አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ህዳር 20–26 (እ.አ.አ)። 1 እና 2 ጴጥሮስ፦ “በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ [ይበላችሁ]”


ህዳር 20–26 (እ.አ.አ)። 1 እና 2 ጴጥሮስ፦ ‘በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ [ይበላችሁ]’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

ህዳር 20–26 (እ.አ.አ)። 1 እና 2 ጴጥሮስ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ዓለም ወንጌል እያስተማረ

ክርስቶስ በመንፈስ ዓለም እያስተማረ፣ በሮበርት ቲ.ባሬት

ህዳር 20–26 (እ.አ.አ)

1 እና 2 ጴጥሮስ

“በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ [ይበላችሁ]”

ጴጥሮስ መልእክቶችን የጴጥሮስን በምታነቡበት ጊዜ፣ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን ልትቀበሉ ትችላላችሁ። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥80) እግዚአብሔር የሚያስተምራችሁን በትክክል ለመያዝ እንድትችሉ “ገና በመንፈስ” እያላችሁ በፍጥነት መዝግቧቸው።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ከትንሣኤው በኋላ ብዙም ሳይቆይ አዳኙ ጴጥሮስን አስጨንቆት የነበረ ትንቢት ተናገረ። እርሱ ጴጥሮስ ስለእምነቱ እንደሚገደል አስቀድሞ፤ “ወደማትወደውም ይወስድሃል…፣ በምን ዓይነት ሞት እግዚአብሔርን ያከብር ዘንድ እንዳለው” በማሳየት ተናግሯል (ዮሐንስ 21፥ 18–19)። ከዓመታት በኋላ፣ ጴጥሮስ መልእክቶቹን ሲጽፍ፣ ትንቢት የተነገረለት ሰማዕትነቱ ቅርብ መሆኑን ያውቅ ነበር፤ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና” (2 ጴጥሮስ 1፥14)። ያም ሆኖ የጴጥሮስ ቃላት በፍርሃት ወይም በአሉታዊነት የተሞላ አልነበረም። ይልቁንም ቅዱሳኑ “በብዙ ፈተናዎች” በከባድ ጭንቀት ውስጥ ቢሆኑም “[እጅግ እንዲደሰቱ]” አስተምሯቸዋል። እሱ “[የእምነታቸው] መፈተን” “ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ምስጋና እና ክብር” እና “ለነፍሳቸው መዳን” እንደሚያመራ እንዲያስታውሱ መክሯቸዋል (1 ጴጥሮስ 1፥6–7፣ 9)። የጴጥሮስ እምነት ለእነዚያ ቀደምት እንዲሁም ዛሬ ላይ ላሉ ቅዱሳን መጽናኛ ነበር፣ “ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረግን ደስ እንዲለን በክርስቶስ መከራ በምንካፈልበት ልክ ደስ ይበለን” (1 ጴጥሮስ 4፥12)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

1 ጴጥሮስ 1፥3–92፥19–243፥14–174፥12–19

በፈተና እና በመከራ ጊዜ ደስታ ማግኘት እችላለሁ።

ከክርስቶስ ስቅለት በኋላ ያለው ጊዜ ክርስቲያን ለመሆን ቀላል ጊዜ አልነበረም፣ እናም የጴጥሮስ የመጀመሪያ መልእክት ለዚህ እውቅና ይሰጣል። በመጀመሪያዎቹ አራት ምዕራፎች ውስጥ፣ መከራን የሚገልጹ ቃላትን እና ሀረጎችን ታያላችሁ ክብደትፈተናዎችሀዘንእንደ እሳት የሆነ መከራ፣ እና መከራ ( 1 ጴጥሮስ 1፥62፥194፥12–13ን ተመልከቱ)። ነገር ግን ደስ የሚሉ ቃላትንም ልብ ትላላችሁ—ያገኛችሁትን ዝርዝር ማዘጋጀት ትፈልጉ ይሆናል። ለምሳሌ 1 ጴጥሮስ 1፥3–92፥19–243፥14–17፤ እና 4፥12–19ን ስታነቡ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ደስታን ማግኘት እንደምትችሉ ምን ተስፋ ይሰጣችኋል?

እንዲሁም የፕሬዝዳንት ረስል ኤም ኔልሰን “ደስታ እና መንፈሳዊ መዳን” (ሊያሆና፣ ህዳር፣ 2016 (እ.አ.አ)፣ 81–84) የሚለውን መልእክት አንብባችሁ ጴጥሮስ ባስተማረው እና ፕሬዝዳንት ኔልሰን ባስተማሩት መካከል ያለውን ተመሳሳይነት ፈልጉ። ስለ መዳን ዕቅድ እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ደስታን የሚሰጣችሁ ምንድነው?

በተጨማሪም ሪካርዶ ፒ. ጊሜኔዝ “ከህይወት አውሎ ነፋስ መጠጊያ ማግኘት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ) 101–3 ተመልከቱ።

1 ጴጥሮስ 3፥18–204፥1–6

በጽድቅ እንዲፈረድባቸው ወንጌል ለሙታን ይሰበካል።

አንድ ቀን እያንዳንዱ ሰው ለፍርድ ቆሞ “በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።”(1 ጴጥሮስ 4፥5)። ወንጌልን የመረዳትና የመኖር እድሎቻቸው በጣም የተለያዩ ሆነው ሳለ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ላይ እንዴት በጽድቅ ይፈርዳል? በ1 ጴጥሮስ 3፥18–204፥6 ላይ ጴጥሮስ ያስተማረው ትምህርት እንዴት ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንደሚረዳ አስተውሉ። እነዚህ ጥቅሶች በእግዚአብሔር ፍትሃዊነት እና ፍርድ ላይ ያላችሁን እምነት እንዴት ያጠናክራሉ?

ይህንን ትምህርት የበለጠ ለመመርመር ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን 138ን፣ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ እነዚህን የጴጥሮስ ጽሑፎች ሲያሰላስሉ የተቀበሉትን ራዕይ አጥኑ። ፕሬዘደንት ስሚዝ ምን ተጨማሪ እውነቶች ተማሩ?

በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች፣ “ለሙታን ጥምቀት፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ይመልከቱ።

2 ጴጥሮስ 1፥1–11

በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል መለኮታዊ ተፈጥሮዬን ማዳበር እችላለሁ።

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆን እና የእርሱን ባሕርያት ማሳደግ እንደማይቻል ሆኖ ተሰምቷችሁ ያውቃል? ሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሄልስ የክርስቶስን መሰል ባሕርያትን እንዴት ማዳበር እንደምንችል ይህን የሚያበረታታ ሐሳብ አቅርበዋል፦ “የአዳኙ ባህሪዎች … እርስ በእርስ የተሳሰሩ ባህሪዎች ናቸው፣ እርስ በእርስ ተደማምረው፣ በእኛ ውስጥ በተገናኙ መንገዶች ያድጋሉ። በሌላ አነጋገር፣ አንድ ክርስቶስን የመሰለ ባህሪን ሌሎችን በተጨማሪ ሳናገኝ እና ተጽዕኖ ሳያሳድር ማግኘት አንችልም። አንዱ ባህርይ እየጠነከረ ሲሄድ፣ ሌሎች ብዙዎች አብረው ያድጋሉ” (“የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 46)”

ምስል
የተወሳሰበ የስጋጃ ንጣፍ

እኛ የምናዳብረው እያንዳንዱ የክርስቶስ ዓይነት ባሕርይ መንፈሳዊ የደቀመዝሙርነት ምንጣፍ እንድናዘጋጅ ይረዳናል።

2 ጴጥሮስ 1፥1–11ን በምታነቡበት ጊዜ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተዘረዘሩትን “የመለኮታዊ ተፈጥሮ” ባሕርያትን አሰላስሉ። በልምዳችሁ ውስጥ፣ ሽማግሌ ሔልስ እንደገለፁት “እርስ በእርስ የተሳሰሩት” እንዴት ነው? እርስ በእርሳቸው እንዴት ይገነባሉ? ክርስቶስን ይበልጥ የመምሰል ሂደትን በተመለከተ ከእነዚህ ጥቅሶች ሌላ ምን ትማራላችሁ?

እንዲሁም እግዚአብሔር እናንተን ጨምሮ ለቅዱሳኑ የሚሰጣቸውን “የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን” (2 ጴጥሮስ 1፥4) ልታሰላስሉ ትችላላችሁ። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ ቤድናር “የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋ” (ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 90–93) ያለው መልእክት እነዚያ ተስፋዎች ምን እንደሆኑ እና እንዴት እንደምትቀበሉ ለመረዳት ያግዛችኋል።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

1 ጴጥሮስ 2፥5–10እነዚህን ጥቅሶች ከቤተሰባችሁ ጋር በምታነቡበት ጊዜ፣ የቤተሰብ አባላት አዳኙ የእኛ “ዋና የማዕዘን ድንጋይ” ስለመሆኑ የጴጥሮስን ትምህርቶች በዓይነ ሕሊናቸው እንዲመለከቱ ለመርዳት ዓለቶችን ለመጠቀም አስቡ። እግዚአብሔር መንግሥቱን ለመገንባት እየተጠቀመበት እንዳለ “ሕያዋን ድንጋዮች” የምንሆነው እንዴት ነው? ስለ አዳኙ እና በመንግስቱ ውስጥ ስላለን ሚና ከጴጥሮስ ምን እንማራለን? ጴጥሮስ ለቤተሰባችሁ ያለው መልእክት ምንድነው?

1 ጴጥሮስ 3፥8–17ስለእምነታችን ለሚጠይቁን “መልስ ለመስጠት ዝግጁ [የምንሆነው]” እንዴት ነው? የእናንተ ቤተሰብ አንድ ሰው ስለወንጌል ጥያቄ ለመጠየቅ ሲቀርብ በሚያሳይ ትወና ሊደሰት ይችላል።

1 ጴጥሮስ 3፥18–204፥6ከቅድመ አያቶቻችሁ ጋር እንደተገናኛችሁ እንዲሰማችሁ ቤተሰባችሁ ምን ማድረግ ይችላል? ምናልባት የሟች ቅድመ አያቶቻችሁ የሚወዱትን ምግብ በማዘጋጀት፣ ፍቶዎችን በማየት ወይም ከሕይወታቸው ታሪኮችን በመናገር የልደት ቀናቸውን ማክበር ይችሉ ይሆናል። የሚቻል ከሆነ በቤተመቅደስ ውስጥ ለቅድመ አያቶቻችሁ ስርዓቶችን ለመቀበል ማቀድ ትችላላችሁ (ለእርዳታ FamilySearch.org ን ጎብኙ)።

2 ጴጥሮስ 1፥16–21በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ፣ ጴጥሮስ በመቀየር ተራራ ላይ ያጋጠመውን ቅዱሳንን ያስታውሳቸዋል ( ማቴዎስ 17፥1–9ን ተመልከቱ)። ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ ነቢያት ትምህርት ምን እንማራለን? (በተጨማሪ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥38ን ተመልከቱ)። ዛሬ ህያው ነብያችንን ለመከተል መተማመን የሚሰጠን ምንድነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “የቤተሰብ ታሪክ—እየተገበርኩት ነው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 94።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

“ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ።” በቤት ውስጥ መደበኛ ያልሆነ የማስተማሪያ ጊዜዎች በፍጥነት ሊመጡ እና ሊሄዱ ይችላሉ፣ ስለዚህ ሲመጡ እነሱን መጠቀሙ አስፈላጊ ነው። (1 ጴጥሮስ 3፥15) ማስተማርያ ቅጽበቶች ሲመጡ ለቤተሰብ አባላት የወንጌልን እውነቶች ለማስተማር እና “በእናንተ ስላለ ተስፋ” ለማካፈል “ዘወትር የተዘጋጃችሁ” ለመሆን እንዴት ልትተጉ ትችላላችሁ? ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣፣ 16ን ይመልከቱ።)

ምስል
ጴጥሮስ ለሰዎች ሲሰብክ

ምንም እንኳን ጴጥሮስ ብዙ ስደት እና ተቃውሞ ቢገጥመውም፣ እርሱ ስለ ክርስቶስ ምስክርነቱ ጸንቷል።

አትም