“ጥቅምት 23–29 (እ.አ.አ) 1 እና 2 ጢሞቴዎስ፤ ቲቶ፤ ፊልሞና፦ ‘[ለሚያምኑ] … ምሳሌ ሁን’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]
“ጥቅምት 23–29 (እ.አ.አ) 1 እና 2 ጢሞቴዎስ፤ ቲቶ፤ ፊልሞና፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 23–29 (እ.አ.አ)
1 እና 2 ጢሞቴዎስ፤ ቲቶ፤ ፊልሞና
“[ለሚያምኑ] ምሳሌ ሁኑ”
አንዳንድ ጊዜ አንድ ወይም ጥያቄዎችን በማሰብ የቅዱሳን መጽህፍት ጥናታችሁን መጀመር ጠቃሚ ነው። በምታጠኑበት ጊዜ ወደ መልሶች እንዲመራችሁ መንፈስን ጋብዙ፣ የምታገኙትንም ማንኛውንም መነሳሳት መዝግቡ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ፣ ለቲቶ እና ለፊልሞና በጻፈው መልእክቶቹ ውስጥ የጌታ አገልጋይ ልብ ውስጥ ስላለው ፍንጭ እናገኛለን። ጳውሎስ ለጠቅላላ ጉባኤ ከጻፋቸው ከሌሎቹ መልእክቶቹ በተለየ፣ እነዚህ የተጻፉት ለግለሰቦች ማለትም ለጳውሎስ የቅርብ ወዳጆች እና በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ አጋሮች ነው—እናም እነሱን ማንበብ ንግግር እንደማዳመጥ ነው። ጳውሎስ ሁለቱ የጉባኤ መሪዎችን ጢሞቴዎስን እና ቲቶን በቤተክርስቲያናቸው አገልግሎት ሲያበረታታቸው እናያለን። ጓደኛው ፊልሞና ከአንድ ቅዱስ ጋር እንዲታረቅና በወንጌል እንደ ወንድም እንዲይዘው ሲማጸነው እናያለን። የጳውሎስ ቃላት በቀጥታ ለእኛ አልተነገሩንም፣ ብዙ ሰዎች አንድ ቀን ያነቡታል ብሎ በፍፁም ላይጠብቅ ይችላል። ሆኖም በክርስቶስ አገልግሎት የግል አገልግሎታችን ምንም ይሁን ምን በእነዚህ መልእክቶች ውስጥ ለእኛ ምክር እና ማበረታቻ እናገኛለን።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ጢሞቴዎስ እና ቲቶ እነማን ነበሩ?
ጢሞቴዎስ እና ቲቶ በአንዳንድ ሚስዮናዊ ጉዞዎቹ ላይ ከጳውሎስ ጋር አገልግለዋል። በአገልግሎታቸው ወቅት የጳውሎስን አክብሮት እና እምነት አግኝተዋል። ጢሞቴዎስ በኤፌሶን ውስጥ የቤተክርስቲያን መሪ ተብሎ ተጠራ፣ ቲቶ በቀርጤስ መሪ ተባለ። በእነዚህ መልእክቶች ውስጥ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እና ለቲቶ ትምህርት እና ማበረታቻ ሰጥቷቸዋል፣ ይህም ወንጌልን መስበክ እና ሰዎችን እንደ ኤጲስ ቆጶስ እንዲያገለግሉ መጠራትን ይጨምራል።
በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ–ቃላት “የጳውሎሳዊ መልእክቶችን፣” “ጢሞቴዎስ፣” “ቲቶ”ን ተመልከቱ።
“[ለሚያምኑ] … ምሳሌ ሁን።”
ጢሞቴዎስ በአንጻራዊ ሁኔታ ወጣት ነበር፣ ነገር ግን ጳውሎስ በወጣትነቱ ጊዜ ታላቅ የቤተክርስቲያን መሪ መሆን እንደሚችል ያውቅ ነበር። በ1 ጢሞቴዎስ 4፥10–16፣ ውስጥ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ምን ምክር ሰጠ? ይህ ምክር ሌሎችን ወደ አዳኙ እና ወደ ወንጌል እንድትመሩ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?
በተጨማሪም አልማ 17፥11ን ይመልከቱ።
“እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።”
2 ጢሞቴዎስ ጳውሎስ የጻፈው የመጨረሻው መልእክት እንደሆነ ይታመናል፣ እናም በምድር ላይ ያለው ጊዜ አጭር መሆኑን ያወቀ ይመስላል (2 ጢሞቴዎስ 4፥6–8)። ጢሞቴዎስ በቅርቡ የሚታመንበት አማካሪውና መሪውን እንደሚያጣው በማወቁ ምን ተሰምቶት ሊሆን ይችላል? ጳውሎስ እሱን ለማበረታታት ምን አለ? እንዲሁም የራሳችሁን ተግዳሮቶች እና ፍርሃቶች በአዕምሯችሁ ውስጥ በማሰብ ታነቡ ይሆናል። በ2 ጢሞቴዎስ፣ ውስጥ ጌታ ለእናንተ ምን ተስፋ እና ማበረታቻ መልእክቶች አሉት?
በተጨማሪም ኬሊ አር. ጆንሰን፣ “የመጽናት ሃይል፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 112–14 ተመልከቱ።
ወንጌልን መኖር ከመጨረሻዎቹ ቀናት መንፈሳዊ አደጋዎች ደህንነት ይሰጠናል።
የምንኖረው ጳውሎስ በተናገረው “በመጨረሻው ቀን” ውስጥ ሲሆን የሚያስጨንቅ ዘመን” ደርሷል (2 ጢሞቴዎስ 3፥1)። 2 ጢሞቴዎስ 3ን በምታነቡበት ጊዜ የተጠቀሱትን የመጨረሻ ቀናት አደጋዎች ፃፉ (በተጨማሪ 1 ጢሞቴዎስ 4፥1–3)።
በዙሪያዎ ባለው ዓለም—ወይም በራሳችሁ ሕይወት ውስጥ የእነዚህን አደጋዎች ምሳሌዎች ማሰብ ትችላላችሁ? በቁጥር 6፣ ላይ እንደተገለጹት ሰዎች እነዚህ አደጋዎች “ወደ ቤታችሁ ሾልከው ገብተው የሚማርኩት” እንዴት ነው? በ2 ጢሞቴዎስ 3፣ ውስጥ እና ሌላ ቦታ በእነዚህ መልእክቶች ውስጥ እናንተን እና ቤተሰባችሁን ከእነዚህ መንፈሳዊ አደጋዎች እንድትጠብቁ የሚረዳችሁ ምን ምክር አለ? (1 ጢሞቴዎስ 1፥3–11፤ 2 ጢሞቴዎስ 2፥15–16፤ ቲቶ 2፥1–8ን ይመልከቱ)።
ፊልሞና ማን ነበር?
ፊልሞና በጳውሎስ ወደ ወንጌል የተቀየረ ክርስቲያን ነበር። አናሲሞስ የሚባል ባሪያ ነበረው ፊልሞና፣ እሱም ወደ ሮም ሸሽቶ ነበር። በዚያ አናሲሞስ ጳውሎስን አግኝቶ ወደ ወንጌል ተለወጠ። ጳውሎስ “እንደ ባሪያ [ሳይሆን] … የተወደደ ወንድም [እንደሆነ]” በማሰብ አናሲሞስን እንዲቀበለው በአናሲሞስ ደብዳቤ ወደ ፊልሞና መልሶ ላከ (ፊልሞና 1፥16)።
የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እርስ በእርስ እንደ ወንድሞች እና እህቶች ናቸው።
የጳውሎስን መልእክት ለፊልሞና ስታነቡ፣ ምክሩን ከሌሎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት እንዴት ተግባራዊ እንደምታደርጉ አሰላስሉ። ሊታሰብባቸው የምትችሏቸው አንዳንድ ጥያቄዎች ከዚህ በታች አሉ፦
-
ቁጥሮች 1–7፦ በቅዱሳን መካከል ስላለው ግንኙነት እንደ “አብሮ የሚሰራ” እና “አብሮ ወታደር ለሆነ” ያሉ ቃላት ለእናንተ ምን ይጠቁማሉ? በክርስቶስ አንድ ወንድም ወይም እህት “[ሲያርፍ]” የተሰማችሁ መቼ ነው?
-
ቁጥሮች 8–16፦ “ማዘዝ” እና “መለመን” ማለት ምን ማለት ነው? ጳውሎስ ፊልሞናን ከማዘዝ ይልቅ ለመለመን ለምን መረጠ? ጳውሎስ አናሲሞስን ወደ ፊልሞና መልሶ በመላክ ይፈጸማል ብሎ ተስፋ ያደረገው ምንድን ነው?
-
ቁጥር 16፦ “በጌታ … የተወደደ ወንድም [ወይም እህት]” ማለት ምን ማለት ነው? በዚህ መንገድ መቀበል ያለባችሁ ሰው ታውቃላችሁ?
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
1 ጢማቴዎስ 2፥9–10።ራሳችንን “መልካም በማድረግ ማስዋብ” ማለት ምን ማለት ነው? በዚህ ሳምንት ቤተሰባችን ሊያደርጋቸው የሚችሏቸው አንዳንድ ጥሩ ሥራዎች ምንድን ናቸው? ለምሳሌ እንደ “መልካም ነገር አድርጌያለሁ?” የመሳሰሉ መዝሙሮችን አብራችሁ ልትዘምሩ ትችላላችሁ። (መዝሙሮች፥ ቁጥር 223)።
-
1ኛ ጢሞቲዎስ 4፣12።የቤተሰባችሁ አባላት “የአማኞች ምሳሌ” ለመሆን እንዲመኙ ለማገዝ፣ ለእነሱ ጥሩ ምሳሌ የሆኑ ሰዎችን ስዕል እንዲስሉ መጋበዝን አስቡ። እነዚህ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንከተል ያነሳሱን እንዴት ነው? የፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን መልእክት “ምሳሌ እና ብርሃን ሁኑ” (ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 86–88) ለሌሎች ምሳሌ መሆን እንዴት እንደሚቻል አንዳንድ ሀሳቦችን ሊሰጥ ይችላል።
-
1 ጢማቴዎስ 6፥7–12።“ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ” የሆነው ለምን ይመስላችኋል? ሕይወታችንን በገንዘብ ወይም በንብረት ላይ ማተኮር ምን አደጋዎች አሉት? ባለን በረከቶች እንዴት መርካት እንችላለን?
-
2 ጢማቴዎስ 3፥14–17።በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት ቅዱሳት መጻህፍትን ለሚያውቁ እና ለሚያጠኑ ምን በረከቶች ይመጣሉ? ምናልባት የቤተሰብ አባላት በተለይ “ትርፋማ” ሆኖ ያገኙትን ጥቅሶች ሊያጋሩ ይችላሉ።
-
ፊልሞና 1፥17–21።ጳውሎስ ለአናሲሞስ ምን ለማድረግ ፈቃደኛ ነበር? ይህ አዳኙ በፈቃዱ ካደረገልን ጋር እንዴት ይመሳሰላል? (በተጨማሪ 1 ጢሞቴዎስ 2፥5–6፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥3–5ን ተመልከቱ)። የጳውሎስን እና የአዳኙን ምሳሌዎች መከተል የምንችለው እንዴት ነው?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።
በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “አብሩ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 144።