አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦችን መጠቀም


ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦችን መጠቀም፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 ( እ.አ.አ)]

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦችን መጠቀም፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦችና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦችን መጠቀም

ይህ መገልገያ ለማን ነው?

ይህ መገልገያ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ግለሰብ እና ቤተሰብ ነው። በግልዎም ሆነ ከቤተሰብዎ ጋር፣ ወንጌልን እንዲማሩ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ከዚህ በፊት ወንጌልን ዘወትር የማያጠኑ ከሆነ፣ ይህ ጽሁፍ እንዲጀምሩ ይረዳዎታል። ቀድሞውኑ በወንጌል ጥናት ጥሩ ልምድ ካለዎት፣ ይህ ጽሁፍ የበለጠ ትርጉም ያለው ተሞክሮ እንዲኖርዎት ይረዳል።

ምስል
እናት እና ልጅ ቅዱሳት መጻህፍትን እያነበቡ

ይህንን ጽሁፍ እንዴት መጠቀም ይኖርብኛል?

ይህንን ጽሁፍ ለእርስዎ በሚረዳ በማንኛውም መንገድ ተጠቀሙበት። ለግል እና ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እንደ መመሪያ ወይም እንደ እርዳታ ያግዝዎታል። ለቤተሰብ የቤት ምሽትም ይህን ለመጠቀም ይችላሉ። ይዘቶቹ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኙትን ጠቃሚ መርሆዎች ያደምቃሉ፣ የግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን የጥናት ሀሳቦችን እና እንቅስቃሴዎችን ይጠቁማሉ፣ እንዲሁም ግንዛቤአችሁን የምትመዘግቡባቸው ቦታዎችን ያቀርባሉ።

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች ወንጌልን ለመማር ከሚሠሩትን ከሌሎች መልካም ነገሮች ጋር የሚወዳደር ወይም የሚተካ አይደለም። የራስዎን የእግዚአብሔርን ቃል ጥናት እንዴት መቅረብ እንደሚችሉ ለመወሰን የመንፈስ ቅዱስን መመሪያ ይከተሉ።

ይህ መገልገያ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚሆነው ጋር የሚዛመደው እንዴት ነው?

በዚህ መገልገያ ውስጥ ያሉት ይዘቶች በሳምንት የንባብ መርሃግብር መሠረት የተደራጁ ናቸው። የኑ፣ ተከተሉኝ መገልገያዎች ለመጀመሪያ ክፍልለሰንበት ትምህርት ቤት፣ እና ለአሮናዊ ክህነት ቡድኖች እና ለወጣት ሴቶች ክፍሎች ተመሳሳይ መርሃግብርን ይከተላሉ። በቤት ውስጥ ወንጌልን ለመማር እና ለመኖር ያደረጋችሁትን ጥረቶች ለመደገፍ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያሉ አስተማሪዎችዎ በቤትዎ ውስጥ ስላጠኑት የቅዱሳት መጻህፍት ምንባቦች ልምድዎን፣ ሀሳብዎን እና ጥያቄዎን ለማጋራት እድሎችን ይሰጡዎታል።

የሰንበት ትምህርት በወር ሁለት ጊዜ ብቻ ስለሚቀርብ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ሳምንታዊ መርሃግብሩን ለመከታተል ይዘቶቹን ለመዝለል ወይም ለማዋሃድ መምረጥ ይችላሉ። በካስማ ስብሰባ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ መደበኛ የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች በማይካሄዱባቸው ሳምንቶችም፣ (ለሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል እና ለመጀመሪያ ክፍል) ይህ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ሳምንታት ውስጥ አዲስ ኪዳንን በቤትዎ ውስጥ ማጥናት እንዲቀጥሉ ይጋበዛሉ።

መርሃግብሩን መከተል አለብኝን?

መርሃግብሩ በአመቱ መጨረሻ አዲስ ኪዳንን አንብበው እንዲጨርሱ ይረዳዎታል። በተጨማሪም፣ እንደሌሎች ተመሳሳይ መርሃግብርን መከተል በቤት፣ በቤተክርስቲያን፣ እና በማንኛውም ቦታዎች ትርጉም ወዳለው ልምዶች ይመራል። ነገር ግን መርሃግብሩን በመከተል እንደተወሰኑ ወይም እያንዳንዱን ጥቅስ ለማንበብ እንደተገደዱ አይሰማዎት፤ መርሃግብሩ በራስዎ ፍጥነት እንዲከተሉ የሚያግዛችሁ መመሪያ ነው። አስፈላጊው ነገር በግል እና በቤተሰብ ውስጥ ወንጌልን መማራችሁ ነው።

አትም