋል።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ከመንፈሳዊ ባርነት ነፃነትን ይሰጣል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የወንጌልን ነፃነት ያጣጣሙ ሰዎች ዞረው “እንደገና ባሪያዎች” ሆነው ለመኖር ይፈልጋሉ ((ገላትያ 4፥9)። አንዳንድ የገላትያ ቅዱሳን ያደርጉት የነበረው ይኸው ነበር—ክርስቶስ ከሰጣቸው ነፃነት እየራቁ ሄዱ (ገላትያ 1፥6ን ተመልከቱ)። በዚያን ጊዜ የጳውሎስ መልእክት ለገላትያ ሰዎች፣ “በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን” የሚል እንዲመለሱ አስቸኳይ ጥሪ ነበር (ገላትያ 5፥1)። ይህ ጥሪ እኛ ልንሰማው እና ልንተገብረው የሚገባ ነው ምክንያቱም ሁኔታዎች ሲለወጡ፣ በነጻነት እና በባርነት መካከል የሚደረግ ትግል ቀጣይ ስለሆነ ነው። ጳውሎስ እንዳስተማረው “ለአርነት [መጠራት]” (ገላትያ 5፥13) ብቻ በቂ አይደለም፤ እኛም በክርስቶስ በመታመን በውስጡ “[ጸንተን መቆም]” አለብን (ገላትያ 5፥1)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ገላትያ 1–5

የክርስቶስ ህግ ነፃ ያወጣኛል።

ጳውሎስ የገላትያ ቅዱሳን በሐሰት ትምህርቶች እየሳቱ እንደሆነ ባወቀ ጊዜ ጻፈላቸው (ገላትያ 1፥6–9)። ከእነዚህ ትምህርቶች አንዱ ወንጌልን የተቀበሉ አሕዛብ ለመዳን መገረዝ እና ሌሎች የሙሴን ሕግ ወጎች መጠበቅ አለባቸው የሚል ነበር (ገላትያ 2ን ተመልከቱ)። ጳውሎስ እነዚህን ወጎች “የባርነት ቀንበር” ብሎ ጠርቷቸዋል (ገላትያ 5፥1)። ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች የሰጠውን ምክር በምታነቡበት ጊዜ ፣ እውነተኛ ነፃነት ምን እንደሆነ ለመረዳት የሚረዷችሁን መሠረታዊ ሥርዓቶች ፈልጉ። እንዲሁም በሕይወታችሁ ውስጥ ምን የሐሰት ወጎች ወይም ሌሎች የባርነት ቀንበርዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ማሰላሰል ትችላላችሁ። ወንጌል የሚሰጠውን ነፃነት እንዳታጣጥሙ የሚያግዳችሁ ነገር አለ? ክርስቶስ እና የእርሱ ወንጌል “ነፃ ያወጧችሁ” እንዴት ነው? (ገላትያ 5፥1)።

በተጨማሪም 2 ኔፊ 2፥279፥10–12ን ይመልከቱ።

ገላትያ 3

ለአብርሃም ቃል የተገባለትን በረከቶች ወራሽ ነኝ።

አንዳንድ የገላትያ ቅዱሳን በቀጥታ የአብርሃም ትውልዶች (“ዘር”) ስላልሆኑ፣ ከፍ ከፍ ማለትን ጨምሮ ለአብርሃም ቃል የተገባላቸውን በረከቶች እንደማያገኙ አሳስቧቸው ነበር። በገላትያ 3፥7–9፣ 13–14፣ 27–29፣ መሠረት አንድ ሰው “የአብርሃም ዘር” እንዲሆን የሚያበቃው ምንድነው?

ለአብርሃም ስለተሰጡት በረከቶች እና እንደ ዘሩ ልንወርሳቸው የምንችላቸውን በረከቶች ለማወቅ፣ የወንጌል ርዕሶችን “የአብርሃም ኪዳንን፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ። ለአብርሃም ቃል የተገባላቸው በረከቶች ለእናንተ አስፈላጊ የሆኑት ለምንድነው?

ገላትያ 3፥6–25

አብርሃም የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ነበረው።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ በማለት አብራርቷል፤ “በሁሉም ዘመናት የነበሩት የጥንት ሰዎች ብዙዎች እንደሚገምቱት ስለ መንግሥተ ሰማያት ሥርዓት አያውቁም ነበር ብለን አናምንም፣ ምክንያቱም ሁሉም የዳኑት፣ እንዲሁ ከክርስቶስ መምጣት በፊት በዚህ ታላቅ የመዳን ዕቅድ ኃይል አማካኝነት ስለሆነ ነው። … አብርሃም መስዋእት አቀረበ፣ ይህ ቢሆንም፣ ወንጌሉ ተሰብኮለት ነበር” (“በከርትላንድ የሚገኘው የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ለወንድሞቻቸው በውጭ አገር፣” የምሽት እና የማለዳ ኮከብ፣ መጋቢት 1834 (እ.አ.አ) 143፣ JosephSmithPapers.org)። በጳውሎስ ዘመን ለነበሩ ቅዱሳን አብርሃምና ሌሎች የጥንት ነቢያት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንዳላቸው ማወቃቸው ለምን አስፈላጊ ይመስላችኋል? ይህንን ማወቅ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? (ሔላማን 8፥13–20ሙሴ 5፥58–596፥50–66ን ተመልከቱ።)

የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፤ ጆሴፍ ስሚዝ (2007 [እ.አ.አ])፣ 45–56ን ተመልከቱ።

ገላትያ 5፥13–266፥7–10

“በመንፈስ [ብመላለስ]” “የመንፈስን ፍሬ” እቀበላለሁ።

እነዚህን ጥቅሶች ማጥናት በመንፈስ ምን ያህል እየተራመዳችሁ እንደሆነ ለመገምገም ይረዳችኋል። በቁጥሮች 22–23፣ ውስጥ የተጠቀሰውን የመንፈስ ፍሬ እያጣጣማችሁ ነውን? ከመንፈሳዊ አኗኗር ሌላ ፍሬ ወይም ውጤት ምን አስተውላችኋል? ይህንን ፍሬ ይበልጥ ለማዳበር ምን ማድረግ እንዳለባችሁ አስቡ። ይህንን ፍሬ ማልማት በሕይወታችሁ ውስጥ ያሉትን አስፈላጊ ግንኙነቶች እንዴት ያሻሽላል?

አፕል በዛፍ ላይ

በህይወቴ ውስጥ “የመንፈስን ፍሬ” መፈለግ አለብኝ።

በመንፈስ ለመራመድ እየሞከራችሁ ከሆነ ነገር ግን ጥረቶቻችሁ ቃል የተገባውን ፍሬ ያፈሩ ካልመሰላችሁ ገላትያ 6፥7–10ን አንብቡ። ጌታ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ለእናንተ ምን መልዕክት እንዳለው ይሰማችኋል?

በተጨማሪም አልማ 32፥28፣ 41–43ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥32–34ን ተመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ገላትያ 3፡11“በእምነት [መኖር]” ምን ማለት ነው? እንደ ቤተሰብ በእምነት እንዴት እየኖርን ነው?

ገላትያ 4፥1–7በንጉሥ አገልጋዮች እና በልጆቹ መካከል ስላለው ልዩነት በመወያየት ገላትያ 4 ን ማስተዋወቅ ትችላላችሁ። የንጉሥ ልጅ አንድ አገልጋይ የሌለው ምን ዕድሎች ወይም አቅም አለው? ቁጥሮች 1–7፣ አብራችሁ ስታነቡ ይህን አስቡ። እነዚህ ጥቅሶች ከሰማይ አባት ጋር ስላለን ግንኙነት ምን ያስተምራሉ?

ገላትያ 5፥16–26“በሥጋ ሥራ” እና “በመንፈስ ፍሬ” መካከል ያለውን ልዩነት ለመወያየት አስቡ። በውይይታችሁ ላይ ደስታን ለመጨመር፣ ቤተሰባችሁ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ጳውሎስ የመንፈስ ፍሬን ለመግለጽ በተጠቀመባቸው ቃላት ሊለይ ይችላል። ከዚያ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አንዱን መምረጥ፣ መግለፅ እና የዚያን ፍሬ ተምሳሌት አድርገው ስለሚመለከቱት ሰው ማውራት ይችላሉ። ይህ ቤተሰባችሁ መንፈስን ወደ ቤታችሁ እንዲጋብዝ እና ይህን ፍሬ እንዲያዳብር ስለሚችሉባቸው መንገዶች ውይይት ሊያመራ ይችላል። ከውይይቱ በኋላ አብራችሁ በፍራፍሬ ሰላጣ መደሰት ትችላላችሁ።

ገላትያ 6፥1–2ከቤተሰባችሁ ውስጥ አንድ ሰው “በደል [የተገኘበት]” ጊዜ ሊኖር ይችላል። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ በገላትያ 6፥1–2 ላይ ምን ምክር ታገኛላችሁ?

ገላትያ 6፥7–10ቤተሰባችሁ በአንድነት አንድ ነገር ተክሎ የሚያውቅ ከሆነ፣ ያንን ተሞክሮ በመጠቀም “ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል” (ቁጥር 7) የሚለውን መርህ ማብራራት ይችላል። ወይም የቤተሰብ አባላትን ስለሚወዷቸው ፍራፍሬዎች ወይም አትክልቶች ጠይቁ እና ያንን ምግብ የሚያመርትን ተክል ለማልማት ስለሚያስፈልገው ነገር ተናገሩ። (በዚህ ረቂቅ መጨረሻ ላይ ስዕሉን ተመልከቱ።) ቤተሰባችሁ ሊያገኛቸው ስለሚጠብቃቸው በረከቶች እና እነዚያን በረከቶች እንዴት “እንደሚያጭዱ” ማውራት ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “በብርሃኑ እንድጓዝ አስተምሩኝ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 177።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ቤተሰቦቻችሁ ቅዱሳት መጻህፍትን ከራሳቸው ጋር እንዲያመሳስሏቸው እርዷቸው። ኔፊ “ለእኛ ጥቅምና ትምህርት ይሆኑ ዘንድ ሁሉንም ጥቅሶች ከእኛ ጋር [ማመሳሰል]” ይገባናል (1 ኔፊ 19፥23) ብሎ ተናግሯል። ቤተሰባችሁ ይህንን እንዲያደርግ በገላትያ 5፥22–23፣ ውስጥ የተገለጸውን የመንፈስ ፍሬ ያገኙበትን ጊዜ እንዲያሰላስሉ መጋበዝ ትችላላችሁ። (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 21ን ተመልከቱ።)

በዛፍ ላይ

ጳውሎስ በመንፈስ ስንመላለስ በህይወታችን ውስጥ “የመንፈስን ፍሬ” እንደምናገኝ አስተምሯል።