አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ህዳር 27–ታህሳስ 3 (እ.አ.አ)። 1–3 ዮሐንስ፤ ይሁዳ፤ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው”


ህዳር 27–ታህሳስ 3 (እ.አ.አ)። 1–3 ዮሐንስ፤ ይሁዳ፦ ‘እግዚአብሔር ፍቅር ነው’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) (2022)

ህዳር 27–ታህሳስ 3 (እ.አ.አ)። 1–3 ዮሐንስ፤ ይሁዳ፤” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚስቁ ልጆች ጋር ቁጭ ብሎ ፈገግ እያለ

ፍጹም ፍቅር፣ በዴል ፓርሰን

ህዳር 27–ታህሳስ 3 (እ.አ.አ)

1–3 ዮሐንስይሁዳ

“እግዚአብሔር ፍቅር ነው”

የዮሐንስን እና የይሁዳን መልእክቶች በምታነቡበት ጊዜ ለእግዚአብሔር ፍቅራችሁን እንዴት ማሳየት እንደምትችሉ መነሳሳትን ፈልጉ። እነዚህን ግንዛቤዎች መዝግቡ እና በእነሱ ላይ እርምጃ ውሰዱ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ዮሐንስ እና ይሁዳ መልእክቶቻቸውን ሲጽፉ የተበላሸ አስተምሮት ብዙ ቅዱሳንን ወደ ክህደት መምራት ጀምሮ ነበር። አንዳንድ ሐሰተኛ መምህራን ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጥ “በሥጋ” ተገልጦ እንደሆን መጠራጠር ጀምረው ነበር (ለምሳሌ 1 ዮሐንስ 4፥1–32 ዮሐንስ 1፥ 7ን ተመልከቱ)። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የቤተክርስቲያን መሪ ምን ማድረግ ይችላል? ሐዋርያው ዮሐንስ የአዳኙን የግል ምስክርነት በማካፈል ምላሽ ሰጥቷል፦ “እኛ የምንሰጠው ምስክርነታችን ይህ ነው፥ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን” (ጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ 1 ዮሐንስ 1፥1 [1 ዮሐንስ 1፥1፣ የግርጌ ማስታወሻ])። ከዚያም ዮሐንስ ስለ ፍቅር አስተማረ፦ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር እና ለእሱ እና ለልጆቹ ሁሉ ሊኖረን የሚገባው ፍቅር። ለነገሩ ዮሐንስ ለዚህም ምስክር ነበር። እሱ ራሱ የአዳኙን ፍቅር ቀምሶት ነበር (ዮሐንስ 13፥2320፥2ን ተመልከቱ)፣ እናም ቅዱሳኑ ያንን ተመሳሳይ ፍቅር እንዲሰማቸው ፈለገ። በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለ እምነት ጥያቄ ውስጥ ሲገባ እና የሐሰት ትምህርቶች ሲበዙ የዮሐንስ ምስክርነት እና በፍቅር ላይ ያስተማረው ትምህርት ዛሬም የሚያስፈልግ ነው። የዮሐንስ መልእክቶችን ማንበብ የዛሬውን መከራ በድፍረት እንድንቋቋም ይረዳናል፣ ምክንያቱም “ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ [ስለሚጥል] እንጂ በፍቅር ፍርሃት [ስለሌለ]” ነው (1 ዮሐንስ 4፥18)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

1 ዮሐንስ2፥4

እግዚአብሔር ብርሃን ነው፣ እግዚአብሔር ፍቅርም ነው።

እግዚአብሔርን ለመግለጽ አንድ ወይም ሁለት ቃላትን ምረጡ ብትባሉ እነዚያ ምን ይሆናሉ? በመልእክቶቹ ውስጥ፣ ዮሐንስ ብዙ ጊዜ “ብርሃን” እና “ፍቅር” የሚሉትን ቃላት ተጠቅሟል (ለምሳሌ፣ 1 ዮሐንስ 1፥52፥8–113፥16፣ 23–244፥7–21ን ተመልከቱ)። የመጀመሪያዎቹን ሁለት የዮሐንስ መልእክቶችን ስታነቡ፣ ዮሐንስ ከአዳኙ ብርሃን እና ፍቅር ጋር የነበረውን ልምዶች አሰላስሉ። ለምሳሌ፣ በዮሐንስ 3፥16–1712፥35–36፣ 4615፥9–1419፥25–27ውስጥ ዮሐንስ ከኢየሱስ አስተምሮቶች የተማረውን ተመልከቱ። በእነዚህ ትምህርቶች እና በ1 ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ብርሃን እና ፍቅር በሚያስተምረው መካከል ምን ተመሳሳይነት ታያላችሁ? እግዚአብሔር ብርሃን እና ፍቅር መሆኑን ምን ልምዶች አስተምረዋችኋል?

1 ዮሐንስ 2–42 ዮሐንስ

“እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል”

እንዲሁም በዮሐንስ መልእክቶች ውስጥ እንደ “መቆየት” እና “መኖር” ያሉ ቃላትን ተደጋግመው ይገኛሉ። በተለይም 1 ዮሐንስ 2–4 እና 2 ዮሐንስን በምታነቡበት ጊዜ እነዚህን ቃላት ፈልጉ። በእግዚአብሔር እና በትምህርቱ ውስጥ “መቆየት” ወይም “መኖር” ማለት ምን ይመስላችኋል? (2 ዮሐንስ 1፥ 9ን ተመልከቱ)። እግዚአብሔር በእናንተ ውስጥ “እንዲቆይ” ወይም “እንዲኖር” ማለት ምን ማለት ነው?

1 ዮሐንስ 2፥243፥3

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆን እችላለሁ።

ክርስቶስን የመምሰል ግብ ለእናንተ በጣም ከፍ ያለ ይመስላችኋል? የዮሐንስን የሚያበረታታ ምክር ተመልከቱ፤ “ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በእርሱ ኑሩ … እና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን” (1 ዮሐንስ 2፥283፥ 2)። በ1 ዮሐንስ 2፥243፥3 ውስጥ እንደ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርነት መተማመን እና መጽናናት የሚሰጣችሁ ምን አለ? የዮሐንስን መልእክቶች ስታጠኑ፣ ይበልጥ ክርስቶስን ለመምሰል በምታደርጉት ጥረት ሊረዳችሁ የሚችሉ ሌሎች መርሆችን ወይም ምክሮችን ፈልጉ።

በተጨማሪም ሞሮኒ 7፥48ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥67–68፤ ስካት ዲ. ዋይቲንግ፣ “እንደ እርሱ መሆን፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 12–14ን ተመልከቱ።

1 ዮሐንስ 4፥12

መቼም ቢሆን “እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም”?

የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም 1 ዮሐንስ 4፥12ከሚያምኑት በቀርእግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም” በማለት ያብራራል (በ1 ዮሐንስ 4፥12 የግርጌ ማስታወሻ፤ በተጨማሪም ዮሐንስ 6፥463 ዮሐንስ 1፥11ን ይመልከቱ)። ቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔር አብ ዮሐንስን ጨምሮ ለታማኝ ግለሰቦች ራሱን የገለጠበትን በርካታ አጋጣሚዎችን ይመዘግባሉ (ራዕይ 4ን ተመልከቱ፤ በተጨማሪም የሐዋርያት ሥራ 7፥55–561 ኔፊ 1፥8ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥23ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥16–17ን ተመልከቱ)።

1 ዮሐንስ 5

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና ዳግመኛ በመወለድ፣ ዓለምን ማሸነፍ እችላለሁ።

1 ዮሐንስ 5ን በምታነቡበት ጊዜ ዓለምን ለማሸነፍ እና የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን ፈልጉ። በሕይወታችሁ ውስጥ ዓለምን ማሸነፍ ምን ሊመስል ይችላል? እንዲሁም በሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን “ዓለምን ማሸነፍ” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 58–62) መልእክት ውስጥ መልሶችን እና ግንዛቤዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።

ይሁዳ 1

“ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን [አንጹ]”

ይሁዳ 1፥10–19 እግዚአብሔርን እና ሥራውን ተቃውመው ስለሚዋጉ ምን ያስተምራችኋል? በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት እንዴት ጠንካራ ማድረግ እንደምትችሉ ከቁጥር 20–25 ምን ትማራላችሁ?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

1 ዮሐንስ 2፥8–11ቤተሰባችሁ የዮሐንስን ትምህርቶች እንዲያሰላስሉ ለመርዳት፣ የቤተሰብ አባላት “በጨለማ” እና “በብርሃን” መራመድ መካከል ያለውን ልዩነት እንዲረዱ በጨለማ ክፍል ውስጥ ተሰብሰቡ። ጥላቻ በጨለማ እንድንመላለስ እና እንድንደናቀፍ የሚያደርገን እንዴት ነው? እርስ በርስ መዋደዳችን በሕይወታችን ውስጥ ብርሃንን የሚያመጣው እንዴት ነው?

1 ዮሐንስ 3፥21–22በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በእግዚአብሔር ላይ ያለንን “መተማመን” እና ለጸሎቶቻችን መልስን ለመቀበል ያለንን ችሎታ የሚጨምረው ምንድነው?

አንድ ቤተሰብ በጸሎት ተንበርክኮ

የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ ዓለምን እንድናሸንፍ ይረዳናል።

1 ዮሐንስ 5፥2–3“ከባዶች” ወይም ልንከተላቸው የሚያስቸግሩን ትእዛዛት አሉ? ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ስለ ትእዛዛቱ ያለንን ስሜት እንዴት ይለውጣል?

3 ዮሐንስ 1፥4“በእውነት [መሄድ]” ማለት ምን ማለት ነው? ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የቤተሰብ አባላት በእውነት ሲራመዱ እንዴት እንዳያችሁ እና ይህ ስለሚያመጣላችሁ ደስታ መናገር ትችላላችሁ። የቤተሰብ አባላት በብጣሽ ወረቀት ላይ የተማሩትን እውነት በመፃፍ ወይም በመሳል ቤተሰባችሁ አብረው የሚራመዱበትን መንገድ ለመሥራት ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ይሁዳ 1፥3–4በሕይወታችን እና በቤተሰባችን ውስጥ “ሾልከው የገቡ” መንፈሳዊ አደጋዎች አሉን? (ይሁዳ 1፥4)። “ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ” የሚለውን የይሁዳን ምክር መከተል እና እነዚህን አደጋዎች መቋቋም የምንችለው እንዴት ነው? (ይሁዳ 1፥3)። በቤተሰባችን ውስጥ “ምሕረትና ሰላም ፍቅርም [እንዲበዛ]” ለማረጋገጥ ምን እናድርግ? (ይሁዳ 1፥2)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “ፍቅር ባለበት፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 138–39።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የእግዚአብሔርን ፍቅር አግኙ። ፕሬዘደንት ኤም. ረስል ባላርድ እንዳስተማሩት፣ “[ወንጌል] የፍቅር ወንጌል ነው—ለእግዚአብሔር ፍቅር እና ለእርስ በርሳችን ፍቅር” [“እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው ፍቅር፣” ኢንዛይን፣ ግንቦት 1988 (እ.አ.አ)፣ 59]። ቅዱሳት መጻህፍትን በምታነቡበት ጊዜ፣​የእግዚአብሔርን ፍቅር ማስረጃዎች ማስተዋልን ወይም ምልክት ማድረግን አስቡ።

ክርስቶስ በአንድ ሐይቅ ዳርቻ እየተራመደ

ከእኔ ጋር ተራመዱ፣ በግሬግ ኬ. ኦልሰን