“ህዳር 13–19 (እ.አ.አ)። ያዕቆብ፦ ‘ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) (2022 (እ.አ.አ))
“ህዳር 13–19 (እ.አ.አ)። ያዕቆብ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ህዳር 13–19 (እ.አ.አ)
ያዕቆብ
“ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ”
የያዕቆብን መልእክ፣ በምታነቡበት ጊዜ፣ ለእናንተ ልዩ ለሆኑ ሐረጎች ትኩረት ስጡ። የእነዚህን ቃላት “[አድራጊ]” እንድትሆኑ እንዴት ይገፋፋሉ? (ያዕቆብ 1፥22)።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
አንዳንድ ጊዜ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ብቻ ዓለምን ሊለውጥ ይችላል። ያዕቆብ 1፥5 ቀላል ምክር ይመስላል—ጥበብ ከፈለጋችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ። ነገር ግን የ14 ዓመቱ ጆሴፍ ስሚዝ ያንን ጥቅስ ሲያነብ፣ “ወደ ልቡ እያንዳንዱ ስሜት በታላቅ ኃይል የገባ ይመስል ነበር” (ጆሴፍ ስሚዝ–ታሪክ 1፥12)። በመንፈስ አነሳሽነት፣ ጆሴፍ የያዕቆብን ምክር ተግባራዊ አደረገ እና በጸሎት ከእግዚአብሔር ጥበብን ፈለገ። እናም እግዚአብሔር በእውነት በልግስና ሰጥቷል፣ ለጆሴፍ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስደናቂ ከሆኑት ሰማያዊ ጉብኝቶች አንዱን—የመጀመሪያውን ራዕይ ሰጥቶታል። ይህ ራዕይ የጆሴፍን የሕይወት ጎዳና ቀይሮ በምድር ላይ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዳግም መመለስ መራ። ጆሴፍ ስሚዝ ያዕቆብ 1፥5ን ስላነበበ እና ተግባራዊ ስላደረገ ዛሬ ሁላችንም ተባርከናል።
የያዕቆብ መልእክትን ስታጠኑ ምን ታገኛላችሁ? ምናልባት አንድ ወይም ሁለት ጥቅስ እናንተን ወይም የምትወዱትን ሰው ይለውጥ ይሆናል። በሕይወታችሁ ውስጥ ተልእኳችሁን ለመፈጸም ስትፈልጉ መመሪያን ልታገኙ ትችላላችሁ። በደግነት ለመናገር ወይም የበለጠ ታጋሽ ለመሆን ማበረታቻ ልታገኙ ትችላላችሁ። ድርጊቶቻችሁ ከእምነታችሁ ጋር በተሻለ ሁኔታ እንዲስተካከሉ እንደተገፋፋችሁ ሊሰማችሁ ይችላል። የሚያነሳሳችሁ ምንም ቢሆን፣ እነዚህ ቃላት “በልባችሁ ስሜት ሁሉ ውስጥ” እንዲገቡ አድርጉ። እናም ያዕቆብ እንደጻፈው “ቃሉን በየዋህነት” ስትቀበሉ፣ “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ … የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ” (ያዕቆብ 1፥21–22ን ተመልከቱ)።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ያዕቆብ ማን ነበር?
በአጠቃላይ የያዕቆብ መልእክት ጸሐፊ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የማርያም ልጅ፣ የአዳኙ የእንጀራ ወንድም እንደሆነ ይታመናል። በማቴዎስ 13፥55፤ ማርቆስ 6፥3፤ የሐዋርያት ሥራ 12፥17፤ 15፥13፤ 21፥18፤ እና ገላትያ 1፥19፤ 2፥9ላይ ያዕቆብ ተጠቅሷል። ከእነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ያዕቆብ በኢየሩሳሌም የቤተክርስቲያን መሪ እና እንደ ሐዋርያ ተጠርቶ እንደነበር ያሳያል (ገላትያ 1፥19ን ተመልከቱ)።
በትዕግስት መጽናት ወደ ፍጽምነት ይመራል።
ያዕቆብ 1፥2–4፤ 5፥7–11ን ካነበባችሁ በኋላ ስለ ትዕግሥት የያዕቆብ ዋና መልእክት ምን ትላላችሁ? ከእነዚህ ጥቅሶች የሽማግሌ ጄረሚ አር. ጃጊ ቤተሰቦች ስለ ትዕግስት የተማሩትን ለማሰብ ሊረዳ ይችላል (“ትዕግስት ሥራውን ይፈጽም እና እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት!፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 99–101)። የትዕግሥት “ፍጹም ሥራ” ምንድን ነው? (ያዕቆብ 1፥4)። ለመታገስ ፈቃደኛ መሆናችሁን ለጌታ እንዴት ማሳየት ትችላላችሁ?
ያዕቆብ 1፥3–8፣ 21–25፤ 2፥14–26፤ 4፥17
እምነት ተግባርን ይጠይቃል።
በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዳለላችሁ እንዴት ታውቃላችሁ? ሥራዎቻችሁ በእግዚአብሄር ላይ ያላችሁን እምነት የሚያሳዩት እንዴት ነው? የያዕቆብ የእምነት አስተምሮት በምታጠኑበት ጊዜ ስለእነዚህ ጥያቄዎች አስቡ። ያዕቆብ ስለጠቀሳቸው ሁለት ምሳሌዎች፥ ስለ አብርሃምና ስለ ረዓብ ማንበብ አስደሳች ሊሆን ይችላል (ዘፍጥረት 22፥1–12፤ ኢያሱ 2ን ተመልከቱ)። በአምላክ ላይ እምነት እንደነበራቸው ያሳዩት እንዴት ነው?
ያዕቆብ 1፥3–8፣ 21–25፤ 2፥14–26፤ 4፥17 ን ማንበብ ቃሉን በተሻለ ሁኔታ የምታደርጉበትን መንገዶች እንድታስቡ ሊረዳችሁ ይችላል። የተቀበላችሁትን ማናቸውንም ግንዛቤዎች መዝግቡ እና በእነሱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዕቅዶችን አዘጋጁ።
በተጨማሪም አልማ 34፥27–29፤ 3 ኔፊ 27፥21ን ይመልከቱ።
የምናገራቸው ቃላት ሌሎችን የመጉዳት ወይም የመባረክ ኃይል አላቸው።
ያዕቆብ በመልእክቱ ውስጥ ከተጠቀመባቸው ምስሎች መካከል፣ በጣም ግልጽ የሆነው ንግግር ያለው ስለ ቋንቋ በሰጠው ምክር ውስጥ ነው። ያዕቆብ ምላስን ወይም አፍን የገለፀባቸውን መንገዶች ሁሉ ዝርዝር ማዘጋጀት አስቡ። ስለምንናገራቸው ቃላት እያንዳንዱ ንፅፅር ወይም ምስል ምን ይጠቁማል? አንድን ሰው በቃላቶቻችሁ ለመባረክ ልታደርጉ የምትችሉትን አንድ ነገር አስቡ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 108፥7ን ተመልከቱ)።
የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር እንደመሆኔ መጠን ሰዎች ምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑም ሁሉንም መውደድ አለብኝ።
ያዕቆብ ቅዱሳን ለሀብታሞች ከማድላት እና ድሆችን ከመናቅ እንዲጠበቁ አስጠንቅቋል፣ ነገር ግን የእሱ ማስጠንቀቂያ በሌሎች ላይ ሊኖረን በሚችል ማናቸውም አድልዎ ወይም ጭፍን ጥላቻ ላይ ሊሠራ ይችላል። ያዕቆብ 2፥1–9ን በጸሎት ስታጠኑ፣ ልባችሁን ፈትሹ እናም የመንፈስ ቅዱስን ቅስቀሳዎች አድምጡ። (ቁጥር 2) በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ሐረጎችን፣ ለምሳሌ “እድፍ ልብስም የለበሰ ድሃ” ያለአግባብ ለመፍረድ የምትፈተኑበትን ሰው በሚገልጹ ቃላት ወይም ሃረጎች መተካት ሊረዳ ይችላል። ሌሎችን በምታዩበት ወይም ስለ ሌሎች በምታስቡበት መንገድ ላይ ማድረግ ያለባችሁ ለውጥ እንዳለ ይሰማችኋል?
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ያዕቆብ 1፥5። ያዕቆብ 1፥5ን ካነበባችሁ በኋላ ቤተሰባችሁ የመጀመሪያውን ራዕይ ዘገባ ጠቅለል ሊያደርግ (ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥ 8–20ን ተመልከቱ) ወይም “እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ። የሰማይ አባት ጸሎታቸውን የመለሰበትን እና የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ምስክርነቶች ልምዶችን እንዲያካፍሉ የቤተሰብ አባላትን ጋብዙ።
6:46 -
ያዕቆብ 1፥26–27።“እውነተኛ ክርስትና” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪዲዮ ለመመልከት አስቡ። ከዚያም ያዕቆብ 1፥26–27፣ ላይ የያዕቆብን “ንፁህ ሃይማኖት” ትርጓሜ አንብቡ፣ እና ቤተሰባችሁ የሃይማኖትን ልምምዳቸውን ይበልጥ ንፁህ ማድረግ በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ ተወያዩ።
-
ያዕቆብ 3።ያዕቆብ 3 ቤተሰባችሁ በደግነት መናገርን እንዲያስታውሱ የማይረሱ የቁስ ትምህርቶችን ሊያነሳሳ የሚችሉ ብዙ ምስሎችን ያካትታል። ለምሳሌ፣ አብራችሁ እሳት ልታነዱ እና ትንሽ፣ ደግነት የጎደለው ቃል እንዴት ትልቅ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ማውራት ትችላላችሁ (ቁጥር 5–6ን ተመልከቱ)። ወይም ብዙውን ጊዜ ለጣፋጭ ምግብ በምትጠቀሙት ነገር ውስጥ የጎመዘዘ ነገር ማቅረብ ትችላላችሁ—ለምሳሌ በማር ማሰሮ ውስጥ የሎሚ ጭማቂ። ይህ ጣፋጭ እና የሚያነቃቁ ቃላትን ስለመጠቀም ውይይት ሊያመራ ይችላል (ቁጥሮች 9–14ን ተመልከቱ)።
-
ያዕቆብ 4፥5–8።ፈተና ሲገጥመን “ወደ እግዚአብሔር [መቅረብ]” (ያዕቆብ 4፥ 8) ያለብን ለምንድን ነው?
-
ያዕቆብ 5፥14–16።ፕሬዝደንት ዳሊን ኤች. ኦክስ “ወላጆች በቤተሰብ ውስጥ የክህነት በረከቶችን ይበልጥ ማበረታታት አለባቸው” በማለት አስተምረዋል።(“የክህነት ሀይሎች፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 67)። ምናልባት ያዕቆብ 5፥14–16 ን ማንበብ እና የክህነት በረከትን ስለመቀበል ልምዶችን ማካፈል የቤተሰብ አባላት ሲታመሙ ወይም መንፈሳዊ ጥንካሬ ሲፈልጉ በረከትን እንዲጠይቁ ሊያበረታታቸው ይችላል።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።
በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “መልካም ነገር ሰርቻለሁ?፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 223።