አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ተጨማሪ የጥናት ምንጮች


“ተጨማሪ የጥናት ምንጮች፣” ኑ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ተጨማሪ የጥናት ምንጮች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ቤተሰቦች ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነቡ

ተጨማሪ የጥናት ምንጮች

አብዛኛዎቹ እነዚህ የጥናት ምንጮች በወንጌል ቤተ-መጽሐፍት መተግበሪያ ውስጥ እና በChurchofJesusChrist.org ላይ ይገኛሉ።

መዝሙር እና የልጆች መዝሙር መጽሐፍ

ቅዱስ መዝሙር መንፈስን ይጋብዛል፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲሰማን ይረዳናል፣ እናም ትምህርትን በማይረሳ መንገድ ያስተምራል። የታተሙ መዝሙሮችን እና የልጆች ሙዚቃዎችን ከመጠቀም በተጨማሪም፣ የብዙ መዝሙሮች እና የልጆች ሙዚቃዎችን የድምፅ እና የቪዲዮ ቅጂዎችን በmusic.ChurchofJesusChrist.org እና በቅዱስ መዝሙር እና የወንጌል ሚዲያ መተግበሪያዎች ላይ ማግኘት ይችላሉ።

የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት እና የኢንስቲቱት መመሪያ መጽሐፎች

የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት እና የኢንስቲቱት መመሪያ መጽሐፎች በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ለሚገኙት መሰረታዊ መርሆዎች እና ታሪኮች ታሪካዊ መግለጫ እና የመሠረተ ትምህርት አስተያየትን ያቀርባሉ።

የቤተክርስቲያን መጽሔቶች

ጓደኛለወጣቶች ጥንካሬ፣ እና የ ሊያሆና መጽሔቶች ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦችን ሲያስተምሩ መሰረታዊ መርሆዎቹን የሚደግፉ ታሪኮችን እና ተግባሮችን ይዘዋል።

የወንጌል ርዕሶች

የወንጌል ርዕሶች (topics.ChurchofJesusChrist.org) ውስጥ ስለወንጌል ርዕሰ ጉዳዮች፣ እንዲሁም ከእነዚህ ጋር የሚገናኙ እንደ የአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶች፣ መጣጥፎች፣ ጥቅሶች፣ እና ቪዲዮዎች ያሉ የተለያዩ መሰረታዊ መረጃዎች ጠቃሚ አገናኞችን ለማግኘት ይችላሉ። ስለ ትምህርት እና ታሪካዊ ጉዳዮች እንዲሁም ስለ ቤተክርስቲያን እና ስለ ትምህርቷ ለሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ የወንጌል አርእስቶች ድርሰቶችም ማግኘት ይችላሉ።

የአዲስ ኪዳን ታሪኮች

የአዲስ ኪዳን ታሪኮች በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኙ ትምህርት እና ታሪኮችን ልጆች እንዲማሩ ሊረዳ ይችላል። እንዲሁም የእነዚህን ታሪኮች ቪዲዮዎች በወንጌል ቤተመጻሕፍት መተግበሪያ ውስጥ እና በ MediaLibrary.ChurchofJesusChrist.orgማግኘት ይችላሉ።

የቅዱሳን ፅሁፎች ታሪኮች ማቅለሚያ መጽሐፍ፦ አዲስ ኪዳን

ይህ የጥናት ምንጭ ልጆች ከአዲስ ኪዳን የሚማሩትን ትምህርት ለማሳደግ የተነደፉ አዝናኝ ቀለም የመቀባት ተግባራዊ ገጾችን ያካትታል።

ቪዲዮዎች እና ስነ ስእል

የስዕል ስራ፣ ቪዲዮች፣ እና ሌሎች ሚዲያዎች ቤተሰቦቻችሁ ከቅዱሳን መጻህፍት ጋር የተዛመዱትን ትምህርቶችን እንዲገነዘቡ እና ታሪኮችን በአይነ ህሊና እንዲመለከቱ ይረዷቸዋል። የቤተክርስቲያኗን የሚዲያ የጥናት ምንጮችን ክምችት ለማሰስ በ MediaLibrary.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ይጎብኙ። የወንጌል ሚዲያ የሞባይል መተግበሪያም ይገኛል። ብዙ መጠቀም የሚችሏቸው ምስሎችም በ ወንጌል ስነጥበብ መጽሐፍውስጥ ይገኛሉ።

በአዳኙ መንገድ ማስተማር

በአዳኙ መንገድ ማስተማር ስለክርስቶስ መሰል የማስተማሪያ ዘዴ መርሆችን ለመማር እና ተግባራዊ ለማድረግ ሊረዳዎት ይችላል።

አትም