አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
የግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች


“የግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል ሀሳቦች” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022(እ.አ.አ)]

“የግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል ሀሳቦች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ቅዱሳት መጻህፍትን የምታጠና ሴት

የግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የሚገኘውን የእግዚአብሔር ቃል ጥናትዎን የሚያሳድጉ አንዳንድ ቀላል መንገዶች እነሆ።

ስለኢየሱስ ክርስቶስ እውነቶችን ይፈልጉ

ቅዱሳት መጻህፍት ሁሉም ነገሮች ስለክርስቶስ እንደሚመሰክሩ ያስተምሩናል ( 2 ኔፊ 11፥4ሙሴ 6፥63፣ ይመልከቱ)፣ ስለዚህ ስለአዳኝ እና እርሱን እንዴት መከተል እንደሚቻል በሚያስተምሩት ጥቅሶች ላይ ትኩረት መስጠትን ወይም ምልክት ማድረግን አስቡ።

የሚያነሳሱ ቃላትን እና ሃረጎችን ይፈልጉ

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የተወሰኑ ቃላቶች እና ሀረጎች በተለይ ለእርስዎ እንደተጻፉ ሆነው ሊሰሟችሁ ይችላሉ። እነሱ ለግላችሁ ተገቢ እንደሆኑ ይሰማዎታል እናም ያነሳሱዎታል እንዲሁም ያነቃቁዎታል ። እነዚህንም በቅዱሳት መጻህፍትዎ ላይ ምልክት ማድረግን ወይም በጥናት ደብተርዎ ውስጥ መፃፍን ያስቡ።

የወንጌል እውነቶችን ይፈልጉ

አንዳንድ ጊዜ የወንጌል እውነቶች (ብዙውን ጊዜ ትምህርት ወይም መርሆዎች ተብለው ይጠራሉ) በቀጥታ ይገለጻሉ፣ እናም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በምሳሌ ወይም በታሪክ አማካይነት ይገለጻሉ። እራሳችሁን ጠይቁ፣ “እነዚህ ጥቅሶች ምን ዘለዓለማዊ እውነቶችን ያስተምራሉ?”

መንፈስን ስሙ

ከምታነቡት ጋር የማይዛመዱ ቢሆኑም፣ ለሀሳብዎ እና ለስሜትዎ ትኩረት ስጡ። እነዚያ ግንዛቤዎች የሰማይ አባትዎ እንዲማሩ የሚፈልጋቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ።

ቅዱሳት መጻህፍትን ከሕይወትዎ ጋር አመሳስሉ

የምታነቧቸው ታሪኮች እና ትምህርቶች በሕይወትዎ ውስጥ እንዴት እንደሚሠሩ ልብ ይበሉ። ለምሳሌ፣ “እኔ ከማነበው ጋር የሚመሳሰሉ ምን ልምዶች አግኝቻለሁ?” ወይም “በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ያለውን የዚህን ሰው ምሳሌ መከተል የምችለው እንዴት ነው?” ብለው መጠየቅ ይችላሉ።

በሚያጠኑበት ጊዜ ጥያቄዎችን ጠይቁ

ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያጠኑ፣ ጥያቄዎች ወደ አዕምሮዎ ሊመጡ ይችላሉ። እነዚህ ጥያቄዎች ከምታነቡት ጋር ወይም በአጠቃላይ ከሕይወትዎ ጋር ሊዛመዱ ይችላሉ። እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ እና ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናትን ስትቀጥሉ መልሶቹን ፈልጉ።

ምስል
ቅዱሳት መጻህፍትን የሚያጠና ወንድ

የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት መርጃን ይጠቀሙ

በምታነቡት አንቀጾች ላይ ግንዛቤ ለማግኘት የግርጌ ማስታወሻዎቹን፣ የአርዕስት መምሪያን፣ የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ-ቃላትን፣ እና የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org)፣ እንዲሁም ሌሎች የጥናት እርዳታዎችን ይጠቀሙ።

የቅዱሳት መጻህፍትን አገባብ ከግምት ውስጥ ያስገቡ

የቅዱስ ጽሑፍን አገባብ ማለትም ፅሁፉ የተከናወነበትን ሁኔታ እንዲሁም ጊዜ እና ቦታ ከግምት ውስጥ ካስገቡ ትርጉም ያላቸውን ግንዛቤዎችን ማግኘት ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ነቢይ ያነጋገራቸውን ሰዎች ያለፈ ታሪክ እና እምነቶች ማወቁ የቃላቱን ዓላማ በተሻለ ለመረዳት ይረዳዎታል።

ሀሳብዎን እና ስሜትዎን መዝግቡ

በሚያጠኑበት ጊዜ የሚመጡትን ግንዛቤዎች ለመመዝገብ በተለያዩ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ፣ ትርጉም ያለው ቃል ወይም ሐረግ ላይ ምልክት ሊያደርጉ እንዲሁም ሀሳብዎን በቅዱሳት መጻህፍቶችዎ ውስጥ እንደ ማስታወሻ ሊፅፉ ይችላሉ። እንዲሁም የሚቀበሉትን ግንዛቤዎች፣ ስሜቶች፣ እና ሃሳቦች ማስታወሻ ደብተርዎ ላይ መያዝ ይችላሉ።

የኋለኛው ቀን ነቢያትን እና ሐዋርያትን ቃል ያጥኑ

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ስለሚያገኟቸው መርሆዎች የኋለኛው ቀን ነቢያት እና ሐዋርያት ምን እንዳስተማሩ ያንብቡ (ለምሳሌ፣ conference.ChurchofJesusChrist.org እና የቤተክርስቲያን መጸሔቶችን ይመልከቱ።)

ግንዛቤዎችን ያጋሩ

ከግል ጥናትዎ ያገኙትን ግንዛቤዎች መወያየት ሌሎች ሰዎችን ለማስተማር ጥሩ የሆነ መንገድ ብቻ ሳይሆን ያነበቧቸውን በተመለከተ ያሎትን ግንዛቤ ለማጠናከርም ይረዳል።

በተማሩት ይኑሩ

የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ማነቃቃት ብቻ ሳይሆን አኗኗራችንን እንድንቀይር ሊያደርጉን ይገባል። በሚያነቡበት ጊዜ መንፈስ እንዲያደርጉ የሚገፋፋዎትን ያድምጡ፣ ከዚያም በእነዚያ ማነሳሻዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ይወስኑ።

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ ቤድናር እንዳሉት፥ “ቤተክርስቲያኗ እንደ ተቋም ድርጅት እኛ መለኮታዊ ደቀመዛሙርት ለመሆን እና እስከመጨረሻ በጥንካሬ ለመፅናት ማወቅ ወይም ማድረግ የሚያስፈልጉንን ሁሉ እንድታስተምረን ወይን እንድትነግረን መጠበቅ አይገባንም [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥29ይመልከቱ]። ይልቁንም፣ የግል ሀላፊነታችን መማር ያለብንን ለመማር፣ መኖር እንዳለብን በምናውቀው መልኩ ለመኖር፣ እናም መምህር እንድንሆን የሚፈልገንን ለመሆን ነው። ቤታችንም ለመማር፣ ለመኖር፣ እና ለመሆን ዋነኛ አመቺ ስፍራ ነው” (“ማንኛውንም አስፈላጊ ነገር ለማግኘት ተዘጋጁ፣” ሊያሆናግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 102)።

አትም