አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 18፟–24 (እ.አ.አ)። የገና በዓል፦ “የታላቅ ደስታ የምስራች“


“ታህሳስ 18–24 (እ.አ.አ)። የገና በዓል፦ ‘የታላቅ ደስታ የምስራች’” ኑ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ታህሳስ 18–24 (እ.አ.አ)። የገና በዓል፣ ” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ጨቅላ ህጻን

ትንሽ ጠቦት፣ በጄነዲ ፔጅ

ታህሳስ 18፟–24 (እ.አ.አ)።

የገና በዓል

“የታላቅ ደስታ የምስራች”

የአዳኙን ልደት እና ተልዕኮ ማሰላሰል የገና ሰሞን የሰላምና የቅድስና መንፈስን ለማምጣት እንዴት እንደሚረዳ አስቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የሕፃን መወለድ እንዲህ ዓይነቱን ታላቅ ደስታ ለምን ያመጣል? ምናልባት አዲስ ሕፃን የተስፋ ምልክት ስለሆነ ሊሆን ይችላል። ለዚያ ልጅ ሕይወት ምን ሊይዝ እንደሚችል እና እሱ ወይም እሷ የሚያከናውኗቸውን ድንቅ ነገሮች እንድናሰላስል በአዲስ ሕይወት ውስጥ የሚጋብዘን አንድ ነገር አለ። ከእግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ይልቅ ይህ እውነት ሆኖ አያውቅም። በልጅ ውስጥ ከዚህ የበለጠ ተስፋ ተቀምጦ አያውቅም፤ ብዙ ተስፋ ያለው አንድም አልተወለደም።

መልአክ በግርግም ውስጥ አዲስ የተወለደ ሕፃን እንዲፈልጉ እረኞችን ሲጋብዝ ስለዚያ ልጅ መልእክትም ሰጥቷቸው ነበር። የተስፋ መልእክት ነበር—ይህ ሕፃን ቅዱስ ተልእኮ ለመፈጸም ወደ ምድር እንደመጣ። እረኞቹ “የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ … የሰሙትን ሁሉ … በነገሩአቸው ነገር አደነቁ። ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር”(ሉቃስ 2፥17–19)። በዚህ የገና በዓል የማርያምን ምሳሌ መከተል ጥሩ ይሆናል፤ በዚህ ዓመት ስለ አዳኙ የተማራችሁትን በልባችሁ ውስጥ ማሰላሰል። ባነበባችሁት ውስጥ የማዳን ተልእኮውን እንዴት አከናወነ? ከሁሉም በላይ፣ የእርሱ ተልእኮ ሕይወታችሁን እንዴት ቀየረው? ያኔ የእረኞችን ምሳሌ ለመከተል በመንፈስ መነሳሳት ሊሰማችሁ ይችላል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገላችሁን “[ለአገር ሁሉ]” እንዴት ማሳወቅ ትችላላችሁ?

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ 1፥18–252፥1–12ሉቃስ 1፥26–382፥1–20

ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በመካከላችን እንዲወለድ ራሱን ዝቅ አደረገ።

የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ታሪክ ብዙ ጊዜ አንብባችሁ ወይም ሰምታችሁ ቢሆንም፣ በዚህ ጊዜ ይህንን ሀሳብ በመያዝ አጥኑት፤ “የገና በዓል ኢየሱስ ወደ ዓለም እንዴት እንደመጣ ማክበርያ ብቻ ሳይሆን እርሱ ለምን እንደ መጣ፤ ማን እንደ ሆነ የማወቅ በዓል ነው—ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችን እና አዳኛችን ነው” (ክሬግ ሲ ክሪሰተንሰን፣ “የገና ታሪክ ሙሉነት” [ቀዳሚ አመራር የገና አምልኮ፣ ታህሳስ 4፣ 2016 (እ.አ.አ)]፣ broadcasts.ChurchofJesusChrist.org)።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት ማን እንደነበር ምን ታውቃላችሁ? (ለምሳሌ፣ ዮሐንስ 17፥ 5ሞዛያ 3፥5ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥13–14፣ 20–24ሙሴ 4፥ 2ን ተመልከቱ።) ይህ እውቀት ስለ ልደቱ ስታነቡ እናንተ በሚሰማችሁ ስሜት ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ለምን እንደመጣ የምታውቁት ምንድነው? (ለምሳሌ፣ ሉቃስ 4፥16–21ዮሐንስ 3፥16–173 ኔፊ 27፥13–16ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥20–28ን ተመልከቱ)። ይህ እውቀት ስለ አዳኙ በሚሰማችሁ ስሜት ላይ እንዴት ተጽዕኖ ይፈጥራል? ይህ በአኗኗራችሁ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ አለው?

በተጨማሪም 2 ቆሮንቶስ 8፥9እብራውያን 2፥7–181 ኔፊ 11፥13–33አልማ 7፥10–13፤ “የክርስቶስ መወለድ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

1 ቆሮንቶስ 15፥21–26ቆላስይስ 1፥12–221 ጴጥሮስ 2፥21–25

ኢየሱስ ክርስቶስ ተልዕኮውን ፈፅሞ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ አስችሎኛል።

ምንም እንኳን የክርስቶስ ልደት ታሪክ በተአምራዊ ክስተቶች የተከበበ ቢሆንም፣ ኋላ ላይ በሕይወቱ በፈጸመው ታላቅ ሥራ ባይሆን ኖሮ የእሱ መወለድ እንዲሁ ሌላ ልደት ይሆን ነበር። ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሂንክሌይ እንዳሉት፣ “የቤተልሔም ሕፃን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቴሴማኒ እና የቀራንዮ ቤዛ፣ እና የትንሣኤው የድል እውነታ ባይኖር ኖሮ እንዲሁ እንደሌላ ህጻን ይቆጠር ነበር” (“የገና አስደናቂ እና እውነተኛ ታሪክ፣” ኢንዛይን፣ ታህሳስ 2000 (እ.አ.አ)፣ 5)።

ምስል
ኢየሱስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ተንበርክኮ

ጌቴሴማኒበጄ. ከርክ ሪቻርድስ

የአዳኙ መለኮታዊ ተልእኮ እና ለሌሎች ያለው ኃይለኛ ፍቅር ማስረጃ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይገኛል። የትኞቹ ምንባቦች ወይም ጽሁፎች ወደ አእምሯችሁ ይመጣሉ? በዚህ የመማርያ ምንጭ ወይም የጥናት ደብተራችሁ ውስጥ ወደኋላ መለስ በማለት የመዘገባችሁትን አንዳንድ ግንዛቤዎች መከለስ ትችላላችሁ። እንዲሁም 1 ቆሮንቶስ 15፥21–26ቆላስይስ 1፥12–221 ጴጥሮስ 2፥ 21–25 ን ማንበብ እና አዳኙ እና ሥራው ሕይወታችሁን እንዴት እንደባረከ አስቡ። በሕይወታችሁ ውስጥ ምን መለወጥ እንዳለባችሁ ይሰማችኋል? የአዳኙን ኃይል እንዴት መሳብ ትችላላችሁ?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 1፥18–252፥1–12ሉቃስ 1፥26–382፥1–20የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ከቤተሰባችሁ ጋር እንዴት ማክበር ትችላላችሁ? ጥቂት ሀሳቦች እዚህ አሉ፣ ወይም በራሳችሁ ማምጣት ትችላላችሁ፦

  • የኢየሱስ ልደት ታሪክ ክፍሎችን አንድ ላይ አንብቡ ወይም ተውኑ።

  • በተጨማሪም “ህጻኑ ኢየሱስ” የሚለውን ቪድዮ (ChurchofJesusChrist.org) ተመልከቱ።

  • በወንጌል ቤተ-መጽሐፍት በ“ኢየሱስ ክርስቶስ” ክምችት ውስጥ፣ በተለይም “ልደቱ (ገና)” በሚለው ክፍል ውስጥ አንዳንድ ምንጮችን አስሱ።

  • የቀዳሚ አመራሮች የገና አምልኮን ተመልከቱ ((broadcasts.ChurchofJesusChrist.org)

  • የገና መዝሙሮችን አንድ ላይ ዘምሩ፣ ወይም ጎረቤቶችን ወይም ጓደኞችን ለመጎብኘት ምረጡ እና ለእነሱ ዘምሩ (መዝሙሮችንቁ. 201–14ን ተመልከቱ።

  • የአገልግሎት ተግባር አከናውኑ።

  • ኢየሱስ ክርስቶስን ለማስታወስ ሊያደርጉዋቸው የሚችሏቸውን የጌጣጌጥ ወይም የማስዋብያ ሀሳቦች በልደቱ ታሪክ ዝርዝሮችን ውስጥ እንዲፈልጉ የቤተሰብ አባላትን ጠይቁ።

1 ቆሮንቶስ 15፥21–26ቆላስይስ 1፥12–221 ጴጥሮስ 2፥21–25ኢየሱስ ክርስቶስ በመወለዱ ለምን አመስጋኞች ነን? ምን ስጦታዎች ሰጥቶናል? ምስጋናችንን እንዴት አድርገን ልናሳየው እንችላለን? ቤተሰባችሁ ስለ እሱ ተልዕኮ የሚያስተምር መዝሙር ሊዘምር ይችላል፣ ለምሳሌ “ልጁን ላከ” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 34–35)።

ህያው ክርስቶስ፦ የሐዋሪያት ምስክርነትበገና በዓል ወቅት ቤተሰባችሁ በአዳኙ ላይ እንዲያተኩር መርዳት ከፈለጋችሁ፣ ምናልባት “ሕያው ክርስቶስ፦ የሐዋሪያት ምስክርነት“(ChurchofJesusChrist.org) አብራችሁ በማንበብ እና በማጥናት ጊዜ ልታሳልፉ ትችላላችሁ። ምናልባት ከ “ሕያው ክርስቶስ” ምንባቦችን ማስታወስ ወይም በውስጡ ያሉትን መግለጫዎች የሚደግፉ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የአዳኑን ሕይወት መግለጫዎች ትፈልጉ ይሆናል። እንዲሁም እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የኢየሱስ ክርስቶስን የራሱን ምስክርነት እንዲጽፍ መጋበዝ ትችላላችሁ እናም ከተነሳሳችሁ፣ ለቤተሰቡ አንብቡ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “አንዴ በአናሳ ጋጣ ውስጥ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 41።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ። ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉም ነገር ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመሰክር ያስተምራሉ (ሙሴ 6፥62–63) ተመልከቱ)፣ ስለዚህ በሁሉም ነገር እርሱን መፈለግ አለብን። ቅዱሳት መጻሕፍትን በምታነቡበት ጊዜ፣ ስለ እሱ የሚያስተምሯችሁን ጥቅሶች ልብ ማለት ወይም ምልክት ማድረግ አስቡ። ከገና በፊት ባሉት ቀናት ውስጥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ነገሮችን በዙሪያችሁ ለመፈለግ ጊዜ ውሰዱ።

ምስል
ማርያም፣ ዮሴፍ እና ሕፃኑ ኢየሱስ አካባቢ ያሉ እረኞች

የክርስቶስ ልደትበብራይን ኮል

አትም