አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 11፟–17 (እ.አ.አ)። ራዕይ 6–14፦ “ከበጉ ደም የተነሣ … ድል ነሱ”


“ታህሳስ 11–17 (እ.አ.አ)። ራዕይ 6–14፦ ‘ከበጉ ደም የተነሣ … ድል ነሱ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) (2022 (እ.አ.አ))

“ታህሳስ 11–17 (እ.አ.አ)። ራዕይ 6–14፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ በክዋክብት መሃል ቆሞ

የተዋሃደ ጥበብ በኤሪክ ጆንሰን፦ ታላቁ ምክር ቤት፣ በሮበርት ቲ. ባሬት፤ የኮከብ ስብስብ የአውሮፓ የጠፈር ኤጀንሲ

ታህሳስ 11–17 (እ.አ.አ)

ራዕይ 6–14

“ከበጉ ደም የተነሣ … ድል ነሱ”

ፕሬዘደንት ቦይድ ኬ. ፓከር እንዲህ በማለት መክረዋል፦ “የቅዱሳት መጻህፍት ቋንቋ መጀመሪያ ላይ እንግዳ ከመሰላችሁ ማንበባችሁን ቀጥሉ። ብዙም ሳይቆይ በእነዚያ ገጾች ላይ የሚገኘውን ውበት እና ኃይል ትገነዘባላችሁ” (“ለመንፈሳዊ ጥበቃ ቁልፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ) 27)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

“በምጥ ተይዛ ልትወልድ [የተጨነቀች]” ሴትን አስቡ። አሁን በሴትየዋ ላይ “ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች [ያሉት] ታላቅ ቀይ ዘንዶ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ” ሲዘጋጅ አስቡ (ራዕይ 12፥2–4)። እነዚህን የዮሐንስ ራዕይ ጥቅሶች ለመረዳት፣ እነዚህ ምስሎች የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን እና የሚጋፈጡትን መከራ የሚወክሉ መሆናቸውን አስታውሱ። በዮሐንስ ዘመን ከፍተኛ መከራ ለደረሰባቸው ቅዱሳን፣ በክፉ ላይ ድል ማድረግ የማይመስል ሆኖ ሊመስላቸው ይችላል። ጠላት “ቅዱሳንን ይዋጋ ዘንድ” እና “በነገድና በወገንም፣ በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን [በተሰጠው]” (ራዕይ 13፥7) በእንደኛ አይነት ጊዜም ይህን ድል የማይቻል ሊመስል ይችላል። ነገር ግን የዮሐንስ ራዕይ ፍጻሜ መልካም ክፉን እንደሚያሸንፍ ያሳያል። ባቢሎን ትወድቃለች። ቅዱሳኑም ነጭ ለብሰው “ከታላቁ መከራ” ይወጣሉ—ልብሳቸው ፈጽሞ ባለመቆሸሹ ምክንያት ሳይሆን “ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም [ስላነጹት]” ነው (ራዕይ 7፥14)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ራዕይ 6–11

ዮሐንስ በምድር ታሪክ ውስጥ ብዙ ክስተቶችን በተለይም የኋለኛውን ቀናት አይቷል።

በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ሰባት ማኅተሞች ስላሉት አንድ መጽሐፍ ታነባላችሁ። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ካሰባችሁ ብቻችሁን አይደላችሁም። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲሁ አድርጓል። ይህ መጽሐፍ እና ማኅተሞቹ የመሬትን “ምድራዊ ህልውና” ታሪክ እንደሚወክሉ ጌታ ለጆሴፍ ገልጿል፤ እያንዳንዱ ማኅተም አንድ ሺህ ዓመትን ይወክላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 77፥6–7ን ተመልከቱ)። የመጀመሪያዎቹ አራት ማኅተሞች ክስተቶች በዮሐንስ ራእይ ውስጥ በአጭሩ በስምንት ቁጥሮች (ራዕይ 6፥1–8) ውስጥ እንደተጠቃለሉ ለማወቅ ልትፈልጉ ትችላላችሁ። የሚቀጥሉት ሦስት ቁጥሮች አምስተኛውን ማኅተም (ቁጥሮች 9–11) ይገልጻሉ። የተቀሩት ሁለት ማኅተሞች ክስተቶች አብዛኛውን የራዕይ መጽሐፍ ይይዛሉ። በሌላ አገላለጽ፣ የዮሐንስ ራዕይ ዋና ትኩረት የመጨረሻዎቹ ቀናት—የእኛ ቀናት ናቸው። በምታነቡበት ጊዜ፣ ዮሐንስ ስለኋለኞቹ ቀናት የጻፈውን ማወቅ ለምን ጠቃሚ እንደሆነ አስቡ።

ዮሐንስ ስለተነበየባቸው ክስተቶች በምታነቡበት ጊዜ የሚከተሉትን ሀሳቦች እና ጥያቄዎች አስቡ፦

ራዕይ 12–13

የሰማይ ጦርነት በምድር ላይ ቀጥሏል።

በሰማይ ስለነበረው ጦርነት ብዙ አናውቅም፣ ነገር ግን በራዕይ 12፥ 7–11 ውስጥ አጭር ቢሆንም ግልፅ መግለጫ አለ። እነዚህን ጥቅሶች በምታነቡበት ጊዜ፣ የዚያ ቅድመ–ህይወት ግጭት አካል እንደሆናችሁ አድርጋችሁ በአዕምሮአችሁ ሳሉ። ሰይጣን እንዴት እንደተሸነፈ ምን ትማራላችሁ? (ቁጥር 11ን ተመልከቱ)።

በሰይጣን የተጀመረው ጦርነት “የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት ካላቸው” (ራዕይ 12፥17)) ጋር በምድር ላይ ይቀጥላል። ዛሬ ያንን ጦርነት እርሱ እንዴት እንደሚያከናውን ከራዕይ 13 ምን ትማራላችሁ? በዚህ ጦርነት ውስጥ “የበጉ ደም” እና “[የምሥክርነታችሁ] ቃል” (ራዕይ 12፥11) እንዴት እናንተን በመርዳት ይቀጥላሉ?

በተጨማሪም 1 ኔፊ 14፥12–14ሞሮኒ 7፥12–13ሙሴ 4፥1–4ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥36–37፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “በሰማይ ጦርነት፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

ራዕይ 14፥6–7

“የዘለአለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ።”

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያለ አንድ ትንቢት የተፈፀመው ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ ተገልጦ መፅሐፈ ሞርሞን ሆኖ ወደተተረጎመው እና ወደታተመው ጽሁፎች ሲመራው ነው። ይህ መጽሐፍ “በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ” (ራዕይ 14፥ 6) እንድንሰብክ ሃላፊነት የተሰጠን “ዘለአለማዊ ወንጌልን” ይዟል።

በዘለአለማዊው ወንጌል መመለስ ስለተሳተፉ ሌሎች መላእክት ለማወቅ ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 1327፥5–13110፥11–16128፥20–21ን ተመልከቱ።

በተጨማሪም “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሙላት በዳግም መመለስ፦ ለሁለት መቶኛ አመት መታሰቢያ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ራዕይ 7፥9፣ 13–15 ለጥምቀት እና ለቤተመቅደስ ሥርዓቶች ነጭ ለምን እንደምንለብስ እነዚህ ጥቅሶች ምን ያስተምሩናል?

ራዕይ 7፥14–17በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለ ጌታ ተስፋዎች ስሜታቸውን እንዲጋሩ የቤተሰብ አባላትን ለመጋበዝ አስቡ። “[በታላቅ] መከራ” ውስጥ ስንሆን የእርሱ ተስፋዎች እኛን እንዴት ሊረዱን ይችላሉ? (ቁጥር 14)።

ራዕይ 12፥7–1114፥6አንዳንድ የቤተሰብ አባላት በራዕይ ውስጥ የተገለጹትን ራዕዮች ሥዕሎች በመሳል ሊደሰቱ ይችላሉ። ለምሳሌ በራዕይ 12 ላይ የተመሠረቱ ሥዕሎችን መሳል በሰማይ ስለነበረው ጦርነት ውይይት ሊያመራ ይችላል (ቁጥሮች 7–11ን ይመልከቱ)። በራዕይ 14፥ 6 ላይ የተመሠረቱ ሥዕሎች ስለ ወንጌል ዳግም መመለስ ውይይት ሊመሩ ይችላሉ።

እናንተ ራዕይ 14፥6ን አንድ ላይ ካነበባችሁ በኋላ፣ በእኛ ዘመን ወንጌልን ዳግም ለመመለስ የረዱትን የመልአኩ ሞሮኒ እና የሌሎች መላእክትን ሥዕሎች ለማሳየት አስቡ (በዚህ ረቂቅ መጨረሻ ላይ ያሉትን ሥዕሎች ተመልከቱ)። ምናልባት የቤተሰብ አባላት በየተራ ከሥዕሎቹ አንዱን በመያዝ መላእክት “የዘለአለም ወንጌል [ለእኛ ለመስበክ ስላለቸው]” አመስጋኝ ስለመሆናቸው ምክንያት ሊያካፍሉ ይችላሉ።

ራዕይ 12፥11“ከምስክራቸውም ቃል” የሚለው ሃረግ ምን ማለት ሊሆን ይችላል? የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት እኛ እና ሌሎች ሰይጣንን እንድናሸነፍ የሚረዳን እንዴት ነው?

ራዕይ 13፥11–14ስለ አታላዩ አውሬ የቤተሰባችሁ አባላት ምን ሀሳቦች አሏቸው? ዛሬ በዓለም ውስጥ የምናያቸውን ማታለያዎች እንዴት መለየት እና ማስወገድ እንችላለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ተመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ጀግና እሆናለሁ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 162።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ራሳችሁን በቅዱሳt መጻህፍት ውስጥ አጥልቁ። ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በየቀኑ መጥለቅ ለመንፈሳዊ ህልውና፣ በተለይም በእነዚህ ሁከት እየጨመረ በሚሄድባቸው ቀናት ውስጥ፣ ወሳኝ ነው” (“እርሱን ስሙት፣” ሊያሆና” ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 89)። “በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ መጥለቅ” ለእናንተ ምን ማለት ነው?

ክርስቶስ በር እያንኳኳ

በሰዓት አቅጣጫ በግራ ከላይ ጀምሮ፦ ሞሮኒ ወርቃማ ሳህኖቹን እያደረሰ፣ በጋሪ ኤል ካፕ፤ በእናንተ ላይ የእኔ አገልጋዮች፣ በሊንዳ ኩርሊ ክሪሰንሰን እና ሚካኤል ቲ ማል (መጥምቁ ዮሐንስ የአሮናዊ ክህነትን ለጆሴፍ ስሚዝ ሰጠ)፤ የመንግስቱ ቁልፎች፣ በሊንዳ ኩርሊ ክሪሰንሰን እና ሚካኤል ቲ ማል (ፒተር፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የመልከዘዴቅ ክህነት በጆሴፍ ስሚዝ ላይ ሰጡ፤ ራእይ በክርትላንድ ቤተመቅደስ፣ በጋሪ ኢ ስሚዝ (ሙሴ፣ ኤልያስ እና ኤልያስ ለዮሴፍ ስሚዝ እና ሲድኒ ሪግዶን ተገለጡ ።