አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ህዳር 6–12 (እ.አ.አ)። ዕብራውያን 7–13፦ “ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህን”


“ህዳር 6–12 (እ.አ.አ)። ዕብራውያን 7–13፦ ‘ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህን’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) (2022 እ.አ.አ)

“ህዳር 6–12 (እ.አ.አ)። ዕብራውያን 7–13፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

መልከጼዴቅ ለአብርሐም በረከት እየሰጠ

መልከጼዴቅ አብርሐምን ሲባርክ፣ በዋልተር ሬን የአርቲስቱ ስጦታዎች

ህዳር 6–12 (እ.አ.አ)

ዕብራውያን 7–13

“ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህን”

ዕብራውያን 7–13ን በምታነቡበት ጊዜ፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ግንዛቤዎችን ልትቀበሉ ትችላላችሁ። እነሱን መመዝገብ የምትችሉባቸውን መንገዶች አስቡ፤ ለምሳሌ፣ በዚህ ረቂቅ፣ በቅዱሳት መጻህፍት ጠርዝ፣ በማስታወሻ ወይም በግል ደብተር ላይ ልትመዘግቧቸው ትችላላችሁ።

ያሳደረብዎትን ስሜት ይመዝግቡ

ታማኝ ቅዱሳን እንኳን አንዳንድ ጊዜ ልበ ሙሉነታቸውን ሊያናውጡ በሚችሉ “ነቀፋና ጭንቅ” ይሰቃያሉ (ዕብራውያን 10፥32–38ን ተመልከቱ)። ጳውሎስ ወደ ክርስትና የተለወጡ አይሁድ በአዲሱ እምነታቸው ምክንያት ከባድ ስደት እየደረሰባቸው መሆኑን ያውቅ ነበር። ለምስክርነታቸው ታማኝ ሆነው እንዲቆዩ ለማበረታታት፣ ከራሳቸው ታሪክ ጀምሮ የነበረውን የታማኝ አማኞች ረጅም ባህል አስታወሳቸው፤ አቤል፣ ሄኖክ፣ ኖኅ፣ አብርሃም፣ ሣራ፣ ዮሴፍ ሙሴ—የእግዚአብሔር ተስፋዎች እውን ስለመሆናቸውን እና መጠበቅ ዋጋ እንዳለው “[የምስክሮች ደመና]” እንዳሉ ተናግሯል (ዕብራውያን 1112፥1ን ተመልከቱ) ይህ ባህል የእናንተም ነው። “የእምነታችን ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን” በሚመለከቱ ሁሉ የጋራ የእምነት ቅርስ ነው (ዕብራውያን 12፥2)። በእሱ ምክንያት፣ መከራ “[ወደ ኋላ እንድንመለስ]” በፈለገ ቁጥር፣ በአንጻሩ “በእምነት ሙሉ በሙሉ በእውነተኛ ልብ መቅረብ” እንችላለን (ዕብራውያን 10፥22፣ 38)። ለጥንቶቹ ቅዱሳን እንደነበረው ለእኛም ኢየሱስ ክርስቶስ “ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት” ነው (ዕብራውያን 9፥11)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዕብራውያን 7

የመልከጸዴቅ ክህነት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይጠቁመኛል።

አይሁዶች የአሮናዊ ክህነት በመባልም የሚታወቀውን ሌዋዊ ክህነትን ለብዙ መቶ ዘመናት ሲጠቀሙበት ነበር። ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት ታላቁ የመልከጸዴቅ ክህነት ዳግም ተመለሰ፣ ይህም የላቀ በረከቶችን አመጣ። ስለ መልከጸዴቅ ክህነት ዕብራውያን 7፣ ምን ትማራላችሁ? የዚህ መልእክት ዓላማ—ልክ እንደ ሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት—በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን መገንባት መሆኑን አስታውሱ፤ ስለ እርሱ የሚመሰክሩ ምንባቦችን ልብ ልትሉ ትችላላችሁ።

እናንተ ልታገኙ የምትችሏቸው የሌሎች እውነቶች አንዳንድ ምሳሌዎች እነሆ፦

ከመልከጸዴቅ ክህነት እና “ሥርዓቶቹ” ምን በረከቶችን አግኝታችኋል? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥20)። የመልከጸዴቅ ክህነት ወደ ክርስቶስ እንድትመጡ የረዳችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም አልማ 13፥1–13ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥36–46፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “መልከጸዴቅ ክህነት፣” topics.ChurchofJesusChrist.org፤ ለቅዱሳት መጻህፍት መመርያ “መልከጸዴቅ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org፤ ራስል ኤም. ኔልሰን “መንፈሳዊ መዝገቦች፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 76–79፤ ዳለን ኤች. ኦክስ “መልከጸዴቅ ክህነት እና ቁልፎቹ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ) 69–72 ተመልከቱ።

ዕብራውያን910፥1–22

ጥንታዊ እና የዘመናችን ሥርዓቶች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስን ያመለክታሉ።

የዚህ መልእክት የመጀመሪያዎቹ እብራዊ አንባቢዎች ስለ ጥንታዊው ድንኳን እና ጳውሎስ የገለጻቸውን ሥርዓቶች በደንብ ያውቁ ነበር። ነገር ግን አንዳንዶች የእነዚህ ሥርዓቶች ዓላማ የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት መሥዋዕት ለማመልከት መሆኑን ሙሉ በሙሉ አልተገነዘቡም።

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን፣ የሥርየት ቀን ተብሎ በሚጠራው፣ በዓመት አንድ ሊቀ ካህን በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ውስጥ ወደ ቅድስት ስፍራ (ወይም ቅድስተ ቅዱሳን) ገብቶ የእስራኤልን ኃጢአት ለማስተሰረይ ፍየል ወይም በግ መሥዋዕት ያደርጋል።

የጳውሎስን የእነዚህን ሥርዓቶች ገለፃ በምታነቡበት ጊዜ፣ የአዳኙን የኃጢያት ክፍያ ተልዕኮ በተሻለ ለመረዳት የሚረዱ ምልክቶችን እና ትምህርቶችን ፈልጉ።

ዛሬ የምንሳተፍባቸው ሥርዓቶች በጳውሎስ ዘመን ከነበሩት የተለዩ ናቸው፣ ነገር ግን ዓላማቸው አንድ ነው። የዛሬ ላይ ሥርዓቶች ለእናንተ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ይመሰክራሉ?

ስለ ጥንታዊ የአይሁድ ሥነ ሥርዓቶች እና የእነሱ ምሳሌነት የበለጠ ለማወቅ፣ “ድንኳኑ” እና “መስዋዕት እና ቅዱስ ቁርባን” (ChurchofJesusChrist.org) የሚሉ ቪዲዮዎችን ተመልከቱ።

ዕብራውያን 11

እምነት በእግዚአብሔር ተስፋዎች መታመንን ይጠይቃል።

አንድ ሰው እምነትን እንድትገልጹ ቢጠይቃችሁ ምን ትላላችሁ? እህት አኒ ሲ. ፒንግሪ ይህንን የእምነት ፍቺ ለመስጠት የ ዕብራውያን 11 ቋንቋን በመውሰድ “በሩቅ የሚታዩ ነገር ግን በዚህ ሕይወት ሊገኙ የማይችሉትን ተስፋዎች የማመን መንፈሳዊ ችሎታ” በማለት ገልጻለች” (“ቃል ኪዳኖቹን ከሩቅ ማየት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2003 (እ.አ.አ)፣ 14)።

ዕብራውያን 11፣ ላይ ያሉትን ሀሳቦች ስታሰላስሉ የራሳችሁን የእምነት ፍቺ ለማዳበር አስቡ። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ምሳሌዎች ስለ እምነት ምን ያስተምሯችኋል? (በተጨማሪም ኤተር 12፥6–12ን ተመልከቱ።)

“ከሩቅ” ምን ተስፋዎች ታያላችሁ? “እንዳመናችሁ እናም እንደተቀበላችሁ” ለጌታ እንዴት ልታሳዩ ትችላላችሁ? (ዕብራውያን 11፥13)።

በተጨማሪም አልማ 32፥21፣ 26–43፤ ጄፍሪ አር ሆላንድ “የሚመጡ የመልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት፣” ኢንዛይን፣ ህዳር 1999 (እ.አ.አ)፣ 36–38፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን፣” topics.ChurchofJesusChrist.org

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዕብራውያን 10፥32–36የቤተሰብ አባላት የእውነት “ብርሃን [የበራላቸው]” እንደሆነ የተሰማቸውን መንፈሳዊ ልምዶችን እንዲያጋሩ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ። በፈተና ወይም በጥርጣሬ ጊዜ እነዚህ ልምዶች “[መተማመናችንን እንዳንጥል]” እንዴት ሊረዱን ይችላሉ?

ዕብራውያን 11ዕብራውያን 11፣ ላይ ከተጠቀሱት ታማኝ ምሳሌዎች የቤተሰባችሁ አባላት እንዲማሩ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? የእነዚህን አንዳንድ ምሳሌዎች ታሪኮችን መተወን አስደሳች ሊሆን ይችላል። ከእነዚህ ታሪኮች ውስጥ አንዳንዶቹን በብሉይ ኪዳን ታሪኮች፣ ውስጥ መመልከት ትችላላችሁ። ወይም ምናልባት ቤተሰባችሁ እናንተ የምታውቋቸውን ሌሎች ታማኝ ሰዎችን ምሳሌዎች ማለትም ቅድመ አያቶችን፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችን እና የማህበረሰባችሁን አባላት ሊወያይ ይችላል። እንዲሁም ስለ እምነት መዝሙር መዘመር ትችላላችሁ፣ ለምሳሌ “እምነት” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 96)።

ዕብራውያን 12፥2በዚህ ጥቅስ መሠረት ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያለውን ሥቃይና መከራ ለመታገስ ፈቃደኛ የሆነው ለምንድን ነው? ፈተናዎቻችንን እንዴት መቋቋም እንደምንችል ይህ ምን ያስተምረናል? ፕሬዝደንት ረስል ኤም ኔልሰን በዚህ ጥቅስ ላይ በ“ደስታ እና መንፈሳዊ መዳን” (ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ) 81–84) በመልእክቱ ውስጥ አንዳንድ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ሰጥዋተል።

ዕብራውያን 12፥5–11ጌታ ለምን ይቀጣናል እናም ያስተካክለናል? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጌታ ቅጣትን ስለሚመለከትበት መንገድ ምን እናስተውላለን? እነዚህ ጥቅሶች እኛ ተግሳጽ የምንሰጥበት ወይም የምንቀበልበት መንገድ ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራሉ?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “እምነት፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 96።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

መንፈስን ለመጋበዝ እና ትምህርትን ለመማር መዝሙርን ተጠቀሙ። የቀዳሚ አመራሮች፣ “ሙዚቃ [እኛን] ወደ ታላቅ መንፈሳዊነት ለማሸጋገር ወሰን የሌለው ሃይል አለው” (“የመጀመሪያው የአመራር መግቢያ፣” መዝሙሮች፣ x) ምናልባት ስለ እምነት መዘመር፣ ለምሳሌ “ለእምነት እውነተኛ” (መዝሙሮች፣ ቁጥር 254) ዕብራውያን 11፣ የቤተሰብ ውይይት ይጨምር ይሆናል።

የጥንቷ ኢየሩሳሌም ሞደል

የጥንቱ ቤተመቅደስ ምልክቶች እና ሥርዓቶች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሚና አስተምረዋል።