“ጥቅምት 9–15 (እ.አ.አ) ፊልጵስዩስ፤ ቆላስይስ፦ ‘ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) (2022 (እ.አ.አ))
“ጥቅምት 9–15 (እ.አ.አ) ፊልጵስዩስ፤ ቆላስይስ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 9–15 (እ.አ.አ)
ፊልጵስዩስ፤ ቆላስይስ
“ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ”
አዲስ ኪዳንን በምታጠኑበት ወቅት የመዘገባችሁትን መንፈሳዊ ግንዛቤ ለመጨረሻ ጊዜ ያነበባችሁት መቼ ነበር? የተቀበላችሁትን መነሳሳቶች መገምገም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።
ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ
ጳውሎስ በሮም እስረኛ በነበረበት ጊዜ ለፊልጵስዩስና ለቆላስይስ ሰዎች መልእክቶቹን ጽፏል። ነገር ግን እነዚህ ደብዳቤዎች በእስር ቤት ካለ ሰው የሚጠብቁ ቃና የላቸውም። ጳውሎስ ስለ መከራዎች እና ፈተናዎች ከመናገር ይልቅ ስለ ደስታ፣ ስለ ሃሴት እና ስለ ምስጋና ብዙ ተናግሯል፤ “ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል” (ፊልጵስዩስ 1፥18)። እናም “በሥጋ ምንም እንኳ ብርቅ፣ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና … በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል” ((ቆላስይስ 2፥5)። በእርግጥ ጳውሎስ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያገኘው “የእግዚአብሔር ሰላም” “ማስተዋልን ሁሉ ያልፋል” ((ፊልጵስዩስ 4፥7)፣ እውንም ነበር። በእራሳችን ፈተናዎች ውስጥ ይህ ተመሳሳይ ሰላም ሊሰማን እና “ሁልጊዜ በጌታ ደስ [ሊለን]” ይችላል (ፊልጵስዩስ 4፥4)። ልክ እንደ ጳውሎስ፣ “[ቤዛ በሆነው“ በኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ መታመን እንችላለን (ቆላስይስ 1፥14)። “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” ማለት እንችላለን (ፊልጵስዩስ 4፥13፤ በተጨማሪም ቆላስይስ 1፥11ን ተመልከቱ)።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
እምነቴ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ነው።
ፕሬዘደንት ረስል ኤም. ኔልሰን የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ላይ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚጠቅሱ ጥቅሶች ላይ ሲያተኩር “የተለየ ሰው” እንደሆነ እንዲሰማው ተጽዕኖ ፈጥሮበታል። (“የኢየሱስ ክርስቶስን ሀይል ወደ ህይወታችን መሳብ፣” ሊያሆና፣፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 39)። (ፊልጵስዩስ 2፥5–11፤ ቆላስይስ 1፥12–23) በምታነቡበት ጊዜ የእርሱን ምሳሌ ለመከተል አስቡ። ስለ አዳኙ ምን ትማራላችሁ? እነዚህ እውነቶች “የተለየ ወንድ” ወይም ሴት እንድትሆኑ እንዴት ይረዷችኋል?
“የራሳች[ንን] መዳን [እንፈጽማለን]”?
በራሳችን ጥረቶች ብቻ ድነናል የሚለውን ሀሳብ ለመደገፍ አንዳንድ ሰዎች “የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ” (ፊልጵስዩስ 2፥12) የሚለውን ሐረግ ይጠቀማሉ። ሌሎች “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና” (ኤፌሶን 2፥8) የሚለውን የጳውሎስ ትምህርት ለመዳን ምንም ሥራ አያስፈልግም ብለው ለመናገር ይጠቀሙበታል። ሆኖም፣ የቅዱሳት መጻህፍት፣ የጳውሎስን ጽሑፎች ጨምሮ፣ መዳንን ለማግኘት የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና የግል ጥረት አስፈላጊነት በግልፅ ያስተምራሉ። እናም የእኛን መዳናችንን ለመፈጸም የተቻለንን ለማድረግ ሁሉ ስንጥር፣ “[በእኛ] የሚሠራ እግዚአብሔር ነው” (ፊልጵስዩስ 2፥13፤ በተጨማሪም ፊልጵስዩስ 1፥6፤ 2 ኔፊ 25፥23፤ የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላይ “ፀጋ”ን ይመልከቱ)።
የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እያንዳንዱ መሥዋዕት የሚገባው ነው።
ጳውሎስ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሲቀይር ብዙ ነገር አሳልፎ ሰጥቷል፤ በአይሁድ ማህበረሰብ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ፈሪሳዊ የነበረበትን ቦታ ጭምር። በፊልጵስዩስ 3፥4–14፣ ላይ ጳውሎስ ለወንጌል መሥዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኛ ስለነበረ ያገኘውን ፈልጉ። ስለ ከፈለው መስዋዕት ምን ተሰማው?
ከዚያ የራሳችሁን ደቀ መዝሙርነት አስቡ። ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምን መሥዋዕት አድርጋችኋል? ምንስ ተቀበላችሁ? ይበልጥ ቁርጠኛ የአዳኙ ደቀ መዝሙር ለመሆን የሚያስፈልጓችሁ ተጨማሪ መስዋዕቶች አሉ?
በተጨማሪም 3 ኔፊ 9፥19–20፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥2–5፤ ቴይለር ጂ. ጎዶይ “አንድ ተጨማሪ ቀን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ) 34–36ን ተመልከቱ።
ሁኔታዬ ምንም ይሁን ምን በክርስቶስ ደስታን ማግኘት እችላለሁ።
የጳውሎስ ሕይወት በፕሬዝደንት ረስል ኤም ኔልሰን የተገለፀውን የእውነት ቁልጭ ያለ ምሳሌ ነው፤ “የሕይወታችን ትኩረት … በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ ከሆነ፣ በሕይወታችን ውስጥ ምን እየሆነ ቢሆን ወይም ባይሆን ደስታ ሊሰማን ይችላል። ደስታ የሚመጣው በእሱ እና ከእርሱ ነው” (“ደስታ እና መንፈሳዊ መትረፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ) 82)።
ፊልጵስዩስን—በተለይም ምዕራፍ 4ን—በምታነቡበት ጊዜ በማንኛውም የሕይወት ሁኔታ ደስታን ለማግኘት የሚረዱ መግለጫዎችን ፈልጉ። ፈታኝ በሆነ ጊዜ ውስጥ “የእግዚአብሔር ሰላም” ያገኛችሁት መቼ ነው? (ቁጥር 7)። ከባድ ነገሮችን ለማድረግ “በክርስቶስ” ኃይልን መቼ አግኝታችኋል? (ቁጥር 13)። በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ “[መርካት]” ለምን አስፈላጊ ይመስላችኋል? (ቁጥር 11)። በቁጥር 8 ውስጥ ያሉትን ባሕርያት መለማመድ በሁኔታዎቻችሁ ውስጥ ደስታን እንድታገኙ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?
ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ አልማ 33፥23፤ “በማንኛውም ሁኔታ አመስጋኝ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ) 70–77ን ተመልከቱ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የእርሱን ወንጌል ሲኖሩ “አዲስ” ይሆናሉ።
“አዲስ ሰው [ወይም ሴት]” እንድትሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ እየረዳችሁ መሆኑን እንዴት ማወቅ ትችላላችሁ? ይህንን ለማሰላሰል አንዱ መንገድ ቆላስይስ 3፥1–17 ን መመርመር እና የ “አሮጌው ሰው” አመለካከት፣ ባህሪያት እና ድርጊቶች ዝርዝር እና ሌላ “የአዲሱ ሰው” አመለካከት፣ ባህርይ እና ድርጊቶች በመዘርዘር ነው።
ወደፊት እንድትገመግሙ እና እንዴት እየገሰገሳችሁ እንዳለ ለማሰላሰል አዳኙ እንዴት እየቀየራችሁ እንደሆነ ሀሳቦቻችሁን መዝግቡ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ፊልጵስዮስ።ቤተሰባችሁ በፊልጵስዩስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ደስታ ወይም ሃሴት የሚሉ ቃላትን ያስተውሉ ይሆናል። እነዚህን ቃላት ባገኛችሁ ቁጥር፣ ጳውሎስ ደስታን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ያስተማረውን ቆም ብላችሁ መወያየት ትችላላችሁ።
-
ፊልጵስዮስ 2፥14–16።“በዓለም እንደ ብርሃን [መታየት]” እንዴት እንችላለን?
-
ፊልጵስዮስ 4፥8።የቤተሰብ አባላት በዚህ ጥቅስ ውስጥ ከተገለጹት መግለጫዎች ጋር የሚስማሙትን ለመለየት “ማሰብ” ይችላሉ (በተጨማሪም የእምነት አንቀጾች 1፥13ን ተመልከቱ)። የጳውሎስን ምክር በመከተል ቤተሰባችሁ እንዴት ይባረካል?
-
ቆላስይስ 1፥23፤ 2፥7።ምናልባት ቤተሰባችሁ በዛፍ ዙሪያ ተቀምጠው ወይም የዛፍ ምስል እየተመለከቱ (ለምሳሌ ከዚህ ረቂቅ ጋር ተያይዞ ያለውን) እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ ይችሉ ይሆናል። በክርስቶስ “[መመስረት]” እና “ሥር [መስደድ]” ማለት ምን ማለት ነው? እርስ በእርሳችን መንፈሳዊ ሥሮቻችንን ለማጠንከር እንዴት እንረዳዳለን?
-
ቆላስይስ 2፥2–3።በወንጌል ውስጥ ያገኙትን “ሀብት” እና “የጥበብና የእውቀት መዝገብ” በሚወክሉ ነገሮች ቤተሰባችሁ የ“ሀብት ሣጥን” በመሙላት ይደሰቱ ይሆናል።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።
በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ተደሰቱ፣ ጌታ ንጉስ ነው!፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 66።