“ወጣት ልጆችን ማስተማር፣” ኑ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]
“ወጣት ልጆችን ማስተማር፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
ወጣት ልጆችን ማስተማር
በቤተሰባችሁ ውስጥ ወጣት ልጆች ካሉ ለመማር የሚረዷቸው አንዳንድ ተግባራት እነሆ፦
-
ዘምሩ። በልጆች የመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ ያሉ መዝሙሮች እና ሙዚቃዎች ትምህርትን በኃይል ያስተምራሉ። ከምታስተምሯቸው የወንጌል መሰረታዊ መርሆዎች ጋር የሚዛመዱ መዝሙሮችን የርዕሶች ማውጫን በልጆች የመዝሙር መጽሐፍ በስተጀርባ በማግኘት ተጠቀሙ። ልጆቻችሁ የመዝሙሮቹን መልእክቶች በሕይወታቸው ላይ እንዲያዛምዱ እርዷቸው። (በተጨማሪም “ቅዱስ መዝሙርን በወንጌል መማር ላይ ስለመጨመር” አስመልክቶ በዚህ ግብዓት ውስጥ ተመልከቱ።)
-
አንድን ታሪክ አዳምጡ ወይም ተውኑ ወጣት ልጆች ከቅዱሳን መጽሃፍት፣ ከህይወታችሁ፣ ከቤተሰባችሁ ታሪክ፣ ወይም ከቤተክርስቲያን መጽሔቶችውስጥ የሚመጡ ታሪኮችን ይወዳሉ። በትረካው ውስጥ እነርሱን ለማሳተፍ መንገዶችን ፈልጉ። እነርሱ ስዕሎችን ወይም ዕቃዎችን መያዝ፣ የሚሰሙትን በስዕል መልክ መሳል፣ ታሪኩን መተወን፣ ወይም ታሪኩን በመናገር መርዳት ይችላሉ። በምታጋሯቸው ታሪኮች ውስጥ ልጆቻችሁ የወንጌል እውነቶችን እንዲገነዘቡ እርዷቸው።
-
ቅዱሳት መጻህፍትን አንብቡ ወጣት ልጆች በጣም ብዙ ማንበብ አይችሉ ይሆናል፣ ነገር ግን ከቅዱሳት መጻህፍት በመማር እነርሱ እንዲሳተፉ ለማድረግ ይችላሉ። በአንድ ጥቅስ፣ ቁልፍ ሐረግ ወይም ቃል ላይ ማተኮር ያስፈልጋችሁ ይሆናል። ልጆች ከቅዱሳን መፃህፍት ውስጥ አጫጭር ሃረጎችን የተወሰነ ጊዜ ከደጋገሙ ለመሸምደድ ይችላሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰሙ፣ መንፈስ ቅዱስ ይሰማቸዋል።
-
ፎቶግራፍ ወይም ቪዲዮ ተመልከቱ። ለልጆቻችሁ ከወንጌል መርሆ ወይም የመጽሐፍ ታሪካ ጋር የሚዛመድ ምስል ወይም ቪዲዮ ስታሳዪአቸው፣ እየተመለከቱት ካለው ነገር እንዲማሩ የሚረዷቸውን ጥያቄዎች ጠይቋቸው። ለምሳሌ፣ እንደዚህ ብላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ፣ “በዚህ ሥዕል ወይም ቪዲዮ ውስጥ ምን እየሆነ ነው? ምን ስሜት ያሳድርባችኋል? ስዕሎችን እና ቪዲዮዎችን ለመፈለግ፣ የወንጌል ሚዲያ፣ MediaLibrary.ChurchofJesusChrist.org፣ እና children.ChurchofJesusChrist.org ጥሩ ቦታዎች ናቸው።
-
ፍጠሩ። ልጆች ከሚማሩት ታሪክ ወይም መሠረታዊ መርሆ ጋር የሚዛመድ አንድ ነገር መገንባት፣ መሳል ወይም ቀለም መቀባት ይችላሉ።
-
በምሳሌአዊ እቃዎች ትምህርቶች ውስጥ መሳተፍ ቀለል ያለ የእቃ ምሳሌአዊ ትምህርት ልጆቻችሁ ለመረዳት አስቸጋሪ የሆነውን የወንጌል መርህ እንዲገነዘቡ ሊረዳቸው ይችላል። የእቃ ምሳሌአዊ ትምህርቶችን በምትጠቀሙበት ጊዜ፣ ልጆቻችሁ እንዲሳተፉበት የሚያስችሏቸውን መንገዶች ፈልጉ። እነሱ በመመልከት ብቻ ሳይሆን በተሳትፎ ተሞክሮ የበለጠ ይማራሉ።
-
ትወና ልጆች በእውነተኛ ህይወት ውስጥ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉትን ሁኔታዎች በትወና ሲጫወቱ የወንጌል መሰረታዊ መርሆች በህይወታቸው እንዴት እንደሚሠራ የበለጠ ለመረዳት ይችላሉ።
-
ተግባሮችን ደጋግሙ ወጣት ልጆች ፅንሰ ሀሳቦችን ለመረዳት ደጋግመው መስማት ያስፈልጋቸው ይሆናል። ታሪኮችን ወይም ተግባሮችን አዘውትራችሁ ለመድገም አትፍሩ። ለምሳሌ፣ አንድን የቅዱሳት መጻህፍት ታሪክ፣ ከቅዱሳት መጻህፍት በማንበብ፣ በራሳችሁ ቃላት በማሳጠር፣ ቪዲዮን በማሳየት፣ ልጆች ታሪኩን ለመናገር እንዲረዷችሁ በመፍቀድ፣ ታሪኩን እንዲተውኑ በመጋበዝ እና በመሳሰሉ ነገሮች፣ በተለያዩ መንገዶች ደጋግመው ማካፈል ይችላሉ።