አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 25፟–31 (እ.አ.አ)። ራዕይ 15–22፤ “ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል”


“ታህሳስ 25፟–31 (እ.አ.አ)። ራዕይ 15–22፤ ‘ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022(እ.አ.አ)]

“ታህሳስ 25፟–31 (እ.አ.አ)። ራዕይ 15–22፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ሰዎችን ሰላም እያለ

ዘላለማዊ ከተማ፣ በኪዝ ላርሰን

ታህሳስ 25–31 (እ.አ.አ)።

ራዕይ 15–22

“ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል”

አንዳንድ ጊዜ ለመማር ትልቁ እንቅፋት መማር የማያስፈልገን—እኛ አስቀድመን የምናውቅ አድርገን ስንገምት ነው። ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ፣ ጌታ ሊሰጣችሁ ለሚፈልጋቸው አዲስ ግንዛቤዎች ዝግጁ ሁኑ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

እንደምታስታውሱት የራዕይመጽሐፍ የሚጀምረው አዳኙ ራሱን “መጀመሪያው እና መጨረሻው” ብሎ ሲያውጅ ነው (ራዕይ 1፥ 8)። በሚገጥም ሁኔታ፣ በተመሳሳይ ቃላት ያበቃል፤ “መጀመሪያው እና መጨረሻው እኔ ነኝ” (ራዕይ 22፥13)። ነገር ግን ይህ ምን ማለት ነው? የምን መጀመሪያ እና መጨረሻ? የራዕይ መጽሐፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ህልውና እና የመዳን ድርጊት በሁሉም ነገር መጀመሪያ እና መጨረሻ መሆኑን በኃይል ይመሰክራል። እርሱ “ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ [የታረደው] በግ” ነው (ራዕይ 13፥8)። እናም እሱ ክፋትን፣ ሀዘንን፣ እንዲሁም ሞትን ራሱ የሚያቆም እና “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” የሚያመጣ የነገሥታት ንጉሥ ነው (ራዕይ 21፥1)።

ገና ይህ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከመምጣቱ በፊት እኛ ማሸነፍ ያለብን ብዙ ነገሮች አሉ–— መቅሰፍቶች፣ ጦርነቶች፣ የተንሰራፋ ክፋት–—እነዚህን ሁሉ ራዕይ በግልፅ ይገልፃል። በዚህ ሁሉ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ነው። እሱ በቅርቡ ንጋት እንደሚመጣ ተስፋ ሆኖ በጨለመ ሰማይ ውስጥ “የሚያበራም የንጋት ኮከብ” (ራዕይ 22፥16) ነው። እናም በቅርቡ እየመጣ ነውእርሱ እየመጣ ነው። “ወደ እኔ ኑ” (ማቴዎስ 11፥28) በማለት እንደጋበዘን፣ እርሱ ደግሞ ወደ እኛ ይመጣል። እሱ “በቶሎ እመጣለሁ” ይላል። እናም በኋለኛው ቀን የመከራ እሳት በነጻ ተስፋ እና እምነት፣ “አሜን፣ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ና” (ራዕይ 22፥20) ብለን እንመልሳለን።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ራዕይ 16–1821–22

ከባቢሎን ሸሽቼ “ቅድስቲቱን ከተማ” እንድወርስ ጌታ ይጋብዘኛል።

ዮሐንስ የመጨረሻዎቹን ጥፋቶች እና አደጋዎች ከተመለከተ በኋላ “እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” (ራዕይ 21፥5) በሚለው የጌታ መግለጫ ሊጠቃለል የሚችል የወደፊት ቀንን አየ። ያ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት አንዱ መንገድ የዓለም እና የክፋት ምልክት የሆነችውን ባቢሎንን (ራዕይ 16–18ን ተመልከቱ) በእግዚአብሔር ፊት የሰማያዊ ክብር ተምሳሌት ከሆነችው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም የዮሐንስ ገለፃ ጋር ማወዳደር ነው (ራዕይ 21–22ን ተመልከት)። ከዚህ በታች ያለው ሰንጠረዥ ሊረዳችሁ ይችላል፤

ባቢሎን

አዲሲቷ ኢየሩሳሌም

ባቢሎን

ራዕይ 16፥3–6።

አዲሲቷ ኢየሩሳሌም

ራዕይ 21፥622፥1–2፣ 17

ባቢሎን

ራዕይ16፥1018፥23

አዲሲቷ ኢየሩሳሌም

ራዕይ 21፥23–2422፥5

ባቢሎን

ራዕይ 17፥1–5

አዲሲቷ ኢየሩሳሌም

ራዕይ 21፥2

ባቢሎን

ራዕይ 18፥11፣ 15

አዲሲቷ ኢየሩሳሌም

ራዕይ 21፥4

ባቢሎን

ራዕይ 18፥12–14

አዲሲቷ ኢየሩሳሌም

ራዕይ 21፥18–2122፥1–2

ሌሎች ምን ልዩነቶች ታያላችሁ?

እንዲሁም ከባቢሎን “[መውጣት]” ማለት ለእናንተ ምን ማለት እንደሆነ ታስቡ ይሆናል (ራዕይ 18፥4)። ይህን እንድታደርጉ ያነሳሳችሁን በራዕይ 21–22 ውስጥ ምን ታገኛላችሁ?

ኢየሱስ በቀኙ በብርሃን ውስጥ በግራው በኩል ደግሞ በጨለማ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር

የመጨረሻው ፍርድ፣ በጆን ስካት

ራዕይ 20፥12–1521፥1–4

ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች በሕይወት መጽሐፍ ባለው ይፈረድባቸዋል።

አንድ ደራሲ ስለ ህይወታችሁ መጽሐፍ ለመጻፍ አሰበ እንበል። ምን ዝርዝሮች ወይም ልምዶች እንዲካተቱ ትፈልጋላችሁ? የወደፊት ድርጊቶቻችሁ እንዲሁ እንደሚመዘገቡ ብታውቁ፣ ህይወትን በተለየ መንገድ እንዴት ትመለከታላችሁ? ራዕይ 20፥12–15ን በምታነቡበት ጊዜ ይህን አስቡ። በህይወት መጽሐፍ ውስጥ ስለ እናንተ ምን ይፃፋል ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላችሁ? በህይወት መጽሐፋችሁ ውስጥ የአዳኙን ሚና እንዴት ትገልጻላችሁ? በእናንተ አስተያየት “ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ” ተብሎ መጠራቱ ለምን አስፈላጊ ነው? ራዕይ 21፥27

ለመፍረድ በእግዚአብሔር ፊት የመቆም ሀሳብ ለእናንተ የማይመች ከሆነ ራዕይ 21፥1–4ን ለማንበብ አስቡ። እነዚህን ጥቅሶች በመጥቀስ፣ ሽማግሌ ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዲህ ብለዋል፦

“ያ የፍርድ ቀን የምሕረት እና የፍቅር ቀን ይሆናል—የተሰበሩ ልቦች የሚፈወሱበት፣ የሐዘን እንባ በምስጋና እንባ የሚተካበት፣ ሁሉም የሚስተካከልበት ቀን። አዎን፣ በኃጢአት ምክንያት ጥልቅ ሐዘን ይኖራል። አዎን፣ ታላቅ የወደፊት ዕድሎች እንድናጣ ላደረጉን ስህተቶች፣ ለሞኝነቶቻችን እና ግትርነታችን መፀፀት እንዲሁም ሃዘን ይኖራል።

“እኔ ግን በእግዚአብሔር ፍርድ ብቻ እንደማንረካ እርግጠኛ ነኝ፤ ለእኛ፣ ለልጆቹ ባለው ማለቂያ በሌለው ጸጋው፣ ምሕረቱ፣ ልግስናው እና ፍቅርም እጅግ እንደነቃለን” (“ኦ የአምላካችን እቅድ እንዴት ታላቅ ነው!፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ) 21)።

እነዚህ እውነቶች የመጨረሻውን ፍርድ በምትመለከቱበት መንገድ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ? እነዚህ እውነቶች በሕይወታችሁ ውስጥ ምን እንድትለውጡ ያነሳሷችኋል?

በተጨማሪም “የህይወት መጽሐፍ” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ ተመልከቱ።

ራዕይ 22፥18–19

እነዚህ ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሌላ ተጨማሪ ቅዱስ መጽሃፍ የለም ይላሉ?

አንዳንድ ሰዎች መጽሐፈ ሞርሞንን እና ሌሎችን የኋለኛው ቀን ቅዱሳት መጻሕፍትን ላለመቀበል ራዕይ 22፥18–19 ን ይጠቅሳሉ። ለዚህ ተቃውሞ መልስ በሽማግሌው ጄፍሪ አር. ሆላንድ “ቃሎቼ … መቼም አያቆሙም” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2008 (እ.አ.አ) 91–94) መልእክት ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ራዕይ 15፥2–4 ቤተሰባችሁ “[የሙሴን] ቅኔ” እና “የበጉን ቅኔ” የሚያመለክቱትን እነዚህን ጥቅሶች ሲወያይ፣ በዘፀአት 15፥1–19 ውስጥ ያሉትን የሙሴን መዝሙር ለምሳሌ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥98–102 ውስጥ አይነት በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ከተጠቀሱት ሌሎች መዝሙሮች ጋር ለማንበብ ይችላል። “በአውሬው … ላይ ድል ነስተው የነበሩት” (ራዕይ 15፥ 2) እንደነዚህ ያሉትን መዝሙሮች መዘመር ለምን ሊያሰኛቸው ቻለ? ምናልባት ቤተሰባችሁ የመዝሙር ወይም የልጆች የምስጋና መዝሙር ሊዘምር ይችላል።

ራዕይ 19፥7–9 ምናልባት ከቤተሰብ ታሪካችሁ ውስጥ የሠርግ ሥዕሎችን ማየት ወይም ቤተሰባችሁ በሠርግ ክብረ በዓል ላይ ስለተገኘበት ጊዜ ማውራት ትችሉ ይሆናል። ጌታ ከቤተክርስቲያኑ ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ጋብቻ ጥሩ ንፅፅር የሚሆነው ለምንድነው? (በተጨማሪም ማቴዎስ 22፥1–14ንተመልከቱ።)

ራዕይ 20፥2–3 1 ኔፊ 22፥26 የሰይጣን “መታሰር” ምን ማለት እንደሆነ እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው?

ራዕይ 22፥1–4 የአዳኙ ስም “[በግምባሮቻችን]” ውስጥ መኖሩ ምን ማለት ሊሆን ይችላል? (ራዕይ 22፥4፤ በተጨማሪም ዘፀአት 28፥36–38ሞዛያ 5፥7–9አልማ 5፥14ሞሮኒ 4፥3ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥22፤ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “በክብር ስም እና አቋም ያዙ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 97–100)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦“እርሱ ዳግም ሲመጣ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣82–83።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

በተግባር እንዲውሉ የተደረጉ ግብዣዎችን ክትትል አድርጉ። “እርምጃ እንድትወስዱ የቀረበላችሁን ግብዣ ስትከታተሉ [ለቤተሰባችሁ አባላት] እንደምታስቡላቸው እና ወንጌል ህይወታቸውን እንዴት እየባረከ እንደሆነ ታሳያላችሁ። ደግሞም ልምዳቸውን እንዲካፈሉ እድሎችን ትሰጣችኋላችሁ” (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 35)።

ኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ ከሰማይ ፈረስ ሲጋልብ

ክርስቶስ ቀይ ልብስ ለብሶ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ።