“ታህሳስ 4፟–10 (እ.አ.አ)። ራዕይ 1–5፦ ‘ክብር … ኃይልም … ለበጉ ይሁን’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) (2022)
“ታህሳስ 4፟–10 (እ.አ.አ)። ራዕይ 1–5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 4፟–10 (እ.አ.አ)።
ራዕይ 1–5
“ክብር … ኃይልም … ለበጉ ይሁን”
በራዕይውስጥ ስላነበባችሁት ያላችሁን ጥያቄዎች ለመፃፍ አስቡ። ከዚያ ለጥያቄዎቻችሁ መልስ መፈለግ ወይም ከቤተሰብ አባል ጋር ወይም በቤተክርስቲያን ክፍሎች ውስጥ መወያየት ትችላላችሁ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
በኃይለኛ መንፈሳዊ ተሞክሮ ወቅት የተሰማችሁን ለሌሎች ለመግለጽ ተቸግራችሁ ታውቃላችሁ? የዕለት ተዕለት ቋንቋ መንፈሳዊ ስሜቶችን እና ግንዛቤዎችን ለመግለጽ በቂ እንዳልሆነ ሊሰማ ይችላል። ምናልባትም ዮሐንስ አስደናቂ መገለጡን ለመግለጽ እንዲህ ዓይነቱን የበለፀገ ምሳሌ እና ምስል የተጠቀመው ለዚህ ሊሆን ይችላል። እሱ በአጭሩ ኢየሱስ ክርስቶስን አይቶ እንደነበር መግለፅ ይችል ነበር፣ ነገር ግን የእርሱን ተሞክሮ ለመረዳት እንድንችል አዳኙን “ዓይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል፣” “ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፣” እና “ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ” ነበር በማለት ገለጸ (ራዕይ 1፥14–16)። የዮሐንስ ራእይ፣ መጽሐፍን ስታነቡ፣ ከእያንዳንዱ ምልክት በስተጀርባ ያለውን ትርጉም ባትረዱም፣ ዮሐንስ እናንተ እንድትማሩ እና እንዲሰማችሁ የፈለጋቸውን መልእክቶች ለማወቅ ሞክሩ። የቤተክርስቲያኗን ጉባኤን ከሻማ መቅረዝ፣ ሰይጣንን ከዘንዶ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ከበግ ጋር ያወዳደረው ለምን ሊሆን ይችላል? በመጨረሻ፣ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ጭብጥ ጨምሮ ዋና ዋናዎቹን ጭብጦች ለመረዳት በራዕይ ውስጥ እያንዳንዱን ምልክት መረዳት አይጠበቅባችሁም፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ተከታዮቹ በሰዎች እና በሰይጣን መንግስታት ላይ ድል ያደርጋሉ።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
የዮሐንስ ራዕይ የሚያስተምረው የሰማይ አባት ልጆቹን ለማዳን ያለውን ዕቅድ ነው።
የራዕይ መጽሐፍ ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ተስፋ አትቁረጡ። የዮሐንስ ቃል ሙከራችሁን እንድትቀጥሉ ሊያነሳሳችሁ ይችላል፤ “ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፣ እናም የሚሰሙ እና የሚረዱ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው” (ጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ራዕይ 1፥3 [በመጽሃፍ ቅዱስ አባሪ ውስጥ]፣ አጽንኦት ተጨምሮበታል)።
ራዕይ ን ለማጥናት አንደኛው መንገድ ከድህነት ዕቅድ ጋር ያለውን ግንኙነቶች በመፈለግ ነው። ይህ አጠቃላይ እይታ ሊረዳችሁ ይችላል፦
በምታነቡበት ጊዜ ራሳችሁን ጠይቁ፣ “ይህ ስለ እግዚአብሔር ዕቅድ ምን ያስተምረኛል? ክፉን አሸንፌ ወደ እርሱ እንድመለስ እግዚአብሔር ምን አደረገልኝ? ለታማኞች የገባው ቃል ምንድር ነው?
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77 በራዕይ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ምልክቶች የሚያብራራ መሆኑን ማወቁ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም፣ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም በራእይ፣ ውስጥ በርካታ ምንባቦችን ያብራራል፣ ስለዚህ የግርጌ ማስታወሻዎቹን እና የመጽሐፍ ቅዱስ መጨረሻ በመደበኛነት ፈትሹ።
ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ሕያው ልጅ ነው።
የራዕይ የመጀመሪያ ምዕራፍ የኢየሱስ ክርስቶስ በራዕይ ለዮሐንስ መገለጥን ይገልጻል። ምናልባት ይህ ምዕራፍ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገረውን ሁሉ፣ እሱ ማን እንደ ሆነ፣ ለእኛ ምን እንደሚሠራ እና ምን እንደሚመስል ዝርዝር ማዘጋጀት ትችላላችሁ።
አንዳንድ የምትማሯቸው ነገሮች ከምልክቶች ይመጣሉ። በእነዚህ ምልክቶች ጌታ ስለራሱ ሊያስተምራችሁ የሚሞክረውን አስቡ። ለምሳሌ፣ አዳኙ ራሱን “መጀመሪያ እና መጨረሻ” እና “የመጀመሪያው እና የመጨረሻው” ብሎ እንደጠራ አስተውሉ። እነዚህ ማዕረጎች ለምን ጉልህ ናቸው ብላችሁ ታስባላችሁ? እነዚህ ማዕረጎች ስለ አዳኙ ምን ያስተምሯችኋል?
ኢየሱስ ክርስቶስ በግል ያውቀኛል እናም ፈተናዎቼን እንድወጣ ይረዳኛል።
በራዕይ 2–3 ውስጥ የአዳኙ ቃላት በዮሐንስ ዘመን ስለነበሩ ስለ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያኗ ቅርንጫፎች ስኬቶችን እና ትግሎችን እንደተረዳ ያሳያሉ። የቅዱሳኑን ጥረት አድንቋል፤ ለመለወጥ ስለሚያስፈልጋቸው ነገሮችም አስጠንቅቋል። ከአዳኙ ውዳሴ እና ማስጠንቀቂያዎች ምን ትማራላችሁ?
አዳኙ የእናንተን ስኬቶቻችሁን እና ትግሎቻችሁንም ይረዳል፣ እናም ሊረዳችሁ ይፈልጋል። እሱ ድል ለሚነሱ የሚሰጠውን ተደጋጋሚ ተስፋዎች ልብ ይበሉ። ስለ እነዚህ ተስፋዎች ምን ያስደንቃችኋል? ጌታ ምን እንድታሸንፉ ይፈልጋል? የእርሱን እርዳታ ለመቀበል ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
የሰማይ አባት ዕቅድን እውን ማድረግ የሚችለው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።
ከ ራዕይ 4 ስለ ሰማይ አባት እና ከ ራዕይ 5፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ትማራላችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ (“በጉ”) የሰማይ አባት ዕቅድን እንደሚፈጽም ሁላችንም ስንረዳ እንዴት እንደነበር አስቡ (አዳኙ “መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም [መፍታት]”ራዕይ 5፥5ይችላል።) ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ለምን ይህንን ማድረግ ቻለ? እንደ አዳኛችሁ በእርሱ ላይ እምነታችሁን እንዴት ማሳየት ትችላላችሁ?
በተጨማሪም እዮብ 38፥4–7፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77፥1–7፣ ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ራዕይ1፥20።ኢየሱስ ቤተክርስቲያኑን ከሻማ መቅረዞች ጋር ያወዳደረው ለምንድነው? (ማቴዎስ 5፥14–16ን ተመልከቱ)። በመቅረዝ ላይ እንደ ብርሃን መሆን እንደምንችል ስለሚናገር መዝሙር ዘምሩ፣ ለምሳሌ “አብራ” (የልጆች መዝሙር፣ 144)
-
ራዕይ 2–3።ዮሐንስ በዘመኑ ለቤተክርስቲያናት እንደሰጣቸው መልእክት ለቤተሰባችሁ እንዲሰጥ እንደተጠየቀ አስመስሉ። እሱ ምን በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ሊል ይችላል? እንዴት ማሻሻል ትችላላችሁ?
-
ራዕይ 73፥15–16።እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ ቤተሰባችሁ ለብ ያለን ነገር የበለጠ ሙቅ ወይም ቀዝቃዛ የሆነን ነገር ሊጠጡ ይችላሉ። በመንፈሳዊነት ለብ ያለ መሆን ምን ማለት ነው?
-
ራዕይ 3፥20።ቤተሰባችሁ ራዕይ 3፥20ን ሲያነብ አዳኙ በር የሚያንኳኳበትን ምስል አሳዩ (የዚህን ረቂቅ መጨረሻ ተመልከቱ)። ኢየሱስ ወደ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ለምን ያንኳኳል? የቤተሰብ አባላት በየተራ በር ማንኳኳት ይችላሉ። ከዚያ በቤተሰብ ውስጥ ሌላ ሰው ለአዳኙ “[በሩን የምንከፍትበት]” መንገድ ሊጠቁም እና የቤተሰቡ አባል እንዲገባ ሊያደርግ ይችላል። አዳኙ በቤታችን ውስጥ ቢኖር ምን የሚሰማን ይመስላችኋል?
-
ራዕይ 4፥10–11።የሰማይ አባትን ማምለክ ምን ማለት ነው? እርሱን እንድናመልክ የሚያደርገንን ስለ እርሱ ምን እናውቃለን?
-
ራዕይ 5፥6፣ 12–13።ኢየሱስ ክርስቶስ “በግ” የተባለው ለምንድን ነው? ይህ ማዕረግ ስለ እርሱ ምን ያስተምረናል?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።
በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “ኢየሱስ፣” መዝሙር፣ቁጥር 196።