አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
የቤተሰባችሁን የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች


“የቤተሰባችሁን የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“የቤተሰባችሁን የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
እናት እና ልጅ ቅዱሳት መጻህፍትን እያነበቡ

የቤተሰባችሁን የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች

መደበኛ የቤተሰብ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ቤተሰባችሁ የመንፈስ ቅዱስ ተጸዕኖ እንዲሰማቸው እና ወንጌልን እንዲማሩ ለመርዳት ሀይለኛ መንገድ ነው። እንደቤተሰብ የሚያነቡት ነገር ብዛት እና የሚያነቡበት ጊዜ ርዝመት ያላሰለሰ ጥረት የማድረጋችሁን ያህል አስፈላጊ አይደሉም። የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትን የቤተሰባችሁ ህይወት አስፈላጊ ክፍል ስታደርጉት፣ የቤተሰባችሁ አባሎች ወደ ሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲቀርቡ እና በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ምስክርነታቸውን እንዲገነቡ ትረዷቸዋላችሁ። ስለሚከተሉት ጥያቄዎች በአንድነት ለመመካከር አስቡ፤

  • የቤተሰባችሁ አባላት ቅዱሳት መጻህፍትን በግል እንዲያነቡ እርስ በርስ እንዴት ማበረታታት ይችላሉ?

  • የቤተሰብ አባላቶች እያንዳንዱ የተማረውን እንዲያጋራ ለማበረታታት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የምትማሩትን መሰረታዊ መርሆዎች በዕለት ተዕለት ትምህርቶች ጊዜ እንዴት ማጉላት ትችላላችሁ?

ቤት ለወንጌል ትምህርት አመቺ ስፍራ መሆኑን አስታውሱ። በቤተክርስቲያን ክፍል ውስጥ በማይቻል መንገድ ወንጌልን በቤታችሁ ውስጥ መማር እና ማስተማር ይችላሉ። ቤተሰባችሁ ከቅዱሳት መጻህፍት እንዲማሩ ለመርዳት መንገዶችን መፍጠርን አስቡ። የቤተሰባችሁን የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ለማጉላት የሚከተሉትን ሀሳቦች ይመልከቱ።

ምስል
አንድ ቤት ውስጥ ቤተሰብ እና የቤተክርስትያን መሪዎች በአንድነት እየዘመሩ

ሙዚቃን ይጠቀሙ

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የተማራችሁትን መሰረታዊ መርሆዎች የሚያጠናክሩ መዝሙሮች ይዘምሩ። የተመረጡ መዝሙሮች ወይም የህጻናት መዝሙሮች በእያንዳንዱ ሳምንታዊ ማውጫ ውስጥ ተዘርዝረዋል። በግጥሞቹ ውስጥ ስላሉት ቃላት ወይም ሐረጎች የቤተሰባችሁ አባላት ጥያቄዎች መጠየቅ ትችላላችሁ። ከመዘመር በተጨማሪ ቤተሰባችሁ ከመዝሙሮቹ ጋር የሚሄዱ ተግባሮችን ማከናወን ወይም ሌሎች ተግባሮችን በሚያከናውኑበት ጊዜ መዝሙሮቹን እንደ የበስተጀርባ ሙዚቃ ማዳመጥ ይችላሉ። ለበለጠ ሃሳቦች በዚህ የጥናት ምንጭ ውስጥ “ቅዱስ መዝሙርን በወንጌል ትምህርትዎ ውስጥ ማካተት” የሚለውን ይመልከቱ።

ትርጉም ያላቸውን የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶችን አጋሩ።

የቤተሰብ አባላት በግል ጥናታቸው ያገኟቸውን ለእነሱ ትርጉም የሰጧቸውን የቅዱሳት መጻህፍት ምንባቦች እንዲያካፍሉ ጊዜ ስጧቸው።

የራሳችሁን ቃላት ተጠቀሙ

ከምታጠኗቸው ቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ምን እንደተማሩ በገዛ ቃላቸው እዲያብራሩ የቤተሰብ አባሎቻችሁን ይጋብዟቸው።

ቅዱሳት መጻህፍትን ከሕይወታችሁ ጋር አመሳስሉ

የቅዱሳት መጻህፍትን ምንባብ ካነበባችሁ በኋላ፣ የቤተሰብ አባላት መልዕክቱ በህይወታቸው እንዴት ሊሰራ እንደሚችል እንዲያካፍሉ ጠይቋቸው።

ጥያቄ ጠይቁ

የቤተሰብ አባላት የወንጌልን ጥያቄ እንዲጠይቁ ጋብዙ፣ እናም ከዚያ ለጥያቄው መልስ ሊያግዙ የሚችሉ ጥቅሶችን በመፈለግ ጊዜአችሁን አሳልፉ።

የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅስ አሳዩ

ያገኛችሁትን ትርጉም ያለው ጥቅስ ምረጡ፣ እና የቤተሰብ አባላት ብዙውን ጊዜ በሚያዩበት ቦታ ላይ አስቀምጡት። ሌሎች የቤተሰብ አባላት አንድ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅስ በመምረጥ በየተራ እንዲያሳዩ ጋብዙ።

ምስል
እናት እና ልጅ ቅዱሳት መጻህፍትን እያነበቡ

የቅዱሳት መጻህፍት ዝርዝርን አዘጋጁ

እንደ ቤተሰብ በሚመጣው ሳምንት በጥልቀት መወያየት የምትፈልጉትን የተለያዩ ጥቅሶችን ምረጡ።

የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶችን በአዕምሮአችሁ በመያዝ አስታውሱ

ለቤተሰባችሁ ትርጉም ያለው የቅዱሳት መጻህፍት ምንባብን ምረጡ፣ እና የቤተሰብ አባላቱ በየዕለቱ በመድገም ወይም የማስታወሻ ጨዋታ በመጫወት በአዕምሮአቸው በመያዝ እንዲያስታውሱ ጋብዙአቸው።

የምሳሌአዊ ነገሮችን ትምህርቶች አጋሩ

እንደ ቤተሰብ የምታነቧቸው ምዕራፎች እና ጥቅሶች ጋር የሚዛመዱ ነገሮችን ፈልጉ። እያንዳንዱ ነገሮች በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካሉት ትምህርቶች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እንዲናገሩ የቤተሰብ አባላትን ጋብዙ።

ርዕሶችን ምረጡ

ቤተሰቡ አብሮ የሚያጠናውን ርዕስ የቤተሰብ አባላት ተራ በተራ እንዲመርጡ አድርጉ። በቅዱሳት መጻህፍት ምንባብ ውስጥ ስለርዕሶች መረዳጃ ለማግኘት፣ የርዕስ መመሪያን፣ የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትን፣ ወይም የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያን (scriptures.ChurchofJesusChrist.org) ተጠቀሙ።

ስዕል ሳሉ

እንደ ቤተሰብ ጥቂት ጥቅሶችን አንድ ላይ አንብቡ፣ ከዚያ የቤተሰብ አባላቶች ካነበቡት ነገር ጋር የሚዛመድ አንድ ነገር እንዲስሉ ጊዜ ስጡአቸው። ስለ እርስ በራሳችሁ ስዕሎች ለመወያየት ጊዜ መድቡ።

ታሪኩን ተውኑ

አንድ ታሪክ ካነበባችሁ በኋላ የቤተሰብ አባላትን እንዲተውኑት ጋብዙ። ከዚያ በኋላ ታሪኩ በግል እና በቤተሰባችሁ ውስጥ ከሚገኙ ነገሮች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ተነጋገሩ።

ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን እንዳሉት፦ “ቤታችሁን እንደ ወንጌል መማሪያ ክፍል ለመለወጥ በትጋት ስትሰሩ፣ ከጊዜ በኋላ የእናንተ ሰንበት ቀናት በደስታ የተሞሉ ይሆናሉ። ልጆቻችሁ የአዳኝን ትምህርት በመማር እና በመኖር ይደሰታሉ፣ እናም ጠላት በህይወታችሁ እና በቤታችሁ ውስጥ ያለው ተፅዕኖ ይቀንሳል። በቤተሰባችሁ ውስጥ ያለው ለውጥ ታላቅ እና የሚቀጥል ይሆናል” (“ምሳሌያዊ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 113)።

አትም