አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 30–ህዳር 5 (እ.አ.አ) ዕብራውያን 1–6፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ‘የዘላለም ደህንነት ደራሲ’”


“ጥቅምት 30–ህዳር 5 (እ.አ.አ)። ዕብራውያን 1–6፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ‘የዘላለም ደህንነት ደራሲ”’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ጥቅምት 30– ህዳር 5 (እ.አ.አ) ዕብራውያን 1–6፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ክርስቶስ ከአንዲት ወጣት ሴት ጋር ቆሞ

በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት፣ በአኒ ሄንሪ

ጥቅምት 30–ህዳር 5

ዕብራውያን 1–6

ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “የዘላለም ደህንነት ደራሲ”

መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን መመዝገብ መንፈስ ቅዱስ ሊያስተምራችሁ የሚፈልገውን ለመለየት ይረዳችኋል። ግንዛቤዎቻችሁ ላይ እርምጃ መውሰድ እነዚያ መነሳሳቶች እውን ስለመሆናቸው እምነታችሁን ያሳያል።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለመቀበል እያንዳንዳችን የሆነ ነገር መተው አለብን—መጥፎ ልምዶች፣ ትክክል ያልሆኑ እምነቶች፣ ጤናማ ያልሆኑ ህብረቶች ወይም ሌላ ነገር። በጥንታዊቷ የክርስቲያን ቤተክርስቲያን ውስጥ ለአሕዛብ መለወጥ ብዙውን ጊዜ የሐሰት አማልክትን መተው ማለት ነበር። ለዕብራውያን (ወይም ለአይሁዶች)፣ መለወጥ ይበልጥ ከባድና የተወሳሰበ ነበር። ለነገሩ፣ የተከበሩ እምነታቸው እና ወጎቻቸው በእውነተኛው አምላክ አምልኮ እና በነቢያቶቹ ትምህርት ላይ የተመሠረተ እና ለብዙ ሺህ ዓመታት የዘለቀ ነበር። ሆኖም ሐዋርያት የሙሴ ሕግ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተፈጸመ እና ከፍ ያለ ሕግ አሁን ለአማኞች መመዘኛ መሆኑን አስተምረዋል። ዕብራውያን ክርስትናን ለመቀበል የቀድሞ እምነታቸውን እና ታሪካቸውን መተው ነበረባቸው ማለት ነው? የዕብራውያን መልእክት የሙሴ ህግ፣ የነቢያት ሕግ እና ሥርዓቶች ሁሉ አስፈላጊ እንደሆኑ በማስተማር እንደዚህ ያሉትን ጥያቄዎች ለመፍታት ለመርዳት ፈለገ፣ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጣል (ዕብራውያን 1፥1–43፥1–67፥23–28ን ተመልከቱ)። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እና አይሁድ ሲጠብቁት የነበረው የተስፋው መሲሕ እንደሆነ ያሳያሉ።

መለወጥ፣ በእነዚያ ቀደምት ቀናት እና ዛሬ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የአምልኮታችን እና የሕይወታችን ማዕከል ማድረግ ማለት ነው። “ለሚታዘዙት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት” ነውና እርሱን በእውነት አጥብቀን መያዝ እና ከእርሱ የሚለየንን መተው ማለት ነው (ዕብራውያን 5፥9)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ለዕብራውያን መልእክት የጻፈው ማነው?

አንዳንድ ሊቃውንት ጳውሎስ መልእክቱን ለዕብራውያን ተጽፎ እንደሆን ተጠራጥረዋል። የዕብራውያን የአጻጻፍ ዘይቤ ከሌሎቹ የጳውሎስ ደብዳቤዎች በተወሰነ መልኩ የተለየ ነው፣ እና የጽሑፉ የመጀመሪያዎቹ ስሪቶች የደራሲን ስም አይጠቅሱም። ሆኖም፣ በዕብራውያን የተገለጹት ሀሳቦች ከጳውሎስ ሌሎች ትምህርቶች ጋር የሚስማሙ በመሆናቸው፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ከክርስትና ባህል ጋር በሚስማማ መልኩ፣ ጳውሎስ ቢያንስ ይህንን መልእክት በመጻፍ ተሳታፊ መሆኑን በአጠቃላይ ተቀብለዋል።

በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ–ቃላትን “ጳውሎሳዊ መልእክቶች” ተመልከቱ።

ዕብራውያን 1–5

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ አባት “ምሳሌ” ነው።

ብዙ አይሁዶች ኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ አድርገው ለመቀበል ተቸግረዋል። የዕብራውያን መልእክት ስለ እርሱ እንዴት እንደሚመሰክር ልብ በሉ። ለምሳሌ፣ የመጀመሪያዎቹን አምስት ምዕራፎች በምታነብበት ጊዜ፣ የተጠቀሱትን የኢየሱስ ክርስቶስን ማዕረጎች፣ ሚናዎች፣ ባሕርያትና ሥራዎች ዝርዝር ልታወጡ ትችላላችሁ። እነዚህ ነገሮች ስለ አዳኙ ምን ያስተምራችኋል? ስለ ሰማያዊ አባት የሚያስተምራችሁ ምንድነው?

የሽማግሌው ጄፍሪ አር. ሆላንድ የሚከተለው መግለጫ በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ስላሉ ትምህርቶች ምን ግንዛቤን ይጨምራል? “ኢየሱስ … የመጣው የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር ያለውን አመለካከት ለማሻሻል እና የሰማዩን አባታቸውን እርሱ ሁል ጊዜ እንደወደዳቸው እና እንደሚወዳቸው እንዲወዱት ለመማጸን ነው። … ስለዚህ የተራቡትን በመመገብ፣ የታመሙትን በመፈወስ፣ ግብዝነትን በመገሰጽ፣ ለእምነት በመለመን—እንዲህ ነበር ክርስቶስ የአባቱን መንገድ ያሳየን” (“የእግዚአብሔር ታላቅነት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2003 (እ.አ.አ)፣ 72)።

ዕብራውያን 2፥:9–184፥12–165፥7–8

እኔ ስሰቃይ እንዲያግዘኝ እና እንዲረዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም መከራ ተቀበለ።

“በእምነት ወደ ጸጋው ዙፋን” መምጣት እና ምህረትን መፈለግ እንደምትችሉ ይሰማችኋል? (ዕብራውያን 4፥16)። ለዕብራውያን ከተላከው መልእክት አንዱ ምንም እንኳን ኃጢአቶቻችን እና ድክመቶቻችን ቢኖሩም፣ እግዚአብሔር የሚቀረብ እና ጸጋው ሊደረስበት የሚችል እንደሆነ ነው። በዕብራውያን 2፥9–184፥12–165፥7–8 ላይ በምድራዊ ፈተናዎቻችሁ ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚረዳችሁ ያላችሁን እምነት የሚያጠናክር ምን ታገኛላችሁ? አዳኙ ስላደረገላችሁ ነገር ሀሳቦቻችሁን እና ስሜታችሁን በግል ደብተር ውስጥ ለመጻፍ አስቡ።

በተጨማሪም ሞዛያ 3፥7–11አልማ 7፥11–1334፤ ማቲው ኤስ ሆላንድ፣ “የልጁ ድንቅ ስጦታ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 45–47.ተመልከቱ።

ዕብራውያን 3፥74፥11

“ልባቸውን እልከኛ [ለማያደርጉ]” የእግዚአብሔርን በረከቶች ያገኛሉ።

ጳውሎስ የጥንት እስራኤላውያንን ታሪክ በመናገር አይሁዶች አባቶቻቸው የፈጸሙትን ስህተት ማለትም በአምላክ አለማመን ምክንያት የእግዚአብሔርን በረከቶች ውድቅ እንዳያደርጉ ለማሳመን ተስፋ አድርጓል። (ዘሁልቁ 14፥1–12፣ 26–35) ላይ ጳውሎስ የጠቀሰውን ታሪክ ማንበብ ትችላላችሁ።)

ዕብራውያን 3፥74፥11 እናንተን እንዴት እንደሚመለከት ተመልከቱ። ይህንን ለማድረግ እንደነዚህ ያሉትን ጥያቄዎች ማሰላሰል ትችላላችሁ፦

  • እስራኤላውያን ጌታን ያስቆጡት እንዴት ነው? ((ዕብራውያን 3፥8–11ን ተመልከቱ)። ልበ ደንዳና መሆን የሚያስከትለው መዘዝ ምንድን ነው?

  • ልቤ እንዲደነድን የፈቀድኩት መቼ ነው? በእምነት ማጣት ምክንያት ያልተቀበልኩት እግዚአብሔር ሊሰጠኝ የሚፈልገው በረከት አለ?

  • ለስላሳ እና የተሰበረ ልብ ለማዳበር ምን ማድረግ እችላለሁ? (ኤተር 4፥15ምሳሌ 3፥5–6አልማ 5፥14–15ን ተመልከቱ)።

በተጨማሪም 1 ኔፊ 2፥1615፥6–11ያዕቆብ 1፥7–8አልማ 12፥33–36፤ ኒል ኤፍ. ማርየት “ልባችንን ለእግዚአብሔር መስጠት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ) 30–32 ተመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዕብራውያን 1፥8–9ኢየሱስ ጽድቅን እንደሚወድ እና በደልን እንደሚጠላ በምን መንገዶች አሳይቷል? ጻድቅ ያልሆኑ ምኞቶች ካሉን ለመለወጥ ምን እናድርግ?

ዕብራውያን 2፥1–4“[የሰማነውን]” የወንጌል እውነት አጥብቆ መያዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ቤተሰባችሁ እንዲረዳ ቁስ በመጠቀም ለማስተማር ማሰብ ትችላላችሁ? ለመያዝ በሚከብድ ነገር ምሳሌ ይህንን ማስረዳት ትችላላችሁ። ምስክርነታችንን ለመጠበቅ የምናደርገው ጥረት ይህንን ነገር እንደ መቅለብ እና እንደ መያዝ እንዴት ነው? “የሰማነው” ከእኛ “እንዳይወሰድ” እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? (ቁጥር 1)።

ዕብራውያን 2፥9–10“የመዳናቸው ራስ” የሚለውን ሐረግ ለመመርመር፣ ራስ የሆነ የሚያደርገውን በመወያየት መጀመር ይችላሉ። መዳን ማለት ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ እና ለመዳናችን ራስ የሆነው እንዴት ነው?

ዕብራውያን 5፥1–5እነዚህ ጥቅሶች ሥልጣን ባለው ሰው በእግዚአብሔር መጠራት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንድትወያዩ ይረዷችኋል። ጥሪዎችን ስለ መቀበል እና ስለማሟላት ከኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ምን እንማራለን?

ምስል
ሙሴ አሮንን ሲሾም

“እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም” (ዕብራውያን 5፥4)። ሙሴ አሮንን ወደ አገልግሎት ጠራው፣ በሃሪ አንደርሰን

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “በየሰአቱ ታስፈልገኛለህ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 98።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የተለያዩ አቀራረቦችን ሞክሩ። ሁልጊዜ ቅዱሳት መጻሕፍትን በተመሳሳይ መንገድ ከማጥናት ይልቅ የተለያዩ የጥናት ሀሳቦችን አስቡ። ለአንዳንድ ሀሳቦች፣ በዚህ መርጃ መጀመሪያ ላይ “የቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን ለማሻሻል የሚረዱ ሃሳቦች” የሚለውን ተመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ

የአለም ብርሃን፣ በዋልተር ሬን

አትም